Wednesday, June 12, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 117

====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ መደልዋን ፈረሳውያን
ምዕራፍ ፳፫።
                    ******     
፴፫፡ ኦ ትውልደ አራዊተ ምድር እፎ ትክሉ አምሥጦ እምኵነኔ ገሃነም። ማቴ ፫፥፯።
                    ******     
፴፫፡ እናንት የምድር እባብ ልጆች በገሃነም ከሚመጣው ፍዳ መዳን እንደምን ይቻላችኋል።
                    ******  
   ፴፬፡ ወበእንተዝ አነ እፌኑ ኀቤክሙ
                    ******     
፴፬፡ ሶበሰ ሀሎነ የምትሉ ስለሆነ ስለዚህ ነገር ወደእናንተ እልካለሁ
ነቢያተ
፸ አርድዕትን
ወሐዋርያተ
ሐዋርያትን
ወጠበብተ።
ሹማምንትን፤
ወጸሐፍተ
መምህራንን መተርጕማንን እልካለሁ።
ቦ እምኔሆሙ ዘትቀትሉ፤
ከሳቸው ወገን የምትገድሉት አለ
ወቦ እምኔሆሙ ዘትሰቅሉ።
የምትሰቅሉት አለ።
ወቦ እምኔሆሙ ዘትቀሥፉ በምኵራባቲክሙ።
በምኵራባችሁ  አግብታችሁ የምትገርፉት አለ።
ወትሰድድዎሙ እምሀገር ውስተ ሀገር።
ከአንዳ አገር ወደአንዱ አገር አስወጥታችሁ የምትሰዱት አለ።
                    ******     
፴፭፡ ከመ ይብጻሕ ላዕሌክሙ ደመ ኵሎሙ ጻድቃን እምደመ አቤል ጻድቅ እስከ ደመ ዘካርያስ ወልደ በራክዩ ዘቀተልክምዎ በማዕከለ ቤተ መቅደስ ወምሥዋዕ። ዘፍ ፬፥፰፡፡ ዕብ ፩፥፬፡፡ ፪፡ሕፁፃ ፳፬፥፳፪፡፡
                    ******     
፴፭፡ ከአቤል ደም ጀምሮ በዕቃ ቤትና በቤተ መቅደስ መካከል በገደላችሁት እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በዓለም የፈሰሰ የጻድቃን ደም ፍዳ ሊደረግባችሁ
(ሐተታ) ጠርዙንና ጠርዙን ይዞ ተናገረ። ለሰማዕታተ ብሊት ጥንታቸው አቤል ፍጻሜያቸው ዘካርያስ ነውና።
አንድም ግፍ ለግፍ ሲያነጻጽር አቤል የሞተ በግፍ ነው ዘካርያስም የሞተ በግፍ ነውና።
አንድም ደመ ስክየትንና ደመ ስክየትን ሲያነጻጽር መልአኩ ለሄኖክ ማኅደረ ኃጥአንን እያዞረ ሲያሳየው አንዲት ነፍስ እየተንጸረጸረች ስታካስስ ስታሳጣ አይቶ ዛ መንፈስ ዘመኑ ብሎ ጠየቀው ዘአቤል ዘቀተሎ እኁሁ። ይሰኪ ኪያሁ እስከ አመ ይትኃጐሉ ደቂቁ እምገጸ ምድር በማየ አይኅ ብሎታል።
የዘካርያስም ደም ፸ ዘመን ሲፈላ ኑሯል። ጥጦስ አይቶ ምንድነው ብሎ ጠየቀ። ደግ ሰው ነበረ በግፍ አስገድለውት ነው አሉት ከገዳዮቹ ወገን ሰባት ሰዎች አስመጥቶ ቢያሳርድ መፍላቱን ትቷል፤ ከዕቃ ቤትና ከቤተ መቅደስ መካከል ያስገደላችሁት አለ፤ የምትሻው ሕፃን ከዘካርያስ ቤት አለ ሲፀነስ የአባቱን  አንደበት የዘጋ ሲወለድ የፈታ ብለው ነገሩት። አስጸርቶ እንዲህ ያለ ብላቴና አለ ብሎ ጠየቀው። አዎን ምነው ጠየቅኸኝ አለው ይህን ልትነግረኝ ነው ሂድ አለው። ይህ ዓላዊ አለ ነገር አልጠየቀኝም ልጄን ሊያስገድለው ነው ሀብት ሳላሳድርበት ብሎ ከቤተ መቅደስ አግብቶ ሲጸልይለት ግደሉ ብሎ ጭፍራ ላከ፡፡ ከቤት ቢሄዱ አጡት ኋላ መልአኩ ለኤልሳቤጥ ይህ ዓላዊ ልጅሽን ሊያስገድልብሽ ነው ገዳም ይዘሽ ሂጂ አላት ገዳም ይዛ ሂዳለች፤ ከቤተ መቅደስ ቢሄዱ እሱን አገኙት ከዚያ ገድለውታል።
አንድም የምትሻት ሴት ከልጅዋ ጋራ ከዘካርያስ ቤት ትገባለች ትወጣለች ብለው ነገሩት አስጸርቶ ወስዶ እኔ የምሻት ሴት ከአንተ ቤት አለችን አለው አዎን አለው። ምነው ያልነገርከኝ አለው እመቤቴን የሷን ሞት ለኔ ያድርገው አለው። እንዳየህ ውጋው አለው ወጉት ደም ተኩሶት ሂዶ ከቤተ መቅደስና ከዕቃ ቤት መካከል ወድቋል።
                    ******     
፴፮፡ አማን እብለክሙ ከመ ዝንቱ ኵሉ ይበጽሓ ለዛቲ ትውልድ
                    ******     
፴፮፡ በቤተ አይሁድ ይህ ሁሉ እንዲደረግባት በእውነት እነግራችኋለሁ።
                    ******     
ዘከመ ኄሳ ለኢየሩሳሌም።
ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም እንተ ትቀትሎሙ ለነቢያት ወትዌግሮሙ ለሐዋርያት እለ ተፈነዉ ኀቤሃ። ሉቃ ፲፫፥፴፬።
                    ******     
፴፯፡ በመምህርነት ወዳንች የተላኩ ነቢያትን ያጠፋሻቸው ሐዋርያትን የተጣላሻቸው ቤተ አይሁድ።
ሚመጠነ ፈቀድኩ አስተጋብኦሙ ለውሉድኪ ከመ እንተ ታስተጋብዕ ዶርሆ ዕጐሊሃ ታሕተ ክነፊሃ።
ዶሮ ልጆቿን በክንፏ እንድትሰበስብ ማለት ነቢያት ሕዝቡን አንድ ያደርጓቸው እንደ ነበረ ልጆችሽን በትምህርት አንድ አደርጋቸው ዘንድ ምን ያህል ወደድኩ።
(ሐተታ) ዶርሖ አላቸው ነቢያትን፤ ዶሮ ወተት የላትም ልጆቹዋን የምታሳድግ ሰው በፃረበት ነው ነቢያትም በፃዕር የተገኘውን ነውና ሲያስተምሩ የነበረ መልአክ የነገራቸውን መንፈስ ቅዱስ የገለጸላቸውን።
ወአበይክሙ
አናምን አላችሁ
                    ******     
፴፰፡ ናሁ ይትኃደግ ለክሙ ቤትክሙ በድወ።
                    ******     
፴፰፡ እነሆ ቤተ መቅደስ ትፈርሳለች
                    ******     
፴፱፡ አማን እብለክሙ ኢትሬእዩኒ እምይእዜ እስከ ሶበ ትብሉ ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር።
                    ******     
፴፱፡ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እስክትሉ ድረስ ከእንግዴህ ወዴህ አታዩኝም ብዬ በእውነት እነግራችኋለሁ። ሆሣዕና አላለፈም ቢሉ የተመቸ። አልፏል ቢሉ ምጽአትን ያያል።
                    ******     
በእንተ ዘአቅደመ ነጊረ ሙስናሃ ለቤተ መቅደስ።
ምዕራፍ ፳፬።
፩፡  ወወፂኦ እግዚእ ኢየሱስ እምቤተ መቅደስ ሖረ፡፡
፩፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ሄደ
                    ******       
  ይቆየን፡፡
**********
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
05/10/2011 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment