Sunday, June 2, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 109

====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
ዘከመ ቦአ እግዚእ ኢየሱስ ኢየሩሳሌም።
ምዕራፍ ፳፩።
                    ******     
ዘከመ ሰደዶሙ ኢየሱስ ለእለ ያረኵሱ ቤተ መቅደስ።
፲፪፡ ወቦአ እግዚእ ኢየሱስ ውስተ ቤተ መቅደስ።
                    ******     
፲፪፡ ጌታ ከቤተ መቅደስ በገባ ጊዜ።
ወሰደደ ኵሎ እለ ይሰይጡ ወይሳየጡ ውስተ ቤተ መቅደስ
የሚሸጡትን ሁሉ አስወጣ ማለት ገበያውን ፈታ።
ወገፍትዓ ማዕዳቲሆሙ ለመወልጣን።
ብሩን ለወርቅ ወርቁን ለብር የሚለውጡበትን ስፍራቸውን
ወመናብርቲሆሙ ለእለ ይሠይጡ ርግበ ገንጰለ።
ርግብ የሚሸጡትንም ወንበራቸውን ገለበጠባቸው።
(ሐተታ) የከተማ ቅሬ በወንበር ተቀምጣ ዶሮ አንድትሸጥ እነሱም ቋንጤ ወምበር አላቸው ከዚያው ላይ ሁነው ርግብ ይሸጣሉና፡፡
                    ******     
፲፫፡ ወይቤሎሙ ጽሑፍ ቤትየሰ ቤተ ጸሎት ይሰመይ። ኢሳ ፶፮፥፯፡፡ ሉቃ ፲፱፥፵፮፡፡
                    ******     
፲፫፡ ቤቴ ቤተ መቅደስ የጸሎት ቤት ይባላል የሚል ጽሑፍ አለ።
ወአንትሙሰ ረሰይክምዎ በዓተ ፈያት ወሰረቅት።
እናንተ ግን የሌባ ዋሻ የወንበዴ ጋጃ አደረጋችሁት። ገበያ ከሆነ ግን የተሠረቀውን የተቀዋማውን ይሸጡበታል ይለውጡበታልና እንዲህ አለ።
አንድም ገበያው የሕዝቡ ነው ያሉ እንደሆነ ሁለቱን ቅጽር ወደ ውስጥ አንዱን ቅጽር ወደ ውጭ አድርገው ገበያ አድርገዋል ስለምን ቢሉ ቀረጥ ፈርተው። ከዚያ ገብተው አይቀርጧቸውም ቢሉ አይገቡባቸውም እንደ ሕጋቸው ይገዟቸዋል እያወጡ ይሸጣሉ፡፡
አንድም ድል ገበያ ሲሆን አጀም ያስፈራ ነበርና ዘግቶ ለመዋጋት። የካሕናት ክልክል መስክ አለ ከካሕናት አንዱ የሚያስወገሽ ልብስ ለብሶ ወደ ከብቱ ሂዶ ይቆማል ወግሽቶ ይገባል አውጥቼ ልውሰድ ያለ እንደሆነ ከል የገባ አይነጣ ቤተ መቅደስ የገባ አይወጣ እያሉ በምክንያት ያስቀሩባቸዋልና እንዲህ አለ። ገበያው የካህናቱ ነው ያሉ እንደሆነ ከአምስተኛው ቆመ ብእሲ አድርገውታል። ለመሥዋዕት ይሆናል ብሎ የሰባውን ከሩቅ አገር ነድቶ ይዞ ይመጣል፤ ከመንገድ ይከሳበታል እመቦ ዘቦ ዝክር ሠናይ ዘያበውዕ በግዓ ንዉረ ርጉም ውእቱ ትላለች ኦሪት፡፡ ይኽን ለምን አመጣኸው ይሉታል እኔስ የሰባውን ነበር ያመጣሁት ከመንገድ ከሳብኝ እንጂ ይላል ቅንነቱማ ካለ የሰባ የእኛ አለ በአንድ ሁለት ለውጠህ አትሠዋም ይሉታል እሺ ብሎ ያጣ እንደሆነ ነጭ ወርቅ ይዞ ይመጣል፤ ለምን ይኸን አመጣህ ይሉታል ቀይ ወርቅ ባጣ ነው እንጂ ይላል ቅንነቱማ ካለ ከእኛ ቀይ ወርቅ አለ በአንድ ሁለት አትሰጥም ይሉታል እንዲህ እያሉ ሁለተኛ ይቀበሉታልና እንዲህ  አለ፡፡
                    ******     
፲፬፡ ወመጽኡ ኀቤሁ ዕውራን ወሐንካሳን በቤተ መቅደስ።
                    ******     
፲፬፡ ጌታ በቤተ መቅደስ ሳለ ዕውራን ሐንከሳን መጡ።
ወአሕየዎሙ።
አዳናቸው።
                    ******     
፲፭፡ ወሶበ ርእዩ ሊቃነ ካህናት ወጸሐፍት መንክረ ዘገብረ ወደቂቅኒ እንዘ ይጸርኁ በቤተ መቅደስ ወይብሉ ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት።
                    ******     
፲፭፡ ሊቃነ ካህናት ጸሐፍትም ያደረገውን ተአምራት አይተው ለዳዊት ልጅ መድኃኒት መባል ይገባዋል ብለው ሲያመሰግኑ የሕፃናቱንም ምስጋና ሰምተው
ኢሐወዞሙ።
ደስ አላሰኛቸውም። ኢሐወዘኒ ሶበ ሞቁ። ኢሐወዘኒ ስዕሣዔ አፉክሙ እንዲል።
                    ******     
፲፮፡ አላ አንጐርጐሩ።
                    ******     
፲፮፡ አዘኑ እንጂ፣
ወይቤልዎ ኢትሰምዕኑ ዘይብሉ እሉ ሕፃናት። መዝ ፰፥፪።
እሊህ ሕፃናት የሚሉትን አትሰማምን አሉት።
ወይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ እወ።
አዎን እሰማለሁ ይገባኛል ብዬ ነው እንጂ አላቸው።
አልቦሁ አመ አንበብክሙ ይቤ እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐተ።
እንዲገባኝማ ለማጠየቅ ከልጆች ከሕፃናት አፍ ምስጋና አዘጋጀህ ያለውን የተመለከታችሁበት ጊዜ የለም አልተመለከታችሁም አላቸው።
(ሐተታ) ደቂቅ የመንፈቅ የዓመት ሕፃናት የዓመት ከመንፈቅ የሁለት ዓመት።
አንድም ደቂቅ የአርባ የሰማንያ ቀን ሕፃናት የመንፈቅ የዓመት ናቸው። ለነዚህ መሥዋዕት ሊሰዉላቸው ዕጕለ ርግብ ዘውገ ማዕነቅ ይዘውላቸው ወጥተዋል ሕፃናትም እናት አባታቸውን ተከትለው ወጥተዋል አዕባን ሲያመሰግኑ አይተው ከእናቶቻቸው ትክሻ እየወረዱ ሰሌን እየቈረጡ ይዘው አመስግነዋል።
                    ******     
፲፯፡ ወኃደጎሙ ወወጽአ አፍአ እምሀገር ወቦአ ቢታንያ ወቤተ ህየ።
                    ******     
፲፯፡ ትቷቸው ከከተማ ወጥቶ ቢታንያ ገብቶ አደረ።
                    ******     
በእንተ በለስ ዘተረግመት፡፡
ወጸቢሖ እግዚእ ኢየሱስ እንዘ የዓርግ ሀገረ ርኅበ
                    ******     
፲፰፡ ማለዳ ወደ ከተማ ሲወጣ ተራበ፡፡
                    ******     
፲፱፡ ወርእየ ዕፀ በለስ በፍኖት፡፡ ማር ፲፩፥፲፫፡፡
                    ******     
፲፱፡ በመንገድ ዕፀ በለስን አየ
ወሖረ ኀቤሃ ይንሣእ ፍሬ እምኔሃ፤
ፍሬ ባገኝባት ብሎ ወደሷ ሄደ
ወአልቦ ዘረከበ ውስቴታ ዘእንበለ ቈፅል ባሕቲቱ፡፡
ከቅጠል ብቻ በቀር ፍሬ አላገኘባትም
ወይቤላ ኢይኩን ፍሬ እምውስቴትኪ ለዓለም
እንግዲህ ወዲህ ለዘላለም ፍሬ አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፣
ወየብሰት በጊዜሃ ይእቲ በለስ
ያን ጊዜ ፈጥና አንድም በምትለመልምበት ጊዜ ደረቀች
(ሐተታ) በማርቆስ እስመ ኢኮነ ጊዜሁ ለበለስ ይላል ሊቁም እስመ መዋዕለ ክረምት ውእቱ ይላል፤ እንደሌለ ያውቅ የለም ቢሉ አንዳንድ በኩረ በለስ አይታጣም ብሎ ያው ቅሉ እንደሌለ ያውቅ የለም ቢሉ አላዋቂ ሥጋን እንደ ተዋሐደ ለማጠየቅ፡፡ አኮ ኢያእምሮ ኅቡዓተ አላ ከመ የሀብ መካነ ለጥንተ ትስብእቱ ዘኢየአምር ኅቡዓተ እንዲል፡፡
አንድም አውቃለሁ ብሎ ሥራውን አይተውምና በዚያው ሥራውን ለመሥራት፣
አንድም ወጸቢሖ ብለህ መልስ ሰው በሆነ ጊዜ ሰው ሁኖ ሲያስተምር ከሰው ፍቅር ተራበ ወርእየ ፅፀ በለስ እስራኤልን በኢየሩሳሌም አገኘ በለስ ዘይቤ ቤተ እስራኤል እሙንቱ እንዲል፡፡ ወሖረ ሃቤሃ ሃይማኖት ምግባር ባገኝባቸው ብሎ ሄደ፣ አላገኘባቸውም፤ ዘእንበለ ቈፅል ባሕቲቱ  እስራኤል ከመባል በቀር እስራኤል መባል ብቻ ነው እንጂ ወይቤላ ኢይኩን እንከ ፍሬ ደግ ሰው እንዳይገኝብሽ ብሎ ረገማት ወየብሰት ያን ጊዜ ደግ ሰው ጠፋ። ምነው እስጢፋኖስ ጳውሎስ ኤጲፋንዮስ ፲፬ ዕልፍ ከአራት ሽህ ሰማዕታት ሕጻናት የተገኙ ከእስራኤል አይደላም ቢሉ ከኒህ በቀር ሲል ነው፡፡
አንድም መልስ ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና አገኛት፤ ወሖረ ኀቤሃ ፈጻሜ ሕግ ተባለ። ወአልቦ ዘረከበ ዘእንበለ ቈፅል፥ ፈጻሜ ሕግ ከመባል በቀር ድኅነትን አላደረገባትም።
ወይቤላ ኢይኩን ፍሬ፤ በአንች ድኅነት አይደረግ አላት። ወየብሰት፤ ኦሪት ፈጥና አለፈች።
አንድም ወርእየ ዕፀ በለስ ብለህ መልስ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነ ኃጢአትን በዚህ ዓለም ሰፍና አገኛት።
አንድም በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል ቆይቶ ይኮመጥጣል። ኃጢአትም ሲሠሩት ደስ ያሰኛል ኋላ ያሳዝናልና፡፡ ወሖረ ኀቤሃ ኃጥእ ተባለ ወአልቦ ዘረከበ ኃጥእ ተመባል በቀር ኃጢአት አልሠራም። ወይቤላ ኢይኩን እንከ ፍሬ በአንቺ በመጣ ፍዳ የሚያዝ አይኑር አላት። ወየብሰት ኃጢአትም ፈጥና ጠፋች። በአንፃረ በለስ ረገማ ለኃጢአት እንዲል።
                    ******     
በእንተ ትውክልት ኀበ እግዚአብሔር።
፳፡ ወርእዮሙ አርዳኢሁ አንከሩ ወይቤሉ እፎ በጊዜሃ የብሰት በለስ። ማር ፲፩፥፳።
                    ******     
፳፡ ደቀ መዛሙርቱ አይተው በምትለመልምበት ጊዜ ፈጥና እንደምን ደረቀች ብለው አደነቁ።
                    ******          
  ይቆየን፡፡
**********
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
25/09/2011 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment