በተዋሕዶ እና በቅብዐት መካከል ስላለው ሰፊ ልዩነት ሁሉም ያውቅ ይረዳ ዘንድ ሁሉም በየሞባይሉ ሊጭነው እና ሊያነበው የሚችለው መተግበሪያ በወንድማችን በዲ.ን ጌታሁን አማረ ተዘጋጅቶ ቀረበልን፡፡ ይህን መተግበሪያ ለሠራልኝ ወንድሜ ምስጋናዬ ላቅ ያለ ነው፡፡ ባለፈው ሳምንት እንደጻፍኩላችሁ Surprise የማደርጋችሁ በዚሁ ነው፡፡
ይህ መተግበሪያ ደብረ አሚንን የሚተካ አይደለም፡፡ መሠረታዊ የሆኑ ልዩነቶቻችንን ከሦስቱ የቅባት መጻሕፍት ሀሳብ በመነሣት የሚተነትን መተግበሪያ ነው፡፡ የትም ሆነው አውርደው ሊጭኑት የሚችል ሲሆን መተግበሪያውን ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም ግን 20 ብር መክፈልና የመክፈቻ የምስጢር ኮድ መቀበል ይኖርብዎታል፡፡ በዚህ ዝቅተኛ ዋጋ መተግበሪያውን ያቀረብነው ሁሉም ሰው እንዲያነበው በማሰብና ከዚሁ በሚገኘው ገቢም ወደፊት ለምሠራቸው ሥራዎች የማንንም እርዳታ ላለመጠየቅ በማሰብ ነውና እንደ ገንዘብ ሰብሳቢ እንደ ነጋዴ እንዳትቆጥሩኝ አበክሬ እማጸናለሁ፡፡ ገንዘቡን ለመላክ ሞባይል ባንኪንግን መጠቀም ይቻላል፡፡ እንዴት መላክ እና የምስጢር ኮድ መቀበል እንደሚቻል መተግበሪያውን አውርዳችሁ ስትጭኑት በዚያ ላይ ያሳያችኋል፡፡
አፕሊኬሽኑን ለማየትና ለመጫን https://play.google.com/store/apps/details?id=org.goranda.finotetsidk
No comments:
Post a Comment