Thursday, February 14, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 8



====================
ስድስተኛ ጉባኤ
ወሣልሱ ሥርዓት ፤
ሦስተኛውን ሥርዓት ብለውታል ሥርዓት ይባላል።
ወሥርዓተ ዝንቱ መጽሐፍ ክቡር
ክቡር የሚሆን የዚህ መጽሐፍ ሥርዓቱ
ይእቲኬ አንብቦቱ በኵሉ ጊዜ
ኵሎ ጊዜ በኵሉ ጊዜ ይላል ሁልጊዜ እሱን መመልከት ነው እመኒ እንዘ ትነውም ወእመኒ እንዘ ትነቅሕ እመኒ እንዘ ትነብር ወእመኒ እንዘ ትትነሣእ እመኒ እንዘ ትቀውም ወእመኒ እንዘ ተሐውር ኢትርሳዕ ተዘክሮተ እግዚአብሔር አምላክነ ወበኵሉ ጊዜ ወበኵሉ ሰዓት እንዲል ።
ወኃዲገ ሕሊናት ለዓቂበ አቅማሪሁ ወተአምሪሁ
ሰንጠረዥን ቁራኛውን ለማወቅ ሕሊናትን ጨልጦ ገርኝቶ መስጠት ነው ፤ አንድም መብል መጠጥን መተው ነው፤ አንድም ሕሊናትን፤ ማጽናት ነው ኃዲገነ ጥንተ ነገሩ እንዲል
ወተአዝዞ ቦቱ  በሱ ጸንቶ መኖር ነው በጠይቆ ወበገቢር ወቀዊም በኵሉ ትእዛዛቲሁ ፤
በመረዳት በሥራ በትእዛዙ ሁሉ ጸንቶ መኖር ነው በቃል ፤ ባነጋገር
ወበምግባር፤ በሥራ፤
ወተመይጦ ኀበ ጽንዓቱ
ከጸናም ዘንድ መላልሶ መመልከት ነው ፤ ለእመ ረከብከ ቀለመ ጸዋግ ተመያየጥ ዐሠርተ ወክልኤተ ጊዜያተ ወኢትፍቅድ ኃሊፈ ቆጽል እምኔሁ እንዲል ፤
ወምሳሌያቲሁ ዘምሱል ኀበ ትርጓሜያት 
የተመሰለውን ምሳሌውን ወደ ትርጓሜ ሲያፋልሱ መኖር ነው ፤ አንድም ዘምሉስ ይላል አብነት ወደ ትርጓሜ የተመለሰውን ምሳሌውን ማወቅ ነው።
ዘጽሕፍት በብራና
ወዕውቅት ፤ በልቡና ታውቃለች፤
ወበውእቱኬ ይትበየን ለአንባቢ መሌልየ ኵሎ ኃይለ ቃሉ፤     
በዚህም ለተመልካች ደቀ መዝሙር የነገሩ ምሥጢር ብልት ብልቱ ይታወቃልና ስለዚህ ነው  አንድም ምሊላየ ኵሉ ኃይለ ቃሉ ይላል የነገሩ ምሥጢር መለያያ መለያያው ይታወቃልና ስለዚህ ነው።
በብሩህ ብያኔ  በጎላ በተረዳ መለየት።
ወይነሥእ በአስተብዖ ጥይቅና ወተፍጻሜተ ዘሀሎ ውስቴቱ።
በሱዋ ያለውን በመመልከት ዕውቀትን በመረዳት ገንዘብ ያደርጋልና ስለዚህ ነው ፤
እስከ ደኀሪት ነገር
ሳብዕ አርእስተ ነገር ያለው እስኪፈጸም ድረስ አንድም መላው እስኪፈጸም ድረስ። 
ወናሁ ተጠየቀ ሥርዓቱ፤     
የዚሀ መጽሕፍ ሥርዓቱ ታወቀ ተረዳ  አንድም ወጸንዓት ንበቱ ይላል እሱን በመመልከት ጸንቶ የመኖሩ መጽናት ታወቀ ተረዳ ወጸንዓት ንብረቱ ይላል እሱን በመመልከት መኖሩ ታወቀ ተረዳ
ወራብዑ ትእምርት
አራተኛውን ስም ብለውታል ሰምዮት ትእምርት ይላል
ወትእምርተ ዝንቱ መጽሐፍ ክቡር ወንጌል። ክቡር የሚሆን የዚህ መጽሐፍ ስሙ ወንጌል ነው ወንጌል ብሂል በልሳነ ጽርእ ወትርጓሜሁ ስብከት ወንጌል ማለት በጽርእ ቋንቋ ብሥራት ስብከት ማለት ነው።  
እስመ ተሰብክ ውእቱ ወልደ እግዚአብሔር እንደነገሠ ሞተ ሥጋ ሞተ ነፍሰ እንደጠፋ ተናግራለችና ወንጌለ መንግሥት እንዲል። ወደ ግእዝ ቢመልሱት ወንጌል ማለት ስብከት ማለት ነው።
በእንተ ትስብአተ ቃለ እግዚአብሔር በዘመድነ።
በኛ ባሕርይ ቃለ እግዚአብሔር ሰው መሆኑን ተናግሯልና አንድም ሰው መሆኑ ተነግሮበታልና።
ወኅድረተ መንፈስ ቅዱስ ላዕሌነ ወውስቴትነ መንፈስ ቅዱስ በኛ ማደሩን ተናግሯልና ። አንድም መንፈሰ ዋዱስ በኛ ማደሩ ተነግሮበታልና ። ላዕሌነ ወውስቴተነ ማለቱ በነፍስ በሥጋ ሲል ይደጋግመዋል
ዓባይኬ ዛቲ ብሥራት እንት ባቲ ደለዎሙ ለውሉደ ሰብእ ከመ ይኩኑ ታቦተ ለእግዚአብሔር ። የእግዚአብሔር ማደሪያ ለመሆን ምእመናን የነቁበት የተጉባት ወንጌል ደግ ሕግ ናት።
ወማኅደረ መቅደሱ ። ልዩ ማደሪያው ይሆኑ ዘንድ
ወኮነ ሎሙ ዘይበዝኅ ክብር በክብረ ዝንቱ ዕበይ ።
በወንጌል ደገኛ ፍጹም ክብር ተሰጣቸው ።
ኦ ለዝንቱ ክብር ዓቢይ ወኂሩት ዘእንበለ መሥፈርት።
ፍጹም የሚሆን ይህ ክብር ልክ መጠን ወሰን ድንበር የሌለው ቸርነቱ ምን ይረቅ ምን ይጠልቅ ኦ ወዮ እንደምን ያለ ረቂቅ ነው ። አንድም ፍጹም ለሚሆን ለዚያ ክብር ወሰን ድንበር ለሌለው ለቸርነቱ እንክሮ ይገባል።
ወዜነወነ ካዕበ ተሣህሎተ እግዚአብሔር ልዑል ለደቂቀ ዕጓለ እመሕያው ።
ልዑል እግዚአብሔር እኛን ይቅር ማለቱን ነግሮናልና። ተኃድገ ለከ ኃጢአትክ ተኃድገ ለኪ ኃጢአትኪ ማለትን ።     
ወዓብጥሎ ኵነኔያት። ኢትጥዓም ኢትልክፍን ኢትግሥሥን ማሳለፉን ።
ወሰቢረ ሦከ መስሐቲ ጸላዒ። ዲያብሎስ የሚያሠራቸው እኵያት ፍትወታት ኃጣውእን ድል መንሣቱን።   
ወድክመተ ትዝህርቱ።
ዳያብሎስን በሦስቱ አርእስተ ኃጣውእ ድል መንሣቱን ነግሮናልና።
ወዓዲ ዘበቊዓነ ቦቱ በጸውዖትነ ውሉደ።
በጸውዖቱ ውሉደ ብሎ ውሉድ እኛን በመጥራቱ እኛን የጠቀመንን ጥቅም ነግሮናልና አንድም ውሉድ ይላል ውሉድ እኛ እሱን በመጥራታችን የጠቀምነውን ጥቅም ነግሮናልና። 
ወፍግዓ ዘድልው ለነ ውስተ መንግሥተ ስማያት ወሕይወት ለዝሉፉ ።
በማያልፍ ሕይወት በመንግሥተ ሰማያት ተዘጋጅቶልን ያለ ተድላችንን ነግሮናልና ፤ ወሕይወተ ይላል ፍግዓ ላለው ። በመንግሥተ ሰማያት ተዘጋጅቶልን ያለ ተድላችንን የማያልፍ ሕይወታችንን ነግሮናልና ስለዚህ ነው ። 
ወናሁ ተበየነ ትእምርቱ።
እነሆ ስሙ ታወቀ ተረዳ
ወምክንያተ ስሙ።
ወንጌል የተባለበትም ምክንያት ታወቀ ተረዳ ።
ወኃምስ መሠረት አምስተኛውን መሠረት ብለውታል መሠረት ይባላል ። እምአይቴ
ይላል አብነት ፤
ወመሠረተ ዝንቱ መጽሐፍ ክቡር ፤
ክቡር የሚሆን የዚህ መጽሐፍ መሠረቱ መሠረትነቱ በኀበ አግዚአብሔር ዓቢይ ወአዚዝ ።  ዓቢይ አዚዝ የሚሆን እግዚአብሔር ነው ።
ወኮኑ ሎቱ ፬ቱ ጸሐፍት
አራት ጸሐፍት አሉት ፤
፪ቱ እምኔሆሙ ዘእምሐዋርያት ፲ቱ ወ፪ቱ አለ ኃረዮሙ እግዚእነ እምኵሉ አርድእት ወሰመዮሙ ሐዋርያት ፤ ከአራቱ ሁለቱ ከአምስት ገበያ ሰው መርጦ ከሾማቸው ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ወገን ናቸው፤
ወውእቶሙ ማቴዎስ ወዮሐንስ ፤
ሁለት የተባሉትም ማቴዎስ ዮሐንስ ናቸው ፤
ወ፪ቱ እምኔሆሙ እምአርድእት ማርቆስ ወውእቱ ዘኮነ ረድኦ ለጴጥሮስ ፤
ከሁለቱ አንዱ የጴጥሮስ ደቀ መዝሙር ማርቆስ ነው
ወካልኡ ሉቃስ ወውእቱኒ ዘኮነ ረድኦ ለጳውሎስ ፤
ከሁለቱ አንዱ የጳውሎስ ደቀ መዝሙር ሉቃስ ነው
ወጸሐፉ እንከ ወስተ ኵሉ አህጉር ርኁቃት፤
በቦታ ተለያይተው በርኁቃት አህጉር ጻፉ ። ሐተታ ማቴዎስ በፍልስጥኤም ጀምሮ በህንድ ይጨርሰዋል ወጠና በፍልስጥኤም ወፈጾማ በህንድ እንዲል። ማርቆስ በግብጽ በሮምም ይላል ሉቃስ በመቄዶንያ ዮሐንስ በኤፌሶን ሁነው ጽፈዋል። 
ወበአዝማን ውሉጣት፤
በልዩ አዝማን ጻፉ ፤ ሐተታ ማቴዎስ ጌታ ካረገ ስምንተኛው ተፈጽሞ ዘጠነኛው ሲጀመር ቀላውዴዎስ ቄሣር በነገሠ በመጀመሪያው ዘመን ፤ ማርቆስ ጌታ ካረገ ዐሥራ አንደኛው ተፈጽሞ ዐሥራ ሁለተኛው ሲጀመር ቀላውዴዎስ ቄሣር በነገሠ ባራተኛው ዘመን፤ ሉቃስ ጌታ ካረገ ሀያ አንድ ተፈጽሞ ሀያ ሁለተኛው ሲጀመር ቀላውዴዎስ ቄሣር በነገሠ ባሥራ አራተኛው ዘመን፤ ዮሐንስ ጌታ ካረገ በሠላሳ በሠላሳ አምስትም ይላል ፤ ኔሮን ቄሣር በነገሠ በሰባት በስምንትም ይላል ። ሰባት ቢሉ ሲፈጸም ስምንት ቢሉ ሲጀመር ፤
ወጸሐፉ በልሳን ዘዘዚአሁ ፤ ልዩ ልዩ በሚሆን ቋንቋ ጸፉ ፤ ሐተታ ማቴዎስ በዕብራይስጥ  ማርቆስ በሮማይስጥ ሉቃስና ዮሐንስ በዮናኒ ፤ ዮሐንስን ለይቶ በልሳነ ጽርእ የሚል አብነት ይገኛል እንደ በቅላ እንደ ሐማሴን ጥቂት ጥቂት የልሳን መለያየት ነው ወኮነ ኃይለ ቃሎሙ ውስተ ፍጻሜ አሐዱ።
በአንድ ነገር ለመፈጸም የነገራቸው ምሥጢር ፩ ሆነ
ወኮነ ውእቱ ዘይበዝኅ ነገሩ ለጥያቄሆሙ ፤
ብዙው ነገር በመረዳት ነው ።
ሠናይኬ ዘኢኮነ ጸሀፊሁ ፩ዱ።

ጸሐፊው አንድ ያይደል ወንጌል ደግ ሕግ ናት ፤
ወተሰፍሐት ዛቲ ስብከት ውስተ ኵሉ አጽናፈ ዓለም
ወንጌል ባራቱ ማዕዘን ተነገረች
ተጽሕፈት  በብራና ተጻፈች
ወተለክዓት  በልቡና ተቀረጸች
ዘእንበለ ተወልጦ ወተሌልዮ
ጥቂት ጥቂት ከመለወጥ ከመለየት በቀር ጥቂት መለዋወጥ መለያየት ሳይቀር አንድም እንደማቴዎስ እንደ ማርቆስ መለየት መለወጥ ሳይኖር ያለመለወጥ ያለመለየት
ወናሁ ነበረ መሠረቱ ኀበ ባዕሉ
አስገኝው ባለቤቱ እንደሆነ እነሆ ታወቀ ተረዳ ፤
ወጸሐፍቲሁ  አራት ጸሐፍት እንዳሏት ታወቀ ተረዳ ተነገረ ፤
ወሳድሱ ምስማክ ፤
ስድስተኛውን ምስማክ ብለውታል ምስማክ ይባላል
ወምስማከ ዝንቱ መጽሐፍ ክቡር
ክቡር የሚሆን የዚህ መጽሐፍ መከዳነቱ ፤
ወውእቱ ለአይ ግብር ይሤኒ ወለአይ ገጽ እመክፈልተ ጥበብ ዘይፈቅድ ልብ ወየኃሪ ።
ልብ ከሚሻው ጥበብ እድል ወገን ከሥራ ከማናቸውም ሥራ ከነገር በማናቸውም ነገር ይመች እንደሆነ
እስመ ምስማክ ዝንቱ መጽሐፍ ክቡር ወፈቂዶቱ ይስሕብ ኀበ ተጠብቦተ ልብ ፤
ከቡር የሚሆን የዚህ መጽሐፍ መከዳነቱ እሱን መሻቱ ልቡናን ወደማራቀቅ ያደርሳልና ስለዚህ ነው ኀበ ሥርዓት ወንብረት ሉዓላዊ ወአስተጋብኦ በተግሣጽ ፍጽምት ዘበውስቴታ ይበጽሕ ኀበ በቊዔት ዘበአማን ።
በፍጹም እዝናት በእሷ ያለውን በመመልክት ወደ ፍጹም ጥቅም ያደርሳልና ስለዚህ ነው።
ወይፈቅድ ዘሀሎ ውስቴታ ምልአተ ወተፍጻሜተ
በሷ ያለ ደቀ መዝሙር ዕውቀትን መረዳትን ገንዘብ ያደርጋልና ስለዚህ ነው ። አንድም ይትፈቀድ በሷ ያለ ዕውቀት መረዳት ይገኛልና ስለዚህ ነው።
ወውእቱ እስመ ነገር አምላካዊ አመ ነሢኦቱ ወአፍልሶቱ በሕሊና ሠናይ ይፈልስ ውስተ ነፍሳት ንጹሐን እምነ ልባዌ ኀበ ተወክፎ ።
እሱም አምላክ ያስተማረው የአምላክን ነገር የሚናገር ወንጌል መምሩ እበላበታለሁ እጠጣበታለሁ ሳይል በሚያስተምርበት ጊዜ ደቀ መዝሙር እሾምበታለሁ እሸለምበታለሁ እከብርበታለሁ ሳይል በሚማርበት ጊዜ መምር እንዳያውቅ ከመሆን ደቀመዝሙር እንዲያውቅ ወደመሆን ደርሶ ይገልጻልና አንድም እምነ ለባዊ ኀበ ተወካፊ ከአስተዋይ መምር ወደ ብልህ ደቀመዝሙር ደርሶ በንጹሐት ነፍሳት አድሮ ይኖራልና ስለዚህ ነው ።
ወይሠርቅ ውስቴትነ ሥርቀተ እስከ ይቀውም ውስቴተነ እምነ አርአያ እግዚአብሔር ቁመተ ዘበአማን ከአርአያ እግዚአብሔር አሰጥቶ በኛ ዘንድ ፈጽሞ እስኪረዳ በኛ መገለጽን ይገለጸልና ስለዚህ ነው ።
በአስተርክቦ ልቡናዊት ፤
ልቡናን አንድ በማድረግ በአስተርክቦ ልቡና ይላል ሕሊናን አንድ በማድረግ ።
ዘውእቱ ሊቀ ኵሉ ትሩፋት ፤ ይኸውም የትሩፋት አበጋዝ የሚሆን ሕሊና ነው
ወሶበ ኮነ ውእቱ ከማሁ ኮነ እንከ ንሕነኒ ድልዋነ ለነሢአ መንፈስ ቅዱስ በረድኤት አምላካዊት ወበእንተ ዝንቱ ይደሉ ላዕሌነ ንብረት ለዝሉፉ በንጽሕና ወበኂሩት ።
እንዲህ ከሆነ ከአምላክ ዘንድ በሚገኝ ረድኤት መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ነቅተን ተግተን ስለዚህ በንጽሕና ጸንቶ መኖር ይገባናል ።
እንተ ባቲ ኮነ ድልዋነ ለተመጥዎ ሕግ አምላካዊ ወመንፈሳዊ ፤ አምላክ ያስተማረውን መንፈስ ቅዱስ ያጻፈውን ሕግ ለመቀበል በበቃንበት በረድኤት አምላካዊት ኮነ ድልዋነ ለመንፈስ ቅዱስ ፤ ዘቦቱ ኩሉ ነበበ በልሳን ዘዘዚአሁ ውስተ ኵሉ አጽናፈ ዓለም ፤
ሰው ሁሉ በሰባ አንድ ቋንቋ በአራቱ ማዕዘን የተናገረበት ብሎ ለሕግ ቀጸለ አንድም በአራቱ ማዕዘን ያለ ሰውን ሁሉ በሰባ ሁለት ቋንቋ ያናገረው በተስፋ መንፈስ ቅዱስ። በተስፋ መንፈስ ቅዱስ በሀብተ መንፈስ ቅዱስ በፍተ መንፈስ ቅዱስ ይላል አብነት በመንፈስ ቅዱስ አጋዢነት ፤ ዓዲ አንቅሐነ ፈጣሪ ኀበ አእምሮ ቅድምናሁ ወተድኅሮቱ ።
ዳግመኛ ፈጣሪ ቀዳማዊነቱን ደኃራዊነቱን ወደ ማወቅ አነቃቃን።
ይትባረክ ወይትለዓል ፤ ይክበር ይመስገንና በልብ መታስቡ በቃል መነገሩ ከፍ ከፍ ይበልና።
ወኀበ ልሒኮተ ፍጥረቱ መንክር። ድንቅ የሚሆን ፍጥረቱን በልጅነት ማደሱን ወደ
ማወቅ አነቃቃን።
ወተከሥቶ ልቡና ጥበቡ ልዕልት ወብርህት፤
ልዕልት ብርህት የምትሆን የሥጋዌን ዕውቀት መገለጽን ወደማወቅ አነቃቃን     
ወናሁ ተከሥተ ምስማከ ዝንቱ መጽሐፍ
እነሆ የዚህ መጽሐፍ መከዳነቱ ታወቀ ተረዳ
ለአይ ገጽ ወለአይ ግብር  ይኄይስ
ከሥራ በማናቸውም ሥራ ከነገር በማናቸውም ነገር ይመች እንደሆነ።    
ሰባተኛ ጉባኤ
ይቆየን።
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
07/06/2011 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment