Monday, June 10, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 116

====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ መደልዋን ፈረሳውያን
ምዕራፍ ፳፫።
                    ******     
፲፯፡ ዓብዳን ወዕውራን።
                    ******     
፲፯፡ እናንት አላዋቆች ሰነፎች።
ዓይ የዓቢ።
ማን ይበልጣል።
ወርቅኑ።
ወርቅ ይበልጣልን
ወሚመ ቤተ መቅደስ ዘይቄድሶ ለወርቅ።
ወይም ወርቁን የሚያከብረው ቤተ መቅደስ ይበልጣልን።
አኮኑ ቤተ መቅደስ ዘይቄድሶ ለወርቅ።
ወርቁን የሚያከብረው ቤተ መቅደስ ይበልጥ የለምን።
                    ******     
፲፰፡ ወዘመሐለ በምሥዋዕ ኢይጌጊ
                    ******     
፲፰፡ በምሥዋዑ ባለ በታቦቱ የማለ ዕዳ አይሆንበትም ትላላችሁ
ወዘሰ መሐለ በጽንሐሕ ዘላዕሌሁ  ይጌጊ ትብሉ።
በመሥዋዕቱ የማለ ግን ዕዳ ይሆንበታል ትላላችሁ።
                    ******     
፲፱፡ ኦ ዓብዳን ወዕውራን፤
                    ******     
፲፱፡ እናንት አላዋቆች ሰነፎች።
መኑ የዓቢ።
ማን ይበልጣል።
ጽንሐሕኑ ወሚመ ምሥዋዕ።
መሥዋዕቱ ይበልጣልን ወይስ ታቦቱ ይበልጣል።
አኮኑ ምሥዋዕ ዘይቄድሶ ለውእቱ ጽንሐሕ ።
መሥዋዕቱን የሚያከብረው ታቦቱ ይበልጥ የለምን። ከታቦትና ከመሥዋዕት ማን ይበልጣል ቢሉ። እስኪለወጥ ታቦት ይበልጣል ከተለወጠ በኋላ ግን ፩ ነው ከደሙ ደሙ አይበልጥም ከታቦትና ከመስቀል ማን ይበልጣል ቢሉ በሀገራቸው ሜሮን ይቀባሉና ሁሉም እኩል ነው። በሀገራችን ግን ሜሮን አይቀባምና ታቦት ይበልጣል መስቀል ያንሳል።
                    ******     
፳፡ ዘኬ መሐለ በምሥዋዕ መሐለ ቦቱ፡፡
                    ******     
፳፡ በታቦቱ የማለ በታቦቱ ማለ
ወበኵሉ ዘይነብር ዲቤሁ።
በታቦቱ ላይ ባለው ሁሉ ማለ
                    ******     
፳፩፡ ወዘሂ መሐለ በቤተ መቅደስ መሐለ ቦቱ።
                    ******     
፳፩፡ በቤተ መቅደስ የማለ በቤተ መቅደስ ማለ።
ወመሐለ በኵሉ ዘይነብር ውስቴቱ።
በቤተ መቅደስ ውሥጥ ባለው ሁሉ ማለ።
                    ******     
፳፪፡ ወዘሂ መሐለ በሰማይ መሐለ መንበሮ ለእግዚአብሔር።
                    ******     
፳፪፡ በሰማይ የማለ በዙፋኑ ማለ።
ወበዘይነብር ዲቤሁ።
በሰማይም ባለው ማለ፡፡
አንድም ዘሂ መሐለ ብለህ መልስ። በትስብእት የማለ በትስብእት ማለ
ወበዘይነብር ዲቤሁ
ተዋሕዶትም ባለው በመለኮት ማለ።
ወዘሂ መሐለ በሰማይ
በመለኮት የማለ በመለኮት ማለ
ወበዘይነብር ዲቤሁ፤
