Monday, June 3, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 111



    ====================
 የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
ዘከመ ቦአ እግዚእ ኢየሱስ ኢየሩሳሌም።
ምዕራፍ ፳፩።
                    ******    
በእንተ እኵያን ገባዕት።
፴፫፡ ወይቤሎሙ ካልዕተ ምሳሌ ስምዑ። ኢሳ ፭፥፩፡፡ ኤር ፪፥፳፩፡፡ ማር ፲፪፥፩፡፡ ሉቃ ፳፥፱።
                    ******     
፴፫፡ ፪ተኛ ምሳሌ ስሙ፡፡
ብእሲ በዓለ ቤት ተከለ ዓፀደ ወይን።
ባለቤት ወይን ተከለ። ዓፀደ ወይን አፍለስከ እምግብፅ እንዲል። ዓፀደ ወይን ሐረገ ወይን ጕንደ ወይን ምንዳደ ወይን ይላል አብነት።
ወገብረ ሎቱ ፀቈነ።
ቅጽር  ቀጠረለት።
ወአክረየ ሎቱ ምክያደ።
የዘቢብ ማስጫ ውድማ አበጀለት።
ወሐነፀ ማኅፈደ።
ለጠባቂ ግንብ ሥራ፡፡
ወሤመ ዓቀብተ።
ጠባቂ ሾመ።
ወወሀቦሙ ለዓቀብት ወነገደ።
ጠባቂ ሹሞ ሄደ።
                    ******     
፴፪፡ ወአመ በጽሐ ጊዜ ፍሬሁ ፈነወ አግብርቲሁ ኀበ ዓቀብተ ወይን
የሚያፈራበት ጊዜ ቢደርስ ብላቴኖቹን ከጠባቆች ላከ።
ከመ ያምጽኡ ሎቱ እምፍሬ ወይኑ።
ከወይኑ ፍሬ ያመጡለት ዘንድ አምጡ ብሎ።
                    ******     
፴፭፡ ወአኃዝዎሙ ዓቀብት ለአግብርቲሁ።
                    ******     
፴፭፡ ጠባቆች ብላቴኖችን ይዘው።
ዘቀተሉ።
የገደሉት አለ፣
ወቦ ዘወገሩ።
በደንጊያ የመቱት አለ።
ወቦ ዘቀሠፉ።
የገረፉት አለ።
                    ******     
፴፮፡ ወእምዝ ፈነወ ካልዓነ አግብርተ ዘይበዝኁ እምቀደምት።
                    ******     
፴፮፡ ከዚህ በኋላ ከቀደሙት የሚበዙ ሌሎች ብላቴኖች ላከ።
ወኪያሆሙኒ ከማሁ ረሰይዎሙ
እሳቸውንም እንደዘ. አደረጓቸው የገደሉት በደንጊያ የመቱት የገረፉት አለ።
                    ******     
፴፯፡ ወድኅረ ፈነወ ኀቤሆሙ ወልዶ እንዘ ይብል የኀፍርዎ ለወልድየሰ።
                    ******     
፴፯፡ ከዚህ በኋላ ልጄንስ ቢሆን ያከብሩታል ባይሆንም ያፍሩታል ብሎ ልጁን ላከ።
                    ******     
፴፰፡ ወሶበ ርእይዎ ዓቀብት ለወልዱ ወይቤሉ በበይናቲሆሙ ነዋ ዝንቱ ውእቱ ወራሲሁ ንዑ ንቅትሎ ወንርከብ ርስቶ። ማቴ ፳፮፥፬፡፡ ፳፯፥፩።
                    ******     
፴፰፡ ጠባቆች ባዩት ጊዜ ርስቱ ይገባኛል የሚል እነሆ ይህ ነው እሱን ገድለን ርስቱን እጅ እናድርግ አሉ፡፡
                    ******     
