Wednesday, June 19, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 119

====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ ዘአቅደመ ነጊረ ሙስናሃ ለቤተ መቅደስ።
ምዕራፍ ፳፬።
                    ******     
፲፭፡ ወእምከመ ርኢክሙ ትእምርተ ርኵስ ዘምዝባሬ ዘተብህለ በዳንኤል ነቢይ ዘይቀውም ውስተ መካን ቅዱስ ወዘያነብብ ለይለቡ። ዳን ፱፥፳፯፡፡ ማር ፲፫፥፲፬፡፡ ሉቃ ፳፩፥፳።
                    ******     
፲፭፡ በቅዱስ ቦታ የሚቆም ማለት ለቤተ መቅደስ አንባቢነት የሚሾም ያስተውል ተብሎ የተነገረውን ቤተመቅደስ በሚፈርስበት ጊዜ የሚሆን የጥጦስን ጣዖቱን ያያችሁ እንደሆነ ያን ጊዜ ፍጻሜው ይመጣል ማለት የአይሁድ ጥፋት ይሆናል ትእምርተ በላዖር እንዲል።
አንድም ቤተ መቅደስ በሚፈርስበት ጊዜ የሚሆን የጥጦስን ጣዖት ያያችሁ እንደ ሆነ ያን ጊዜ የአይሁድ ጥፋት ይሆናል። ወዘተብህለ በዳንኤልም ለቤተ መቅደስ አንባቢነት የሚሾመው ለይለቡ ያለውን ያስተውል።
አንድም ወይእተ አሚረ ያን ጊዜ የአይሁድ ጥፋት ይሆናል።
ወእምከመ ርኢክሙ
ቤተ መቅደስ በሚፈርስበት ጊዜ የሚሆንን የጥጦስን ጣዖቱን ያያችሁ እንደሆነ ወዘተብህለ። አሜሃ ይትኀተም ራዕየ ነቢያት ወይትቀባዕ ቅዱሰ ቅዱሳን ወየዓርፍ ሙስና ዲበ መትከፈ ርኵሳን ተብሎ በዳንኤል የተነገረውን ይወቅ።
አንድም የተያያዘ ይእተ አሚረ ነው ሐሳዊ መሢሕን ሲናገር መጥቶ ምጽአትን ይእተ አሚረ አለ፡፡ ለቤተ መቅደስ አንባቢነት የሚሾም ለይለቡ ተብሎ በዳንኤል የተነገረለትን ይህ ዓለም በሚያልፍበት ጊዜ የሚሆን የሐሳዌ መሢሕን ጣዖቱን ጣዖትነቱን ያያችሁ እንደሆነ ያን ጊዜ ኅልፈተ ዓለም ይሆናል። አንድም ይህ ዓለም በሚያልፍባት ጊዜ የሚሆን የሐሳዊ መሢሕን ጣዖትነቱን ጣዖቱን ያያችሁ እንደሆነ ኅልፈተ ዓለም ይሆናል ወዘተብህለ በዳንኤልም ለይለቡ ተብሎ የተነገረለትን ያስተውል።
አንድም ወይእተ አሚረ ያን ጊዜ ኅልፈተ ዓለም ይሆናል። ወእምከመ ርኢክሙ ይህ ዓለም በሚያልፍበት ጊዜ የሚሆን የሐሳዊ መሢሕ ጣዖቱን ጣዖትነቱን ያያችሁ እንደሆነ ዘተብህለ፤ አሜሃ ይትኀተም ራዕየ ነቢያት ወይቅትቀባዕ ቅዱሰ ቅዱሳን ወየዓርፍ ሙስና ዲበ መትከፈ ርኵሳን ተብሎ በዳንኤል የተነገረውን ያስተውል። ወእምከመ ርኢክሙ ኃሣሮ ለሙስና ይላል በማርቆስ።
                    ******     
፲፮፡ አሜሃ እለ ውስተ ይሁዳ ይጐዩ ውስተ አድባር።
                    ******     
፲፮፡ ያን ጊዜ በይሁዳ ዕፃ ያሉ ወደ ተራራ ይሸሻሉ።
                    ******     
፲፯፡ ወዘሂ ሀሎ ውስተ ናህስ ኢይረድ ይንሣእ ዘውስተ ቤቱ።
                    ******     
፲፯፡ ከሰገነት የወጣም ከምድር ቤት ያለውን ያነሣ ዘንድ ወደ ምድር ቤት አይወርድም።
                    ******     
