Wednesday, June 19, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 120

====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ ዘአቅደመ ነጊረ ሙስናሃ ለቤተ መቅደስ።
ምዕራፍ ፳፬።
                    ******     
፴፩፡ ወይፌንዎሙ ለመላእክቲሁ ምስለ ቃለ ቀርን። ፩፡ቆሮ ፲፭፥፳፪።
                    ******     
፴፩፡ አዋጅ ከመንገር ጋራ መላእክትን ያዛቸዋል።
ወስብሐት ዓቢይ።
ብርሃነ መለኮቱን ገልጾ በመጣ ጊዜ።
ወያስተጋብዕዎሙ ለጎኅሩያኒሁ እም፬ቱ ነፋሳት አምአጽናፈ ሰማይ እስከ አጽናፊሃ።
ሙታንን ከአራቱ ማዕዘን ይሰበስቧቸዋል። ይመጽእ ወያስትጋብዖሙ ይፌንዎሙ ወያስተጋብእዎሙ ይላል።
                    ******     
፴፪፡ ወእምበለስ አእምሩ አምሳሊሁ
                    ******     
፴፪፡ ነገሩን በበለስ ዕወቁ።
እምከመ ለምለመ አዕፁቂሁ ወሠረፀ ቈፅሉ ተአምሩ ከመ ቀርበ ማዕረር።
በለስ ቅጠሉ የለመለመ ዓፅቅ ያወጣ እንደሆነ መከር እንደ ደረሰ ዕወቁ።
(ሐተታ) የጥጦስን በቅጠል የሐሳዊ መሢሕን በአበባ የምጽአትን በፍሬ መስሎ ይናገራል።
አንድም እንደ ቅጠሉ ሐሳዊ መሢሕ ነግሦላቸው ቤተ አይሁድ ደስ ብሏቸዋል። እንደ አበባው የምዕመናን መከራቸው እንደ ፍሬው ሞታቸው።
አንድም እንደ ፍሬ ሞታቸው እንደ አበባ ክብራቸው፡፡
አንድም ቈጽል አይለወጥም። እንደ አበባው የአይሁድ መከራቸው እንደ ፍሬው ሞታቸው።
አንድም እንደ አበባው ሞታቸው እንደ ፍሬው ፍዳቸው።
                    ******     
፴፫፡ ከማሁኬ አንትሙኒ እምከመ ርኢክሙ ዘንተ ኵሎ አእምሩ ከመ ቀርበ ኀበ ኆኅት።
                    ******     
፴፫፡ እናንተም ይህን ሁሉ ያያችኹ እንደሆነ እንደቀረበ ከደጅ እንዳለ እወቁ ከደጅ የቆመ ፈጥኖ እንዲገባ ፈጥኖ እንዲደረግ እወቁ ማለት ነው።
                    ******     
፴፬፡ አማን እብለክሙ ከመ ኢተኃልፍ ዛቲ ትውልድ እስከ ዝ ኵሉ ይትገበር።
                    ******     
፴፬፡ ይህ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ ቤተ አይሁድ አታልፍም ብዬ እንዳታልፍ እነግራችኋለሁ።
                    ******     
፴፭፡ ሰማይ ወምድር የኃልፍ፡፡ ማር ፲፫፥፴፬።
                    ******     
፴፭፡ ሰማይና ምድር ያልፋል።
ወቃልየሰ ኢየኃልፍ።
ሕጌ ግን አያልፍም።
አንድም ዕለፍ ያልሁት ያልፋል ዕለፍ ያላልሁት አያልፍም።
አንድም ሕጌን የያዘ አያልፍም ሕጌን ያልያዘ ግን ያልፋል።
                    ******     
ዘከመ ይደልዎ ተጊህ ለክርስቲያን እስመ ኢየአምር ሰአተ ሞቱ።
፴፮፡ ወበእንተሰ ይእቲ ዕለት ወይእቲ ሰዓት አልቦ ዘየአምራ።
                    ******     
፴፮፡ ያችን ዕለት ያችን ሰዓት የሚያውቃት የለም። ይእቲ ባለው ወኪያሃ ይላል አብነት ወይእቲ ማለት ነው። ወሰምዓት ዮዲት በኪያሆን መዋዕል እንዲል፡፡
(ሐተታ) ዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ ወርኁ ወርኃ መጋቢት ዕለቱ ዕለተ እሁድ ሰዓቱ መንፈቀ ሌሊት አይደለም ቢሉ ብዙ ዘመነ ዮሐንስ ብዙ ወርኃ መጋቢት ብዙ ዕለተ እሁድ ብዙ መንፈቀ ሌሊት አለና።
ኢመላእክተ ሰማይ።
መላአክትም ሁነው
ወኢወልድ።
ደቂቀ አዳምም ሁነው አያውቋትም። ኦሪት ዘልደት እንዲል፡፡
ዘእንበለ አብ ባሕቲቱ።
ከብቻው ከአብ በቀር አብ ብቻ ያውቃታል እንጂ።
(ሐተታ) ከፍጡራን ሲለየው ነው እንጂ ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ሲለየው አይደለም።
አንድም ወልድ ቅድመ ተዋሕዶ የነበረ አላዋቂ ሥጋን እንደ ተዋሐደ ለማጠየቅ። አኮ ኢያእሚሮ ኅቡአተ አላ ከመ የሀብ መካነ ለጥንተ ትስብእቱ ዘኢየአምር ኅቡዓተ እንዲል።
አንድም አብ ለልጁ በመስጠት አውቋታል ወልድ ግን በሥራ አላወቃትም ሲል እንዲህ አለ።
አንድም። ኢወልድ ባሕቲቱ ዘእንበለ አብ ወልድ ብቻ ያለ አብ አያውቃትም።
                    ******     
፴፯፡ ወበከመ ኮነ በመዋዕሊሁ ለኖኅ ከማሁ ይከውን ምጽአቱ ለወደ እጓለ እመሕያው፡፡ ዘፍ ፯፥፯፡፡ ሉቃ ፲፯፥፳፮፡፡
                    ******     
፴፯፡ በኖኅ ዘመን እንደተደረገው የወልደ እጓለ እመሕያው የክርስቶስ ምጽአቱ እንዲህ ይደረጋል።
                    ******     
፴፰፡ እስመ በከመ ኮነ በመዋዕለ ኖኅ እምቅድመ ማየ አይህ ይበልዑ ወይሰትዩ።
                    ******     
፴፰፡ ከማየ አይህ አስቀድሞ ሲበሉ ሲጠጡ።
ያወስቡ ወይትዋሰቡ።
ሲያገቡ ሲጋቡ እንደነበረ።
እስከ አመ ቦአ ኖኅ ውስተ ንፍቀ
ንፉቀ ታቦተ ሲል ነው ስጠተ ልብስ ጠፈረ ቤት እንዲል ስጡጠ ልብሰ ጥፉረ ቤተ ሲል ኖኅ ክፍል ክፍል ካለው መርከብ እስኪገባ ድረስ።
                    ******     
፴፱፡ ወኢያእመሩ እስከ አመ መጽአ ማየ አይኅ ወአጥፍአ ኵሎ
                    ******     
፴፱፡ የጥፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን እስኪያጠፋ ድረስ እንዳላወቁ
ከማሁኬ ይከውን ምጽአቱ ለወልደ እጓለ እመሕያው።
የክርስቶስ ምጽአቱ እንዲህ ነውና በኖኅ ጊዜ እንደተደረገ ይደረጋል።
                    ******     
፵፡ አሜሃ ፪ቱ ይሄልው ውስተ ፩ዱ ገራህት።
፵፡ ያንጊዜ ሁለት ሰዎች በአንድ እርሻ ይኖራሉ።
                    ******     
  ይቆየን፡፡
**********
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
12/10/2011 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment