Sunday, June 9, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 115

====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ መደልዋን ፈረሳውያን
ምዕራፍ ፳፫።
                    ******     
፩፡ ወእምዝ ይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ ለሕዝብ  ወለአርዳኢሁ።
                    ******     
፩፡ ከዚህ በኋላ ጌታ ነገራቸው።
                    ******  
፪፡ እንዘ ይብል ዲበ መንበረ ሙሴ ነበሩ ለክሙ ጸሐፍት ወፈሪሳውያን። እዝራ ፰፥፬።
                    ******     
፪፡ ጸሐፍት ፈሪሳውያን በሙሴ ለሕዝቡ ወንበር ማለት በሙሴ መምህርነት አሉላችሁ።
                    ******     
፫፡ ኵሎ ዘይቤሉክሙ ግበሩ።
                    ******     
፫፡ ያዘዟችሁን ሁሉ ሥሩ።
ወዘመሐሩክሙ ዕቀቡ።
ያስተማሯችሁንም ጠብቁ።
ወዘከመ ምግባሮሙሰ ኢትግበሩ።
እንደ ሥራቸው ግን አትሥሩ
እስመ እሙንቱ ይሜህሩ ለባዕድ።
ለሌላ ያስተምራሉና ግበሩ ፅቀቡ።
ወኢይገብሩ፤
እሳቸው አይሠሩትምና ኢትግበሩ።
አንድም ንግሩ እንጂ ግበሩ የለምና ኢትግበሩ በል፡፡
                    ******     
፬፡ ወየዓሥሩ ፆረ ዓቢየ ወክቡደ ወያሰክምዎ ለሰብእ ዲበ መትከፍቱ፡፡ ሉቃ ፲፩፥፵፮፡፡ ግብ ፲፭፥፲።
                    ******     
፬፡ ጽኑ ሸክም አሥረው ሰውን ተሸከም ይሉታል።
ወለሊሆሙሰ ኢይለክፍዎ በአጽባዕቶሙ ጥቀ።
እሳቸው ግን ስንኳን ሊሸከሙት በጣታቸው አይዳስሱትም።
አንድም ወየዓሥሩ። ጽኑ ሥርዓት ሠርተው ሰውን ጠብቅ ይሉታል።
ወለሊሆሙሰ
እሳቸው ግን ስንኳን ሊሰሩት እንሠራዋለን ብለው አያስቡም።
                    ******     
፭፡ ወኵሉ ምግባሮሙ ዘይገብሩ ለዓይነ ሰብእ ይገብሩ። ዘኊል ፲፭፥፴፰። ዘዳ ፳፪፥፲፪። ማር ፲፪፥፴፱። ሉቃ ፲፩፥፵፪፡፡ ፳፥፵፮፡፡
                    ******     
፭፡ የሚሠሩት ሁሉ ለሰው ይምሰል ነው።
ወይሰፍሑ ኵርበታቲሆሙ።
እንደጎልጎታ ያለ አላቸው ያን ባደርባይ ዘርግተው ይታያሉ
ወየዓብዩ አዝፋረ አልባሲሆሙ
የልብሳቸውን ዘርፍ አስፍተው ያስጥሉታል፣
(ሐተታ) ጌታ ሙሴን በልብሳችሁ ሰማያዊ ሐር አስጥሉ ብሎታል ለጊዜው ሰማይ የሚመስል ባሕር ከፍዬ አሻገርኋችሁ ሲል ነው ፍጻሜው ግን ሰማያዊ ሕግን ጠብቁ ሲል ነው፡፡ ከሕዝቡ ይልቅ እኛ እንጠብቃለን ለማለት እሳቸው እያሰፉ የሚያስጥሉ ሁነዋል።
አንድም አልፈው አልፈው ያስጥሉበታል እንደ ሱሲ መጠብር እንደቀሽመሪ መታጠቂያ እንደ መረሻት።
አንድም ፲ቱ ቃላትን በልብሳቸው ይጽፉ ነበር ከሰውነታችን የተረፈው በልብሳችን አለ ለማለት ቄስ አፄ ምህርካ ድንግል ኢየሱስ ናዝራዊ ብለው በልብሳቸው ጽፈው እንደነበረ፡፡
                    ******     
፮፡ ወያፈቅሩ ርእሰ ምርፋቃት በውስተ ምሳሐት፣
                    ******     
፮፡ በምሳም ጊዜ በላይ መቀመጥን ይወዳሉ ምንጣፍ መጨጊያ ከአለበት ወጥ ከተደራረበበት እንጀራ ከበዛበት ጽዋ ከሚጀመርበት ይህ ለጊዜው ጥቅም ያለበት ነው።
ወነቢረ ፍጽም በውስተ አዕዋዳት፤
በአደባባይ ፊት ለፊት መቀመጥን ይወዳሉና
                    ******     
፯፡ ወተአምኆ በውስተ ምሥያጣት
                    ******     
፯፡ በአደባባይ እጅ ሊነሷቸው ሊያከብሯቸው ይወዳሉ
ወይበልዎሙ ሰብአ መምሕራን፤
መምሕራን ይሏቸው ዘንድ
                    ******     
፰፡ አንትሙሰኬ ኢትስምዩ መምሕረ በዲበ ምድር፡፡ ያዕ ፫፥፩፡፡
                    ******     
፰፡ እናንተስ ምድራዊ መምህር አይኑራችሁ
እስመ ፩ዱ ውአቱ መምሕርክሙ፤
መምሕራችሁ አንድ ሰማያዊ ክርስቶስ ነውና፡፡
(ሐተታ) ዲበ መንበረ ሙሴ ነበሩ ያለውን ማፍረሱ ነው ቢሉ ያንም እንጂ ወዘከመ ምግባሮሙሰ ኢትግበሩ ባለው አፍርሶታል፡፡
አንድም ለጣዖት ስገዱ ሃይማኖታችሁን ካዱ የሚል መምህር አይኑራችሁ ሲል ነው፡፡
                    ******     
፱፡ ወኢትረስዩ ለክሙ አበ በዲበ ምድር። ሚልክ ፩፥፮።
                    ******     
፱፡ ምድራዊ አባት አይኑራችሁ፤
እስመ ፩ ውእቱ አቡክሙ ሰማያዊ ፤
አባታችሁ አንዱ ሰማያዊ ክርስቶስ ነውና፣
(ሐተታ) አክብር አባከ ወእመከ ይል የለም ቢሉ ከአክብሮተ አብ ወእም አክብሮተ እግዚአብሔር እንዲበልጥ  ለማጠየቅ፤
አንድም ለጣዖት ስገዱ የሚል አባት አይኑራችሁ ሲል ነው፤ ዘኢኃደገ አባሁ ወእሞ ኢይክል ይጸመደኒ እንዲል፥
አንትሙሰ አኃው ኩልክሙ
እናንተስ ወንድማማች ናችሁ
                    ******     
፲፡ ወኢትስምዩ እግዚአ በዲበ ምድር
                    ******     
፲፡ ምድራዊ ጌታ አይኑራችሁ፤
(ሐተታ) ዘቄሣር ሀቡ ለቄሣር ብሎ የለም ቢሉ ያንም እንጂ ወዘእግዚአብሔር ለእግዚአብሔር ባለው አፍርሶታል፡፡
አንድም ለጣዖት ስገዱ ሃይማኖታችሁን ካዱ የሚል ጌታ አይኑራችሁ ሲል ነው፡፡
እስመ ፩ዱ ውእቱ እግዚአክሙ ክርስቶስ፡፡
ሰማያዊ ጌታችሁ አንድ ክርስቶስ ነውና።
                    ******     
፲፩፡ ወባሕቱ ዘይፈቅድ እምኔክሙ ይኩን ዓቢየ ይኩንክሙ ገብረ፡፡
                    ******     
፲፩፡ ከእናንተ ወገን በላይ ሊሆን የወደደ አገልጋይ ይሁናችሁ
ወዘይፈቅድ እምኔክሙ ይኩን ሊቀ ይኩንክሙ ላዕከ።
ገዥ ሊሆን የወደደ ተገዥ ይሁናችሁ።
                    ******     