፲፰፡ ወዘሂ ገዳመ ሀሎ ኢይትመየጥ ድኅሬሁ ይንሣአ ልብሶ።
                    ******     
፲፰፡ በበረሀም ያለ ልብሱን ያነሣ ዘንድ ወደ ኋላው አይመለስም እንደ ወጣ ይቀራል ማለት ነው፡፡
                    ******     
፲፱፡ ወባሕቱ አሌ ሎን ለፅኑሳት ወለእለ የሐፅና በውእቱ መዋዕል
                    ******     
፲፱፡ ነገር ግን በዚያ ወራት ለፀነሱ ወልደው ለሚያሳድጉ ሴቶች ወዮላቸው።
(ሐተታ) የፀነሱት ከመንገድ ይወልዳሉ የወለዱት ወተት ፍትፍት አምጡ ብለው ያስቸግሯቸዋልና።
                    ******     
፳፡ ወጸልዩ ባሕቱ ከመ ኢይኩን ጉያክሙ በክረምት ወበሰንበት
ግብ ፩፥፲፬።
                    ******     
፳፡ ነገር ግን ስደታችሁ በክረምት በሰንበት እንዳይሆንባችሁ ለምኑ።
(ሐተታ) ክረምት ላዩ ውሀ ታቹ ውሀ ነው አያሸጋግርምና፡፡ ሰንበትም ዕለተ ፅርዓት ነው። መንገድ ቅሉ የሚያሳይ አይገኝምና።
አንድም ሦስት ወር ክረምት አርፋለሁ ብሎ ዘጠኝ ወር ምግቡን ሲሰበስብ ይባጃል በ፮ኛው ቀን አርፋለሁ ብሎ ፮ቱን ቀን በተገብሮ ይሰነብታል አርፋለሁ ባለባት ጊዜ ስደት የመጣ እንደሆነ ከቀቢጸ ተስፋ ይደርሳልና፡፡
አንድም አሜሃ እለ ውስተ ይሁዳ ብለህ መልስ፡፡ በሃይማኖት ያሉ ሰዎች ረድኤተ እግዚአብሔርን ጥግ ያደርጋሉ
ወዘሂ ውስተ ናሕስ
ልዕልና ነፍስ ያለውም ወደ ትሕትና አይወርድም፡፡
ይንሣእ ዘውስተ ቤቱ
ሥጋዊ ሥራ ይሠራ ዘንድ፤
ወዘሂ ሀሎ ገዳመ
የመነነም ወደ ዓለም አይመለስም
ይንሣእ ልብሶ
ዓለማዊ ሥራ ይሠራ ዘንድ፡
ወባሕቱ አሌ ሎን ለፅኑሳት
ነገር ግን በዚያ ወራት ኃጢአትን በሐልዮ ፀንሰው በነቢብ ወልደው በገቢር ለሚያሳድጉ ሰዎች ወዮላቸው መከራ ነፍስ አለባቸውና
አንድም ምዕመናንን በትምህርት ፀንሰው በትምህርት ወልደው በትምህርት የሚያሳድጉ መምሕራን  ወዮላቸው መከራ ሥጋ አለባቸውና፡፡
ወጸልዩ ባሕቱ
ነገር ግን በሃይማኖት ብቻ ሳላችሁ ምግባር ሳትሠሩ ሞት እንዳይታዘዝባችሁ ለምኑ። ክረምት ወርኃ ልምላሜ ነው ፍሬ የለውም ሰንበትም ዕለተ ጽርዓት ናትና በጽርዓት ሳላችሁ ሲል
ነው፣
                    ******     
፳፩፡ እስመ ይከውን ይእተ አሚረ ዓቢይ ሕማም ወምንዳቤ ዘኢኮነ ከማሁ እምፍጥረተ ዓለም እስከ ዮም፤
                    ******     
፳፩፡ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ተደርጎ የማያውቅ
ወኢይከውንሂ።
ከእንግዲህም ወዲህ የማይደረግ መከራ ጸዋትወ መከራ ያን ጊዜ ይደረጋልና።
                    ******     
፳፪፡ ወሶበ ኢሐፀራ እማንቱ መዋዕል እምኢድኅነ መኑሂ ዘሥጋ
                    ******     
፳፪፡ ቀኑስ ባያጥር ሥጋዊ ደማዊ ሰው ሁሉ ከመከራ ከክህደት ባልዳነም ነበር።
ወባሕቱ በእንተ ኅሩያኒሁ የሐፅራ እማንቱ መዋዕል
ነገር ግን ስለ ምዕመናን ቀኑ ያጥራል። ከመዓልቱ አራት ከሌሊቱ አራት ስምንት ሰዓት ይነሣለታል።
                    ******     
፳፫፡ አሜሃ እመቦ ዘይቤለክሙ ነዋ ዝየ ሀሎ ክርስቶስ። ማር ፲፫፥፳፩። ሉቃ ፲፯፥፳፫።
                    ******     
፳፫፡ ያን ጊዜ ክርስቶስ ከወዲህ አለ ከወዲያ የለም ከወዲህ ወዲያ ይሄዳል።
ወነዋ ከሀከ
ከወዲያ አለ ከወዲህ የለም ከወዲያ ወዲህ ይመጣል ቢሏችሁ።
ኢትእመኑ።
በእጅ አትበሉ።
                    ******     
፳፬፡ እስመ ይትነሥኡ ሐሳውያነ መሢሕ፣
                    ******     
፳፬፡ መሢሕ ክርስቶስን የሚያሳብሉ በመሢሕ በክርስቶስ የሚያብሉ ሐሰተኞች መምሕራን ይነሣሉና፤
ወሐሳውያነ ነቢያት፤
መምሕራንን የሚያሳብሉ በመምሕራን የሚያብሉ ሐሰተኞች መምሕራን ይነሣሉና
ወይገብሩ ተአምራተ ወመንክራተ ዓበይተ ለአስሕቶ
ሰውን ለማሳት በምትሐት ደጋግ ተአምራት ያደርጋሉ፤
አንድም ከመ ያስሕቱ ይላል ያስቱ ዘንድ
ሶበሰ ይትከሀሎሙ ለኅሩያንሂ እምአስሐትዎሙ፤
አይቻላቸውም እንጂ ቢቻላቸውስ ምዕመናንንም ባሳቷቸው ነበር፤
                    ******     
፳፭፡ ወናሁ አቅደምኩ ነጊሮተክሙ
                    ******     
፳፭፡ እነሆ አስቀድሞ ነገርኳችሁ፤
                    ******     
፳፮፡ እመቦ ዘይቤለክሙ ነዋ ገዳመ ሀሎ ኢትፃዑ፣
                    ******     
፳፮፡ ክርስቶስ በገዳም ኅብስት አበርክቶ ያበላል ቢሏችሁ አትውጡ ማለት በጅ አትበሉ።
ወነዋ ውስተ አብያት ኢትእመኑ።
እነሆ በምኵራብ ያስተምራል ቢሏችሁ በጅ አትበሉ።
                    ******     
፳፯፡ እስመ ከመ መብረቅ ዘይወፅእ እምጽባሕ ወያስተርኢ እስከ ዓረብ።
                    ******     
፳፯፡ ፀሐይ በወጣ ጊዜ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ እንዲታይ።
ከማሁኬ ይከውን ምጽአቱ ለወልደ እጓለ እመሕያው።
የወልደ እጓለ እመሕያው የክርስቶስ ምጽአቱ እንዲህ ነውና ማለት ሁሉ ያየዋልና።
                    ******      
፳፰፡ ሀበ ሀሎ ገደላ ህየ ይትጋብኡ አንስርት። ሉቃ ፲፯፥፴፭።
                    ******     
፳፰፡ በአይቴ ንትራከብ ብለውታል በሉቃስ ያቀናዋል ምግብ ካለበት አንስርት ይሰበሰባሉ አለ፡፡ እኔ ካለሁበት እናንተ ትሰበሰባላችሁ።
(ሐተታ) ገደላ አለው ራሱን ነፍስ የተለየችውን መለኮት የተወሐደውን ሥጋውን ነውና የምንቀበለው። አንስርት አላቸው ሐዋርያትን አንስርት ክንፍ አላቸው። ሐዋርያትም ክንፈ ጸጋ አላቸውና። አንስርት ተመስጦ እንዳላቸው ሐዋርያትም ተመስጦ አላቸውና።
                    ******     
በእንተ ካልአዊት ምጽአት ዘወልደ እጓለ እመሕያው
፳፱፡ ወእዎድኅረ ሕማሞን ለእማንቱ መዋዕል ፀሐይኒ ይፀልም። ኢሳ ፲፫፥፲። ሕዝ ፴፪፥፯። ኢዮ ፪፥፲፫-፲፭፡፡ ማር ፲፫፥፳፬። ሉቃ ፳፩፥፳፭። ራዕ ፩፥፯።
                    ******     
፳፱፡ በሐሳዊ መሢሕ የሚደረገውን መናገር ነው፤ ይህ ሁሉ መከራ ከተደረገ በኋላ ፀሐይ ያልፋል።
ወወርኅኒ ኢይሁብ ብርሃኖ።
ጨረቃም ብርሃኑን አይሰጥም ማለት ያልፋል።
ወከዋክብትኒ ይወድቁ እምሰማይ።
ከዋክብትም ያልፋሉ
ወያንቀለቅል ኃይለ ሰማያት።
አድማስ ጽንዑን ይለቃል።
                    ******     
፴፡ ወይእተ አሚረ ያስተርኢ ትእምርቱ ለወልደ እጓለ እመ ሕያው ውስተ ሰማይ።
                    ******     
፴፡ ያን ጊዜ የወልደ እጓለ እመሕያው ክርስቶስ ምልክቱ በሰማይ ይታያል ዓሠረ ርግዘቱን ዓሠረ ቅንዋቱን እሥራቱን ሳያጠፋ ይመጣልና።
(ታሪክ) ላባ ጳኵሚስ እንደታየው፤ ሲሰግድ ወዙ ወርዶ መሬቱን ጭቃ አደረገው ወዲያው ጌታ ተገለጸለት አንተን አገኝ ብዬ እንዲህ እደክማለሁ አለው አኔም እንጂ ላንተ ብዬ እንዲህ ሁኜ ተሰቅዬ አለሁ ብሎ በዕለተ ዓርብ እንደ ተሰቀለ ሁኖ ጐኑን እንደ ተወጋ ደሙ እንደፈሰሰ ሆኖ ታይቶታል።
አንድም ወእምድኅረ ሕማሞን ብለህ መልስ። በጥጦስ የሚደረገው መከራ ነው። ይህ ሁሉ መከራ ካለፈ በኋላ ፀሐይ ይጨልማል።
ወወርህኒ ኢይሁብ ብርሃኖ። ወከዋክብትኒ ይወድቁ እምሰማይ።
ጨረቃ ይጨልማል ከዋክብትም ይወድቃሉ፡፡ በዕለተ ዓርብ በሠሩት ኃጢአት እንደ ተፈረደባቸው ለማጠየቅ በዕለተ ዓርብ የተደረገው ሁሉ ተደርጓል።
ወይእተ አሚረ
ያን ጊዜ የወልደ እጓለ እመሕያው የክርስቶስ ምልክቱ በሰማይ ይታያል።
(ታሪክ) በሮም አንፃርና በኢየሩሳሌም አንፃር ያሉ ከዋክብት ሰልፍ ሰርተው ሲዋጉ በሮም አንፃር ያሉት በኢየሩሳሌም አንፃር ያሉትን ድል ሲያደርጓቸው ታይተዋል። ሮማውያን አይሁድን ድል ለማድረጋቸው ምሳሌ ነው።
አሜሃ ይበክዩ ኵሎሙ አሕዛበ ምድር ሶበ ይሬእይዎ ለወልደ እጓለ እመሕያው እንዘ ይመጽእ በደመና ሰማይ።
በሰማይ ደመና ማለት በባሕርይ ክብሩ ሲመጣ ባዩት ጊዜ ያን ጊዜ አሕዛብ ሁሉ ያዝናሉ።
(ሐተታ) የዕርገት የደብረ ታቦር የምጽአት ደመና የባሕርይ ክብር ነው።
አንድም በሥጋ ማርያም መጥቶ ባዩት ጊዜ ሰማይ ዳግሚት እንዲል
አንድም በክበበ ትስብእት መጥቶ ባዩት ጊዜ ያዝናሉ።
ምስለ ኃይል።
ከኃይል ጋራ ማለት ዓለምን ከማሳለፍ ጋራ።
ወስብሐት ብዙኅ።
ቅዱስ እግዚአብሔር ዘያነቅሖሙ ለምውታታን ተብሎ ከመመስገን ጋራ ሲመጣ ባዩት ጊዜ።
                    ******     
፴፩፡ ወይፌንዎሙ ለመላእክቲሁ ምስለ ቃለ ቀርን። ፩፡ቆሮ ፲፭፥፳፪።
፴፩፡ አዋጅ ከመንገር ጋራ መላእክትን ያዛቸዋል።
                    ******     
  ይቆየን፡፡
**********
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
11/10/2011 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment