Thursday, February 8, 2018

ቅብዓት ባሕለ ትምህርት ወይም ምሥጢር ነውን?



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

አውቀናል በቅተናል የሚሉ የቅብዓት አስተማሪዎች ቅብዓት ምስጢር ነው ባህለ ትምህርት ነው እንጅ ሃይማኖት አይደለም ይላሉ፡፡ ካሳሁን ምናሉ የተባለው የመሠረተ ሐይማኖት መጽሐፍ ጸሐፊ ግን እውነቱን እንዲህ ሲል ተናግሮታል፡፡ “የናንተ የሆነ አሐዳዊ መጽሐፍ የላችሁ ጳጳስ የላችሁ እዚህ በሃይማኖት በኩል አናሳ የምንባለው ግፍና መከራ ዛሬ እንሆ የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ ለመጀመሪያ ጊዜ ይኸው መሠረተ ሐይማኖት መጽሐፍ ታትሞ በገበያ ላይ ዋለ” ይላል፡፡ ስለዚህ ቅብዓት የእምነት ስም እንጅ ባህለ ትምህርት ወይም ምሥጢር አይደለም፡፡ ምስጢር ነው እንዳንል በቤተክርስቲያናችን የምናውቃቸው ምሥጢራት አምስቱ አእማደ ምሥጢራት እና ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን ናቸው፡፡
እነዚህም

Wednesday, January 31, 2018

ገዳም እና ሰንበት ትምህርት ቤት



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
በዚህ ርእስ ላይ የምንመለከተው ሰንበት ትምህርት ቤት እና ገዳማትን በተመለከተ ስላላቸው ዝምድና ይሆናል፡፡ ለጽሑፌም ማስረጃ የማደርገው የቤተክርስቲያናችንን መተዳደሪያ ደንብ ቃለ ዓዋዲ ይሆናል፡፡ የምጠቀመው ቃለ ዓዋዲም አዲሱን ባለፈው ዓመት በ፳፻፱ ዓ.ም ለዐራተኛ ጊዜ የተሻሻለውን ይሆናል፡፡

ቃለዓዋዲው ሰንበት ትምህርት ቤት እንዴት ለምን የት በማን ለማን ሊቋቋም እንደሚገባው የሚናገረውን ያህል ስለገዳማትም እንደዚሁ በማብራራት ይናገራል፡፡ ስለዚህ በመጀመሪያ ስለገዳማት ቃለ ዓዋዲው የሚለውን እንመልከትና በመቀጠልም ስለሰንበት ትምህርት ቤት አደረጃጀት እንመለከታለን፡፡

Sunday, January 28, 2018

ጾመ ነነዌ እና የድንግል ማርያም በዓለ እረፍት



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ጾመ ነነዌ እና የእመቤታችን የቅድስተ ቅዱሳን የድንግል ማርያም በዓለ እረፍት አንድ ላይ ተገጣጥመዋል፡፡ ነነዌ ከጥፋት የዳኑበት ዕለት የአዳም ተስፋ ከሆነችው ከድንግል ማርያም እረፍት ጋር አንድ ላይ ተገናኝተዋል፡፡ ጾመ ነነዌ ከዐቢይ ጾም ፪ ሳምንታት ቀደም ብሎ ለሦስት ቀናት /ከሰኞ እስከ ረቡዕ/ ድረስ የሚጾም ነው፡፡ የነነዌ ሰዎች ከመጣባቸው የእግዚአብሔር ቁጣ የዳኑበት በመሆኑ እኛም ከሚመጣብን ፈተና ሁሉ እንድን ዘንድ፣ ከመከራ ሥጋና ከመከራ ነፍስ እንድንና እናመልጥ ዘንድ አምነን እንጾመዋለን፡፡ ሙሉ ታሪኩን /ትንቢተ ዮናስን በሙሉ ተመልከት/ ይህ ጾም የዐዋጅ ጾም መሆኑን በፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፲፭ ቁጥር ፭፻፷፯ ላይ “…የነነዌ ሰዎች ጾም ፫ ቀን…” ብሎ ይናገራል፡፡ ይህ ጾምም እንደ ዐቢይ ጾም በመጠንቀቅ እንዲጾም ያዝዘናል፡፡


Monday, January 22, 2018

ወልዲያን ሳስብ ደብረ ማርቆስ መጣብኝ



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

በዓለ ጥምቀት በዓለ ቃና ዘገሊላ ጥንተ ነገሩን የለወጠ ክስተት ነው የተፈጸመው፡፡ ወልዲያ ታቦቱን የተሸከሙ ካህናት ራሳቸውን ስተው ወድቀዋል ምእመናን ከታቦቱ ፊት ነፍሳቸውን ሰጥተዋል፡፡ የዚህን ክስተት ሙሉ ኃላፊነት ቤተክርስቲያናችን መውሰድ ይገባታል፡፡ ምክንያቱም የበዓላት ሥነሥርዓት አስከባሪ የቤተክርስቲያኒቱ የሰበካ ጉባዔ እያለ ከሰበካ ጉባዔው ቁጥጥር በላይ የሆነ አንዳች ችግር ሳይፈጠር የመንግሥትን ጸጥታ አስከባሪዎች ወደቦታው መጥራት አስፈላጊ ስላልነበር ነው፡፡ ሕገመንግሥቱ ሃይማኖት እና ፖለቲካ የተለያዩ ናቸው ሃይማኖት በፖለቲካ ፖለቲካም በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም ብሎ በደነገገበት ሁኔታ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ከታቦቱ ፊት እንዲገኙ ማድረጋቸው የቤተክርስቲያኒቱን አባቶች ያስተቻል፡፡

Tuesday, January 16, 2018

ውግዘት በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት




፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ሰስብከት በበርካታ ሃይማኖታዊ እና አስተዳደራዊ በደል የተሞላ ሀገረ ስብከት ነው፡፡ ታዲያ ይህን ሃይማኖታዊ እና አስተዳደራዊ በደል ተመልክቶ ዝም ማለት ለተዋሕዶ ልጆች አላስቻላቸውም ነበርና የሚጠበቅባቸውን የልጅነት ድርሻ በመወጣት ላይ ይገኛሉ፡፡ በርካታዎች ታስረዋል ተደብድበዋል ተንገላተዋል ተጉላልተዋል ተርበዋል ተጠምተዋል፡፡ ይህ ሁሉ ግን አያሳስባቸውም ምክንያቱም ትግላቸው ዘላለማዊ ርስትን ስለሚወርሱባት ሃይማኖታቸው ሲሉ ነውና፡፡ ህጋዊውን መንገድ ተከትለው ተስፋ ባለመቁረጥ በልበ ሰፊነት ከሰባት ጊዜ በላይ በግል ወጫቸው አዲስ አበባ ድረስ በመሄድ ለቅዱስ ሲኖዶስ አቤት ብለዋል፡፡ ሆኖም ግን አጥጋቢ መልስ ማግኘት አልተቻለም፡፡

አጣሪ ኮሚቴ ተብሎ በብጹእ ሥራ አስኪያጁ ተልከው የነበሩት ሦስቱ ልዑካንም የእግዚአብሔርን ነገር ትተው ራሳቸውን በይሁዳ መስመር አገኙት፡፡ ይሁዳ እግዚአብሔርን ለአይሁዳውያን ጠቁሞ ስሞ አሳልፎ ይሰጠው እንደሆነ እንጅ ሐዋርያትን መስሎ ከጎኑ አይቆምም፡፡ የእነዚህ የልዑካኑ ጉዳይም እንዲሁ ሆኖ ነው የተገኘው፡፡

Wednesday, January 3, 2018

ምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ብጹእ አቡነ ዘካርያስን እረፍት ነስቷቸዋል



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ብጹእ አቡነ ዘካርያስን የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ወቅታዊ ሁኔታ ከማንም በላይ አሳስቧቸወል፡፡ ብጹእነታቸው አንድ ሊቀ ጳጳስ በሌላው ሀገረ ስብከት ጣልቃ አይገባም የሚለውን ህግ ሳያውቁ እንዳልሆነ ለቅዱስ ፓትርያርኩ በጻፉት ደብዳቤ ላይ ገልጠዋል፡፡ ብጹእነታቸው አቡነ ዘካርያስ የምሥራቅ ጎጃም ጉዳይ እጅጉን ያሳሰባቸው በጎጃም ተወልደው ያደጉ በዚያው የተማሩ ያስተማሩ በሊቀ ጳጳስነትም ደረጃ በቅዱስ ሲኖዶስ ተመድበው ብዙ ዲያቆናትን እና ካህናትን ክህነት የሰጡ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን ጉዳዩ የሃይማኖት ጉዳይ ስለሆነ ሃይማኖትን ደግሞ አድማስ እንደማይገድበው በመግለጽ ጭምር ነው ለቅዱስ ፓትርያርኩ ደብዳቤ የጻፉ፡፡






Sunday, December 31, 2017

ደብረ ምሕረት የረቦ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
የረቦ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት በደጀን ወረዳ ቤተክህነት ሥር የሚገኝ ቤተክርስቲያን ነው፡፡ ቤተክርስቲያኑ ከደጀን ከተማ በምሥራቅ አቅጣጫ ሃያ ሰባት ኪሎሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ወደቦታው ለመሄድ ለሚፈልጉ ሰዎች ከደጀን ከተማ ተነሥተው ጉባያ በሚለው መኪና ገብተው ቦታውን ያለምንም ችግር ማግኘት ይችላሉ፡፡ እንደአሁኑ መኪና ሳይኖር ግን ከሦስት ሰዓት እልህ አስጨራሽ የእግር ጉዞ በኋላ ነበር ቦታው የሚገኘው፡፡ ቦታው ጥንታዊ ቦታ መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ሆኖም ግን መዛግብትን ማገላበጥ አባቶችንም መጠየቅ የሚያስፈልገው ጉዳይ ስለሆነ የተመሰረተበትን ቀን እንዴት እንደተመሠረተ ሙሉ ታሪኩን መናገር አልችልም፡፡ እኔም በቦታው ተወልጀ ያደግሁ መሆኑን እንጅ ጥንታዊነቱን ጠይቄም ሆነ መዛግብትን አገላብጨ አላውቅም፡፡ ሆኖም ግን መዛግብትን ማገላበጥ አባቶችን መጠየቅ እንደሚኖርብኝ አውቃለሁ፡፡ ከቤተክርስቲያኑ በታች የሚገኘው ዋሻ ጥንታዊ የቤተክርስቲያኑ መገኛ እንደነበር ይነገራል ሆኖም ግን በመዛግብት እና በአባቶች ማረጋገጫነት መታገዝ ስለሚኖርበት ወደፊት እገልጥላችኋለሁ፡፡

“ቅባት መጠመቅ አለበት” ሊቀ ሊቃውንት ሰሎሞን ዳዊት



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
በመጀመሪያ እንኳን ለመልአኩ ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም በፍቅር በአንድነት አደረሳችሁ እያልሁ ከዛሬ ሁለት  ዓመታት በፊት የጻፍኋትን ግጥም እነሆ እላለሁ፡፡ ከዚህ በፊት ያነበበው ሰው ይህንን አልፎ ወደዋናው ርእሰ ጉዳይ መሄድ ይችላል፡፡ መብቱ በሕግ የተፈቀደ ነው ብያለሁ!
                         *********************************
በዱራ ሜዳ ላይ ናቡከደነፆር አምላኩን አቆመው፣
በስድሳ ክንድ ቁመት በስድት ክንድ ወርድ ከወርቅ አቅልጦ ሠራው፡፡
አምላኩን ሊያስመርቅ ያልተመረቀ አምላክ መርቁልኝ ብሎ፣
መኳንንት፣ ሹማምንት፣ አዛዥ፣ አዛውንቱን፣ መጋቢውን ሁሉ ጠራቸው በቶሎ፡፡
የንጉሥ ትዕዛዝ ነው ከታች ባትን ከላይም አንገትን ሊያስቆርጥ የሚችል፣
ታዲያ ማን ይቀራል? ማንስ ይንቀዋል? ማን ያቃልለዋል? READ MORE!
         ****************************************

“ለካስ ጊዜው ኖሯል”



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ድጋሜ እንድለጥፈው ጊዜው አስገደደኝ! ይህንን ጽሑፍ ከዚህ በፊት በራሴ ገጽ ላይ ለጥፌው ነበር፡፡ የዚህን ልጥፍም እዚህ ላይ ጠቅ በማድረግ ማግኘት ይቻላል፡፡ http://melkamubeyene.blogspot.com/2015/05/blog-post_98.html ዛሬም መጠነኛ ማሻሻል በማድረግ እነሆ ብያለሁ!
                                 ******************
አንድ ስሙን ለጊዜው የማላስታውሰው ሰው እንዲህ የሚል አባባል አለው “ALL COLOURS WILL AGREE IN THE DARK” ይህን አባባሉን ሳነበው ትልቅ መልእክት እንዳለው ልቤ ተረዳ፡፡ የተረዳው ልቤም መላ አካላቴን አነቃቃው እና አጆቼን ወደ መጻፊያ ሰሌዳው ወሰዳቸው፡፡ በዚያም የሚንኳኳውን የመጻፊያ ሰሌዳ በእኛው በአገራችን በለመድነው ቋንቋ እንዲጽፍ የመጻፊያ ስልቱን ቃኘሁት (ቀየርሁት)፡፡ ከዚያም ይህንን ቁም ነገር በኢትዮጵያዊ ለዛው ተናዘዝሁ፡፡ እነሆ ኑዛዜየን!
                                *********************

Sunday, December 10, 2017

መሠረተ ሐይማኖት ወይስ መሠረተ ክህደት? ክፍል ፲፮--ተፈጸመ



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ዛሬ ከገጽ ፵፯ ጀምረን  እስከ መጨረሻ ገጽ ድረስ ያሉ ስህተቶችን በማስረጃ እንመለከታለን፡፡ በፎቶ ከስር ስለማያይዝላችሁ ሙሉውን ማንበብ ትችላላችሁ እኔ ግን ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ብቻ ነው ትኩረት የማደርገው፡፡
ይህ የመጨረሻየ ክፍል ስለሆነ እስከ ረቡዕ ድረስ ቀስ ብላችሁ ተረጋግታችሁ እንድታነቡት ሰፋ አድርጌ ነው የጻፍሁላችሁ፡፡ ረዘመ እንዳትሉኝ ከወዲሁ እጠይቃለሁ፡፡
********************************

Friday, December 8, 2017

መሠረተ ሐይማኖት ወይስ መሠረተ ክህደት? ክፍል ፲፭



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ዛሬ ከገጽ ፵፪ ጀምረን  ያሉ ስህተቶችን በማስረጃ እንመለከታለን፡፡ በፎቶ ከስር ስለማያይዝላችሁ ሙሉውን ማንበብ ትችላላችሁ እኔ ግን ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ብቻ ነው ትኩረት የማደርገው፡፡
ካሳሁን ምናሉ በዚህ ገጽ ላይ ምእራፍ ዘጠኝን ይጀምራል፡፡ ምእራፉም ስለጌታችን የልደት በዓል ነው የሚናገረው፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ከዚህ በፊት ጥቂት ነገሮችን የተመለከትን ቢሆንም እዚህ ክፍል ላይም በጥልቀት እንመለከታለን፡፡
****************************
ሊቃውንቱ በዚህ ጉዳይ በጥሩ ሁኔታ ያብራሩበት የቪዲዮ ትምህርት አለ ይህንን ሊንክ ጠቅ አድርጉና ተከታተሉት፡፡ ሙሉውን ተከታተሉት እንዳያመልጣችሁ ለሚጠይቋችሁ መልስ ለመስጠት የተዘጋጃችሁ ሁኑ ተብለናል ይህ ደግሞ አንዱ ዝግጅታችን ነው፡፡ https://www.youtube.com/watch?v=sbriV-ou5NU&feature=youtu.be
***************************

Thursday, December 7, 2017

መሠረተ ሐይማኖት ወይስ መሠረተ ክህደት? ክፍል ፲፬




   ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

የቅባቶቹ መጽሐፍ መሠረተ ሐይማኖት
ዛሬ ከገጽ ፴፪ ጀምረን  ያሉ ስህተቶችን በማስረጃ እንመለከታለን፡፡ በፎቶ ከስር ስለማያይዝላችሁ ሙሉውን ማንበብ ትችላላችሁ እኔ ግን ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ብቻ ነው ትኩረት የማደርገው፡፡
#ረዝሟል_አሳጥረው_እንዳትሉኝ_አደራ_አልቻልሁም፡፡ ምስጢር ከምሥጢር ጋር ሲያያዝ ነውና የሚያምረው ቆራርጨ ማቅረብ አልቻልሁም፡፡ ከዚህ በፊት ቆራርጨ ለወልደ አብ መጽሐፍ ክህደቶች መልስ ስጽፍ አቅርቤው ነበር ሆኖም ግን ምሥጢሩ ከምሥጢሩ ጋር አልተያያዘልንም ነበር፡፡ ዛሬ ግን ሁሉንም በአንድ ማቅረብ ችያለሁ፡፡ “የበረታ ቆሞ የደከመ ተቀምጦ” ብላለች ተአምረ ማርያም እና የበረታ ያንብብ የደከመ #SHARE ያድርግና ጊዜ ሲኖረው ያንብበው፡፡ አንድ ጊዜ ማንበብ ሊደክም ይችላልና፡፡

Monday, December 4, 2017

መሠረተ ሐይማኖት ወይስ መሠረተ ክህደት? ክፍል ፲፫



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ዛሬ ከገጽ ፳፰ ጀምረን  ያሉ ስህተቶችን በማስረጃ እንመለከታለን፡፡ በፎቶ ከስር ስለማያይዝላችሁ ሙሉውን ማንበብ ትችላላችሁ እኔ ግን ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ብቻ ነው ትኩረት የማደርገው፡፡
ከዚህ በተጨማሪም መድሎተ አሚን ላይ በቅባተ መንፈስ ቅዱስ ከበረ ብለዋል የሚለውን ውሸት መድሎተ አሚንን በፎቶ አስቀምጫለሁ፡፡ ፍትሐ ነገሥቱንም እንዲሁ ለማጣቀሻነት እንድትመለከቱት በፎቶ አያይዠላችኋለሁ፡፡

Friday, December 1, 2017

መሠረተ ሐይማኖት ወይስ መሠረተ ክህደት? ክፍል ፲፪



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ዛሬ ከገጽ ፳፯ ጀምረን  ያሉ ስህተቶችን በማስረጃ እንመለከታለን፡፡ በፎቶ ከስር ስለማያይዝላችሁ ሙሉውን ማንበብ ትችላላችሁ እኔ ግን ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ብቻ ነው ትኩረት የማደርገው፡፡
ቅዳሜ እና እሁድን ቀስ ብላችሁ አንብቡት በዛ ብላችሁ እንዳትሰለቹ!
ካሳሁን ምናሉ ገጽ ፳፯ ላይ ምዕራፍ ሰባት ብሎ በሚጀምረው የገጹ መጨረሻ ላይ እንዲህ ይላል “መንፈስ ቅዱስን ትቶ ወልድን ብቻ በተዋሕዶ ከበረ ማት እንደንስጥሮስ መንፈስ ቅዱስ ህፀፅ እንደማለት ይቆጠራል ምክንያቱም የባሕርይ አባቱን አብን የባሕርይ ሕይወቱን መንፈስ ቅዱስን ትቶ ወልድን በተዋሕዶ ከበረ ማለት ስተት ነው፡፡ ወልድ በማኅጸነ ማርያም ሲፀነስ በመንፈስ ቅዱስ ሲወለድም በመንፈስ ቅዱስ ቀስ በቀስ ሲያድግም በመንፈስ ቅዱስ ነውና ወልደ አብ ወልደ ማርያም በመንፈስ ቅዱስ ከበረ ማለት ይገባል” ይላል፡፡ እስካሁን ድረስ ካሳሁን ምናሉ ከመምህራን እግር ስር ቁጭ ብሎ የተማረ ሰው ይመስለኝ ነበር ለካ የኔቢጤ ነው በተባራሪ የሰማውን ብቻ ነው የጻፈው፡፡ በፊደል ግድፈቱም ስንወቅሰው የነበረ በስህተት ነው ለካ፡፡ ምን ይፈረድበታል ነገሩን አላወቀውማ አያያዙ አልገባውማ፡፡ 

Tuesday, November 28, 2017

መሠረተ ሐይማኖት ወይስ መሠረተ ክህደት? ክፍል ፲፩



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ዛሬ ከገጽ ፳፭ ጀምረን  ያሉ ስህተቶችን በማስረጃ እንመለከታለን፡፡ በፎቶ ከስር ስለማያይዝላችሁ ሙሉውን ማንበብ ትችላላችሁ እኔ ግን ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ብቻ ነው ትኩረት የማደርገው፡፡


ለእመቤታችን ዓመታዊ በዓል እንኳን አደረሳችሁ!




ካሳሁን ምናሉ በዚህ በክህደት መጽሐፉ ገጽ ፳፭ እና ፳፮ ላይ የጻፈውን ነገር ሁላችሁ ተመልከቱት፡፡ አንብቡት እኔ ከዚህ በፊት “ወልደ አብ” ላይ ይህንኑ ራሱን መልስ ስለሰጠሁበት ባለፈው የሰጠሁትን መልስ ለዚህ በሚመጥን መልኩ አቀርብላችኋለሁ፡፡ 

“በቅባት ካህን የተጠመቀ ልጅነት የለውም” ብጹእ አቡነ ዘካርያስ




                       ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

ይህን ሸር ያላደረገ ሰው #የማርያም_ጠላት ታዲያ ምን ሸር ልታደርጉ ነው!
የምሥራች ነው ደግሞ እኮ!
****************
ብጹእነታቸው አቡነ ዘካርያስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን ምሥራቅ፣ ደቡብ ምሥራቅና መካከለኛው አሜሪካ ኒዮርክ ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ስላለው ሃይማኖታዊ እና አስተዳደራዊ በደል ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው እየሠሩ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ብጹእ አቡነ ዘካርያስ ከአቡነ ማርቆስ በፊት ሊቀ ጳጳስ ከነበሩት ብጹእ አቡነ ጴጥሮስ በፊት የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ነበሩ፡፡ ብጹእነታቸው አቡነ ዘካርያስ ምሥራቅ ጎጃምን እያስተዳደሩ በነበሩበት ጊዜ ቅባቶች ላይ ቆራጥ አቋም የነበራቸው እንደነበሩ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን በዚያን ወቅት ቅባቶች በጾም ጊዜያት ላይ ብቻ ክርክር ያነሡ ስለነበር ልዩነታቸው እንደ አሁኑ ጎልቶ አለመታየቱ ብጹእነታቸው በሰፊው አልሄዱበትም ነበር፡፡ እንዲያውም በተፈጠረው ወቅታዊ ችግር ቅባት እና ተዋሕዶ በአንድነት ሲቀድሱ ሁሉ ዝም ይሉ እንደነበር እና በዚህም የተነሣ ከዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም ጋር እና ከምእመናን ጋር ቅሬታ ውስጥ ገብተው እንደነበር ለሁሉም የታወቀ ነው፡፡ ምክንያቱ ባልተገለጠ መንገድ ከሀገረ ስብከቱ ገንዘብ ሲጠፋባቸው ሀገረ ስብከቱን ለቀው እንደሄዱም ይታወቃል፡፡ ብጹእነታቸው ግን የገንዘቡን መጥፋት አምነው ጠፍቶብኛል ያሉትን ገንዘብም ከልጆቻቸው አሰባስበው ለሀገረ ስብከቱ እንደሚመልሱ በወቅቱ ለአሜሪካን ድምጽ አሳውቀው ነበር፡፡ በቃላቸውም መሠረት አምና ፳፻፱ ዓ.ም አንድ ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ብር ለሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ለብጹእ አቡነ ማርቆስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በተገኙበት አስረክበዋል፡፡ ሆኖም ግን ይህ ገንዘብ ለሀገረ ስብከቱ መግባት አለመግባቱን የሚያውቅ ምእመን የለም፡፡ ገንዘቡ ምን ሥራ ላይ እንደዋለም ከሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የተባለ ነገር የለም፡፡



Monday, November 27, 2017

”በሃይማኖታችን አንደራደርም” ደጀን ደብረ አሚን



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ደጀን ከተማ በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሥር የምትገኝ አነስተኛ ከተማ ናት፡፡ ደጀን የከተማዋም የወረዳዋም መጠሪያ ስም ነው፡፡ ጎጃምን ማየት የሚፈልግ ሁሉ የዓባይን ድልድይ ተሻግሮ በመጀመሪያ የሚያገኛት ደጀንን ነው፡፡ ዋና ዓላማየ ደጀንን ማስተዋወቅ አይደለም፡፡ ደጀን ደብረ አሚን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ላይ ትናንትና እሁድ ኅዳር ፲፯/ ፳፻፲ ዓ.ም ፀረ ተሐድሶ ጉባዔ ተዘጋጅቶ ነበር፡፡ በዚህ ለሁለተኛ ጊዜ በተዘጋጀው ጉባዔ ላይ የደብሩ አስተዳዳሪ የደብሩ አገልጋይ ካህናት ዲያቆናት እና በርካታ ህዝበ ክርስቲያን ተገኝቶ ነበር፡፡ በምሥራቅ ጎጃም ሐገረ ስብከት እንዲህ ያለ ጉባዔ ሲዘጋጅ ደጀን የመጀመሪያዋ መሆኗ ነው፡፡ ይህ ጉባዔ ያስፈለገበት ምክንያት፡-

Sunday, November 26, 2017

ጾመ ነቢያት መቸ ይገባል?



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
“መሠረተ ሐይማኖት ወይስ መሠረተ ክህደት? የሚለው ተከታታይ ጽሑፍ ይቀጥላል፡፡ ለዛሬ ስለጾመ ነቢያት ትንሽ እንነጋር እስኪ፡፡ እዚህ ላይም በቅባች እና በተዋሕዶ ልጆች መካከል ልዩነት አለ፡፡ ቅባቶች እንብላ ተዋሕዶዎች እንጹም የሚል ክርክር አለ እርሱን በጥቂቱ እንመልከት፡፡

Thursday, November 23, 2017

መሠረተ ሐይማኖት ወይስ መሠረተ ክህደት? ክፍል ፲



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ዛሬ ከገጽ ፳፩ ጀምረን  ያሉ ስህተቶችን በማስረጃ እንመለከታለን፡፡ በፎቶ ከስር ስለማያይዝላችሁ ሙሉውን ማንበብ ትችላላችሁ እኔ ግን ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ብቻ ነው ትኩረት የማደርገው፡፡
ካሳሁን ምናሉ “መሠረተ ሐይማኖት” በተሰኘው የክህደት መጽሐፉ  ገጽ ፳፩ ላይ “ቃልን በስጋ ርስት ትሑት ነዳይ ካላልነው፡፡ ማወራረስ አይቀርብንም ተዋሕዶ አይጎላብንም ቢሉ፡፡ አይጎላብንም በቅርብዓት እንመላዋለን፡፡ በቅብአት እንዴት እንመላዋለን ቢሉ፡፡ ይህ ስጋ ሲፈጠር ንዴት ትሕትና ያድርበት ነበር፡፡ ይህ አንዴት ትህትና ያድርበት የነበረ ስጋ ከቃል ሲዋሐድ ጊዜ ሳይሻ መንፈስ ቅዱስ ቢያድርበት ንዴት ትሕትና ቀረለት” ይላል፡፡ በዚህ ጉዳይ ብዙ ጊዜ ስለተነጋገርን መድገሙ አስፈላጊ መስሎ አልታየኝም፡፡ በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ከበረ እንዳንልማ የተወገዘ ሃይማኖት ነው  “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በእርሱ አጋዥነት ድንቅ ተአምራትን ያደርግ ዘንድ በመንፈስ ቅዱስ ከበረ የሚለው፤ ርኩሳን አጋንንትን በማውጣት ጊዜም ኃይልን ተአምራትን ከመንፈስ ቅዱስ ይቀበላል፤ በሰውም የአምላክነትን ሥራ ይሠራል የሚለው፤ መንፈስ ቅዱስ የባሕርዩ ነው፤ የአምላክነትንም ሥራ እርሱ ራሱ ይሠራል የማይል ቢኖር ውጉዝ ይሁን” ሃይማኖተ አበው ዘቄርሎስ ፸፫÷፵፱ ስለዚህ በመንፈስ ቅዱስ ከበረ ማለት ክህደት ነው፡፡


Wednesday, November 22, 2017

መሠረተ ሐይማኖት ወይስ መሠረተ ክህደት? ክፍል ፱



፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ዛሬ ከገጽ ፳ ጀምረን  ያሉ ስህተቶችን በማስረጃ እንመለከታለን፡፡ በፎቶ ከስር ስለማያይዝላችሁ ሙሉውን ማንበብ ትችላላችሁ እኔ ግን ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ብቻ ነው ትኩረት የማደርገው፡፡
ካሳሁን ምናሉ “መሠረተ ሐይማኖት” በተሰኘ የክህደት መጽሐፉ ገጽ ፳ ላይ እንዲህ ይላል “ስጋ በርስቱ ከበረ ብዕለ እንዳይባል በተዋሕዶ ከበረ ማለት ነው፡፡ በተዋሕዶ ከበረ ማለትም በህድረት ከበረ  ማለት ነውና እንደ ንስጥሮስ ሁለት አካል ማድረግ ነው ስለዚህ ስጋ ከቃል ከተዋሐደ በኋላ ክቡር ባዕል መባል ይገባዋል ዕንጅ፡፡ ክብረ ብዕለ መባል አይገባውም፡፡ በተዋሕዶ ከበረ ማለት እንዴት ነው ቢሉ፡፡ ሁለት አካል ማድረግ ነውና ከንስጥሮስ ባህል ይገባል ማለት እንዴትና፡፡ ተዋሕዶ አንድነትን ይፀናል እንጅ፡፡ ሁለትነትን ያመጣልን እንጅ ቢሉ፡፡ በተዋሕዶ ከበረ ወልድ ቅብዕ ማለት ስም ሰጥቶ ግብር መንሳት ነው” ይላል፡፡