==================
አራተኛ ጉባኤ።
ወፈቀደ እግዚአብሔር አድኅኖተ
ዓለም በሣህሉ ወበምሕረቱ ።
በይቅርታው በቸርነቱ ብዛት
እግዚአብሔር ዓለምን ማዳን ወዶ፤
ወርእየ ተግባረ እደዊሁ እለ
አምጽኦሙ እምተኃጥኦ በተረክቦ ፤
ካለመኖር ወደ መኖር እምኀበ
አልቦ ኀበ ቦ ከኢምንት ወደምንት አምጥቶ የፈጠራቸውን ፍጥረቶቹን
አይቶ ። አንድም እምኃጢዕ ኀበ ረኪብ ይላል አብነተ ካጣ በኋላ ያገኛቸውን ፍጥረቶቹን አይቶ ወአክበሮሙ ላዕለ ኩሉ ፍጥረት ዘታሕተ
ሰማይ ከሰማይ በታች ባሉ ፍጥረታት ሁሉ እንዳሠለጠናቸው አይቶ።
ከመ በዝኃት ወፈድፈደት ኀበ
ተጼውዎተ ሰይጣን
ወደ ሰይጣን ምርኮኝነት መሄዳቸው
ፈጽማ እንደጸናች ዐውቆ ።
ወቀንዮቱ መሪር
ወደ ጽኑ አገዛዙ መሄዳቸው
እንደጸናች ዐውቆ ።
ምሕሮሙ በዕበየ ሣህሉ ወምሕረቱ
ወኂሩተ ሠናይቱ ፤
በይቅርታው በቸርነቱ ብዛት
አዘነላቸው ።
ወፈትሖሙ እመዋቅሕቲሁ፤
ከቁራኝነቱ አዳናቸው ።
ወእምጽዋዌሁ ማኅጐሊ ፤
ጥፋት ካለበት ምርኮኝነቱ
፤ ወእምጼዋዌ ማኃጉሊ ይላል ። ሰይጣንን በግብሩ ማኃጉሊ አለው ከሰይጣን ምርኮኝነት ፈትሖሙ አዳናቸው።
በዘይሤኒ ጽድቁ ወርትዑ።
ባማረ በተወደደ ፍርዱ አዳናቸው
። ወበድልወት ኮነ ኩነኔ እግዚአብሔር ወአድኃነነ በፍትሐ ጽድቅ ወርትዕ እንዲል ። ጌታ የገደልክ ገደልከ የበደልክ በደልክ በቃህ
አላለምና በካሳ ብሏል እንጅ ፤
ወኢኃደጎሙ ውስተ ኃጉል ለዝሉፉ
በዕደ ሰይጣን ።
በሰይጣን እጅ እንደተያዙ
ሊቀሩ በቁራኝነት ፈጽሞ አልተዋቸውም ።
ወኢሞኦ በኃይሉ መዋኢት ፤
በአምላክነቱ ድል አልነሣውም
።
ወአኃየሎ በክሂሎቱ ።
በከሃሊነቱ አልተዋጋም አልሠለጠነበትም
።
ወኢበምንትኒ እምዕበዩ፤
ከጌትነቱ ወገን በምንም በምን
በአምላከነቱ ድል አልነሣውም። አላ በትሕትናሁ ወፍትሐ ጽድቁ በትሩፋተ ምሥጢር እንግዳ።
እንግዳ በሚሆን ተዋርዶ በሠራው
ሥራ ነው እንጅ በዘየዓቢ ጥበቡ እምነ ኩሉ ጥበብ ወልባዌ። ከጥበብ በሚበልጥ ጥበቡ ከእውቀት በሚበልጥ ዕውቀቱ፤ ሐተታ ዓለምን ከፈጠረበት
ጥበቡ ሰው ሁኖ ማዳኑ ይበልጣልና ።
ቀዳማዊ ዘውእቱ እምቀዲሙ
ዘአልቦ ጥንት ቃለ እግዚአብሔር፤ ቀዳማዊ ጥንት የነበረ በዚህ ጊዜ ተገኘ የማይባል አካላዊ ቃል ፤ ዘቦቱ ኩሉ ኮነ። ሁሉ በሱ ሕልውና
በሱ አንድነት የተፈጠረ። ወዘእንበሌሁሰ አልቦ ዘኮነ ወኢምንትኒ እምዘኮነ ያለሱ ሕልውና ግን ምንም ምን የተፈጠረ የሌለ እስመ ቃለ
ኩሉ ፍጥረት ትመስል ፍጥረታት ።
የሰው ሁሉ ቃል እንጅ የሰው
ሁሉ ቃል እኮን ባሕርይዋን ትመስላለች ፤ አንድም የሰው ሁሉ ቃል ባሕርይዋን ትመሰላሰች እኮን ፤ ወአምጣናሰ እስመ ቃለ ሰብእ ሐማሚት ወጸምሔያዪት ። መጠኑዋ ግን የሰው ቃል
ደካማ የምትጸወልግ ናትና ወሕይወታ ምሱጥ በከመ ንሬእያ እምተሣትፎትነ ዘበኅቡዕ በረቂቅ ተዋሕዳው ባለበሥጋ አነዋወሯ ተጠልፎ ኸያጅ
ነውና።
ኃላፊት ወማሳኒት ፤
ከመኖር ወዳለመኖር እምኀበ
ቦ ኀበ አልቦ ከምንት ወደ ኢምንት ኸያጅ ናትና። ወቃለ እግዚአብሔርሰ ልዕልት ፤ አካላዊ ቃል ግን ከዚህ ሁሉ የራቀች ናት።
ይእቲኬ አርዓያ ገጹ እግዚአብሔር
አብን በመልክ የምትመስለው በባሕርይ የምትተካከለው ናት።
ቀዳሚት ወፈጣሪት ። ቀዳማዊት ፈጣረት ናት
ወሕያውት ለዓለም ህላዊት።
ለዘላለሙ ሕያውት ባሕርያዊት
ናት ።
ወነባሪት ዘኢትማስን የማትለወጥ ነባሪት ናት
ወሶበ ኮነት ይእቲ ቃል ፈጣሪተ
ወሕያውተ ወባሕርያዊተ ነባሪተ ለዓለም ይደሉ እንከ በዛቲ ግብር ባሕርያዊት ትሰመይ ሕላዌ አካለ።
እንዲህ እንዲህ ከሆነች ባሕርያዊት
በምትሆን በዚህም ሥራ ፤ ሕላዌ አካል ባሕርይ ልትባል ይገባል እስመ
ትርጓሜሃ ለሕላዌ በኀበ መምህራን ነባብያን በጥይቅና
አስረድተው በሚተረጉሙ በመምህራን
ዘንድ የሕላዌ ትርጓሜ አካል ነውና አካል ባሕርይ ነውና ባሕርይ ልትባል ይገባል፤
ውእቱ ዘአልቦ እሠር ለባሕርይ፤
ባሕርዩ የማይመረመር እርሱ፤
ፈቀደ በፈቃደ አቡሁ ወበሥምረተ
መንፈሱ ቅዱስ ከመ ይቤዙ ኩሎ ነፍሳተ እለሙቁሐን ኀበ ጽልመተ ሞት ወጥንቃቃተ ሲኦል።
ባባቱ ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስ
ፈቃድ ሞት ባመጣው ጨለማ ተግዘው የነበሩ ነፍሳትን በሲኦል ምቸግነት ያሉ ነፍሳትን ሊያድን ወዷልና።
ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ በተለየ
አካሉ፤
ወኀብአ ብርሃነ መለኮቱ ዘኢይትከሃል
ከመ ያስተርኢ በተሠግዎቱ እመንፈስ ቅዱስ ወእማርያም እምቅድስት ድንግል ።
በፈቃደ አቡሁ ወበሥምረተ
መንፈሱ ቅዱስ በተሠግዎቱ ። ባባቱ ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ከመንፈስ ቅዱስ ከፋይነት ከመቤታችን ተከፋይነት የተነሣ ሰው በመሆኑ
ኀብአ ፤ አንድም በግብረ መንፈስ ቅዱስ ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ሰው መሆኑ ሊታይ የማይቻል ብርሃነ መለኮቱን
በሥጋ ሰወረ።
ከመ ይቅረብ እምኔሁ ጸላዒ
ወይብጻሕ ኀቤሁ ይቅረብ ያለውን ይብጻህ እምኔሁ ያለውን ኀቤሁ አለው ጸላዒ ዲያብሎስ ወደሱ ይደርስ ዘንድ አንድም ሰው ከመሆኑ የተነሣ
የሰውነት ሥራ ከመሥራቱ የተነሣ ወደርሱ ይቀርብ ዘንድ ወደርሱ ይደርስ ዘንድ
ወያምስሎ ከመ ካልዓን ሰብእ እለ ውስተ ጼዋሁ በምርኮኝነት እንዳሉ እንደ ሌሎች ሰዎች ያደርገው ዘንድ።
ወያስተጌብሮሙ ግብሮ
ሥራውን የሚያሠራቸውን ያስመስለው
ዘንድ ሥራውን እንደደሚያሠራቸው ያደርገው ዘንድ ወያስተጌብሮ ግብሮ
ሥራውን የሚያሠራውን ሰው ያስመስለው ዘንድ።
ወኢይፍራህ እምነ ዕበዩ ወመንክራቲሁ
ሶበ ርእየ ከተአምራቱ ከጌትነቱ ወገን ባየ ጊዜ እንዳይፈራ ወበከመ ኮነ እንከ ሰይጣን በጉሕሉት ተኃብዓ ውስተ ሥጋ ከይሲ ።
ኮነ ያለውን ተኃብአ ብሎ
አመጣው ፤ ሰይጣን በተንኮል በሥጋ ከይሲ እንደ ተሠወረ
እስከ ተሠልጠ ወጸንዓ ላዕለ
ፍጥረትነ እምቀዳሚ ከጥንት ዠምሮ በባሕርያችን እስኪሠለጥን ድረስ ሐተታ ተሠልጠ ጸንዓ ማለቱ ግን ሥጋን በመቃብር ነፍስን በገሃነም
ተቆራኝቶ ይኖር ነበርና ነው ከማሁ ኮነ ድኅነትነ እማዕሰር በተሰውሮተ ቃለ እግዚአብሔር በዘመድነ።
እኛም ከፍዳ መዳናችን ቃለ
እግዚአብሔር በባሕርያችን በመሰወሩ ሆነ። ወበተዋሕዶቱ ቦቱ ፤
ሥጋን በመዋሐዱ ሆነ፤
እስከ ቤዘወነ እምኔሁ ፤ ከሱ እስኪያድነን
ወአድኃነነ በፍትሐ ጽድቅ
ወርትዕ።
በፍተሐ ጽደቅ በፍትሐ ርትዕ
አዳነን ። ሐተታ እንዳለፈው።
ወኮነ ከመ ኩሉ ሰብእ ዘእንበለ
ኃጢአት ባሕቲታ ፤ ከብቻዋ ከኃጢአት በቀር እንደ ሰው ሁሉ ሆነ ወኮነ ኩሎ ከመ ሰብእ እንደ ሰው ሁሉን ሆነ። ወእምድኅረ ዝንቱ
ወእምቅድሜሁኒ ኢተዓርቀ እመንበረ ስብሐቲሁ።
ከፅንስ በኋላ ከልደት በፊት
ዘጠኝ ወር ካምስት ቀን በማኅፀን ሳለ ከጌትነቱ መንበር አልተለየም ። አንድም ከልደት በኋላ ሠላሳ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ከልደተ
በፊት ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ከጌትነቱ መንበር አልተለየም።
ወኢያንከር እንከ ወኢ፩ዱሂ
እምዝንቱ ነገር ፤ ከዚህ ነገር የተነሣ አንድ ስንኳ አያድንቅ እንዳይደነቅ ወንሕነኒ ምድራውያን እለ ፍጡራን ኢነአምር ፍጥረተ ነፍስነ
ነባቢት እምውስጠ ወሰነ ሥጋነ ። ምድራውያን ፍጡራን የምንሆን እኛ የሥጋ ሕይወት ከምትሆን ከደመ ነፍስ ጋራ ተዋሕዳ ያለች የነባቢት
ነፍሳችንን ባሕርይንስ እንኳ ዐናውቅም ። በእንተ ዘትሰፍሕ መልዕልተ ሰማያት ። ወዶ ሰማይ የምትደርስ ስለሆነች ትደርስም እንደ
ሆነ አትደርስም እንደሆነ ዐናውቅም።
ወትሬኢ ኃይላተ ሰማያውያነ
ወፍጥረታተ ሉዓላውያነ ሰማያውያን መላእክትን ሉዓላውያን ፍጥረታትን የምታይ ስለ ሆነች ታይም እንደሆነ አታይም እንደሆነ አናውቅም
።
ዘርእዩ ዳንኤል ነቢይ ወዮሐንስ
ወልደ ዘብዴዎስ ወካልዓንሂ ።
እነ ዳንኤል እነ ዮሐንስ
እነ ሕዝቅኤል ያዩትን በከመ ርእዩ ይላል ። በከመ ባለቤቶችን ማምጣት ነው እነ ዳንኤል እነ ዮሐንስ እነ ሕዝቅኤል እንዳዩ ።
ወኢትትአኃዝ ላቲ ነፍስ ወኢበምንትኒ
እምግዘፈ ሥጋ ።
ከሥጋ ግዘፍ የተነሣ ነፍስ
በምንም በምን አትገታም ወኢይትበሐል እንክ እፎ ተዋሐደ ቃል በሕላዌ ሥጋ ወኢዓርቀ እመንበረ ስብሐቲሁ ። እንዲህ ከሆነ አካላዊ
ቃል በባሕርየ ሥጋ እንደምን ተዋሐደ ከተዋሐደስ ከጌትነቱ መንበር እንደምን አልተለየም አይባልም።
ወሶበ ኮነ ከመዝ ለነፍስተ
ፍጡራን ወእፎ ፈድፋደ ይከውን ማዕከለ ፍጥረት ወፈጣሪሃ ለፍጡራን ባሕርይ እንዲህ ከሆነ በፍጥረትና በፈጣሪዋ ዘንድ የቱን ያህል
መበላለጥ ይኖር ይሆን ።
ወእምድኅረዝ ከሠተ ኃይሎ
ወዕበዮ። ወእምድኅረ ዝንቱ ወእምቅድሜሁኒ ኢተዓርቀ እመንበረ ስብሐቲሁ ብሎ ነበርና ከተወለደም በኋላ ከሃሊነቱን ጌትነቱን ገለጠ።
ወዓዲ በተአምራት ።
ከሠተ ዓዲ ዳግመኛም በተአምራት
ገለጠ።
እንተ ገብረ በከሢተ አዕይንተ
እውራን ።
እውራንን ከማብራት ወገን
ባደረገው ተአምራት ፤
ወአንጽሖ እለ ለምጽ። ልሙፃንን ከማንጻት ወገን ወአንሥኦተ መፃጉዓን።
ደዌያቸው የጸናባቸውን ከማዳን
ወገን
ወአውፅኦተ አጋንንት እምድውያን
።
ከሕሙማን አጋንንትን ከማውጣት
ወገን ።
ወአሕይዎ ሕሙማን ዘዘዚአሁ
ሕማሞሙ። ደዌያቸው ልዩ ልዩ የሚሆኑ ሕሙማንን ከማዳን ወገን ።
ወገሥጾ ነፍሳት ነፋሳትን ከመገሠጽ ወገን።
ወሐዊር ዲበ ማይ ። በውኃ ላይ ከመሄድ ወገን
ወአጽግቦ አእላፋት እምነ
ኅዳጥ ኅብስት ።
አምስት እንጀራ አበርክቶ
ለአምስት ሽህ ሰው ከማብላት ወገን ።
ወአንሥኦተ ምውታን እመቃብራት
።
ሙታንን ከመቃብራት ከማሥነሣት
ወገን ። ሐተታ ያሥነሣ አንድ አልዓዛርን አይደለምን ቢሉ ፤ መጽሐፍ ስም ካልጠራ ማብዛት ልማዱ ነውና ። አንድም በተአምረ ኢያሱስ
እነ አብርሃምን ነቢያትን ሁሉ አሥነሥቷል ይላል ።
ወዘይመስሎ ለዝንቱ ።
ይህን የመሰለ ሁሉ ባደረገው
ተአምራት ከሠተ
ጌትነቱን ገለጸ።
ወገብረ ዘንተ ተአምራተ በእንተ
ብዙኅ ግብራት
ስለ አራት ነገር ይህን ተአምራት
አደረገ ።
አሐቲ እምኔሃ ከመ ይነጽር
ሰይጣን ዕበዮ ወክሂሎቶ ካራቱ አንዱ ሰይጣን ጌትነቱን ከሃሊነቱን ያውቅ ዘንድ ነው፤
ከመ ይኩን ምክንያተ ለዘሀለወ
ውእቱ ከመ ይግበር ቦቱ ከመ ኩሉ ሰብእ ጽሩዓን ።
እርሱ እንደ ዕሩቅ ብእሲ
አድርጎ በሱ ያደርግበት ዘንድ ስላለው ነገር ምክንያት ሊሆን ነው ። ወካልዕታሂ ከመ ይኩን ተበቅሎተ ለእለ ርእዩ ዘንተ ተአምራተ
ወኢተለውዎ ወርኅቁ እምኔሁ ወአስተርአይዎ በክሕደት ወበዕልወት በፍትሐ ጽድቅ ወርትዕ ሁለተኛ ተአምራቱን አይተው ባላመኑ መፈራረጃ
ይሆን ዘንድ ነው ወሣልስታ ከመ ይኩን ጽንዓ ለእለ የአምኑ ቦቱ፤ ሦስተኛም ላመኑበት ኃይል ይሆናቸው ዘንድ ነው
ኃይለ መስተጋድሎቶሙ። ለመዋጋት ጽንዕ ይሆናቸው ዘንድ ነው ።
ወራብዕታሂ እስመ ትመርሆሙ
ይእቲ ለእለ ተመይጡ እምኃጉል ወተለው ጽድቀ።
አራተኛም ከክሕደት ወደ ሃይማኖት
ከኃጢአት ወደ ጽድቅ ለተመለሱ መሪ ትሆናቸዋለችና ሰለዚህ ነው።
ወዘኮነ ይገብር ምግባራተ
ዘይደሉ ለሰብእ ። ለሰው የሚሰማማ ሥራ ይሠራ የነበረ ማሰት ለሰውነቱ የሚሰማማ ሥራ ይሠራ የነበረ።
እምኀዘን ያዝን የነበረ
ወፍርኃት ይፈራ የነበረ። ወረሀብ ይራብ የነበረ ወንዋም፤ ይተኛ የነበረ። ወጸዊረ ጽእለታት ስድቡን ታግሦ ይቀበል የነበረ። ወዘአምሳለ
ዝንቱ ። ነሣሣለትና ይህን የመሰለ ሥራ ይሠራ የነበረ።
እስመ ፈቀደ ውእቱ በዝንቱ
ከመ ይንሥት ጥበቦ ለሰይጣን ። በዚህ የሰይጣንን ጥበብ ሊያፈርስበት ስለወደደ ነው አንድም ወዷልና ስለዚህ ነው ።
እሰመ ውእቱ ኮነ ሶበ ይሬኢ
ተአምረ ወመንክረ ይፈርህ ወይቴክዝ ።
ኮነ ያለውን ይሬኢ ብሎ አመጣው
እሱ ተአምራቱን ባየ ጊዜ ይፈራ ያዝን ነበርና
ወይርሕቅ እምትውክልና ቦቱ
ወተሣልቆት ላዕሌሁ እሱን እቆራኛለሁ ከማለት በሱ ከመዘበት ይርቅ ነበርና ። ወአመ ርእየ ምንተኒ እምነ ሕጸታት ወጽርዓታት ይትፌሣሕ።
የሰውነት ሥራ ባየበት ጊዜ
ግን የላሜ ልጅ ያውራዬ ውላጅ ብሎ ደስ ይለው ነበርና ። ወይትኤበይ ።
ይታበይ ነበርና ።
ወይትመየጥ ኀበ ትውክልና
ቦቱ
እሱን እቆራኛለሁ ወደማለት
ይመለስ ነበርና
ከመ ሙቁሕ ውስተ እዴሁ።
በእጁ እንደ ተያዘ አድርጎ
ወሞኦ እንከ ። ድል ነሣው፤
ወነሠተ ጥበቢሁ በዛቲ ገጻት
ንሥተታት ዘዘዚአሃ ኩለንታሃ ብይንት ።
እየራስ እየራሷ የጎላ የተረዳ
መለየትን በተለየች የፈረሠች በምትመሰል በሰውነቱ ሥራ ጥበቡን አፈረሠበት ።
ወተከሥተት ሎቱ ተመውኦቱ
ድል መሆኑ ተገለጸችለት።
ወጸርዓት ጥበቡ። ጥበቡ ዛገች።
ወጽዕቀቶ ቦቱ ስሕተቱ ወምክንያቱ
እምተቃርናተ ተአምራት ብሩሃት ወንሥተታት ክሡታት።
የጎላ የተረዳ መፍረሰን የፈረሱ
የሚመስሉ ተአምራትን ከመቃወሙ የተነሣ ስሕተቱ ምክንያቱ ወለሌ አሰኘችው
ሐተታ የሰውነቱን ሥራ ሲሠራ የአምላክነቱ የፈረሰ ይመበሰላል
የአምላክነቱን ሥራ ሲሠራ የሰውነቱ የፈረሰ ይመስላልና ያንንም ንሥተታት አለ።
ወኮነት ልማድ ንብርተ ለካህናት
አይሁድ።
ለካህናተ አይሁድ የለመደች
ሥርዓት ነበረች አንድም ኮነት ልማድ ንብርተ ፤ ሥርዓት የጸናች ሁና ነበረች ።
ከመ ይፍትሑ ላዕለ ጊጉያን
።
በበደለኞች ይፈርዱ ዘንድ
ቀተልት ወሠረቅት ወፈያት
በስቅለት ።
ነፍስ በገደሉ ሞትን በሠረቁ
ግርፋትን በወምበዴ ስቅለትን ይፈርዱ ዘንድ የቀረው ቅጣቱ ስልት ስልት አለው ለወምበዴ ግን ስቅለት ነው።
ወአልሆሰሰ ሎሙ ፀራዊ ከመ
ዝንቱ ውእቱ ኢየሱስ ዘነሠተ ሕገ ወገብረ ተአምራት ወመንክራት በዕለተ ሰንበት።
ሥርዓት አፍርሶ ቅዳሜ ተአምራትን
ያደረገ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ጸላዒ ዲያብሎስ ሹክ አላቸው ዝንቱ ብእሲ ዘኢየዓቅብ ሰንበተ ኢኮነ እምእግዚአብሔር እንዲሉ አደረጋቸው
ወኮኑ ሎቱ አርድእት ብዙኃን እምነ አይሁድ ከአይሁድ ወገን ብዙ ደቀ መዛሙርት እንዳሉት ሹክ አላቸው ናሁ ኩሉ ዓለም ተለዎ ድኅሬሁ ኢተአምሩኑ ከመ አልቦ ዘንበቁዕ እንዲሉ አደረጋቸው
ወእምከመ ተሰምዓ ዝ ግብር
ከመዝ ይተልውዎ አይሁድ ኩሎሙ በእንተ ዘርእዩ እምዕበየ ተአምራት ዘላዕሌሁ ።
ተአምራቱ የታወቀ የተነገረ
እንደሆነ በሥልጣኑ ካደረገው ከተአምራቱ ብዛት ወገን አንድም ከፍጹም ተአምራቱ ወገን ስለ አዩ መላው አይሁድ እንዲያምኑበት ሹክ
አላቸው ዝንቱ ብእሲ ብዙኀ ተአምረ ይገብር ወእመ ኀደግናሁ ከመዝ
ይመጽኡ ሰብአ ሮሜ ወይነሥኡ ብሔረነ ወሕዝበከነኒ እንዲሉ አደረጋቸው።
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
05/06/2011 ዓ.ም
No comments:
Post a Comment