Wednesday, October 18, 2017

✍✝የሊቃውንት ጉባዔ ወልደ አብን አወገዘ✝✍




፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
የሊቃውንት ጉባዔ መስከረም ፳፫/፳፻፲ ዓ.ምባደረገው ስብሰባ “ወልደ አብ” የተባለውን የቅባቶች የክህደት መጽሐፍ በሚገባ መርምሮ የውሳኔ ሃሳቡን አስፍሯል፡፡ በዚህ ስብሰባ የሊቃውንት ጉባዔ የበላይ ኃላፊ ብጹእ አቡነ እንድርያስ፣ የሊቃውንት ጉባዔ ሰብሳቢ ሊቀ አእላፍ ያዝ ዓለም ገሰሰ፣ የእለቱ ቃለ ጉባዔ ጸሐፊ መጋቤ ምሥጢር ፍሬ ስብሐት ዱባለ እና ሌሎች ስምንት ሊቃውንት በአባልነት ተሳትፈዋል፡፡ በዚህም መሠረት ሊቃውንቱ በሰፊው ተመልክተው የሚከተለውን ውሳኔ አሳርፈዋል፡፡

·        «ወልደ አብ» የተባለው መጽሐፍ «የቅብዐትና የጸጋ የክህደት ትምህርትን የማስፋፋት ዓላማ ያለው የክህደት መጽሐፍ ነው» ሲል ውሳኔ አስተላልፈዋል፡፡
·        የዚህ መጽሐፍ ጸሐፊ ገብረ መድኅን እንዳለውም «መጽሐፉን አውግዞ ይቅርታ የማይጠይቅ ከሆነ ከቤተ ክርስቲያን እንዲለይ ይደረግ» ሲል የውሳኔ ሃሳብ ሰጥተዋል፡፡
በዚህ የሊቃውንቱ ውሳኔ መሠረትም “ወልደ አብ” የተባለው መጽሐፍ የቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ አለመሆኑን ሁሉም እንዲረዳ በኔ በኩል ማሳሰቢያ መስጠቴን ልብ በሉልኝ፡፡ ገብረ መድኅን እንዳለው የተባለ ግለሰብም የቤተክርስቲያናችን ልጅ እንዳልሆነ ጸጋ እና ቅባት የተከሉት እሾኽ መሆኑን እንዳትዘነጉ፡፡ ይህ ግለሰብ ገና ሌላም ነገር ሊያሳትም እንደሚችል የታወቀ ነው፡፡ ሆኖም ግን ይህን መጽሐፍ አውግዞ ቤተክርስቲያንን ይቅርታ የሚጠይቅ ከሆነ ከቤተክርስቲያን አባልነቱ ማንም እንደማያስወጣው የታወቀ ነው፡፡ ይህን ካላደረገ ግን መጽሐፉ እና የመጽሐፉ ጸሐፊ ሁለቱም በሊቃውንቱ የውሳኔ ሃሳብ መነሻነት ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዘው እንደሚለዩ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ የዘንድሮው የጥቅምት ወር የሲኖዶስ ስብሰባ ይህን መጽሐፍ ከነጸሐፊው እንዲሁም አይዟችሁ ባይ ከሆኑት ከሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ጋር ምክር ተግሳጽ እና ውግዘት እንደሚተላለፍ እንጠብቃለን፡፡

ይህ መጽሐፍ እንዲወገዝልን ባለፈው ዓመት ጀምረን ፊርማ አሰባስበናል መረጃዎችን በሚገባ አደራጅተን አቅርበናል በዚህም መሠረት የድካማችን ዋጋ ፍሬ ወደ ማፍራት እየተሸጋገረ ነው፡፡ በነገራችን ላይ በዚህ የፊርማ ማሰባሰብ ሥራ ላይ ሙሉ ኃላፊነት ወስዳችሁ ስትሰሩ የነበራችሁ እና የፈረማችሁ በሙሉ አመሰግናችኋለሁ፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ያሰባችሁትን ይፈጽምላችሁ እመ ብርሃን ወላዲተ አምላክ አትለያችሁ አሜን፡፡

በቀጣይ ስለ አቡነ ዲዎስቆሮስ ትንሽ እንነጋገራለን፡፡ ለካ እንዲህ ያሉ ሰው ናቸው እንዴ ያልሰማችሁትን ጉድ ነው የምነግራችሁ!!!
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍
© መልካሙ በየነ
ጥቅምት ፰ / ፳፻፲ ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍
 

No comments:

Post a Comment