ተዋሕዶትም ባለ በትስብእት ማለ።
                    ******     
፳፫፡ አሌ ለክሙ ጸሐፍት ወፈሪሳውያን መደልዋን እለ ታበውኡ አሥራተ እዴሁ ለአዛብ። ሉቃ ፲፩፥፵፭፡፡
                    ******     
፳፫፡ ያብሽ፤
ወለሲላን፤
የድንብላል
ወለከሙን።
ፌጦ።
አንድም የባሕር ከሙን ከአሥር አንድ የምትሰጡ።
ወኀደግሙ ዘየዓቢ ትእዛዛተ ኦሪት።
በኦሪት የታዘዘውን ደገኛውን ትእዛዝ የምታስቀሩ።
ፍትሐ።
ፍርድን ማለት ዘቄሣር ሀቡ ለቄሣር ያለውን፡፡
ወጽድቀ።
ምጽዋተ አበድር እመሥዋዕት ያለውን።
ወሃይማኖተ።
ወዘእግዚአብሔር ለእግዚአብሔር ያለውን የምታስቀሩ
ዘኒ መፍትው ትግበሩ።
ይህንስ ልታደርጉ ይገባል ማለት ደጋጉን ልትሰጡ ይገባል
ወዝክተኒ ኢትኅድጉ።
ያነንም አትተዉ ማለት ጥቃቅኑንም አታስቀሩ።
                    ******     
፳፬፡ አምርሀተ ዕውራን እለ ጻጹተ ትነጥፉ።
                    ******     
፳፬፡ ጥቃቅኑን ከአሥር አንድ አጥርታችሁ የምትሰጡ። ወይነጥፎሙ ለደቂቀ ሌዊ እንዲል፡፡
ወገመለሰ ትውኅጡ
ታላላቁን ሠውራችሁ የምታስቀሩ ወዮላችሁ፤
                    ******     
፳፭፡ አሌ ለክሙ ጸሕፍት ወፈሪሳውያን መደልዋን አለ ተሐጽብዎ ለጽዋዕ ወለጻሕል እንተ አፍአሁ፤
                    ******     
፳፭፡ ፃሕል ጽዋውን ውጭውን የምታጥቡት ግብዞች ወዮላችሁ
ወአንተ ውሥጡሰ ምሉዕ ሐይደ ወትእግልተ፤
በውሥጥ ግን ቅሚያን የተመላ ነው በአስበ ደነስ በመማለጃ ሰርቀው ቀምተው ያመጡታልና
አንድም በዚህ የመጣውን ይበሉበታልና፤
                    ******     
፳፮፡ ኦ ፈሪሳዊ ዕውር ቅድመ ሕጽቦ ለፅዋዕ ወለፃሕል እንተ ውሥጡ
                    ******     
፳፮፡ አንት አላዋቂ ፈሪሳዊ ፃሕል ጽዋውን አስቀድመህ ውሥጡን እጠበው።
ከመ ይኩን ንጹሐ እንተ አፍአሁኒ።
በአፍአም ንጹሕ ይሆን ዘንድ
አንድም እለ ጻጹተ ትነጥፉ ብለህ መልስ፡፡
ጥቃቅኑን ኃጢአት አጥርታችሁ የምትናገሩ።
ወገመለሰ።
ታላላቁን ሠውራችሁ የምታስቀሩ።
እለ ተሐጽብዎ ፃህል
ጽዋ ሰውነታችሁን በአፍአ ንጹሕ የምታደርጉ።
ወአንተ ውሥጡሰ።
በውሥጥ ግን ኃጢአትን የተመላ ነው
ቅድመ ሕጽቦ፤
አስቀድመህ ፃህል ጽዋ ሰውነትህን በውሥጥ ንጹሕ አድርገው። ከመ ይኩን
በአፍአም ንጹሕ ይሆን ዘንድ፡፡ የሥጋ ንጽሕ ለነፍስ አይሆንም ነፍስ የነፃች እንደሆነ ግን ለሥጋም ይተርፈዋል ቅዱሳን የበቁ እንደሆነ የነፍሳቸው ለሥጋቸው፤ የሥጋቸው ለልብሳቸው ተርፎት በልብሳቸው በመቋሚያቸው በጭራቸው ከመ ፈወስ ይደርሳሉና።
                    ******     
፳፯፡ አሌ ለክሙ ጸሐፍት ወፈሪሳውያን መደልዋን እለ ትመስሉ መቃብረ ግብሱሳነ እለ እምአፍአሆሙ ያስተርእዩ ሠናያነ
                    ******     
፳፯፡ በአፍአ አጊጠው የሚታዩ የተለሰኑ መቃብራትን የምትመስሉ ግብዞች ወዮላችሁ።
ወአንተ ውሥጦሙሰ ምሉዓን አዕፅምተ ወኵሎ ርኵሰ።
ርኵስ ነገር ማለት በውሥጥ ግን እዝኁ ፈሶ ዥማቱ ተበጣጥሶ አጥንቱ ተከስክሶ ሥጋው ተልከስክሶ ለዓይን የሚያስከፋ ለአፍንጫ የሚከረፋ ነገር ያለባቸውን መቃብራት የምትመስሉ።
                    ******     
፳፰፡ ከማሁኬ አንትሙኒ ትጼደቁ ለዓይነ ሰብእ።
                    ******     
፳፰፡ እኒያ በአፍአ አጊጠው እንዲታዩ እናንተም በአፍአ ደጋግ መስላችሁ ትታያላችሁ።
ወእንተ ውሥጥክሙሰ ምሉዓን አንትሙ ዓመፃ ወአድልዎ
በውሥጥ ግን ኃጢአትን የተመላችሁ ናችሁ።
                    ******     
፳፱፡ አሌ ለክሙ ጸሐፍት ወፈሪሳውያን መደልዋን እለ ተሐንጹ መቃብሪሆሙ ለነቢያት ወታሤንዩ ዝኅሮሙ ለጻድቃን።
                    ******     
፳፱፡ ደጋግማ ካልሆኑ የነቢያትን መቃብር ያንጻሉ ይበሉን ብላችሁ የነቢያትን መቃብር የምታንጹ የጻድቃንን መቃብር የምታስጌጡ ግብዞች ወዮላችሁ
                    ******     
፴፡ ወትብሉ ሶበሰ ሀሎነ በመዋዕለ አበዊነ እምኢተሣተፍነ ምስሌሆሙ በክዒወ ደመ ነቢያት።
                    ******     
፴፡ በአባቶቻችን ዘመን ኑረንስ ቢሆን የነቢያትን ደም በማፍሰስ ከሳቸው ጋራ አንድ ባልሆነም ነበር ትላላችሁ።
                    ******     
፴፩፡ ናሁኬ ለሊክሙ ትከውኑ ስምዓ ከመ ደቂቆሙ አንትሙ ለቀተልተ ነቢያት።
                    ******     
፴፩፡ ነቢያትን ለገደሉ ሰዎች ልጆቻቸው እንደሆናችሁ እነሆ ትመሰክራላችሁ።
                    ******     
፴፪፡ አንትሙሂ ፈጽሙ መሥፈርተ አበዊክሙ።
                    ******     
፴፪፡ እናንተም ከአባቶቻችሁ የቀረውን ፈጽሙ። አጸንሆ ለአሞሬዎን እስከ አመ ይትፌጸም ኀጢአቱ እንዲል። እሱስ አይዛቸውም እንዳይተውት ያውቃልና እንዲህ አለ እንጂ። የጌታ ሞት ለነቢያት ሞት ምልዓት እንደሆነ የውሉድም ኃጢአት ለአበው ኃጢአት ምልዓት ይሆናል።
                    ******     
፴፫፡ ኦ ትውልደ አራዊተ ምድር እፎ ትክሉ አምሥጦ እምኵነኔ ገሃነም። ማቴ ፫፥፯።
፴፫፡ እናንት የምድር እባብ ልጆች በገሃነም ከሚመጣው ፍዳ መዳን እንደምን ይቻላችኋል።
                    ******       
  ይቆየን፡፡
**********
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
04/10/2011 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment