Wednesday, June 19, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 121

====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ ዘአቅደመ ነጊረ ሙስናሃ ለቤተ መቅደስ።
ምዕራፍ ፳፬።
                    ******     
፵፡ አሜሃ ፪ቱ ይሄልው ውስተ ፩ዱ ገራህት።
                    ******     
፵፡ ያንጊዜ ሁለት ሰዎች በአንድ እርሻ ይኖራሉ።
                    ****** 
፵፩፡ ፩ደ ይነሥኡ።
                    ******     
፵፩፡ አንዱን በሞት ይወስዳሉ።
ወካልዖ የኃድጉ።
አንዱን በሕይወት ይተዋሉ።
ወ፪ቲ የሐርፃ በ፩ዱ ማኅረፅ
ሁለት ሴቶች ባንድ ወፍጮይፈጫሉ።
(ሐተታ) ተራ አንድም ሽርሞ። አንድም መቀበያውን አንድ አድርገው።
አሐተ ይነሥኡ።
አንዲቱን በሞት ይወስዳሉ።
ወካልዕታ የኃድጉ።
አንዲቱን ይተዋሉ።
፪ቱ ይሰክቡ ውስተ ፩ዱ አራት
ባልና ሚስት በአንድ አልጋ ይተኛሉ።
፩ደ ይነሥኡ
አንዳቸውን በሞት ይወስዳሉ
ወካልዖ የኀድጉ።
አንዳቸውን በሕይወት ይተዋሉ
አንድም ፪ቱ ይሄልዉ ብለህ መልስ ለያርኅብ እግዚአብሔር
ምድሮ ለያፌት እንዲል። በያፌት ዕፃ ፪ት ሰዎች ይኖራሉ፡፡ ምግባር ሃይማኖት የያዘውን ይነሥኡ ወደ ገነት። ምግባር ሃይማኖት ያልያዘውን የኀድጉ በገሃነም። ወ፪ቱ ይሰክቡ ውስተ ፩ዱ አራት። ለይኅድር እግዚአብሔር ውስተ ቤቱ ለሴም እንዲል በሴም ዕፃ ፪ ሰዎች ይኖራሉ ምግባር ሃይማኖት የያዘውን ወደ ገነት ያልያዘውን ወደ ገሃነም ይተዋሉ።
አንድም ፪ቱ ይሄልዉ ብለህ መልስ፡፡ ባሕታውያን በበረሀ ይኖራሉ እንደ አንጦንስ እንደ መቃርስ እንደ አቡነ ተክለሃይማኖት ያሉትን ይነሥኡ ወደ ገነት። እንደ ሠናየ ዝክር እንደ በዓለ መቅጹት ያሉትን የኃድጉ በገሃነም።
ወ፪ቲ የሐርጻ።
ነዳያን በዚህ ዓለም ይኖራሉ፡፡ አንደ አልዓዛር እንደ ሐዋርያት ያሉትን ወደ ገነት። እንደ ይሁዳ እንደ አይሁድ ያሉትን በገሃነም።
ወ፪ቱ ይሰክቡ ውስተ ፩ዱ አራት፡፡ ባለጸጎች በዚህ ዓለም ይኖራሉ እንደ ኢዮብ እንደ አብርሃም ያሉትን ይነሥኡ ወደ ገነት፤ እንደ ነዌ እንደ ኪራም ያሉትን የኀድጉ በገሃነም።
                    ******     
፵፪፡ ትግሁ እንከ እስመ ኢተአምሩ በዓይ ሰዓት ይመጽእ እግዚአክሙ፡፡ ማር ፲፫፥፳፫። ሉቃ ፲፪፥፴፱፡፡
                    ******     
፵፪፡ ጌታችሁ በማናቸውም ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና ለትሩፋት ተግታችሁ ኑሩ።
                    ******     
፵፫፡ ወዘንተ ባሕቱ አእምሩ ወኢትርስዑ
                    ******     
፵፫፡ ባሕቱ ዋዌ ነው፡፡ ይህንም ዕወቁ
ሶበሁ የአምር በዓለ ቤት ጊዜ ይመጽእ ሠራቂ እምተግሀ ወእምሀለወ።
ባለቤት ሌባ የሚመጣበትን ጊዜ ቢያውቅ ተግቶ በጠበቀ ነበር።
ወእምኢኃደገ ይክርዩ ቤቶ።
ግድግዳውን ምሰው ናሱን አፍርሰው ይሠርቁት ዘንድ ቸል ባላለም ነበር።
                    ******     
፵፬፡ ወበእንተዝ አንትሙኒ ድልዋኒክሙ ሀልዉ እስመ በጊዜ ኢተኃዘብክሙ ይመጽእ ወልደ እጓለ እመሕያው።
                    ******     
፵፬፡ ወልደ እጓለ እመሕያው ክርስቶስ ባልጠረጠራችሁት ዕለት ባላወቃችሁት ሰዓት ይመጣልና እንደዚህ እናንተም ተዘጋጅታችሁ ኑሩ።
                    ******     
፵፭፡ መኑ እንጋ ውእቱ ገብር ምዕመን ጠቢብ ዘይሠይሞ እግዚኡ ውስተ ኵሉ ቤቱ።
                    ******     
፵፭፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ለነሁ ትሜህረነ ወሚመ ለኵሉ ብሎታል በሉቃስ። ምን እናንተን ብቻ እናንተን ለመሰለ ሁሉ ነው እንጂ ብሎ አያይዞ በዚያውስ ላይ ጌታው አምኖ የሚሾመው ብልህ በጎ ባሪያ ማነው።
ከመ የሀቦሙ ሲሳዮሙ በበጊዜሁ።
በየጊዜው ምግባቸውን ይሰጣቸው ዘንድ የዕለት የሳምንት የወር የዓመት ምግቡን የሚቀበል አለና።
                    ******     
፵፮፡ ብፁዕ ውእቱ ገብር ዘመጺኦ እግዚኡ ይረክቦ እንዘ ከመዝ ይገብር። ራዕ ፲፮፥፲፭።
                    ******     
፵፮፡ ጌታው በመጣ ጊዜ እንዲህ ሲያደርግ ማለት ምግባቸውን ሲሰጣቸው የሚያገኘው ባሪያ ንዑድ ክቡር ነው።
                    ******     
፵፯፡ አማን እብለክሙ ከመ ዲበ ኵሉ ጥሪቱ ይሠይሞ፡፡
                    ******     
፵፯፡ በገንዘቡ ሁሉ ይሾመዋል ብዬ እንዲሾመው በእውነት እነግራችኋለሁ።
                    ******     
፵፰፡ ወእመሰ ይቤ ውእቱ ገብር አኵይ ይጐነዲ አቲወ እግዚእየ።
                    ******     
፵፰፡ ያ ክፉ ባሪያ ግን ጌታዬ የሚመጣበት ጊዜ ገና ነው ብሎ።
                    ******     
፵፱፡ ወይዘብጥ አብያጺሁ አግብርተ ይበልዕ ወይሰቲ ምስለ ሰከርያን።
                    ******     
፵፱፡  የጌታውን ባሮች ባልንጀሮቹን ቢመታ ማለት በበትረ ረኀብ ሲመቱ ከአዝማሪ ከዘዋሪ ጋራ እየበላ እየጠጣ ምግባቸውን አልሰጥም ቢል።
                    ******     
፶፡ ወይመጽእ እግዚኡ ለውእቱ ገብር በዕለተ ኢተሀዘበ ወበጊዜ ኢያእመረ ወይሠጥቆ እማዕከሉ።
                    ******     
፶፡ ባላወቀው ዕለት ባልጠረጠረው ሰዓት መጥቶ ጌታው ከሹመቱ ይሽረዋል።
ወይሬሲ መክፈልቶ ምስለ መደልዋን ኀበ ሀሎ ብካይ ወሐቅየ ስነን። ማቴ ፲፫፥፵፪፡፡ ፳፭፥፴።
፶፩፡ ዕድል ፈንታውን ጽዋእ ተራውንም ልቅሶ ጥርስ ቊርጥማት ካለበት ቦታ ከግብዞች ጋራ ያደርግበታል።
አንድም መኑ ውእቱ ብለሀ መልስ፡፡ ጌታው አምኖ በነዳያን ላይ የሚሾመው ባለጸጋ ማነው፡፡ ጌታ ለሰው ብዕል መስጠቱ ለነዳያን መሾሙ ነውና፡፡
ከመ የሀቦሙ
ስጠን ባሉት ጊዜ ለነዳያን ሊሰጣቸው።
ብፁዕ ውእቱ፡፡
ጌታው በመጣ ጊዜ ለነዳያን ምግባቸውን ሲሰጣቸው የሚገኝ ባለጸጋ ንዑድ ክቡር ነው።
አማን እብለክሙ
በወዲያውም ዓለም ብዕል ይሾመዋል ብዬ በእውነት እነግራችኋለሁ።
ወእመሰ ይቤ፤
 ያ ክፉ ባለጸጋ ግን የምሞትበት ጊዜ ገና ነው ብሎ ከአዝማሪ ከዘዋሪ ጋራ እየበላ እየጠጣ ነዳያን በበትረ ረኃብ ሲሞቱ አልሰጥም ቢል፡፡ ዘሰ ይዳደቅ በአናቅጽ ውእቱኬ ያመነድብ ነፍሳተ እንዲል፡፡
ወይመጽእ እግዚኡ፡፡
ባልጠረጠረው ዕለት ባላወቀው ሰዓት ጌታው መጥቶ በማዕከለ ዘመኑ ነፍሱን ከሥጋው ይለያታል እድል ፈንታውን ጽዋ ተራውን ከኃጥአን ጋራ ጽኑዕ ሥቃይ ባለበት ቦታ በገሃነም ያደርግበታል።
አንድም መኑ ውአቱ ብለሀ መልስ፡፡ ጌታው አምኖ በምዕመናን የሚሾመው ቄስ መምህር ማነው።
ከመ የሀቦሙ ሲሳዮሙ፡፡
ያስተምራቸው ዘንድ ንስሐን ሥጋውን ደሙን ይሰጣቸው ዘንድ።
ብፁዕ ውእቱ
ጌታው በመጣ ጊዜ ሲያስተምራቸው የሚገኝ መምህር ንስሐን ሥጋውን ደሙን ሲሰጣቸው የሚገኝ ቄስ ንዑድ ክቡር ነው።
አማን እብለክሙ
በወዲያው ዓለም ምሥጢር ክብር ይሾመዋል ብዬ እንዲሾመው በእውነት እነግራችኋለሁ።
ወእመሰ ይቤ ውእቱ ገብር እኵይ።
ያ ክፉ መምህር ቄስ ግን የምሞትበት ጊዜ ገና ነው ብሎ።
ወይዘብጥ አብያጺሁ
ምዕመናን በበትረ ክህደት ሲመቱ አላስተምርም ቢል በበትረ ኃጢአት ሲመቱ ንስሐን ሥጋውን ደሙን አልሰጥም ቢል። ኢትዘበጥ አንተ ከመ ኢይላሁ አነ ዛቲ ምጽንጋዕ ምዕረ ትዘብጠከ ወምዕረ ትዘብጠኒ እንዲል።
ወይመጽእ እግዚኡ።
ባላወቀው ዕለት ባልጠረጠረው ሰዓት ጌታው መጥቶ ነፍሱን ከሥጋው ይለያታል።
ወይሬሲ መክፈልቶ፤
እድል ፈንታውን ጽዋ ተራውንም ከኃጥአን ጋራ ጽኑ ሥቃይ ባለበት በገሃነም ያደርግበታል።
                    ******
በእንተ ደናግል ጠባባት ወአብዳት፡፡
ምዕራፍ ፳፭።
፩፡ አሜሃ ትመስል መንግሥተ ሰማያት አሥሮን ደናግለ እለ ነሥአ መኃትዊሆን ወወፅአ ውስተ ቀበላ መርዓዊ
፩፡ አብነት አሜሃ ይእተ አሚረ ይላል ያን ጊዜ መንግሥተ ሰማይ ሕገ ወንጌል። ሕገ ወንጌል ተስፋ፡፡ ተስፋ ኢየሱስ ክርስቶስ ፋና ይዘው አሥሩ ደናግል ሊቀበሉት የወጡ ሙሽራን ትመስላለች።     
                        ******     
  ይቆየን፡፡
**********
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
13/10/2011 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment