====================
የጌታችን
የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ
ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
ዘከመ
ቦአ እግዚእ ኢየሱስ ኢየሩሳሌም።
ምዕራፍ
፳፩።
******
በእንተ
ትውክልት ኀበ እግዚአብሔር።
፳፡
ወርእዮሙ አርዳኢሁ አንከሩ ወይቤሉ እፎ በጊዜሃ የብሰት በለስ። ማር ፲፩፥፳።
******
፳፡
ደቀ መዛሙርቱ አይተው በምትለመልምበት ጊዜ ፈጥና እንደምን ደረቀች ብለው አደነቁ።
******
፳፩፡
ወአውሥአ ወይቤሎሙ አማን እብለክሙ ከመ እመ ብክሙ ሃይማኖት ወኢትናፍቁ አኮ ከመ ዕፀ ባሕቲቶ ዘትገብሩ፡፡ ማቴ ፲፯፥፲፱፡፡
******
፳፩፡
ሃይማኖት ቢኖራችሁ ባትጠራጠሩ እንጨት ብቻ አድርቃችሁ አትቀሩም ብዬ
በእውነት እነግራችኋለሁ።
አላ
ለዝንቱኒ ደብር አመ ትብልዎ ፍልስ ወተመው ውስተ ባሕር ይትገበር ለክሙ።
ይኸንም
ተራራ ከዚህ ተነሥተህ ከባሕር ግባ ብትሉት ይደረግላችኋል እንጂ ታሪክ እንዳለፈው ም ፲፯ ቊ ፩።
******
፳፪፡
ወኵሎ ዘሰአልክሙ በጸሎት እንዘ ትትአመኑ ትነሥኡ። ማቴ ፯፥፯፡፡ ማር ፲፩፥፳፬፡፡ ዮሐ ፲፬፥፲፫፡፡፲፮፥፳፫።
******
፳፪፡
በሃይማኖት ጸንታችሁ የለመናችሁትን ሁሉ ታገኛላችሁ።
******
ዘከመ
ተስአሎሙ እግዚአ ኢየሱስ በእንተ ጥምቀተ ዮሐንስ
፳፫፡
ወበዊዖ ቤተ መቅደስ እንዘ ይሜሕር መጽኡ ኀቤሁ ሊቃነ ካህናት ወመላህቅተ ሕዝብ ወይቤልዎ በመባሕተ መኑ ትገብር ዘንተ። ማር ፲፩፥፳፰፡፡
ሉቃ ፳፥፪፡፡
******
፳፫፡
ከቤተ መቅደስ ገብቶ ሲያስተምር ሊቃነ ካህናት የሕዝቡም አለቆች መጥተው ይህን የምታደርግ ከምድራውያን ነገሥታት ከሌዋውያን ካህናት
ወገን ያይደለህ ገበያውን መፍታትህ ማን አሰናብቶህ ነው።
ወመኑ
ወሀበከ ዘንተ ሥልጣነ
በማን
ሥልጣን ነው አሉት
******
፳፬፡
ወአውሥአ።
******
፳፬፡
መለሰ
ወይቤሎሙ
እሴአለክሙ አነሂ አሐተ ቃለ።
እኔም
አንድ ነገር እጠይቃችኋለሁ አላቸው።
(ሐተታ)
ቢጠይቁት መመለስ ነው እንጂ መጠየቅ ይገባልን ቢሉ ቅድሚያ አለኝ ሲል ነው ምሳሌ በግዕን ጠይቋቸው አልመለሱለትም ነበርና።
አንድም
እንደ ምላሽ ያለ ጥያቄ ነው። እምከመ ነገርክሙኒ አነሂ አየድዓክሙ በአይ ሥልጣን እገብር ዘንተ።
የነገራችሁኝ
እንደሆነ ገበያውን የምፈታ በማንም ሥልጣን እንደሆነ እኔም እነግራችኋለሁ፡፡
******
፳፭፡
ጥምቀቱ ለዮሐንስ እምአይቴ ውእቱ፤
******
፳፭፡
የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነው ማለት ዮሐንስ ማስተማሩ በማን ፈቃድ ነው።
እምሰማይኑ
ወሚመ እምሰብእ
ከሰማይ
ነውን ማለት በእግዚአብሔር ፈቃድ ነውን ወይስ በሰው ፈቃድ ነው አላቸው
ወሐለዩ
በበይናቲሆሙ ወይቤሉ።
እርስ
በእርሳቸው እንዲህ አሉ፤
******
፳፮፡
እመ ንብሎ እምሰማይ ይብለነ በእፎ ዘኢአመንክምዎ፤ ማቴ ፲፬፥፲፭፡፡
******
፳፮፡
በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ብንለው ምነው ያላመናችሁበት ይለናል፡፡
ወእመ
ንብሎ እምሰብእ ንፈርሆሙ ለሕዝብ፤
በሰው
ፈቃድ ነው ብንለው ሕዝቡን እንፈራለን።
እስመ
ከመ ነቢይ ይሬስይዎ ለዮሐንስ በኀቤሆሙ
ዮሐንስን
እንደ አባት ያከብሩታል እንደ መምህር ያፍሩታልና
ወአውሥኡ
መለሱ።
******
፳፯፡
ወይቤልዎ ለእግዚእ ኢየሱስ ኢነአምር ።
******
፳፯፡
አናውቅም አሉት።
አነሂ
ኢያየድዓክሙ በአይ ሥልጣን አገብር ዘንተ።
ገበያውን
በማንም ሥልጣን እንደ ፈታሁት እኔም አልነግራችሁም አላቸው።
******
፳፰፡
ወምንተ ትብሉ።
******
፳፰፡
ምን ትፈርዳላችሁ።
ብእሲ
ቦቱ ፪ቱ ደቂቅ አኃው
ለአንድ
ሰው ሁለት ልጆች አሉት።
ወይቤሎ
ለቀዳማዊ ሑር ወወልድየ ተቀነይ ዮም ውስተ ዓፀደ ወይንየ።
ታላቁን
ልጁን ልጄ ዛሬ ሂደህ ወይን ጠብቅ አለው።
******
፳፱፡
ወአውሥአ ወይቤ ኦሆ እግዚእየ።
******
፳፱፡
እሺ አለው።
ወኢሖረ።
ሳይሄድ
ቀረ።
******
ወለካልዑኒ
ይቤሎ ከማሁ።
******
፴፡
ታናሹን ሂደህ ወይኑን ጠብቅ አለው።
ወይቤ
እንብየ።
አይቻለኝም
አለ።
ወእምድኅረዝ
ነስሐ ወሖረ።
ከዚህ
በኋላ የአባቴን ትእዛዝ አፈረስሁን ብሎ ሄደ።
******
፴፩፡
መኑ እንከ እም፪ሆሙ ዘገብረ ፈቃደ አቡሁ።
******
፴፩፡
እሄዳለሁ ብሎ ከቀረውና አልሄድም ብሎ ከሄደው የአባቱን ፈቃድ የፈጸመ ማነው አላቸው።
ወይቤልዎ
ደኃራዊ።
ታናሹ
ነዋ ታላቁማ ዘበተበት እንጂ አደረገለትን አሉት።
(ሐተታ)
ታላቅ ልጅ የተባሉ ጸሐፍት ፈሪሳውያን። ታናሽ ልጅ የተባሉ ኃጥአን መጸብሐን ናቸው። እሄዳለሁ ብሎ እንደ ቀረ ኦሪትን ተቀብለው
በወንጌል ሳያምኑ ቀርተዋል። አልሄድም ብሎ እንደ ሄደ ኃጥአን መጸብሐንም ሕጉን ካፈረሱ በኋላ በወንጌል አምነዋልና።
ወይቤሎሙ
እግዚእ ኢየሱስ አማን እብለክሙ ከመ መጸብሐን ወዘማውያን ይቀድሙክሙ በዊአ ውስተ መንግሥተ እግዚአብሔር።
ኃጥአን
መጸብሐን ቀድመዋችሁ መንግሥተ ሰማይ ይገባሉ ብዬ እንዲገቡ በእውነት እነግራችኋለሁ። መከተሉስ አለና እንዲህ አለ ቢሉ ቢያምኑ እንዲያገባቸው
ለማጠየቅ፡፡
******
፴፪፡
እስመ መጽአ ኀቤክሙ ዮሐንስ በፍኖተ ጽድቅ ወኢአመንክምዎ።
******
፴፪፡
ዮሐንስ ወንጌልን ቢያስተምር አንቀበልህም ብላችሁታልና
ወመጸብሐንሰ
ወዘማውያን አምንዎ።
ኃጥአን
መጸብሐን ግን አምነውታልና።
ወአንትሙሰ
ርኢክሙሂ ኢነሳሕክሙ።
እናንተ
ግን አይታችሁ አላመናችሁም።
ድኅረ
ለአሚን ቦቱ ።
ኋላ
ለማመን።
አንድም
ድኅረ ከመ ትእመኑ ቦቱ። ኋላ ታምኑበት ዘንድ፡፡
አንድም
ነሳሕክሙ ድኅሬሁ ለአሚን፤ ከማመን ወደኋላ አፈገፈጋችሁ።
አንድም
ድኅረኑ፤ ኋላ ታምኑበታላችሁን። ድኅረሰ ተአምኑ ቦቱ ኋላ ግን ታምኑበታላችሁ እፎኑ ርእይ ታመጽአ አሚነ፤ እንዲል፤ እፎ ኮነ ወልደ
እጓለ እመሕያው ይሉታልና።
******
በእንተ
እኵያን ገባዕት።
፴፫፡
ወይቤሎሙ ካልዕተ ምሳሌ ስምዑ። ኢሳ ፭፥፩፡፡ ኤር ፪፥፳፩፡፡ ማር ፲፪፥፩፡፡ ሉቃ ፳፥፱።
፴፫፡
፪ተኛ ምሳሌ ስሙ፡፡
******
ይቆየን፡፡
**********
መልካሙ
በየነ
ደብረ
ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
26/09/2011
ዓ.ም
No comments:
Post a Comment