Saturday, June 8, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 113

====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ ምሳሌ ንጉሥ ዘገብረ ከብካበ ለወልዱ ።
ምዕራፍ ፳፪።
                    ******     
፲፬፡ እስመ ብዙኃን እሙንቱ ጽውዓን።
                    ******     
፲፬፡ የተጠሩ የቀሩ ብዙ ናቸውና ለምንት ቦእከ ዝየ።
ወኅዳጣን ኅሩያን
የተጠሩ የተመረጡ ጥቂት ናቸውና
እሥሩ እደዊሁ ወእገሪሁ በል።
አንድም ትመስል መንግሥተ ሰማያት ብለህ መልስ፡፡ መንግሥተ ሰማይ አብ ለልጁ ሥጋዌን ያደረገ ንጉሥን ይመስላል ማለት እሱ ነው።
ወፈነወ አግብርቲሁ
ትንቢት የተነገረላቸውን በኦሪት፤ ተስፋ መስቀል የተነገረላቸውን በወንጌል ያሳምኑ ዘንድ አስተምሩ ብሎ ዓበይተ ነቢያትን ሐዋርያትን ላከ፡፡
ወዓበዩ
አናምንም አሉ፡፡
ወዳግመ ፈነወ ካልዓነ አግብርተ
ለዓበይተ ነቢያት ካልዓን የሚሆኑ ደቂቀ ነቢያትን ለሐዋርያት ካልዓን የሚሆኑ አርድእትን ፤ ትንቢት የተነገረላቸውን በኦሪት፡ ተስፋ መስቀል የተነገረላቸውን በወንጌል አሳምኑ ብሎ ላከ።
ናሁ ምሳህየ አስተዳሎኩ፤
ኦሪትን ወንጌልን ሠርቻለሁ፣
ወኩሎ ድልው
በኦሪት በወንጌል ጥቃቅኑ ደጋጉ ተአምራት ይደረጋል።
ንዑ ውስተ ከብካብየ
በኦሪት በወንጌል እመኑ ብላችሁ አስተምሩ ብሎ ላካቸው፡፡
ወእሙንቱሰ ተሐየዩ፤
እሳቸው ግን ቸል ብለው ሂደው
ቦ ዘሖረ ውስተ ገራህቱ፤
እርሻችሁን ተዉ የምትል ሕግ አንሻም ብሎ ወደ እርሻው የሄደ አለ።
ቦ ዘሖረ ውስተ ተግባሩ፣
ንግዳችሁን ተዉ የምትል ሕግ አንሻም ብሎ ወደ ንግዱ የሄደ አለ።
ወቦ ዘሖረ ውስተ ዓፀደ ወይኑ፤
ወይናችሁን ተዉ የምትል ሕግ አንሻም ብሎ ወደ ወይን ጥበቃው የሄደ አለ፡፡ የቀሩት ግን ዓበይተ ነቢያትን ደቂቀ ነቢያትን ሐዋርያትን ፸ አርድአትን ይዘው ገደሏቸው
ወኪያሁኒ ጸዓሉ።
እሱንም እሩቅ ብእሲ አሉት።
ወተምዓ ንጉሥ፤
ጌታ ፈርዶ ነቢያትን በገደሉ ነገሥተ ፋርስን፣ ሐዋርያትን ፸ አርድእትን በገደሉ ነገሥተ ሮምን አስነሥቶ አጠፋቸው
ወሀገሮሙኒ አውአዩ፤
ሀገራቸውንም በእሳት አቃጠሉ።
ወእምዝ ይቤሎሙ ከብካብየሰ ድልው
ሕጉስ ተሠርቷል
ወባሕቱ ኢደለዎሙ ለእለ ንሠርናሆሙ።
ትንቢት ተስፋ መስቀል ላናገርንላቸው አልሆነላቸውም እንጅ።
ሑሩኬ ውስተ መራህብት፤
በ፬ቱ መዓዝን ዙራችሁ አስተምራችሁ ያገኛችሁትን በኦሪት በወንጌል አሳምኑ።
ወወፀፂኦሙ ውስተ ፍናው
በአራቱ መዓዝን ዙረው አስተምረው በኦሪት በወንጌል አሳመኑ።
እኩያነ ወኄራነ።
እኩያን አምነው ተጠምቀው ሥራ ያልሠሩ ናቸው ኄራን አምነው ተጠምቀው ሥራ የሠሩ ናቸው።
ወመልዓ ቤተ በዓል እምእለ ይረፍቁ፣
ከምዕመናን ብዛት የተነሣ መንግሥተ ሰማያት መላች። መምላትስ የለም ብዛታቸውን መናገር ነው እንጅ
ወበዊዖ ንጉሥ
ያመኑትን የተጠመቁትን በተመራመራቸው ጊዜ
ረክበ ብእሴ ዘኢለብሰ ልብሰ መርዓ።
አምኖ ተጠምቆ የክርስቲያን ሥራ ያልሠራ ሰው አገኘ። ወይቤሎ አርክየ ለምንት ቦእከ ዘኢለበስከ ልብሰ መርዓ።
መፍቀሬ ሰብእ ነውና አርክየ ይለዋል ወዳጄ የክርስቲያን ሥራ ላትሠራ ለምን አመንኩ ተጠመቅሁ አልህ አለው።
ወተፈጽመ
ምላሽ አጣ፡፡ ባሕርዬ ደካማ ቢሆን ባይቻለኝ አይለውም ቢሉ ያኑ ከመምህረ  ንሥሐህ ባደረስኸው ይለዋልና፡፡
ወእምዝ አዘዞሙ ንጉሥ ለአግብርቲሁ።
ከዚህ በኋላ መላእክትን ከመንግሥተ ሰማይ በአፍአ ጽኑ ፍዳ ወዳለበት ወደ ገሃነም አውጡት አላቸው።
እስመ ብዙኃን ጽውዓን።
እንዳለፈው በል።
                    ******     
፲፭፡ ወእምዝ ሖሩ ፈሪሳውያን ወተማከሩ ከመ ያስሕትዎ በቃሉ፡፡ ማር ፲፪፥፲፫። ሉቃ ፳፥፳።
                    ******     
፲፭፡ ከዚህ በኋላ ፈሪሳውያን ሂደው በነገር ሊያስቱት መከሩ።
                    ******     
በእንተ ዘከመ ይደሉ ውሂበ ጸባሕት ለቄሣር።
፲፮፡ ወፈነዉ ኀቤሁ አርዳኢሆሙ ምስለ ሰብአ ሄሮድስ።
                    ******     
፲፮፡ ብላቴኖቻቸውን ከሄሮድስ ብላቴኖች ጋራ ላኩ በሀገር የሊቀ መጣኔ ወምበር እንዲኖር ያገር ምዝክር ሹማምት አሉና።
አንድም ብላቴኖቻቸውን የሄሮድስ ብላቴኖች ነን በሉ ብለው ላኩ።
ወይቤልዎ ሊቅ ነአምር ከመ ራትዕ አንተ፡፡
መምህር አዋቂ ቅን እንደሆንህ እናውቃለን።
ወበጽድቅ ትሜሀር ፍኖተ እግዚአብሔር።
በእውነት ወንጌልን እንድታስተምር።
ወኢተሐስብ መነሂ፡፡
ማንንም ማንን እንዳትፈራ።
ወኢየኃዝነከ መኑሂ ይላል ማንም ማን እንዳያሳፍርህ
ወኢታደሉ ለገጸ ሰብእ።
ፊት አይተህ እንዳታደላ እናውቃለን።
                    ******     
፲፯፡ ንግረነኬ ዘይረትዕ።
                    ******     
፲፯፡ የሚገባውን ንገረን።
ይከውነነሁ ነሀብ ጸባሕተ ለንጉሥ
ለቄሣር ግብር መስጠት ይገባናል።
አው አልቦ።
ወይም አይገባንም አሉት ፤
(ሐተታ) ይገባል ቢላቸው የእግዚአብሔር ወገን ነኝ ይላልነ ለእግዚአብሔር የሚገባውን ለቄሣር ስጡ አለን ለማለት፤ አይገባም ቢላቸው ከቄሣር ለማጣላት ነው፣
                    ******     
፲፰፡ ወአእመሮሙ እግዚእ ኢየሱስ እከዮሙ።
                    ******     
፲፰፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተንኮላቸውን አውቆባቸው ሚኖሙ ይላል አብነት እከዮሙ ማለት ነው።
ወይቤሎሙ ምንተ ታሜክሩኒ ኦ መደልዋን።
እናንት ግብዞች ለምን ትፈትኑኛላችሁ።
                    ******     
አርእዩኒ አላደ ዲናሩ።
                    ******     
፲፱፡ ቅርፁን አሳዩኝ አላቸው።
ወአምጽኡ ሎቱ ዲናረ።
አመጡለት።
                    ******     
፳፡ ወይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ ዘመኑ ዝንቱ መልክኡ ወመጽሐፉ።
                    ******     
፳፡ ቅርፁ መጽሐፉ የማነው አላቸው።
                    ******     
ወይቤልዎ ዘቄሣር። ሮሜ ፲፫፥፮።
የቄሣር ነው አሉት።
                    ******     
፳፩፡ ወይቤሎሙ ዘቄሣር ሀቡ ለቄሣር፡፡ ሮሜ ፲፫፥፮።
፳፩፡ የቄሣርን ለቄሣር ስጡ።
                    ******     
  ይቆየን፡፡
**********
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
01/10/2011 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment