Tuesday, October 31, 2017

"ምእመናን አልከሰሱኝም” ብጹእነታቸው አቡነ ማርቆስ




፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
#የምሥራቅ_ጎጃም_ሀገረ_ስብከት_ጉዳይ_ጉዳየ_ነው_በሚል_ለብጹአን_አባቶቻችን_የስልክ_መልእክት_እያደረሳችሁ_እና_ስልክ_እየደወላችሁ_ያላችሁ_ወንድሞች_እህቶች_አባቶች_እናቶች_ጉዳዩ_ስለታየልን_ስልክ_መደወሉን_እና_መልእክት_መላኩን_እንድታቆሙ_እናሳስባለን፡፡ #ብጹአን_አባቶቻችን_ሥራ_መሥራት_አልቻልንም_መልእክት_በዛብን_ስላሉ_አሁን_ጀምሮ_ቢቆም_መልካም_ነው፡፡ ላደረጋችሁት ትብብር ግን ከልብ እናመሰግናለን፡፡
************************



Sunday, October 29, 2017

የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ጉዳይ በቸልታ ባይታይ!




፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
አሁን ለአቡነ ሳዊሮስ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊ የጽሑፍ መልእክት እንድናደርስ በተጠራው የተማጽኖ ጥሪ ላይ ብዙ ሰው እየላከ እንደሆነ ነው የሚታወቀው አሁንም ይላክ፡፡ ከምሥራቅ ጎጃም እያላችሁ በእነዚህ ስልክ ቁጥሮች የተማጽኖ መልእክት አድርሱ፡፡
0911862433 ላይ እባካችሁ የምሥራቅ ጎጃምን ህዝብ አቤቱታ መላ ስጡት እንበላቸው፡፡ አቤቱታ ባቀረብን ጊዜ የምስል የድምጽ እና ሌሎች ማንኛውንም መረጃ ለአቡነ ሳዊሮስ በእጃቸው በፍላሽ አድርገን የሰጠን ሲሆን እስካሁን ግን ምንም ዓይነት መረጃ እንዳልቀረበ ነው የተነገረው፡፡
**************************************
የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት አሁን ባለበት ሁኔታ አስተዳደራዊ ብቻ ሳይሆን ሃይማኖታዊ በደልም እየተፈጸመበት ነው የሚገኘውው፡ ይህንንም ጉዳይ ለሰባት ጊዜ በራሱ ወጭ አቤቱታውን ለቅዱስ ሲኖዶስ ሲያሰማ የነበረው ጨዋው የምሥራቅ ጎጃም ህዝብ የዘንድሮውን የጥቅምት ሲኖዶስ የድካሙ ማረፊያ እንደሚሆን ገምቶ ነበር ሆኖም ግን በፓትርያርኩ እምቢተኝነት የምሥራቅ ጎጃም ህዝብ አቤቱታ አጀንዳ መሆን የለበትም ብለው በፈጠሩት አምባጓሮ በአጀንዳነት ሳይያዝ ቀርቷል፡፡ በትናትናው የቅዱስ ሲኖዶስ ውሎ ምሥራቅ ጎጃምን ብቻ ሳይሆን ዓለምን በሙሉ ሲያውቅ የነበረው የቅባቶች መጽሐፍ “ወልደ አብ” ተምርምሮ ውግዘት ተላልፎበታል፡፡ አሁን እየተሠራጨ ካለበት አካባቢም ተሰብስቦ እንዲቃጠል በተለይም መጽሐፉ ታትሞ በተሠራጨበት ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ቤተክህነት የእቅበተ እምነት ሥራ በሰፊው መሠራት እንዳለበት ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔውን አስተላልፏል፡፡ ይህንንም ተከትሎ መጽሐፉ የሚሠራጭባቸው ቦታዎች ምስካበ ቅዱሳን ቆጋ ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም ጎንቻ ሲሶ ውስጥ የሚገኝ እና አባ ዐስራት ገዳም ደብረ ማርቆስ ውስጥ የሚገኝ መጽሐፉን በመደበቅ ላይ እንደሆኑ ተነግሯል፡፡

በዚህ የክህደት መጽሐፍ ዙሪያ የተጠየቁት የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማርቆስ “ወልደ አብ” የኑፋቄ መጽሐፍ መሆኑን አላውቅም ነበር በማለት በጉባዔው ሲሳለቁ ተስተውለዋል፡፡ እንዲያውም የዚህን የመጽሐፉን ጉዳይ በመሸፋፈን ነገሩን ወደ ማኅበረ ቅዱሳን ለማላከክ ሲሞክሩ ተስተውለዋል፡፡ “ማኅበረ ቅዱሳን ዳግም እያጠመቀ ነው” በማለትም ሲከሱ ውለዋል፡፡ ሆኖም ግን ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት በተለይም እነ አቡነ እንድርያስ፣ አቡነ ኤልሳዕ፣ አቡነ ሉቃስ፣ አቡነ ዘካርያስ፣ አቡነ አብርሃም፣ አቡነ ቀውስጦስ እና ሌሎችም ጉዳዩን በጥልቀት ስለሚያውቁት “ጥምቀት የሚያጠምቅ ቄስ እንጅ ማኅበረ ቅዱሳን አይደለም፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ሥራው ማስተማር ብቻ ነው” ብለው መልሰውላቸዋል፡፡ አቡነ ማርቆስም ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳትን በመሳደብ ለማሸማቀቅ ሞክረዋል፡፡ በዚህም የተነሣ ጥቅምት ፲፯ ከሰዓት በኋላ በተደረገው ስብሰባ የአቡነ ማርቆስ የዲሲፕሊን ጉዳይ ታይቶ ይቅርታ እንዲጠይቁ ተደርጓል፡፡ ብጹአን አባቶች እንዳሉት “ከጳውሎስ ሳምሳጢ የተጠመቀ ሰው ቢኖር ይጠመቅ” ይላልና በቅብአተ መንፈስ ቅዱስ ከበረ ባዮች ወደ ርትእት ተዋሕዶ እምነታችን ሲመለሱ መጠመቅ እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከትን የሚከታተል ቋሚ ኮሚቴ ተዋቅሯል፡፡ በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ዙሪያ ያስተዳድሩታል ይመሩታል ብለን እምነት ልንጥልብዎ አንችልም ተብለው አቡነ ማርቆስም ተገስጸዋል ተመክረዋል፡፡

ከፍተኛ ፍጥጫ የነበረበት የትናንትናው የቀትር በኋላው ስብሰባ አቡነ ማርቆስ ላይ ከፍተኛ ወቀሳ ደርሶባቸዋል፡፡ “የክህደት መጽሐፍ ታትሞ ሲሰራጭ አላውቅም የሚሉ ምን እየሠሩ ነው” ተብለው ከምልአተ ጉባዔው ደረቅ ጥያቄ የተተየቁት ብጹእነታቸው ምልአተ ጉባዔውን በማሸማቀቅ ለማለፍ ጥረት አድርገዋል፡፡ አቡነ እንድርያስ እና አቡነ ቀውስጦስ ከፍተኛ ክርክር ያደረጉ ሲሆን አቡነ አብርሃም እና አቡነ ዘካርያስም በከፍተኛ ቁጭት ለምእመናን በመጨነቅ በአቡነ ማርቆስ ላይ ወቀሳቸውን ሰንዝረዋል፡፡ አቡነ ሳዊሮስም በጣም በማዘን “መንፈስ ቅዱስ የሚመራውን ጉባዔ እንዲህ እላፊ ቃል መነጋገሪያ ሲሆን ማየት በጣም ያሳዝናል” ብለዋል ተብሏል፡፡
የምሥራቅ ጎጃም ህዝብ በጉጉት የሚጠብቀው ጉዳይ የአቡነ ማርቆስን ከሀገረ ስብከቱ መነሣታቸውን ጉዳይ ነው፡፡ አቡነ ማትያስ እና አቡነ ማርቆስ ግን የተስማሙበት ነገር ያለ ይመስላል፡፡ ምልዓተ ጉባዔው ከምሥራቅ ጎጃም እንዲነሡ ውሳኔ እንዳያስተልልፍ ይቅርታ ይጠይቁ ብለው የመከሯቸውም ይመስላል፡፡ የዕቅበተ እምነቱ ሥራ የሚራው አቡነ ማርቆስ ሀገረ ስብከቱ ላይ እያሉ ከሆነ በጣም ትልቅ ፈተና ነው፡፡ “ሚሥጢረ ሃይማኖት ወትንቢተ ዘዝክሪ ወጳውሊ” የሚለው ሁለተኛው የክህደት መጽሐፍም በሊቃውንት ጉባዔ እንዲታይ ምልአተ ጉባዔው ወስኗል፡፡ ነገር ግን እነዚህን የምልዓተ ጉባዔውን ውሳኔዎች ተግባራዊ ለማድረግ አቡነ ማርቆስ መነሣት የለባቸውም ነበር ወይ? የሚለው ጉዳይ ይታሰብበት ባይ ነኝ፡፡ ምእመናንን በማያውቁት ነገር ለምን እናስጨንቃቸዋለን ለምንስ እንፈታተናቸዋን፡፡ #ብጹአን_ሊቃነ_ጳጳሳት_ሆይ! የምሥራቅ ጎጃምን ሀገረ ስብከት እንዲህ በቀላሉ ባታልፉት መልካም ነው፡፡ “ወልድ ፍጡር ነው” የሚለውን ትምህርት በመድረክ እያስተማሩ ያለበትን ሁኔታ ማስቆም ይኖርብናል ይኖርባችኋል፡፡ በቀላሉ በስልጠና ይፈታል ተብሎ የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም፡፡ ነገሩ የተወሳሰበ እየሆነ ነው ያለው፡፡ ይህንን ትምህርት አሰልጥነው በተለያዩ ቦታዎች እንዲስተምሩ የተዋቀሩ ማህበራትም እንዳሉ መረጃው አለን፡፡ ስለዚህ የማያዳግም ምላሽ ለመስጠት ይመች ዘንድ የአቡነ ማርቆስ ጉዳይ ይታሰብበት፡፡

በአቡነ ማርቆስ ላይ የቀረበ ምንም ዓይነት ክስ የለም መረጃችሁ ተደብቆ ነው የቀረው ያሉን የመረጃ ምንጮች አሁንም በቀጥታ መረጃውን ለብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት ማድረስ እንደሚገባ ተነግሯል፡፡ ስለዚህ አዲስ አበባ አካባቢ የምትገኙ ልጆች ይህን የምስል እና የድምጽ መረጃ በተለይ ለብጹእ አቡነ ዘካርያስ እንዲደርስ ይደረግ፡፡ አቡነ ዘካርያስ ይህንን መረጃ ለምልአተ ጉባዔው በማቅረብ አቡነ ማርቆስ እንዲነሡ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ናቸው ተብሏል፡፡
አሁን ለአቡነ ሳዊሮስ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊ የጽሑፍ መልእክት እንድናደርስ በተጠራው የተማጽኖ ጥሪ ላይ ብዙ ሰው እየላከ እንደሆነ ነው የሚታወቀው አሁንም ይላክ፡፡ ከምሥራቅ ጎጃም እያላችሁ በእነዚህ ስልክ ቁጥሮች የተማጽኖ መልእክት አድርሱ፡፡
0911862433 ላይ እባካችሁ የምሥራቅ ጎጃምን ህዝብ አቤቱታ መላ ስጡት እንበላቸው፡፡

፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍
© መልካሙ በየነ
ጥቅምት ፲፰ / ፳፻፲ ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍

የ “ወልደአብ” መወገዝ ያስደሰተን የምንፍቅና መጽሐፍ ስለሆነ እንጅ ቅባቶችን ለማበሳጨት አይደለም!




፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠


የዘንድሮው ቅዱስ ሲኖዶስ እንደ መጀመሪያው የመክፈቻው ቀን ቢሆን ኖሮ ቤተክርስቲያንን በታሪክ የሚያስወቅሳት ጉዳይ እንደነበር የታወቀ ነው፡፡ እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነው በመንፈስ ቅዱስ የሚመራውን የሐዋርያት ጉባዔ በተከፋፈለ ሃሳብ ሲሰነጣጥቁት እና አንድ ልብ አንድ ሃሳብ መሆን ሲሳናቸው ሁላችንም አዝነን ነበር፡፡

Thursday, October 26, 2017

✍✝ቀጣዩ ውግዘት ለማን ይሆን?✝✍




፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
አጫጭር መረጃዎች!
·        “ቅባት የሚባል ነገር የለም ዳግም ጥምቀትም የለም” በሚል በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት የሚገኙ የወረዳ ቤተክህነት ሥራ አስኪጆች የየአጥቢያዎችን ካህናት ሰብስበው እያወያዩ ነው፡፡
·        አቡነ ማርቆስን በመደገፍ አዲስ አበባ የሄዱ ሥራ አስኪጆች ጸሐፊዎች እና ካህናት የውሎ አበላቸውን ከቤተክርስቲያኒቱ ሊወስዱ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

Wednesday, October 25, 2017

✍✝ከፓትርያርኩ በላይ የለም እያላችሁ ካቶሊክ እንዳታደርጉን ተጠንቀቁ!✝✍




፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
በገዛ፡ ደሙ፡ የዋጃትን፡ የእግዚአብሔርን፡ ቤተ፡ ክርስቲያን፡ ትጠብቋት፡ ዘንድ፡ መንፈስ፡ ቅዱስ፡ እናንተን፡ ጳጳሳት፡ አድርጎ፡ ለሾመባት፡ ለመንጋው፡ ዅሉና፡ ለራሳችኹ፡ ተጠንቀቁ። ግብ.ሐዋ ፳፥፳፰

Monday, October 23, 2017

✍✝የምሥራቅ ጎጃም ምእመናን የደርሶ መልስ ዘገባ✝✍



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
አጫጭር መረጃዎች!
·        አባ ማርቆስ ባስተላለፉት አስቸኳይ የድጋፍ ጥሪ መሠረት ከእነማይ ከደጀን እና ከደብረ ማርቆስ የተውጣጣ የሥራ አስኪጆች የጸሐፊዎች እና የአድባራት እና የገዳማት አስተዳዳሪዎች ስብስብ ወደ አዲስ አበባ በማቅናት ላይ ነው፡፡
·        አባ ማርቆስን ደግፈው ከብቸና ታርጋ ቁጥሩ 15835 ከደጀን ታርጋ ቁጥሩ 13552 በሆኑ መኪናዎች እየሄዱ እንደሆነ መረጃው ደርሶኛል፡፡
·        ይህንን ጉዞ በዋናነት ያስተባበሩትም የእነማይ ወረዳ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ አባ ፍቅረ ሥላሴ እና ጸሐፊያቸው ሊቀ ጠበብት አብርሃም ካሳ እንደሆኑ ተጠቁሟል፡፡
·        ዛሬ አዲስ አበባ ካልገባችሁ ከሥራ ትታገዳላችሁ ደመወዝም አይከፈላችሁም ተብለው እንደተነገሩ ከተጓዦች መካል አንዱን ዋቢ አድርጎ “መጽሔተ ተዋሕዶ” መዘገቧንም ዓይተናል፡፡



·        የምሥራቅ ጎጃም ምእመናን ጉዟቸውን በሰላም ፈጽመው ወደ መካነ ግብራቸው ተመልሰዋል፡፡

Friday, October 20, 2017

✍✝“ሥልጣን እለቃለሁ”--ቅዱስ ፓትርያርኩ✝✍



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ይኼ ፌስቡክ ደግሞ ዛሬ ሰበር ዜና አድርጎ በጠዋቱ የነገረኝ  አቡነ ማትያስ “ሥልጣን እለቃለሁ” አሉ የሚለውን ነው፡፡ በእውነት ቅዱስነታቸው አቡነ ማትያስ ይህንን ተናግረውት ይሆን? ብየ ራሴን ስጠይቅ ብዙ ቆይቻለሁ፡፡ ቅዱስነታቸው “ሥልጣን እለቃለሁ” የሚሉ የሆነ አካልን አስገድደው የሆነ ሥራ ለማሠራት ፈልገው እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ በዚህ ጥቅምት ፮/ ፳፻፲ ዓ.ም ትናንት ጥቅምት ፱/ ፳፻፲ ዓ.ም በተጠናቀቀው ፴፮ኛ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ ላይ በሁለት ጎራ የተከፈሉ ሀሳቦች ተስተውለዋል፡፡ ሃሳቦቹም በዋናነት ያተኮሩት ከማኅበረ ቅዱሳን የሥራ እንቅስቃሴ ላይ ነበር፡፡ የሥራ ፍሬው በጉባዔው መቅረብ አለበት እና መቅረብ የለበትም የሚሉ ጎራዎች ነበሩ፡፡ ሆኖም ግን እውነት ምንጊዜም እውነት ስለሆነች እውነቱ በጉባዔው መካከል ቀርቧል፡፡




Thursday, October 19, 2017

✍✝እንቅልፍ ያጡ መናፍቃን✝✍







የዘንድሮው ጥቅምት ፮/፳፻፲ ዓ.ም የጀመረው ፴፮ኛ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ ከፍተኛ ልዩነቶች እየታዩበት ያለ ጉባዔ ነው፡፡ ገና ጉባዔው ከመጀመሩ አስቀድሞ በርካታ የደብዳቤ ልውውጦች የተካሄዱበትም እንደነበረ እናስታውሳለን፡፡ ፓትርያርክ አባ ማትያስ በተለይም ከቅዱስ ሲኖዶሱ ሥልጣን ውጭ በመሆን የማኅበረ ቅዱሳን ማንኛውም ዓይነት የሥራ
አቡነ ዲዮስቆሮስ

Wednesday, October 18, 2017

✍✝የሊቃውንት ጉባዔ ወልደ አብን አወገዘ✝✍




፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
የሊቃውንት ጉባዔ መስከረም ፳፫/፳፻፲ ዓ.ምባደረገው ስብሰባ “ወልደ አብ” የተባለውን የቅባቶች የክህደት መጽሐፍ በሚገባ መርምሮ የውሳኔ ሃሳቡን አስፍሯል፡፡ በዚህ ስብሰባ የሊቃውንት ጉባዔ የበላይ ኃላፊ ብጹእ አቡነ እንድርያስ፣ የሊቃውንት ጉባዔ ሰብሳቢ ሊቀ አእላፍ ያዝ ዓለም ገሰሰ፣ የእለቱ ቃለ ጉባዔ ጸሐፊ መጋቤ ምሥጢር ፍሬ ስብሐት ዱባለ እና ሌሎች ስምንት ሊቃውንት በአባልነት ተሳትፈዋል፡፡ በዚህም መሠረት ሊቃውንቱ በሰፊው ተመልክተው የሚከተለውን ውሳኔ አሳርፈዋል፡፡

Sunday, October 15, 2017

✍✝ቅዱስ ያሬድን በምን ቃል ነው የምንገልጸው?✝✍




፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ዛሬ ጽጌን ደጀን ደብረ አሚን ቤተክርስቲያን ነው ያሳለፍሁት፡፡ አምላክ ሲፈቅድ ሁሉ ይደረጋል፡፡ ምሽት አንድ ሰዓት ተኩል አካባቢ እዚህ ደብረ ማርቆስ ከሚገኘው ወንቃ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ልናድር ከአንድ ወንድሜ ጋር ወጣን፡፡ ነገር ግን ወደ መንገድ ስንወጣ ደጀን ሊወስደን የሚችል መኪና ነበር የፈለግን የገረመኝ እሱ ነው፡፡ ደግሞ መኪናው ተገኘ ከምሽት አንድ ሰዓት ተኩል በኋላ በአይሱዙ መኪና ተጭነን ደጀን ለሦስት ሩብ ጉዳይ አካባቢ ደረስን፡፡ ከዚያም ወደ ደብረ አሚን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አመራን በዚያም አደርን፡፡ ደጀን ደብረ አሚን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ላይ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ታቦት ተደርቦ ስለሚገኝ ሁሉንም ነገር አግኝተን ኪዳን አስደርሰን ወደ መነኸሪያ ሄድን፡፡
እኛ ስንሰማው ያደርነውን ጣዕሙ ልዩ የሆነውን ያሬዳዊ ዜማ በትንሹ ብናካፍላችሁስ ምናለበት ብለን አሰብንና ይኸው አዳምጡት ብለን ጋበዝናችሁ፡፡
‹‹እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፡፡
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፡፡
ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፡፡
ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፡፡
ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ፡፡›› https://www.youtube.com/watch?v=Ez2JT9Lgfow
ሊቃውንቱን ስሟቸውማ እንዴት እንዴት አድርገው እንደሚያዜሙት፡፡ አቤት ያለው የልብ ደስታ ነፍስ ልትወጣ እኮ ነው የምትደርስ፡፡ ያሬድ ግን ምን ያለ ጸጋ ነው የተሰጠው ግን! ይህን የመሰለ ዜማ ከሰማይ ሰምቶ የመላእክትን ዝማሬ እኮ ነው ያስተማረን ያለማመደን፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=Wn9MS88yjHk
https://www.youtube.com/watch?v=DRteAbc572Q&t=131s

፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍
© መልካሙ በየነ
ጥቅምት ፭ / ፳፻፲ ዓ.ም
ደጀን፣ ኢትዮጵያ

✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍

Friday, October 13, 2017

ስለእያንዳንዳችን የልጅነት ድርሻ ብንነጋገርስ




፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ግንቦት ፲፯/ ፳፻፲ ዓ.ም ለቤተክርስቲያናችን ዘበኞች ራሳችን እንሁን! በሚል ርእስ ቤተክርስቲያናችንን ከመናፍቃን ለመታደግ በርካታ የዘብነት ሥራዎችን መሥራት እንደሚገባን ገልጨ ጽፌ ነበር፡፡ ይህንንም ሙሉውን ይህንን ሊንክ ተጭናችሁ እንድትመለከቱ እጠይቃለሁ፡፡ https://melkamubeyene.blogspot.com/2017/05/blog-post_25.html በዚህ ጽሑፍ በዋናነት ያነሣኋቸው ነገር ግን በእናንተም የሚጨመርባቸው እና የሚጠናከሩ ነጥቦች የሚከተሉት ነበሩ፡፡ ዘብነት በሚል ያስቀመጥኋቸው የልጅነት ድርሻችንን ነው፡፡ እኛ እንደ አንድ የቤተክርስቲያን ልጅነት መወጣት የሚገባን ምንድን ነው?
#ዘብነት_፩. ሁሉም ሰው የአብነት ትምህርትን በሚችለው አጋጣሚ ሁሉ መማር አለበት፡፡ የሚችል ሰው ጉባዔ ቤት ገብቶ ሁሉንም የቤተክርስቲያናችን እውቀት ማወቅ አለበት፡፡ ያልቻለ ሰው ደግሞ ዘመናችን ቴክኖሎጅው የተራቀቀበት ዘመን ስለሆነ ሁሉንም የአብነት ትምህርቶችን በድምጽም ሆነ በምስል እየቀረጸ ከቤቱ ቁጭ ብሎ ጊዜ ሰጥቶ ማጥናት እና መማር ይችላል፡፡ ያጠናውን ነገር በአግባቡ መያዙን ለማረጋገጥ ከአብነት መምህራን ጋር ተገናኝቶ ስህተቱን በማረም ሙሉ መሆን ይቻላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ማኅበረ ቅዱሳን በሚያቀርባቸው የአብነት ትምህርቶች ውስጥ በመሳተፍ ጊዜን በአግባቡ በመጠቀም መማር ይቻላል፡፡ አሁን ድራማ ፊልም ጨዋታ ምናምን የሚባል አሸንክታብ ጥለህ መገኘት አለብህ፡፡
#ዘብነት_፪. በነጻ ማገልገል፡፡ ይህኛው ዘብነት ከዘብነት ፩ በኋላ የሚመጣ ጸጋ ነው፡፡ የአብነት ትምህርቶችን ከተማርክ በኋላ ክህነት ማምጣት ከቻልህ ክህነት ታመጣለህ ማምጣት የማትችል ከሆነ ግን ትምህርትህን ብቻ ይዘህ ቤተክርስቲያን ውስጥ ትገባለህ፡፡ ታዲያ አገልግሎትህ ፍቅረ ንዋይ የሌለበት ለነፍስህ ብቻ ብለህ ይሁን፡፡ በቃ በነጻ አገልግል፡፡ በነጻ ማገልገል ስትጀምር ለ ”ቢዝነስ” ብሎ ቆቡን ያጠለቀው መሸሽ ይጀምራል፡፡ የምንኩስናው ቦታ ከተማ እንዳልሆነ መረዳት ይጀምራል፡፡ የምንኩስናው ቦታ በጾም በጸሎት የሚታገሉበት በረኃ ነው፡፡ እዚያ የአራዊቱን ድምጽ ፈርቶ የአጋንንቱን ፈተና ሸሽቶ ከተማ ለከተማ ቀሚሱን እያዝረከረከ የሚዞረውን አስመሳይ መነኮስ ሁሉ ቀልብ ያስገዛልሃል፡፡ በቃ አገልግሎት በነጻ ይሁን፡፡ ጳጳስም በለው የመምሪያ ኃላፊም በለው ሥራ አስኪያጅም በለው ቀዳሽም በለው ምንም በለው ምን በነጻ ያለገንዘብ አገልግል ተብሎ የነጻ አገልግሎት መስጠት ከተጀመረ ያን ጊዜ ቆቡን እየጣለ አዲስ “ቢዝነስ” ይጀምራል፡፡ ቤተክርስቲያናችንን ለቅቆ ይሄድልናል፡፡ ለአገልግሎት ሳይሆን ለፊርማ ብሎ ሰዓታት እና ማኅሌት የሚቆመው፣ ኪዳን የሚያደርሰው ቅዳሴ የሚቀድሰው ሁሉ በነጻ አገልግል ሲባል በሉ ደህና ሁኑ ብሎ ከቤታችን መውጣት ይጀምራል፡፡ 
#ዘብነት_፫. የያገባኛልነት ስሜትን መላበስ፡፡ ሁሉም ሰው ለቤተክርስቲያኑ ክብር ያገባዋል ይመለከተዋልም፡፡ ስለዚህ ቃጭል እያቃጨለ ስለ ጊዮርጊስ ስለ ማርያም እያለ የስእላትን ክብር ዝቅ በማድረግ በየመንገዱ በስእላት የሚነግደውን ነጋዴ ሁሉ እያነቁ ለፖሊስ ማስረከብ አለብን፡፡ የቤተ ክርስቲያን ማሰሪያ ተዘከሩን እያለ ተሰርተው በተመረቁ አብያተ ክርስቲያናት ሳይቀር ለልመና መናኸሪያ ለመናኸሪያ የሚዞረውን ነጋዴ ሁሉ እያነቁ መያዝ ነው፡፡ ስእላችን ክብር ይኑረው፣ ስማችን ክብር ይኑረው፣ ለማኞች ናቸው አንባል፡፡ ይህ ይቆጨን፡፡ ባለቤት የሌላት እስከምትመስል ድረስ ሁሉም ተነሥቶ የሚነግድባት ቤተክርስቲያናችን ታሳስበን እንጅ፡፡ ሁላችንም ያገባናል ሁላችንም ይመለከተናል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ የሚባል ደንቀራ መወገድ አለበት ይመለከተናል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተሸነፈ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስህተት ሰራ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወራጅ ቀጠና ገባ ወዘተ እየተባለ ሲነገር እንዴት አይሰቀጥጠንም፡፡ ስእላትን አስፋልት ላይ አንጥፈው የሚሸጡ፣ ከደብረ ሊባኖስ ከግሸን ተባርኮ የመጣ መስቀል እያሉ በሞንታርዶ የሚጮኹብንን እያነቅን ለፖሊስ እንስጣቸው፡፡ የራሷ የቤተክርስቲያናችንን ሱቅ እንከፍትላታለን፡፡
#ዘብነት_፬. የቶማስን እምነት መያዝ፡፡  ዘንድሮ መጠርጠር ጥሩ ነው፡፡ ቶማስ ኢየሱስ ክርስቶስን የተወጋ ጎንህን ካልዳሰስሁ አላምንም ብሎታል፡፡ በቃ! ይህ ለዘንድሮ ሰዎች ለእኛ ጥሩ ትምህርት ነው፡፡ ቀሚሱን ስለለበሰ አስኬዋውን ስለደፋ ብቻ መነኩሴ ነው ብለህ አትታለል፡፡ ውስጡን ማንነቱን ዳሰው ካልዳሰስኸው አትመን፡፡ እርሳቸው ጳጳስ ናቸው አይሳሳቱም አትበል ንስጥሮስ ፓትርያርክ እንደነበረ አትዘንጋ፡፡ እኛ ከሰበክንላችሁ ወንጌል ውጭ የሰማይ መልአክም ቢሰብክላችሁ አትቀበሉ ብሎናል ቅዱስ ጳውሎስ፡፡ በቃ መልአክ መስሎ ከሰማይ ቢወርድም አንሰማም!!!
#ዘብነት_፭. ከቤተክርስቲያን አለመራቅ፡፡ ብዙዎቻችን እኔን ጨምሮ ከቤተክርስቲያን ርቀናል፡፡ መቅደሳችን ውስጥ ገብተው ሲቀድሱ ላለማየት ሸሽተኛል፡፡ ይህ ግን መፍትሔ አይደለም፡፡ ሕጓን ሥርዓቷን እንማር ሁላችንም ሰንበት ትምህርት ቤት እንግባ፡፡ ልጆቻችንን እየያዝን እንማማር፡፡ ታሪካችንን እምነታችንን እናጥና፡፡ ሥርዓቷን ሕጓን እንማር፡፡ ከዚህ የወጣ ካየን ግን እንታገል፡፡
አሁን ሁላችንም ከእነዚህ ዋና ዋና ብየ ካነሣኋቸው ዘብነቶች በተጨማሪ እናንተም መጨመር እና ማጠናከር ትችላላችሁ፡፡ ይህንን የምንለው እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያኒቱ አያስብላትም ብለን አይደለም፡፡ እርሱ ያስብላታል ነገር ግን የእኛ በረከት ማግኛችን መንገዶች እነዚህ ናቸውና ነው፡፡ ከላይ ከተዘረዘሩት ዘብነቶች በተጨማሪም ዛሬ ላይ የምጨምራቸው የዘብነት ሥራዎች ይኖራሉ፡፡
#ዘብነት_፮. ንስሐ መግባት፡፡ ሁሉም ሰው ተዘጋጅቶ መኖር ያስፈልገዋል፡፡ የት፣ መቼ፣ እንዴት፣ ማን ላይ ንስሐ እገባለሁ የሚለው የየራሳችን ምርጫ እና ፍላጎት ነው፡፡ መንግሥተ ሰማያትን ለመውረስ ንስሐ የግድ እንደሆነ ማወቅ ከቻልን ከዚህ በኋላ ስላለው ዝርዝር አፈጻጸም የራሳችን ድርሻ ነው የሚሆነው፡፡ ንስሐ ገብተን ነጽተን በሥጋ ወደሙ ተወስነን እንኑር፡፡ አሁን ላይ ተሐድሶ እንዲፈነጭብን ዕድሉን የፈጠርንለት ራሳችን ነን፡፡ የመድረክ ላይ ስብከቶችን እንሰማለን ግን ለውጥ አምጥተን አናውቅም ለምን ቢባል ሰባኪውን ስለምናይ ነው፡፡ የምንናገረውን እና የምንጽፈውን ነገር ሆነን መገኘት ከቻልን በቃ እኛ ለተሐድሶ እሳቶች መሆን እንችላለን፡፡ ነውር ነቀፋ እንዳይገኝብን ራሳችንን ከሁሉ ነገር መጠበቅ ይኖርብናል፡፡ በንስሐ እንኑር በሥጋ ወደሙ እንወሰን፡፡
#ዘብነት_፯. ጾም እና ጸሎት፡፡ እስኪ ሃያ ዐራት ሰዓት መብላት እና መተኛት እናቁም፡፡ መናፍቃን  ሃያ ዐራት ሰዓት ለጥፋት ሲሰሩ እኛ ግን የሚመች ፍራሽ እየቀያየርን ሃያ ዐራት ሰዓት ሙሉ አልጋችን ላይ ነን ቆይ ግን አይቆጫችሁም፡፡ አሁን እኛ ሰዎች ነን፡፡ ሥራ በጣም ስለሚበዛብኝ ስለሚደክመኝ አልቻልኩም ወዘተ ብለን ለምን ተልካሻ ምክንያት እንደረድራለን፡፡ በእውነት እንደምናወራው እና እንደምንጽፈው ያለን ሰዎች ከሆንን እኮ ሌሊቱ ሙሉ የእኛ ነው፡፡ እስኪ ለዚሁ ብለን ጸሎት እንጀምር ጾም እናውጅ፡፡ እሽ ማን ብላ ብሎ አስገድዶህ ነው ጾም የምትሽረው እሽ ማን አትጸልይ ብሎህ ነው ሌሊቱን ሙሉ ተኝተህ የምታድረው፡፡ ይህን የምላችሁ እኔ ስለማደርገው አይደለም እኔንም ራሴንም ነው እየወቀስኩ ያለሁት፡፡ እኔማ እንዲያውም ቢሮ ውስጥም ሳንቀላፋ የምውል እልም ያልሁ እንቅልፋም ነኝ፡፡ ግን መሻሻል እንዳለብኝ አውቃለሁ መጸለይ አለብኝ መጾም አለብኝ፡፡ ይህ እኮ ለራሳችንም የበረከት ምንጭ ነው፡፡
#ዘብነት_፰. ለገዳማውያኑ ማሳሰብ፡፡ እስኪ መጸለይ ደከመን መጾም አልችል አልን ጸልዩልን ብሎ ገዳማውያኑንንስ መማጸን መባዕ መስጠት አንችልም፡፡ የተነሣብን ወረራ ቀላል አይደለም የዚህ ታሪክ አባል መሆናችን ደግሞ ለበጎ ነው፡፡ ከሠራን የምንመሰገንበት ለትውልድ የሚተላለፍ ሐውልት የምንተክልበት ካልሠራን ደግሞ ስም አጠራራችን የማይታወስበት ዘመን ነው፡፡ አባታችን ዲዎስቆሮስን ዛሬ ድረስ የምንዘክረው እኮ ለተዋሕዶ እምነቱ ጥርሱን እስኪያወልቁት ድረስ ስለታገሰ ጽሕሙ እስኪነጭ ድረስ ስለታገሰ ነው፡፡ አርዮስን በክፉ የምናነሳውስ ስለምንድን ነው ወልድ ፍጡር ስላለ ስለካደ እኮ ነው፡፡ የእኛም እጣ ፈንታ እንደዚሁ ያለ ነው፡፡ በእውነት አንተ እያለህ አንቺ እያለሽ ተዋሕዶ ስትደፈር ድንበሯ ሲፈርስ ቆመህ ትመለከት ቆመሽ ትመለከች፡፡ በቃ አንተ ካልቻልህ የሚችሉትን ገዳማውያኑን ቅዱሳን አባቶችን አሳስብ መባዕ ውሰድ፡፡
#ዘብነት_፱. ማኅበራትን ማጠናከር፡፡ አሁን በርካታ ማኅበራት አሉ እነዚህ ማኅበራት በጋራ ሆነው ለአንድ ዓላማ ወደፊት መገስገስ አለባቸው፡፡ ሰንበት ትምህርት ቤቶች፣ የጽዋ ማኅበራት፣ ዕድሮች፣ግቢ ጉባዔያት፣የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ወዘተ ሁሉም ለአንድ ዓላማ ኅብረታቸውን ማጠናከር አለባቸው፡፡ መርዝ የሚረጩትን አካላት ለይቶ ለህግ እስከማቅረብ ድረስ መጠናከር አለብን፡፡ በጋራ እየተረዳዳን እውነተኛ ስብከቶችን ያሬዳዊ መዝሙር ካሴቶችን ልዩ ልዩ መጽሐፎችን እና መጽሔቶችን በራሪ ወረቀቶችን ሳይቀር በማዘጋጀት ለህብረተሰቡ ማዳረስ ይኖርብናል፡፡ እውነቱን እውነት ሀሰቱን ሀሰት የሚል መልካም ራእይ ያለው ትውልድ መገንባት ያስፈልገናል፡፡ ይህን ማድረግ ስንችል መናፍቃኑን ከራሳችን ትክሻ ላይ አውርደን በባዶ እግራቸው መንዳት እንችላለን፡፡

በነገራችን ላይ ሌሎችንም በርካታ ነገሮችን መጨመር ትችላላችሁ እኔ ግን ለዛሬ ያለኝን ሃሳብ እዚህ ላይ ልቋጨው ተገደደሁ፡፡
#ውይይቱ_ጠንካራ_ሃሳቦችን_ማፍለቅ_አለበት_እስኪ_እንነጋገር_ዝም_አትበሉ_አስተያየት_ስጡ_እንወያይበት_ወደፊት_እንዴት_እንቀጥል? በረከት ማግኘት የምንችልበት ጊዜ ቢኖር አሁን ነው፡፡ ከዚህ በረከት መሳተፍ ካልቻልን አለቀልን መቼ በረከቱን ጸጋውን ልናገኝ እንችላለን ታዲያ፡፡
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍
© መልካሙ በየነ
ጥቅምት ፫ / ፳፻፲ ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍✝✍