====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ ምሳሌ ንጉሥ ዘገብረ ከብካበ ለወልዱ ።
ምዕራፍ ፳፪።
******
፩፡ ወአውሥአ እግዚእ ኢየሱስ ዳግመ ወነገረ በምሳሌ።
******
፩፡ ጌታ ሁለተኛ በምሳሌ ነገራቸው
******
፪፡ እንዘ ይብል ትመስል መንግሥተ ሰማያት ብእሴ ንጉሠ ዘገብረ ከብከበ ለወልዱ፡፡ ሉቃ ፲፬፥፪፡፡ ራዕ ፲፱፥፱፡፡
******
፪፡ መንግሥተ ሰማያት ሕገ ወንጌል ሕገ ወንጌል ተስፋ ተስፋ ኢየሱስ ክርስቶስ ለልጁ ሰርግ ያዘጋጀ ንጉሥን ትመስላለች።
******
፫፡ ወፈነወ አግብርቲሁ ይጸውእዎሙ ለእለ ተዓሠሩ ውስተ ከብካብ
******
፫፡ የታደሙትን ወደ ሰርግ ጥሯቸው ብሎ ብላቴኖቹን የላከን
ወዓበዩ መጺአ።
አንመጣም ያሉትን።
******
፬፡ ወዳግመ ፈነወ ካልዓነ አግብርተ።
******
፬፡ ሁለተኛ ሌሎችን ላከ።
እንዘ ይብል በልዎሙ ለእለ ዓሠርናሆሙ።
ያደምናቸውን ንእህ በሏቸው ብሎ
ናሁ ምሳህየ አስተዳሎኩ
እነሆ ሠርግ አዘጋጅቻለሁ።
ወጠባሕኩ መጋዝዕትየ ወአስዋርየ።
ሜል ገች አርጃለሁ ።
ወኵሉ ድልው።
ሁሉ ተዘጋጅቷል።
ንዑ ውስተ ከብካብየ።
ወደ ሰርግ ኑ ብሎ ላከ።
******
፭፡ ወእሙንቱሰ ተሐየዩ ወኃለፉ
******
፭፡ እሳቸው ግን ቸል ብለው ሄዱ
ቦ ዘሖረ ውስተ ገራህቱ፡፡
ወደ እርሻው የሄደ አለ።
ወቦ ዘሖረ ውስተ ንግዱ።
ወደ ንግዱ የሄደ አለ።
ወቦ ዘሖረ ውስተ ዓፀደ ወይኑ
ወደ ወይን ጥበቃው የሄደ አለ
******
፮፡ ወእለሰ ተርፉ አኃዙ አግብርቲሁ ወቀተልዎሙ
******
፮፡ የቀሩት ግን ብላቴኖቹን ይዘው ገደሏቸው። ወኪያሁኒ አግዚኦሙ ጸአሉ።
እሱንም ነቀፉት።
******
፯፡ ወተምዓ ንጉሥ ወፈነወ ሐራሁ ይቅትልዎ ለእልክቱ ቀተልት።
******
፯፡ ንጉሥ ተቈጥቶ ግደሏቸው ብሎ ጭፍራ ላከ።
ወቀተልዎሙ።
ገደሏቸው።
ወሀገሮሙኒ አውዓዩ በእሳት
ሀገራቸውን አቃጠሉ።
******
፰፡ ወእምዝ ይቤሎሙ ለአግብርቲሁ ከብካብየሰ ድልው ውእቱ
******
፰፡ ከዚህ በኋላ ለብላቴኖቹ ሠርጉስ ተዘጋጅቷል።
ወባሕቱ ኢደለዎሙ ለእለ ዓሠርናሆሙ።
ነገር ግን ላደምናቸው ኣላደላቸውም አላቸው።
******
፱፡ ሑሩኬ እንከ ውስተ መራህብት ወአናቅጽ ወኵሎ ዘረከብክሙ ጸውዑ ሊተ ውስተ ከብካብ።
******
፱፡ እኒያ አይሆንም ካሉ ወደ አደባባይ ወጥታችሁ ክፉውንም በጎውንም ጠርታችሁ ይዛችሁ ኑ አላችው።
******
፲፡ ወወፂኦሙ እሙንቱ አግብርት ውስተ ፍናው አስተጋብኡ
ኵሎ ዘረከቡ እኩያነ ወኄራነ
ወደ አደባባይ ወጥተው ክፉውንም በጎውንም ያገኙትን ጠርተው ይዘው መጡ።
ወመልዓ ቤተ በዓል እምእለ ይረፍቁ።
ከተቀመጡት የተነሣ የሠርግ ቤት መላ።
******
፲፩፡ ወበዊዖ ንጉሥ ይርአዮሙ ለእለ ይረፍቁ ረከበ በህየ ዘኢለብሰ ልብሰ መርዓ።
******
፲፩፡ ንጉሥ ከሠርግ ቤት ገብተው የተቀመጡትን ሊያያቸው በገባ ጊዜ የሠርግ ልብስ ያለበሰ አንድ ሰው አገኘ።
******
፲፪፡ ወይቤሎ አርክየ ለምንት ቦእከ ዝየ ዘኢለበስከ ልብሰ መርዓ።
******
፲፪፡ ወዳጄ የሠርግ ልብስ ያለበስህ ከሠርግ ቤት ለምን ገባህ አለው።
ወተፈጽመ ውእቱ ብእሲ።
ያ ሰው ምላሽ አጣ።
(ሐተታ) ባጣ ቢቸግረኝ አይለውም ቢሉ ያነኑ ከውሀ ባደረስከው ይለዋልና።
******
፲፫፡ ወእምዝ አዘዞሙ ንጉሥ ለአግብርቲሁ ይዕሥርዎ እዴሁ ወእገሪሁ ወያውፅእዎ ውስተ ጸናፌ ጽልመት። ማቴ ፰፥፲፪፡፡ ፲፥፫፡፡ ፵፪፥፳፭-፴።
******
፲፫፡ ከዚህ በኋላ እጁን እግሩን አሥራችሁ ወደጽኑ ጨለማ አውጡት።
ኀበ ኵሎ ብካይ ወሐቅየ ስነን
ልቅሶ ጥርስ ቁርጥማት ወዳለበት ቦታ ብሎ ብላቴኖቹን አዘዛቸው።
******
፲፬፡ እስመ ብዙኃን እሙንቱ ጽውዓን።
******
፲፬፡ የተጠሩ የቀሩ ብዙ ናቸውና ለምንት ቦእከ ዝየ።
ይቆየን፡፡
**********
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
28/09/2011 ዓ.ም
Wednesday, June 5, 2019
ወንጌል ቅዱስ ክፍል 112
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment