አቡነ ዲዮስቆሮስ |
ጉባዔው ሰኞ ጥቅምት ፮/፳፻፲ ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን በዚህ ጉባዔ ላይ ሥራ አስኪጁ አቡነ ዲዮስቆሮስ በአባ
ማትያስ ትእዛዝ እንዳይካተት የተባለውን የማኅበረ ቅዱሳን ሪፖርት በታዳሚዎች ፊት ምንም ሳያስቀሩ ልቅም አድርገው ተናግረዋል፡፡
ይህ የአቡነ ዲዮስቆሮስ ሪፖርት አንዳንዶቹን ያስቆጣ አንዳንዶቹን ደግሞ በሀሴት ያስፈነጠዘ እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ እንግዲህ
በማኅበረ ቅዱሳን ሪፖርት መቅረብ አለመቅረብ ላይ ሁለት ዓይነት አመለካከቶች እንዳሉ ልብ ብለናል፡፡ በነገራችን ላይ አቡነ ማትያስ የተሳካላቸው ነገር እንዳለ መዘንጋት የለብንም፡፡
አንደኛ የማኅበረ ቅዱሳን ተወካዮች ለመጀመሪያ ጊዜ እንዳይገኙ አድርገዋል፡፡ ሁለተኛም በ “ዓዋጅ ነጋሪ” መጽሔት ተካቶ ይታተም
የነበረው የማኅበሩ የሥራ እንቅስቃሴ ተቆርጦ እንዲወጣ አድርገዋል፡፡ ዘንድሮ አንድ እና አንድ የሆነ እልባት ካልተበጀለት አቡነ
ማትያስ በቀጣዩ ዓመት በሚካሄደው ጉባዔ ላይ የማኅበረ ቅዱሳን ሪፖርትም እንዳይካተት ሊደረግ እንደሚችል ነው የሚያሳየን፡፡
በዚህ ጉባዔ ላይ የማኅበሩን ሪፖርት በኩራት ያቀረቡትን አቡነ ዲዮስቆሮስን “ዳግማዊ ዲዮስቆሮስ” ብለው
እንዲጠሯቸውም ምክንያት የሆናቸው ይኸው እውነትን ብቻ ይዘው መነሣታቸው ነበር፡፡ አቡነ ዲዮስቆሮስ ይህን እውነት ለታዳሚው ማቅረባቸው
እውነተኛ የተዋሕዶ ልጆችን በሐሴት ቢያስፈነጥዝም በመናፍቃኑ ዘንድ ግን ጆሯቸውን ጭው አድርጎ አጥወልውሎ እንደደፋቸው ማረጋገጥ
ይቻላል፡፡ ለዚህም እንቅልፍ አጥተው የፈበረኩት አንድ የፈጠራ ወሬ አለ፡፡ ይህን የፈጠራ ወሬ ከዚህ ሙሉ ንባቡን አያዠላችኋለሁ፡፡
ይህን የውሸት ወሬ እያራገበ ያለው “ኣግኣዝያን ንሕበር” የተባለ የፌስቡክ ገጽ ነው፡፡ ይህን ጽሑፍ የለቀቀውም አቡነ ዲዮስቆሮስ የማኅበረ ቅዱሳንን ሪፖርት በማቅረባቸው
የፌስቡክ ተጠቃሚዎች በብዛት የአቡነ ዲዮስቆሮስን ፎቶ እየለቀቁ ደስታቸውን በገለጹበት ማግስት ማክሰኞ ጥቅምት ሰባት ቀን ነው፡፡
ይህ ሀሳዊ የለቀቀውን የውሸት ሪፖርት ሙሉውን ተመልከቱት፡፡
****************************************************************
የማ/ቅርሱሳን የህሊናው እስረኛ ኣባት፦===================
ከዚህ ጽሑፉ ጋራ ያያዘው ፎቶ ግራፍ
|
ኣቡነ ዲዮስቆሮስ ይባላሉ ፤ እሳቸው በዝዋይ መነኩሴ እያሉ የምታይዋትን የእህታችን ንስሃ
ኣባት የነበሩና በኣሁኑ ሰኣትም ቢሆን የድብቅ (ቅምጥ) ባለቤታቸው እንደሆነች የማ/ቅርሱሳን ኣባላት የውስጥ ኣዋቂዎች ይጠቋቆሙባቸዋል።
የምታዩት ደስ የሚል ህጻንም እንደወለዱላትም በማህበሩ ኣባላት እየተነገረ ነው። እኝህ የማ/ቅ የህሊናው እስረኛ ኣባት ይሄ ብቻ
ኣልበቃ ብሏቸው ብዙ ነውርና ነቀፌታ እንዳላቸው ማ/ቅርሱሳን በደንብ ስለሚያውቅ በሚፈልገው መልኩ እያስፈራራ እና ስጋት እየሰጠ
የባ/ዳሩ ጳጳስ ኣብርሃምን ጨምሮ ለዓላማው መሳካት ከሚጠቀምባቸው 7ቱ ሊቃነ ጳጳሳት እና ቆሞሳት መነኩሳት መካከል ዋነኛው ናቸው።
እውነት ህሊና ላለው ሰው የማ/ቅርሱሳን የህሊናው እስረኞች ኣባቶች እጅግ ያሳዝናሉ።
አባ ዲዮስቆሮስ በአሁኑ ሰዓት ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ኣደጋ ላይ የጣሉት የማ/ቅርሱሳን
ጠበቃና ሻንጣ ተሸካሚ ሆነው ሳይወዱ በግዳቸው በማገልገል ላይ ይገኛሉ። እኚህ መከረኛ ኣባት የፓትርያርኩን ትእዛዝ ተጋፍተውና የካሳ
ተክለብርሃንና የማ/ቅርሱሳንን ሪፖርት እስከማቅረብ የተገደዱበት ሚስጥርም ይህ ነው። ማህበሩ በ36ኛው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ
ባልተገኘበት ሁኔታ እሳቸው ከማህበሩ በተሰጣቸው ቀጭን የማስፈራርያ ትእዛዝ መሰረት በጉባኤው መክፈቻ ላይ የማ/ቅርሱሳን ሪፖርት
እንዲያቀርቡ ተገደዋል።
አባ ዲዮስቆሮስ ይህንን ጉድ ኣድርገውት ይሁን ኣይሁን እሳቸው ፤ እናትየዋና እግዚኣብሄር
ብቻ ናቸው የሚያውቁት ፤ ምናልባትም ማ/ቅርሱሳን ለዓላማው ያልተገዙና ዓይንህን ላፈር ያሉትን የብዙዎች ብፁኣን ኣባቶች ስም በፈጠራና
እንዲሁም በክፉዎች የማህበሩ ሴት ኣባላቱ ተልእኮ ኣሳሳችነት የወደቁም ሊሆኑ ይችላል ፤ ነገር ግን እኝህ ኣባት ማ/ቅርሱሳን ኣሽክላ
ውስጥ ኩፉኛ ወድቀው ለማህበሩ ሳይወዱ በግዳቸው በትሮይ ፈረስነት እያገለገሉ ይገኛሉ። ማህበሩ እንደ ባርያ በደንብ ተጠቅሞ እንደሚተፋቸውም
ይጠበቃለ።
እሳቸው ከእናት ቤተክርስቲያን ይልቅ ለኣጋንንት
ማህበር ያገለግሉ ዘንድ ተገደዋል።አባ ዲዮስቆሮስ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ስለተያዘ ኣሁንም በመመላለስ ላይ ይገኛሉ።
****************************************************
ይህ ግለሰብ የጤና ችግር ሊኖርበት እንደሚችል እገምታለሁ፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንን “ቅርሱሳን” በሚል ተክቶ
ነው እየጻፈ ያለው፡፡ አጻጻፉ በትግራይ ክልል የሚገኝ የተሐድሶ መናፍቃን ቅጥረኛ እንደሆነ ያሳውቃል፡፡ “አ” በማለት ፈንታ ራብዕ
“ኣ” ን በብዛት ይጠቀማል፡፡ ራብዕ ሆሄያት ላይ በብዛት አትኩረው ያለ ቦታቸው (በአማርኛ ማለቴ ነው) የሚጠቀሙ እነማን እንደሆኑ
እናውቃለን፡፡ ስለዚህ ይህ ልጅ ቦታው ታውቋል ግበሩም ተረጋግጧል፡፡
እነዚህ መናፍቃን ሌት ከቀን እንቅልፍ በማጣት ነው እየሠሩ ያሉት ከታች የተያያዘው ፎቶም በዚሁ ልጅ ገጽ
ላይ ተያይዞ የተለጠፈ ነው፡፡ አቡነ ዲዮስቆሮስ የማኅበረ ቅዱሳንን ሪፖርት ስላቀረቡ ብቻ ይህን ስም መለጠፍ በጣም ያሳፍራል፡፡
የማንስማማባቸው የማንገናኝባቸው ልዩነቶች ሊኖሩ ይችላሉ በነዚያ ልዩነቶች ላይ በጥልቀት መመካከር መወያየት ልዩነትን እንደያዙ መቀመጥ
ይቻላል፡፡ ከዚያ ውጭ ግን ያልሆነ ነገር ምንም የሌለ ነገር ከባዶው ተነስተን እንዲህ ማለት ያሳዝናል፡፡ ይች በፎቶ የተለጠፈችው
ግለሰብ እና ይህ ህጻን በእውነቱ የማን እንደሆኑ እነማን እንደሆኑ ብትለዩልን እና በሚገባ ብንጽፍ ደስ ይለኛል፡፡ ፍርድ ቤት ክስ
ተመስርቶባቸው እስካሁን ድረስ ማን ነው ደብቆ ያስቀመጣቸው? እንኳን ትንሽ እንከን ዓይታችሁ ሳታዩስ ወሬ እየፈጠራችሁ አይደል እንዴ?
እውነት ነው ካልክ ዝም ብለህ ሜዳ ላይ ያነሣኸውን ፎቶ ከምትለጥፍ የክሱን መጥሪያ አያይዝልን፡፡
“አባ ሰላማ” የተባለ ድረገጽ ይህንን ዓይነት ወሬ በመፈብረክ የመጀመሪያው ነው፡፡ የዚህም ዋና አንቀሳቃሽ
አባ ሰረቀ ብርሃን ናቸው ይባላል፡፡ እስኪ ለማንኛውም እውነት እውነቱን ብቻ በመረጃ እያስደገፍን እናውራ፡፡ አቡነ አብርሃምን ጨምሮ
ሰባት ሊቃነ ጳጳሳት በማኅበረ ቅዱሳን ተይዘዋል የምትለውስ እስኪ መረጃህን አሳየን እና እንመንህ፡፡ ለነገሩ እኔ ሃሳብህ ስላናደደኝ
እንጅ የሚያነብልህ ሰው ራሱ ያለ አይመስለኝም፡፡ በጅል ወሬ ጊዜ የሚያባክን ያለ አይመስለኝም እኔ ግን አንተ ተጃጅለህ አጃጃልከኝና
አነበብሁልህ ምላሽም እነድሰጥህ ተገደድሁ፡፡ የቤተክርስቲያኒቱ የበላይ ኃላፊ አዛዥ ቅዱስ ሲኖዶስ እንደሆነ ስለማታውቀው “ለፓትርያርኩ
ሳይታዘዙ ቀርተዋል” እያልህ ወሬህን ትነዛለህ፡፡ ፓትርያርኩ እኮ ከቅዱስ ሲኖዶስ በላይ አይደሉም በታች እንጅ፡፡ አቡነ ዲቆስቆሮስ
ያደረጉት እኮ የቅዱስ ሲኖዶስን ትእዛዝ ሰምተው ነው፡፡ አቡነ ማትያስ ከቅዱስ ሲኖዶስ በላይ የሚሆኑበት ምንም ዓይነት መንገድ የለም፡፡
ማኅበረ ቅዱሳንን መጥላት ሌላ ማኅበሩ ይህን ሠርቷል ብለው እውነቱን የተናገሩትን ጥላሸት መቀባት ሌላ ነው፡፡ ማኅበሩን የወደዱትን
መውደድ ማኅበሩን የጠሉትን መጥላት አይደለም አሁን ሥራችን፡፡ እውነቱ ምኑ ጋር ነው ብለን እውነቱን መቆፈሩ ላይ ነው እንጅ፡፡
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍
© መልካሙ በየነ
ጥቅምት ፱
/ ፳፻፲ ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣
ኢትዮጵያ
✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍
No comments:
Post a Comment