====================
ስምንተኛ ጉባኤ
አልፈህ ግፃዌ ሥርዓት በል
፤ ታሪክ የመጻሕፍትን መልክ ከዚህ ይናገራሉ ፤ ታችኛው ግልየት ኅዳግ ፤ ላይኛው ገጽ እርእስት ግልየት ኅዳግ፤ ዳርና ዳሩ ገጽ
ምስማክ ግልየት ኅዳግ መካከሉ ዓምድ ሐውልት ግልየት ኅዳግ ቀለም የወደቀበት መስመር ወስፌ የሄደበት ሲራክ አራት ጥቁር አምስት
ቀይ ነቁጥ ሁለት ጥቁር ሦስት ቀይ ሰረዝ ሁለት ጥቁር ነጥብ ይባላል ። ግጻዊ ሥርዓት በእንተ ኅብረተ ቃላት የ፬ቱ ወንጌላት ።
የአራቱ ወንጌላውያንን ነገር
ለማስተባበር የአራቱ ወንጌላውያን የተገለጸ ሥርዓት ይህ ነው ያጌጹ ወደለዎ ለዮሐንስ ግጻዌ እንዲል ።
እንዘ ይተሉ ረድኤተ እግዚእነ
ኢየሱስ ክርስቶስ ክልኤቱ ባሕቲቶሙ ጸሐፉ እንከ ወንጌለ እምሐዋርያት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እየቃኛቸው እያገዛቸው ከሐዋርያት
ሁለቱ ብቻ ወንጌልን ጻፉ ።
ወክልኤቱ እመትሎሆሙ
ሁለቱ ሐዋርያትን ተከትለው
ከሚያስተምሩ ከሰባ አርድእት ወገን ናቸው ።
አሐዱ ዘጳውሎስ ፤ አንዱ
የጳውሎስ ደቀመዝሙር ሉቃስ ነው ፤
ወአሐዱ ዘጴጥሮስ ረድአ ዚአሁ
።
አንዱ የጴጥሮስ ደቀመዝሙር
ማርቆስ ነው ።
ምስለ ማቴዎስ ወዮሐንስ ጸሐፉ
እንከ ወንጌላተ እንዘ ኢየኃሥሥ ክብረ ለርእሶሙ ።
ለራሳቸው ክብር ሳይሹ እንበላበት
እንጠጣበት እንሾምበታለን እንሸለምበታለን ሳይሉ ከማቴዎስ ከዮሐንስ ጋራ ጻፉ እነዚያ እንደጸፉ ጸፉ ።
አላ በከመ ይትፈቀድ፤
እንደሚወደድ አድርገው ንባቡን
አጉልተው ምሥጢሩን አርቅቀው ጻፉ ሐተታ የፈላስፎች መጽሐፍ የሆነ እንደሆነ ንባቡ ረቂቅ ጨጨጨ ጀጀጀ ሸሸሸ እያሉ ምሥጢር የለውም
።
ወንጌልሰ ሶበ ተጽሕፈ አሐዱሄ
እምአከለ ፤
ወንጌል ካራቱ አንዱ ቢጻፍ
በበቃ ነበር ።
ወየአክልሂ ።
እስከ ዕለተ ምጽአት ለልጅ
ልጅ ይበቃ ነበር
ዳዕሙ አርባዕቲሆሙ ኃብሩ
እለ ይጽሕፉ ፤
ወንጌልን የጻፉ አራቱ አንድ
ሆኑ እንጂ ፤ወኮኑ እንዘ ኢይትረአዩ ፤
ሳይተያዩ ጸፉ።
ወአኮ በ፩ዱ መካን ሀልዎሙ
ዘጸሐፉ፤
ባንድ ቦታ ሁነው አልጻፉም
፤
ወኢሂ ተማከሩ ለአኅብሮ ቃላት
።
ነገሩን ለማስተባበር አልተማከሩም
ይህ እንዲህ ይሁን ይህን እንዲህ እንበለው ብለው ፤
ወአልቦ ኃሠሣ ማእክሎሙ ።
በሳቸው ዘንድ መጠያየቅ የለም
አልተጠያየቁም ይህስ እንደምን ይሁን ይህንስ እንደምን እንበለው ብለው ዳዕሙ ከመ ዘአሐዱ አፍ ነበቡ ኩሎሙ ።
እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ
አንድ ቃል ተናጋሪ ሁነው አንድ ነገር ተናገሩ እንጂ።
እሩየ ስብሐተ ወርእየተ ዘበአማን
ዝንቱ ኮነ ፤
ተለያይተው የጻፉት ይህ ተያይተው
እንደጻፉት ሁኖ ተገኘ ።
ወሶበ ኢኮነ ከመዝ ጸላኢ
ወኢመኑሂ እምኢአምነ
ተለያይተው ጽፈዋት አንድ
ሁና ባትገኝስ ማንም ማን መናፈቅ ወንጌል ደግ ሕግ እንደሆነች ባላመነም ነበር።
ወአኮ ድንቀተ ዘኮነ ዘመጠነዝ
አኅብሮ ቃላት ፤
ድድቀተ ድድቀተ ይላል ይህን
ያህል የነገር ማስተባበር የተደረገ በሐሰት በምትሐት አይደለም ።
ወእምኩሉ ሐሜት ወትሕዝብተ
ጸላዒ አድኃነት ።
አራት ወገን ሁና ተጽፋ አንድ
ሁና በመገኘቷ ከጠላት ጥርጥር ከጠላት ነቀፋ ራሷን አዳነች ሐተታ ወንጌል ተራ ሕግ ናት ብሎ የጠረጠራት የነቀፋት የለምና፡፡
ወፈድፈደ ያከብሮሙ ሰብእ
በእንተ ዘጸሐፉ በብሩኅ ይልቁን ምንባቡን አጉልተው ምሥጢሩን አርቅቀው ስለጸፉ ሰው ሁሉ ፈጽሞ ያከብራቸዋል ።
ወጽሕፈቱሰ ከመዝ ውእቱ ፤
ጽሕፈቱም ይህ ነው።
እስመ አምላክ ኮነ ሰብእ
፤
አምላክ ሰው ሆነ ብለው ነው
።
ወበእንተ ትእምርታት ዘኮነ
፤
ድውይ ፈወሰ ብለው ነው ።
ወመንክራተ ዘገብረ ፤
ጋኔን አወጣ ሙት አነሣ ብለው
ነው።
ወበእንተ ዘተሰቅለ ወበእንተ
ዘተቀብረ ።
ተሰቀለ ተቀበረ ።
ወበእንተ ትንሣኤሁ ወበእንተ
ዕርገቱ ።
ተነሣ ዓረገ።
ወበእንተ ምጽአቱ ።
ዳግመኛ ይመጣል ብለው ነው
።
እስመ ሀለዎ ይኰንን ሕያዋነ
ወሙታነ ፤
ሕያዋንን ሙታንን ይገዛ ዘንድ
በሕያዋን በሙታን ይፈርድ ዘንድ አለውና ። ወከመ ዘወሀበ መድኃኒተ በምጽዋት ፤
አብ ቢሉ ልጁን እንደ ምጽዋት
አደርጎ ሰጥቷል ወልድ ቢሉ አካሉን እንደ ምጽዋት አደርጎ ሰጥቷል አንድም ሥጋውን ደሙን እንደ ምጽዋት አድርጎ ሰጠ ብለው ነው።
ወዘከመ ይቤ ኢያምጻእኩ ካልአ
ሥርዓተ ዘይትቃወማ ለብሊት ሕግ ።
አስቀድማ የተሠራች ኦሪትን
የምታሳልፍ ሕግን አልሰራሁም አለ ብለው ነው ። ኢይበልክሙ ዘመጻእኩ አሰዐሮሙ ለኦሪት ወለነቢያት አለ ብለው ነው።
እስመ ወልድ ፍቁር ባሕቲቱ
ብሑተ ልደተ ዘከመዝ ፤
በልደት ሥሉጥ የሚሆን ፍቁር
ወልድ ብቻ ዛሬ ወንጌልን እንደሠራ ቀድሞም ኦሪትን የሠራ እሱ ነውና፡፡ በእንተዝ ያለው ማንሻ ፤ አንድም በልደት ሥሉጥ የሚሆን
ፍቁር ወልድ ብቻ ቀድሞ ኦሪትን እንደ ሠራ ዛሬም ወንጌልን የሚሠራ እሱ ነውና።
ወበእንተዝ ኮነ ዘመጠነዝ
አኅብሮ ቃላት፤
ስለዚህ ይህን ያህል የነገር
ማስተባበር ተደረገ ።
ሉቃስ ዝልፈተ አርአየ ፤
ሉቃስ አሌ ለክሙ አብዕልት
እስመ ሠለጥከሙ ትፍሥሕተከሙ በዝንቱ ዓለም ብሎ ዘለፋን ተናገረ።
ከመ ንትመራሕ ነገረ ርትዕ
ጽንዕተ፤
የማትፈርስ እውነተኛ ነገርን
እናውቅ ዘንድ ፤
ወዮሐንስ እኅድአ ወክሐ እንዘ
ይብል እምላዕሉ እምኀበ አቡሁ ወረደ።
እም እና እም አንድ ወገን
ዮሐንስ ወልደ ዕጓለ እመሕያው ወረደ እምሰማይ ብሎ ጽፎ የመናፍቃንን ክርክር ጸጥ አደረገ ከበበ እንዘ ክርስቶስ የሐውሶሙ ፤
ክርስቶስ እየቃኛቸው ዮሐንስ
አኅድአ ወከሐ ሉቃስ ዝልፈተ አርአየ፤
ወእምካልዓኒሁ ውእቱ አንኀ፡፡
ከወንደሞቹ አብልጦ አካል
ከህልውና ተገልጾለት ንጽሐ ሥጋ ንጽሐ ነፍስ ንጽሐ ልቡና ተሰጥቶት ቀዳሚሁ ቃል ብሎ ተናገረ።
ወማቴዎስኒ ዘእምአይሁድ ብዙኃነ
አእመነ ፤
ማቴዎስም ከአይሁድ ወገን
ብዙ ሰው አሳመነ ።
አንድም ከአይሁድ ወገን የሚሆን
የጌታችን ልደት ለብዙ ሰው አስተማረ አንድም ከአይሁድ ወገን የሚሆን ማቴዎስም ብዙ አሳመነ፡፡
ወማርቆስኒ እንዘ ሀሎ ብሔረ
ግብጽ አስተብቁዕዎ አርድአተ ዚአሁ ከመ ይግበር ከመዝ ፤
ማርቆስም በግብጽ ሳለ ደቀ
መዘሙርቱ በቃል ያለ ይረሳል በመጽሐፍ ያለ ይወረሳል ሦስቱ ደቀ መዛሙርቶቻቸው
እንደጻፉ ጻፍልን ብለው ለመኑት ማለዱት ።
ወሉቃስሂ ካዕበ በሐዲስ ተናገረ።
ዝልፈተ አርአየ ላለው ዳግመኛም
ሉቃስ አብዝቶ ወእስከ አዳም አልዓለ ፤ እስከ አዳም ደረሰ ሐተታ ሌሎች የሚቈጽሩ እስከ ስድስት እስከ ሰባት ነው እንደሱ አብዝቶ
የቈጠረ የለምና አንድም በሐዲስ ከነበረ ከዮሴፍ ጀምሮ በብሉይ እስከ ነበረ እስከ አዳም ደረሰ ወልደ ዮሴፍ ብሎ አዳም ወልደ እግዚአብሔር
እስከ ማለት ደረሰ ።
ወአኮ በአሐቲ ማዕዘንት ጽሒፎሙ
ዘደፈኑ፤
ጽፈው ባንድ ቦታ አልተውም
።
አላ በኩሉ ምድር ወበኩሉ
ባሕር ሰፍሑ ስምዓተ ለኩሉ ሰብእ ።
ባራቱ ማዕዘን ላሉ ሁሉ ጻፉ
እንጂ ።
ወእንዘ መቃርዓት ህልው ይትነበብ
ዝንቱ እስከ ዮም
መናፍቃን ሳሉ ወንጌል እስከ
ዛሬ ድረስ ይነበባል ይተረጐማል ።
ወአልቦ ዘአዕቀፈ አምዘጽሑፍ
ወኢመኑሂ ፤
ከተጻፈው ጽፈት ማንም ማን
የነቀፈ የለም ፤ አንድም አላ በኩሉ ብለህ መልስ ። ባራቱ ማዕዘን ዙረው ወንጌልን ለሰው ሁሉ አስተማሩ እንጂ አይሁድ መናፍቃንም
ሳሉ ሁልጊዜ ይህ መጽሐፍ ይነገራል ትምህርቱንም የነቀፈ የለም ።
እንዘ ታረትዕ ኃይለ አምላክ
ከሃሊተ ኩሉ ።
ሁሉን ማድረግ የሚቻላት ኃይል
አምላካዊት እያቀናናት ፤
ወፈድፋደ እምኩሉ ።
ይልቁንም ወንጌል ስትጻፍ፤
ወሶበ ኢኮነ ከመዝ እፎ መጸብሐዊ
ወመገልብ እምጠቡ ከመዝ፤
እንዲህ ባይሆን መጸብሐዊ
ማቴዎስ መግለቦ ሠሪ ዮሐንስ እንደምን በተራቀቁ ነበር አንድም እፎ እምጠበ በል ሰውን በግብር ምክንያት ያሸሽ የነበረ መጸብሐዊ
ማቴዎስ እንደምን በተራቀቀ ነበር ገለቦ ይላል ትግሬ ሸሸ ሲል።
ወኢኮነ በምትሐት ወኢበሕልም
ዘኮነ ዝ ለእለ በየዋሃት ወበሃይማኖት ያነብብዎ ወየአምኑ አምነው በሃይማኖት ባለመቃወም ጸንተው ለሚመለከቱት የተደረገ ይህ በሐሰት
በምትሐት አይደለም ወአኮ በሕይወቶሙ ክመ ፤
ማመናቸውም በሕይወተ ሥጋ
ሳሉ ብቻ አይደለም
ዓዲ መዊቶሙሂ ፤
ከሞቱም በኋላ ነው እንጂ።
አኮ ለ፳ ወ፬ቱ ሰብእ ወኢለ፻ት። የጻፉ ለመቶ ሀያ ቤተ ሰብእ ብቻ አይደለም። አላ ለአህጉር ወለአሕዛብ ወለሕዝብ
ወለምድር ወለባሕር ወለዓላዳስ ወለፀር ወለኩሉ ዓለም ።
ለሁሉም ነው እንጂ አንድም
ለጥቂት ሰው ብቻ አይደለም በባሕር በየብስ በደሴት በሀገር ላሉ ለሕዝብም ለአሕዛብም ነው እንጂ ።
አእመኑ በዛኅን ዘእግዚእነ
ኢየሱስ ክርስቶስ ወውስተ መርሶ አብኡ ፤
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ
አጋዥነት አሳምነው ወደ መንግሥተ ሰማያት ወደብ አገቡ ።
መጥዎ ኀብረተ ቃላት ቅዱሳት
ዘ፬ቱ ወንጌላት
ተፈጸመ ።
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
09/06/2011 ዓም
No comments:
Post a Comment