፴፱፡ ወነሥእዎ ወአውጽእዎ አፍአ እምዓፀደ ወይን ወቀተልዎ። ዮሐ ፲፩፥፶፫።
                    ******     
 ፴፱፡ ይዘው ከወይኑ ቦታ አውጥተው ገደሉት የሰው ደም ተክል ያደርቃል ይባላልና።
                    ******     
፵፡ ወሶበ መጽአ በዓለ ዓፀደ ወይን ምንተ ይሬስዮሙ ለእሉ ዓቀብት፡፡
                    ******     
፵፡ የወይኑ ባለቤት በመጣ ጊዜ ምን ያደርጋቸዋል እነዚህን ጠባቆች አላቸው፣
                    ******     
፵፩፡ ወይቤልዎ በዕኪት ለእኩያን ያጠፍዖሙ
                    ******     
፵፩፡ እንደመሰለባቸው ያወቁት እንዲህ የሚያደርግ የለም ብለዋል፤ ያላወቁት ግን ይሞት በቃ ፈርዶ ይገላቸዋል አሉ፡፡
ወወይኖሂ ይሁብ ለካልዓን ዓቀብት፤
ወይኑንም ለሌሎች ሰዎች ያስጠብቃል
ለእለ ይሁብዎ ፍሬሁ በበጊዜሁ
ፍሬውን በየጊዜው ለሚያቀርጡለት።
ወበበአግዋሊሁ።
በየዘለላው። ካንዱ ዘለላ ቀይ ጥቁር ነጭ ያፈራልና።
አንድም ብእሲ በዓለ ቤት ብለህ መልስ። አምጸኤ ዓለማት ፈጣሬ ዓለማት አብ ሕገ ኦሪትን ሠራ፤ ወገብረ ሎቱ ፀቈነ። በኦሪት ረድኤት እንዲገኝ ማድረጉን መናገር ምሥዋዓ ብርትን፣ ወሐነፀ፤ ቤተ መቅደስን ሠራ
አንድም ወአክረየ፡ ልቡናን። ወሐነፀ ማኅፈደ ተልዕሎተ ትንቢትን፡፡
አንድም አምጸኤ ዓለማት ፈጣሬ ዓለማት አብ በልጁ ህልው ሁኖ ወንጌልን ሠራ ወገብረ ሎቱ በወንጌል ልጅነት እንዲገኝ አደረገ። ወአክረየ፡ ንዋየ ቅድሳትን። ወሐነፀ፡ ቤተ ክርስቲያንን ሠራ።
አንድም ወአክረየ ስፍሐ አእምሮን፣ ወሐነፀ ተልዕሎተ ሃይማኖትን ሠራ
ወወሀቦሙ  ለዓቀብት። ጠብቁ ብሎ ሕግ መሥራቱን መናገር ነው ወአመ በጽሐ። ሃይማኖት የሚይዙበት ምግባር የሚሠሩበት ጊዜ ቢደርስ ፈነወ አግብርቲሁ ሃይማኖት ምግባር ያሠሩለት ዘንድ ዓበይተ ነቢያትን ላከ ወነሥእዎሙ ሕግ መጠበቅ የሚገባቸው ሕዝቡ ዓበይተ ነቢያትን ደቂቀ ነቢያትን ይዘው ዘቀተሉ የገደሉት አለ እነኢሳይያስን ወቦ ዘወገሩ እነኤርምያስን። ወቦ ዘቀሠፉ አለ አሞፅን ሠያጤ በለስ ብለው ገርፈውታል፡፡ ወእምዝ ፈነወ ከዚህ በኋላ ከዓበይተ ነቢያት የሚበዙ ደቂቀ ነቢያትን አስተምሩ ብሎ ላከ። ወኪያሆሙኒ ከማሁ። እሳቸውንም እንደነዚያ አደረጓቸው። ወእምዝ ፈነወ ከእነዚህ ሁሉ በኋላ ልጁን በሥጋ ላከ። ልጄንስ ቢሆን ያከብሩታል ባይሆን ያፍሩታል ብሎ፥ ወሶበ ርእይዎ። ሕግ መጠበቅ የሚገባቸው ሕዝቡ ሰው ሁኖ ባዩት ጊዜ መምህርነት ይገባኛል የሚል እነሆ መጣ ንዑ ንቅትሎ እሱን ገድለን መምሕርነቱን ገንዘብ እናድርግ አሉ። ወአውፅእዎ ከከተማው አፍአ አውጥተው በቀራንዮ ሰቅለው ገደሉት፡፡
አንድም ሕግ መጠበቅ ከሚገባው ከልቡናቸው አውጥተው ጠልተው ተመቅኝተው ሰቅለው ገደሉት። ወሶበ መጽአ ምንተ ይሬስየክሙ ሲል ነው። የሕጉ ባለቤት ጌታ በመጣ ጊዜ ምን ያደርጋችኋል አላቸው፤ ወይቤልዎ በእኩይ ለእኩያን ይቀትሎሙ፡ ፈርዶ ያጠፋቸዋል አሉት። ወወይኖሂ ይሁብ፤ ሕጉንም ለሌሎች ያስጠብቃል። ለእለ ይሁብዎ። በዓሉን በየጊዜው ለሚያከብሩ መጸለት ሰዊት ፋሲካ ነው። ወበበአግዋሊሁ፤ በየአገባቡ።
                    ******     
፵፪፡ ወይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ አልቦሁ አመ አንበብክሙ ውስተ መጻሕፍት ዕብን እንተ መነንዋ ነደቅት ይእቲ ኮነት ውስተ ርአሰ ማዕዘንት። መዝ ፻፲፯፥፳፩፡፡ ግብ ፬፥፲፩፡፡ ሮሜ ፱፥፴፫፡፡ ፩፡ጴጥሮ ፪፥፯።
                    ******     
፵፪፡ አናጢዎች የናቋት ደንጊያ የማዕዘን መሰብሰቢያ ሆነች፤
እምኀበ እግዚአብሔር ኮነት ዛቲ።
ይህች በእግዚአብሔር ፈቃድ ሆነች።
ወነካር ይእቲ ለአዕይንቲነ
ለንይነ ልቡናችን ድንቅ ናት ብሎ መጽሐፍ የተናገረውን የተመለከታችሁበት ጊዜ የለምን አላቸው፡፡
አንድም እንተ መነንዋ ብለህ መልስ አሕዛብ የናቋት ኦሪት በ፬ ማዕዘን መከበሪያ መጽደቂያ ሆነች። እም ኀበ አግዚአብሔር። መናቋም መከበሪያ መጽደቂያ መሆንዋም በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። ነቋም እግዚአብሔር አብ ነው። ወነካር ለዓይነ ልቡናችን ድንቅ ናት።
አንድም ዕብን እንተ መነንዋ። አሕዛብ የናቁት ዘሩባቤል ንጉሠ ነገሥት ሆነ። መናቁም ንጉሠ ነገሥት መሆኑም በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ወመንክር በል፡፡ ለዓይነ ልቡናችን ድንቅ ነው ወያዕቆብሰ ያስተኤሪ ንጉሠ እንዲል ሁለቱ ከአሥሩ ነገድ ከተለዩ በኋላ አንድ አድርጎ ነግሷልና፡፡
አንድም ዕብን እንተ መነንዋ ሐና ቀያፋ የካዱት ክርስቶስ ንጉሠ ነገሥት በኵረ ምዕመናን ሆነ
(ሐተታ) ነደቅት አላቸው የሰውን ልቡና በትምህርት እናንፃለን ይላሉና እምኀበ እግዚአብሔር ኮነት። መናቁም በኵረ ምዕመናን ንጉሠ ነገሥት መሆኑም በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ነቁም እግዚአብሔር ነው፡፡
ወመንክር
ለዓይነ ልቡናችን ድንቅ ነው።
አንድም ዕብን እንተ መነንዋ፣ ጸሐፍት ፈሪሳውያን የናቋት ወንጌል በ፬ ማዕዘን መክበሪያ መጽደቂያ ሆነች፤
እም ኀበ እግዚአብሔር።
መናቋም መክበሪያ መጽደቂያ መሆንዋም በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፡፡ ነቋም እግዚአብሔር ወልድ ነው።
ወነካር።
ለዓይነ ልቡናችንም ድንቅ ናት።
                    ******     
፵፫፡ ወበእንተዝ እብለክሙ ከመ ይነሥእዋ እምኔክሙ ለመንግሥተ እግዚአብሔር ወይሁብዋ ለሕዝብ ዘይገብሩ ፍሬሃ።
                    ******     
፵፫፡ ስለዚህ ነገር ማለት አንቀበልም ስላላችሁ ወንጌልን ከእናንተ ነሥተው ሥርዓቷን ለሚሠሩ ለሌሎች ሰዎች ያስጠብቋታል ብዬ እነግራችኋለሁ። እንዲህም ባለ ጊዜ ክህነትንም መንግሥትንም ከእሳቸው እንዳለፈባቸው ያጠይቃል።
                    ******     
፵፬፡ ዘሰ ወድቀ ዲበ ይእቲ ዕብን ይትቀጠቀጥ።
                    ******     
፵፬፡ ከደንጊያ ላይ የወደቀ ይሰበራል
ወለዘሂ ወድቀት ዲቤሁ ተሐርፆ
የወደቀችበትም ይሰበራል።
(ሐተታ) በላይም ሆነ በታችም ሆነ ደንጊያ ሰባሪ ሰው ተሰባሪ ነው።
አንድም ዘሰ ወድቀ በዕለተ ዓርብ በጌታ በጠላትነት የተነሣበት አይሁዳዊ።
ይትቀጠቀጥ፤
በተአምራት ይጠፋል
ወዘሂ ወድቀት።
ጌታ በተአምራት የተነሣበት አይሁዳዊ።
የሐርፆ።
በአርባ ዘመን በጥጦስ ይጠፋል።
አንድም ዘሰ ወድቀ ዲበ ዕብን፤
በዕለተ ዓርብ በጌታ በጸላትነት የተነሣበት አይሁዳዊ በ፵ ዘመን በጥጦስ ይጠፋል።
ወለዘሂ ወድቀት ዲቤሁ።
ጌታ በአርባ ዘመን በጥጦስ በጠላትነት የተነሣበት አይሁዳዊ ተሐርፆ በምጽአት ይጠፋል፡፡
አንድም በመባሕተ መኑ ትገብር ዘንተ በማለት በጌታ በጠላትነት የተነሣ አይሁዳዊ ይትቀጠቀጥ። ጥምቀቱ ለዮሐንስ እምኀበ አይቴ ባለው ይረታል። ክርስቶስ ወልደ መኑ በማለት ጌታ በጠላትነት የተነሣበት አይሁዳዊ ዘለሊሁ ዳዊት እግዚእየ ይቤሉ በእፎ ይከውኖ ወልዶ ባለው ይረታል።
                    ******     
፵፭፡ ወሰሚዖሙ ሊቃነ ካህናት ወፈሪሳውያን ምሳሌያቲሁ አንከሩ ወአእመሩ ከመ በእንቲአሆሙ ይብል።
                    ******     
፵፭፡ ፈሪሳውያን ሊቃነ ካሀናት ምሳሌውን ሰምተው አደነቁ በእሳቸው እንደመሰለባቸው አወቁ፡፡
                    ******     
፵፮፡ ወፈቀዱ የአኃዝዎ።
                    ******     
፵፮፡ ሊይዙት ወደዱ።
ወፈርሁ ሕዝበ።
ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩ።
እስመ ከመ ነቢይ ይሬእይዎ
ሕዝቡ ጌታን እንደ አባት ያከብሩታል እንደ መምህር ያፍሩታልና
                    ******     
በእንተ ምሳሌ ንጉሥ ዘገብረ ከብካበ ለወልዱ
ምዕራፍ ፳፪።
፩፡ ወአውሥአ እግዚእ ኢየሱስ ዳግመ ወነገረ በምሳሌ።
፩፡ ጌታ ሁለተኛ በምሳሌ ነገራቸው
                    ******       
  ይቆየን፡፡
**********
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
27/09/2011 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment