፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ከነገ ጥቅምት ፩/፳፻፲ ዓ.ም
ጀምሮ ማንኛውንም ዓይነት መረጃ የምታገኙት በ facebook.com/melkamubeyeneB በሚለው የፌስቡክ ላይክ ገጼ ብቻ ይሆናል፡፡
በ facebook.com/beyenemelkamuA አድራሻ እጠቀምበት የነበረውን የላይክ ገጽ ከ
facebook.com/melkamubeyeneB አንድ ላይ የቀላቀልሁት (Merge) ስለሆነ ከዚህ በኋላ የምጠቀምበት አንድ የላይክ
ገጽ ብቻ ይሆናል፡፡ እርሱም facebook.com/melkamubeyeneB ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ማንኛውንም መረጃ ለማግኘት በዚህ
ገጽ እየገባችሁ እንድትከታተሉኝ እጠይቃለሁ፡፡ ላይክ አድርጉ ሸር አድርጉ ወዘተ የሚለውን ጥሪም በፈቃዴ ከነገ ጀምሬ አንስቻለሁ፡፡
የወደደ የወደደውን ያድርግ!!!
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ገዳመ አስቄጥስ አቡነ ተክለ
ሃይማኖት ገዳም በደብረ ማርቆስ ከተማ ከሚገኙ ጥንታውያን ገዳማት መካከል አንዱ ነው፡፡ ይህ ገዳም ባለፈው ፳፻፱ ዓ.ም አዲስ ህንጻ
ቤተክርስቲያን አሰርቶ ለማስመረቅ በቅቷል፡፡ አዲሱ ህንጻ ቤተክርስቲያን ከዚህ በታች በምስል የምትመለከቱት ነው፡፡ ይህን ህንጻ
ገንብቶ ለዚህ ደረጃ ለማድረስ የደብረ ማርቆስ ህዝብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ይህ ገዳም ለከተማው ቅርብ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ
ጠዋትም ማታም ምእመናን ቦታውን ሳይረግጡ አይውሉም፡፡ በተአምር አድራጊ ጸበሉ የሚታወቀው ይህ ገዳም በየቀን ገቢው የተሻለ እንደሆነ
ይታወቃል፡፡ በዚህ ገዳም አካባቢ አዲስ የቦታ ምሪት የተደረገላቸው የከተማው ነዋሪዎች በብዛት ቤታቸውን ገንብተው በመኖር ላይ ይገኛሉ፡፡
ከዚህ ጋራም ተያይዞ ክረምት ላይ ከመኖሪያ ቤቶች ተጠራቅሞ ወደ ገዳሙ የሚመጣው ጎርፍ ለገዳሙ የወደፊት ስጋት እንደሆነ ገዳሙን
የተመለከተ ሁሉ የሚፈርደው እውነታ ነው፡፡ ገዳሙ መንፈስን የሚያድስ ልዩ ቦታ ሆኖ ሳለ የገዳሙ የበላይ ጠባቂ ነኝ የሚሉት ብጹእ
አቡነ ማርቆስ የገዳሙን ስጋት የተረዱት አልመሰለኝም፡፡
ሁልጊዜ ትችት ወቀሳ ምን
ይሠራልሃል እንዳትሉኝ እንጅ ይህን የመሰለ የቀን ገቢው ከፍተኛ የሆነን ገዳም ገንዘቡን ለመቀራመት ብቻ ዓይንን ወደዚያ ቦታ ማሳረፍ
በተለይ አባት ለተባለ ሰው በጣም አሳፋሪ ነው፡፡ ብጹእነታቸው አቡነ ማርቆስ የዚህ ገዳም የበላይ ጠባቂ ነኝ ሲሉ ገንዘቡን ለመመዝበር
ታቅዶ እንደሆነ ለማንም የታወቀ ነው፡፡ ገዳሙ የራሱ ሰበካ ጉባዔ ያለው የራሱ ህንጻ አሠሪ ኮሚቴ የነበረው እንዲያውም በዐቢይ እና
በንዑስ ኮሚቴዎች ተዋቅሮ ከአዲስ አበባ እስከ ጎጃም፤ ከጎጃም እስከ ውጭ አገር ድረስ ከፍተኛ ጥምረት የነበራቸው ህንጻውንም ለዚህ
ደረጃ ለማብቃት አምላክ የፈቀደላቸው ነበሩ፡፡ ሆኖም ግን የገዳሙ የዕለት ገቢው መጨመሩ ያስጎመጃቸው ብጹእነታቸው የገዳሙን ገቢ
እንደፈለጉ ለማንቀሳቀስ ይመቻቸው ዘንድ ህዝበ ክርስቲያኑ አምኖባቸው የመረጣቸው የሰበካ ጉባዔ አባላትን በመሻር የሂሳብ ደብተሩ
በእርሳቸው ፊርማ እንዲንቀሳቀስ አድርገዋል፡፡ ጥር ፲፯/፳፻፱ ዓ.ም በብጹእነታቸው ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤ እንደሚያስረዳው ከሆነ
በገዳሙ ስም የተከፈተው የሂሳብ ቁጥሩ 708S01003793 የሆነን አካውንት ለሥራው ጥንቃቄ ሲባል በሦስት ሠዎች ፊርማ እንዲንቀሳቀስ
በሚል ለንግድ ባንክ ጽፈዋል፡፡ ይህንን ሂሳብ ለማንቀሳቀስ የተጻፈላቸውም የገዳሙ ሰበካ ጉባዔ አባላት ወይም ህዝብ የመረጣቸው ክርስቲያኖች
ሳይሆኑ፡-
፩ኛ. ብጹእ አቡነ ማርቆስ
የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ
፪ኛ. ሊቀ ማእምራን ቆሞስ
አባ እንባቆም ጫኔ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ
፫ኛ. መልአከ ጽዮን ቆሞስ
አባ ብርሃነ መስቀል ፈጠነ የገዳመ አስቄጥስ አስተዳዳሪ ናቸው፡፡
አቡነ ማርቆስ ይህንን ደብዳቤ
ፈርመው ለባንክ ሲልኩት በዚህ ብቻ አላበቁም፡፡ በገዳሙ ሥር የሚገለገሉ ምእመናን አቤቱታ ቢያቀርቡ እና አስተዳዳሪውን ተጽእኖ ቢያደርጉባቸው
እና ሂሳቡን ለማንቀሳቀስ አልፈርምም ቢሉ ገንዘቡን ማግኘት ስለማይችሉ ከሦስቱ ፈራሚዎች መካከል ሁለቱ እንኳ ቢገኙ ማንቀሳቀስ እንዲችሉ
ብለው ነበር የጻፉት፡፡ የገዳሙ ገንዘብ በሁለት ሰዎች ፊርማ ብቻ እንደፈለገው ይደረጋል ማለት አይደል ታዲያ፡፡ ይህንንም የውሸት
ክስ የውሸት ፈጠራ ነው ብላችሁ አስተያየት ለመስጠት የምትሞክሩ በዝምድና የተቀጠራችሁ ግለሰቦች እንደምትኖሩ አልጠራጠርም፡፡ ሆኖም
ግን ይህንን ጉዳይ የሚመለከተው ሰው ሁሉ ይፈርደዋል፡፡ ከመቼ ጀምሮ ነው አንድ ጳጳስ የባንክ ሂሳብ ፈራሚ ሆኖ ገንዘብ ማንቀሳቀስ
የጀመረው ያውም ታች ወርዶ የአንድን ገዳም ሂሳብ፡፡ ነገሩ በጣም የሚያሳዝን በጣምም የሚያሳፍር ነው፡፡
የቤተክርስቲያናችን ገንዘብ
በዚህ መልኩ ነው እየተመዘበረ ያለው፡፡ ቅርሶቻችንም በዚህ መልኩ ነው እየተዘረፉ ያሉት፡፡ ወገኔ! ቤተክርስቲያንህን እንደ ዓይንህ
ብሌን ጠብቃት፡፡ አምላክ አይጠብቃትም ወይ አንተ ከእግዚአብሔር በላይ እንዲህ የምትናገር ሳትሉ አትቀሩም መቼም፡፡ ታዲያ አቡነ
ማርቆስ የገዳሙ የበላይ ጠባቂ ነኝ ያሉት አምላክ ነኝ ማለታቸው ይሆን እናንተው ፍረዱት፡፡
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍
© መልካሙ በየነ
መስከረም ፴
/ ፳፻፲ ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣
ኢትዮጵያ
✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍
No comments:
Post a Comment