፲፪፡ እስመ ዘአዕበየ ርእሶ የኃሥር፡፡ ሉቃ ፲፱፥፲፩።
                    ******     
፲፪፡ ራሱን ያከበረ ይዋረዳልና።
ወዘአትሐተ ርእሶ ይከብር
ራሱን ያዋረደ  ይከብራልና።
                    ******     
፲፫፡ አሌ ለክሙ ጸሐፍት ወፈሪሳውያን።
                    ******     
፲፫፡ ጸሐፍት ፈሪሳውን እናንተ ግብዞች ወዮላችሁ።
እለ ትበልዑ አብያተ መበለታት በምክንያተ አንኆ ጸሎትክሙ።
አብዝተን አንጸልያለን በማለት ምክንያት የድሆችን ገንዘብ የምትበሉባቸው ማዕዜመ እገብር ቤተ ለርእስየ ያጠርያ ቤተ እምጽድቀ ዚአሆን እንዲል፤ አብዝተው ሲጸልዩ ያዩዋቸው እንደሆነ የባሎቻችነን ነፍስ ያስምሩልናል ልጆቻችነን ያሳድጉልናል እያሉ ይሰጧቸዋልና።
ወበእንተ ዝንቱ ትረክቡ ኵነኔ ፈድፋደ፣
ስለዚህ ጽኑ ፍዳ ትቀበላላችሁ
                    ******     
፲፬፡ አሌ ለክሙ ጸሐፍት ወፈሪሳውያን መደልዋን።
                    ******     
፲፬፡ እናንት ግብዞች ወዮላችሁ።
እስመ ተዓፅዉ መንግሥተ ሰማያት ቅድመ ገጹ ለሰብእ፤
በሰው ፊት መንግሥተ ሰማይን ትዘጉበታላችሁና። አብነት ሁናችሁ እንዳይገቡ ታደርጓቸዋላችሁ ማለት ነው።
አንትሙሂ ኢትበውዑ።
እናንም አትገቡ።
ወለእለሂ ይበውዑ ትክልዕዎሙ በዊአ።
የሚገቡትንም አብነት ሁናችሁ እንዳይገቡ  ታደርጓቸዋላችሁ።
                    ******     
፲፭፡ አሌ ለክሙ ጸሐፍት ወፈሪሳውያን መደልዋን።
                    ******     
፲፭፡ እናንተ ግብዞች ወዮላችሁ። እስመ ተዓውዱ ባሕረ ወየብሰ ከመ ታጥምቁ አሐደ ፈላሴ ትግዝሩ ሲል ነው ከጣዖት ከኃጢአት ፈልሶ የመጣውን ትገዝሩ ዘንድ የብሱን በእግር ባሕሩን በሐመር ትዞራላችሁና፤
ወተጠሚቆ ትሬስይዎ ወልደ ገሃነም።
የገሃነም ልጅ ማለት ከተዘረም በኋላ ተማልታችሁት ገሃነም ትወርዳላችሁ።
                    ******     
፲፮፡ አሌ ለክሙ ጸሐፍት ወፈሪሳውያን አምህርተ ዕውራን።
                    ******     
፲፮፡ አምርህት ይላል የዕውራነ አእምሮ መሪዎች መምህሮች ወዮላችሁ።
እለ ትብሉ ዘመሀለ በቤተ መቅደስ ይጌጊ።
በቤተ መቅደስ ቢምል ዕዳ አይሆንበትም የምትሉ።
ወዘሰ መሀለ በወርቀ ቤተ መቅደስ ኢይጌጊ።
በመባው ቢምል ግን ዕዳ ይሆንበታል የምትሉ።
                    ******     
፲፯፡ ዓብዳን ወዕውራን።
፲፯፡ እናንት አላዋቆች ሰነፎች።
                    ******       
  ይቆየን፡፡
**********
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
03/10/2011 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment