====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ ደናግል ጠባባት ወአብዳት፡፡
ምዕራፍ ፳፭።
******
በእንተ ምሳሌ ዘመካልይ።
፲፬፡ እስመ ከመ ብእሲ ዘይነግድ ወጸውአ አግብርቲሁ ወወሀቦሙ ንዋዮ ይትገበሩ ቦቱ። ሉቃ ፲፱፥፲፪፡፡
******
፲፬፡ መንግሥተ ሰማይ ሕገ ወንጌል፣ ሕገ ወንጌል ተስፋ ተስፋ ኢየሱስ ክርስቶስ ብላቴኖችን ጠርቶ ወጥተው ወርደው ያተርፉበት ዘንድ ገንዘቡን የሰጣቸውን ነጋዴን ትመስላለችና ትግሁ። አንድም ትመስላለች እኮን።
******
፲፭፡ ቦ ለዘወሀቦ ፭ተ መክሊተ።
******
፲፭፡ አምስት መክሊትን ለሰጠው ሰው አምስት መክሊት አለው አምስት መክሊትን ለሰጠው ሰው ስጦታ አለው ለሰጠው አምስት መክሊት አለው። አምስት መክሊት የሰጠው ሰው አለ።
ወቦ ለዘወሀቦ ፪ተ መክሊተ።
ሁለት መክሊት የሰጠው ሰው አለ እንዳለፈው በል።
ወቦ ለዘወሀቦ አሐደ መክሊተ፣
አንድ መክሊት የሰጠው ሰው አለ።
ወለለ፩ዱ እምኔሆሙ በአምጣነ ይክሉ።
ከሳቸው ወገን ለአንዱም ለአንዱ እንደሚቻላቸው መጠን።
ወነገደ በጊዜሃ።
ሰጥቷቸው ሄደ።
******
፲፮፡ ወሖረ ዝኩ ዘኃምስ መክሊተ ነሥአ ወተገበረ ቦቱ።
******
፲፮፡ አምስት መክሊት የተቀበለው ወጥቶ ወርዶ አተረፈ።
ወረብኃ ካልዓተ ፭ተ መካልየ።
አምስት አተረፈ አሥር አደረገ።
******
፲፯፡ ወከማሁ ዘሂ ፪ተ መካልየ ረብኃ ካልዓተ መካልየ
******
፲፯፡ እንደዚህ ሁሉ ሁለት መክሊት የተቀበለውም ወጥቶ ወርዶ አተረፈ አራት አደረገ።
******
፲፰፡ ወዘአሐደሰ መክሊተ ነሥአ ሖረ ወኃለፈ ወከረየ ምድረ ወኃብአ ወርቀ እግዚኡ።
******
፲፰፡ አንድ መክሊት የተቀበለው ግን ሌባ ቢሠርቀኝ ወንበዴ ቢቀማኝ ቀጣፊ ቢያታልለኝ ብሎ ፈርቶ ሄዶ ምድር ቆፍሮ የጌታውን ወርቅ ቀበረ።
******
፲፱፡ ወእምድኅረ ብዙኅ መዋዕል አተወ እግዚኦሙ ለእሉ አግብርት።
******
፲፱፡ ከብዙ ዘመን በኋላ የነዚያ የባሮች ጌታቸው መጣ።
ወአኀዘ ይትሐሰቦሙ።
ተቈጣጠራቸው።
******
፳፡ ወቀርበ ዘኃምስ መካልየ ነሥአ ወአምጽአ ካልዓተ ኃምሰ መካልየ።
******
፳፡ አምስት መክሊት የተቀበለው ወጥቶ ወርዶ ያተረፈውን አምስቱን ደርቦ አመጣ።
እንዘ ይብል እግዚኦ ኃምሰ መካልየ ወሀብከኒ።
አቤቱ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር።
አንድም ዘወሀብከኒ የሰጠኸኝ። አምስት መክሊት ነበር።
አኮሁ ኃምስ መካልየ ወሀብከኒ
አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ አልነበረምን።
አንድም ዘወሀብከኒ የሰጠኸኝ አምስት አልነበረምን።
ወናሁ ኃምስ መካልይ ዘረባሕኩ ዲቤሆን።
እነሆ ወጥቼ ወርጄ አምስት አትርፌአለሁ አሥር አድርጌአለሁ አለው።
******
፳፩፡ ወይቤሎ እግዚኡ ኦ ገብር ኄር ወምዕመን ዘበኅዳጥ ምዕመነ ኮንከ ዲበ ብዙኅ እሰይመከ።
******
፳፩፡ አንተ በጎ ባሪያ በጥቂቱ ከታመንክ በብዙው እሾምሀለሁ።
ባዕ ውስተ ፍሥሐሁ ለእግዚእከ።
ጌታህ ተድላ ከሚያደርግበት ግባ ማለት ተሾም ተሸለም አለው።
******
፳፪፡ ወመጽአ ዘ፪ተ መክሏተ ነሥአ
******
፳፪፡ ሁለት መክሊት የተቀበለውም መጣ።
ወይቤ እግዚኦ አኮሁ ፪ተ መካልየ ወሀብከኒ።
አቤቱ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ አልነበረምን።
ወናሁ ፪ተ ካልዓተ መካልየ ረባሕኩ
እነሆ ወጥቼ ወርጄ ሁለት አተረፍኩ አራት አደረግሁ አለው።
******
፳፫፡ ወይቤሎ እግዚኡ ኦ ገብር ኄር ወምዕመን ዘበውኍድ ምዕመነ ኮንከ ዲበ ብዙኅ እሠይመከ ባዕ ውስተ ፍሥሐሁ ለእግዚእከ።
******
፳፫፡ አንተ በጎ ባሪያ በጥቂቱ ከታመንክ በብዙ ወገን እሾምሀለሁ ጌታህ ተድላ ከሚያደርግበት ግባ ማለት ተሾም ተሸለም አለው።
******
፳፬፡ ወመጽአ ዘሂ ዘ፩ደኒ መክሊተ ነሥአ።
******
፳፬፡ አንድ መክሊት የተቀበለውም መጣ።
ወይቤ እግዚኦ አአምረከ ከመ ብእሲ ድሩክ አንተ ተአርር ዘኢዘራእክ ወታስተጋብዕ ዘኢዘረውከ፡፡
አቤቱ ያልዘራኸውን የምታጭድ ያልበተንኸውን የምትሰበስብ ትነሥእ ዘኢያንበርከ ይላል በሉቃስ ያላኖርኸውን የምታነሳ ጽኑ ጨካኝ መሆንክን አውቃለሁና።
******
፳፭፡ ወፈሪህየ ሖርኩ ወከረይኩ ምድረ ወደፈንኩ መክሊተከ ውስተ ምድር።
******
፳፭፡ ሌባ ቢሠርቀኝ ወምበዴ ቢቀማኝ ቀጣፊ ቢያታልለኝ ብዬ ፈርቼ ምድር ቆፍሬ ቀብሬ አኑሬአለሁ። ጠብለልክዋ ውስተ ሰበንየ ይላል በሉቃስ። በመጠምጠሚያዬ ቋጥሬ ይዣለሁ።
ናሁ ንሣእ ንዋየከ።
እነሆ ገንዘብክን ተቀበለኝ አለው።
ወአውሥአ እግዚኡ።
ጌታው መለሰ።
******
፳፮፡ ወይቤሎ ኦ እኩይ ገብር ወሀካይ ተአምረኒኑ ከመ ብእሲ ድሩከ አነ አዓርር ዘኢዘራዕኩ ወአስተጋብዕ ዘኢዘረውኩ።
******
፳፮፡ ያልዘራሁትን የማጭድ ያልበተንሁትን የምሰበስብ ጽኑ ጨካኝ መሆኔን ታውቃለህን።
******
፳፯፡ ወእምደለወከ ተግብዕ ወርቅየ ውስተ ማዕድየ።
******
፳፯፡ ይኸን ከአወቅህ ገንዘቤን ልትሰጠኝ የተገባህ ነበር።
ወመጺአየ አነ ለልየ እምአስተገበርክዎ በርዴ።
ወጥቶ ወርዶ ለሚያተርፍልኝ በሰጠሁት ነበር።
አንድም እኔ ወጥቼ ወርጄ ባተረፍኩበት ነበር፡፡
******
፳፰፡ ወይቤሎሙ ለእለ ይቀውሙ ህየ ንሥኡ እምኔሁ ዘንተ መክሊተ ወሀብዎ ለዘቦ ፲ቱ መክሊት። ማቴ ፲፫፥፲፪፡፡ ማር ፬፥፳፭፡፡ ሉቃ ፰፥፲፰፡፡ ፲፱፥፳፮፡፡
******
፳፰፡ ይህን መክሊት ከሱ ተቀብላችሁ አሥር መክሊት ላለው
ስጡት።
******
፳፱፡ እስመ ለዘቦ ይሁብዎ።
******
፳፱፡ ላለው ይሰጡታልና ማለት አምስት ላለው አምስት ይሰጡታልና።
ወይዌስክዎ።
ይደርቡለታል አለ አንዱን።
ወለዘለሰ አልቦ ዘሂ ቦ የሀይድዎ።
የሌለውን ግን ያኑ ያለውን ቅሉ ይወስዱበታልና ንሥኡ።
******
፴፡ ወለገብርሰ እኩይ ወሀካይ አውፅእዎ አፍአ ወደይዎ ውስተ ጽልመት ጸናፊ ኃበ ሀሎ ብካይ ወሐቅየ ስነን።
******
፴፡ ያን ሐኬተኛ ባሪያ ግን ልቅሶ ጥርስ ቁርጥማት ወዳለበት ወደጽኑ ጨለማ አግዙት አለ።
አንድም። ቦ ለዘወሀቦ ፭ተ መክሊተ ብለሀ መልስ። ባለ፭ት የተባለ ፍጹም ትምህርት ተምሮ መክሮ አስተምሮ ራሱን አስመስሎ ያወጣ ነው፡፡ ባለሁለት የተባለ ፍጹም ትምህርት ተምር መክሮ አስተምሮ ራሱን አስመስሎ ያወጣ ነው፤ ቅዱስ ጴጥሮስ ቀሌምንጦስን፤ ጳውሎስ ጢሞቴዎስን እንዳወጡ፡፡ ባለአንድ የተባለ ተምሮ ሳያስተምር የቀረ ነው።
ወሖረ ዝኩ ዘኃምስ መክሊተ ነሥአ፡፡
ፍጹም ትምህርት የተማረው ወጥቶ ወርዶ መክሮ አስተምሮ ራሱን አስመስሎ አወጣ።
ወዘ፩ደሰ መክሊተ ነሥአ፤
ባለአንድ ዓላውያን እሳት ስለት አሳይተው ቢያስክዱኝ መናፍቃን ተከራክረው ምላሽ ቢያሳጡኝ ብሎ ፈርቶ ሃይማኖቱን በልቡ የያዘ።
ወይቤሎ አአምረከ ከመ ብእሲ ድሩክ አንተ፡፡
ሕግ ሳትሠራ በአእምሮ ጠባይዕ አውቃችሁ መምህር ሳትሰጥ በስነ ፍጥረት ተመራምራችሁ በሠራችሁ ብለህ የምትፈርድ ጽኑ ጨካኝ መሆንክን አውቃለሁና፡፡ አላውያን እሳት ስለት አሳይተው ቢያስክዱኝ መናፍቃን ተከራክረው ምላሽ ቢያሳጡኝ ብዬ ፈርቼ
ደፈንኩ ውስተ ምድር
በልቡናዬ ይዣዋለሁ።
ጠብለልክዋ ውስተ ሰበንየ ባለው በአእምሮዬ ጠብቄ አለሁ አለ።
ገብር ሐካይ ተአምረኒኑ።
ሕግ ሳልሠራ በአእምሮ ጠባይዕ አውቃችሁ መምህር ሳልሰጥ በስነ ፍጥረት ተመራምራችሁ በሠራችሁ ብዬ የምፈርድ ጽኑ ጨካኝ መሆኔን ታውቃለህን።
ወእምደለወከ።
እንዲህስ ካወቅህ ሹመትክን ልታበረክተኝ ይገባኝ ነበር።
ለልየ እምአስተገበርክዎ።
ወጥቶ ወርዶ ለሚያስተምር በሰጠሁት ነበር።
አንድም ከሁለት ከሦስት ጆሮ ባደረስከው እኔ ተራድቼ ባሰፋፋሁት ነበር፡፡
ንሥኡ እምኔሁ
የእሱን መምህርነት ነሥታችሁ ለዚያ ደርቡለት።
ወለገብርሰ እኩይ አውፅአዎ፡፡
እሱን ግን አውጡት አለ። ከመንግሥተ ሰማይ አይወጣም በመምሕርነት መግባት ቢቀርበት በሕዝባዊነት ይገባል።
(ታሪክ) ይህም በአባ መልክአ ክርስቶስ ታውቋል፡፡ ፍጹም ትምህርት ሳያስተምሩ ቀርተዋል በተባሕትዎ ፈጽመውታል በሚሞቱበት መልአክ ገሰጻቸው ቀለሙ አካል እየገዛ ሲወጣ ታይቷል።
አንድም ባለአምስት ሙሴ ነው አምስቱ መጻሕፍት አሉትና። ባለሁለት ቅዱስ ጴጥሮስ። እንዲህ ግን ስለሆነ ቅዱስ ጴጥሮስ ይበልጣል ሁለት የተባሉ ብሉይና ሐዲስ ናቸውና። ባለአንድ ይሁዳ አውፅእዎ አሁን የተመቸ።
አንድም ባለአምስት ሊቀ ጳጳሳት አንብሮተ እድ ላዕለ ጳጳስ፣ ሰይመ ቀሲስ፣ ሠይመ ዲያቆን፣ ማጥመቅ፣ ማቊረብ። ባለሁለት ቄስ ማጥመቅ፣ ማቊረብ፤ ባለአንድ ዲያቆን ተልእኮ።
አንድም ባለአምስት አሚን፣ ፍሥሐ፣ ምሕረት፣ ትእግሥት ተስፋ፡፡ ባለሁለት አሚን፣ ፍሥሐ፤ ባለአንድ አሚን፡፡
አንድም ባለአምስት ጥምቀት፣ ተአምኖ ኃጢአት፣ ከዊነ ሰማዕት፣ ተባሕትዎ፣ ምንኩስና፤ ባለሁ.ለት ጥምቀት፣ ተአምኖ ኃጢአት፤ ባለአንድ ጥምቀት።
አንድም ባለአምስት ፍጹም ባለጸጋ፤ ባለሁለት እንደ መጠኑ ባለጸጋ፤ ባለአንድ ፍጹም ድኃ።
******
በእንተ ኅልቀተ ዓለም።
፴፩፡ ወአመ ይመጽእ ወልደ እጓለ እመሕያው በስብሐቲሁ ወኵሎሙ መላእክቲሁ ቅዱሳን ምስሌሁ።
******
፴፩፡ የቀደሙ መምሕራን ትመስልን ለምዕመናን መክሊትን ለመምሕራን ወአመ ይመጽእን ለባለጸነች ሰጥተው ይተረጕሙ ነበር። ዛሬ ሁሉም በሁሉ አሉ ብሎ ትመስልን ለምዕመናን ለመምሕራን ለባለጸጎች መክሊትን ለምዕመናን ለመምሕራን ለባለጸጎች። ወአመ ይመጽእን ለምዕመናን ለመምሕራን ለባለጸጎች ሰጥተው ይተረጕማሉ። ወልደ እጓለ እመሕያው መላእክትን አስከትሎ በጌትነት በመጣ ጊዜ።
አሜሃ ይነብር ዲበ መንበረ ስብሐቲሁ።
በሚመሰገን ዙፋን ማለት በጌትነት ይገኛል።
******
፴፪፡ ወይትጋብዑ ኵሎሙ አሕዛብ ቅድሜሁ።
፴፪፡ ሙታን ሁሉ ከሱ ዘንድ ይሰበሰባሉ።
******
ይቆየን፡፡
**********
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
15/10/2011 ዓ.ም
Saturday, June 22, 2019
ወንጌል ቅዱስ ክፍል 123
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment