====================
የጌታችን
የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ
ማቴዎስ እንደ ጻፈው ።
ምዕራፍ
፩።
******
በእንተ
ልደተ ክርስቶስ።
፲፰፤
ወለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመዝ ውእቱ ልደቱ።
******
፲፰፤
የነትዕማርን የነራኬብን የነሩትን ሲናገር መጥቶ ነበርና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደቱ እንዲህ ነው አለ። ከጥንት ሲነገር ሲያያዝ
የመጣው ነው እንጂ እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ አይደለም።
ወሶበ
ተፍኅረት ማንሻ አንድም ወለእግዚእነሰ ይላል በዘር በሩከቤ የሚወለዱ የአበውን ልደት ሲናገር መጥቶ ነበርና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ
ግን ልደቱ እንዳህ ነው አለ። እንበለ ዘር ነው ከመዝ ያለውን ያመጣዋል። ወሶበ ተፍኅረት እሙ ማርያም ለዮሴፍ። ሉቃ ፩፥፳፯። እናቱ
እመቤታችን ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ።
ዘእንበለ
ይትቃረቡ ተረክበት ጽንስተ እንዘ ባ ውስተ ማኅፀና እመንፈስ ቅዱስ።
ዘእንበለ
ይትቃረቡ ዘእንበለ ይትራከቡ ይላል። እሱ ሴት እንደሆነች ሳያውቃት እሱዋ ወንድ እንደሆነ ሳታውቀው ዮሴፍ ጠባቂ ሳላት አጋዥ ሳትሻ።
አንድም ድንጋሌ ሥጋ ድንጋሌ ነፍሰ ሳላት። አንድም እምዘ ባ ካላት ከባሕርይዋ በግብረ መንፈስ ቅዱስ ጸንሳ ተገኘች። ወገባሪሁሰ
ለውእቱ ሥጋ መንፈስ ቅዱስ እስመ ውእቱ ቀብዖ ወተዋሐደ ቦቱ አምላክ ቃል እንዲል። ይህ እም በ ሲሆን ነው። እስመ እም ይተረጐም
ለኀበ ብዙኅ ፍና እንዲል።
ሰማያት
ወምድር ተፈጥሩ እምእግዚአብሔር አዳም ወሔዋን ተፈጥሩ እምእግዚአብሔር እንዲል። እመንፈስ ቅዱስም ቢል በመንፈስ ቅዱስ ተከፍሎ ኑሮበት
አይደለም። አነጻት ሲል ነው እንጂ። ወአኮ ዘቦቱ ሥጋ ለመንፈስ ቅዱስ አላ መንፈስ ቅዱስ አንጽሐ ሥጋሃ ለማርያም ወረሰያ ድሉተ
ለተወክፎ ቃለ አብ እንዲል። አነጻትም ቢል ኑሮባት አነጻት ማለት አይደለም ከለከላት ሲል ነው እንጂ። ውእቱሰ ንጹሕ እም፫ቱ ግብራት
እለ ሥሩዓን በእጓለ እመሕያው ወእሙራን ቦሙ ዘውእቶሙ ሩካቤ ወዘርዕ ወሰስሎተ ድንግልና እንዲል። ከለከላትም ቢል ብታደርገው ዕዳ
የሚሆንባት ሁኖ አይደለም አላደረገችውም ሲል ነው እንጂ። ከዚያ ሁሉ ወኮነ ይስሐቅ ያፈቅሮ ለዔሳው እስመ ዘውእቱ ነዐወ ይሴሰይ
ብሎ ወያዕቆብሰ ንጹሕ እምዝንቱ ይላል። አሁን በኤሳው አድኖ መብላት ዕዳ
ሁኖበትን ነው? ያዕቆብን አላደረገውም ድልድል ቅምጥል ከቤት ዋይ ነው ሲል ነው እንጂ።
ልደቱን
በዘር ያላደረገው እንበለ ዘር ያደረገው ስለምን ቢሉ ቀዳማዊ ልደቱን ለመግለጥ። አምስት ሽህ አምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም ከእመቤታችን
ያለአባት መወለዱ ቅድመ ዓለም ከአብ ያለእናት እንደተወለደ ያስረዳልና። ልደት ቀዳማዊ ተዓውቀ በደኃራዊ ልደት እንዲል።
ዳግመኛ
በዘር በሩካቤስ ተወልዶ ቢሆን ዕሩቅ ብእሲ ባሉት ነበርና። ሶበሰ ተወልደ በሩካቤ ብእሲ ወብእሲት ዘከማየ ብዙኃን እምተኃዘብዎ ወእምረሰይዎ
ሐሰተ እንዲል።
ያውስ
ቢሆን ልደቱን ተፈትሖ ካላት ያላደረገው ተፈትሖ ከሌላት ያደረገው ስለምን ቢሉ። ትንቢቱ ምሳሌው እንደተፈጸመ ለማጠየቅ። ትንቢት
ናሁ ድንግል ትፀንስ ወትወልድ ወልደ ተብሎ ተነግሯል። ምሳሌም አዳም ከኅቱም ምድር ተገኝቷል ጌታም በኅቱም ማኅፀን ለመገኘቱ ምሳሌ
ነውና። ሔዋን ከኅቱም ገቦ ተገኝታለች ጌታም ከኅቱም ማኅፀን ለመገኘቱ ምሳሌ ናትና። ቤዛ ይስሐቅ በግዕ ከኅቱም ጒንድ ተገኝቷል።
ቤዛ ዓለም ክርስቶስም በኅቱም ማኅፀን ለመገኘቱ ምሳሌ ነውና። ጽምዓ እስራኤልን ያበረደ ውሀ ከኅቱም ኰኵሕ ተገኝቷል ጽምዓ ነፍሳትን
ያበረደ ማየ ሕይወት ጌታም በኅቱም ማኅፀን ለመገኘቱ ምሳሌ ነውና። ጽምዓ ሶምሶንን ያበረደ ውሀ ከኅቱም መንሰከ አድግ ተገኝቷል ጽምዓ ነፍሳትን
ያበረደ ማየ ሕይወት ጌታም በኅቱም ማኅፀን ለመገኘቱ ምሳሌ ነውና። ትንቢቱን አውቆ አናግሯል። ምሳሌውንም እንጂ አውቆ አስመስሏል።
ፍጻሜው እንደምን ነው ቢሉ ከመ ትኩን መራሂተ ለሃይማኖት ዓባይ እንጂ ይላታል። ድንግል ወእም ስትባል መኖሯ አምላክ ወሰብእ ሲባል
ለመኖሩ ምሳሌ ነውና።
ስትወልደው
ማኅተመ ድንግልናዋ አለመለወጡ ሰው ሲሆን ባሕርየ መለኮቱ ላለመለወጡ ምሳሌ ናትና።
******
፲፱፡
ወዮሴፍሰ ፈኀሪሃ እስመ ጻድቅ ውእቱ ኢፈቀደ ይክሥታ።
******
፲፱፡
እጮኛዋ የሚሆን ዓቃቢሃ ተለአኪሃ አገልጋይዋ ጠባቂዋ የሚሆን ዮሴፍ
ግን ደግ ነውና ሊገልጣት ሊገልጥባት አልወደደም። አላ መከረ ጽሚተ ይኅድጋ ትቷት ሊሄድ ወደደ እንጂ።
ሐተታ
ይህን ደግነቱን ያስቀርበታልን በኦሪት ታዞ የለምን ሚስቱን የጠረጠራት እንደሆነ ውሀ በመንቀል የገብስ ዱቄት አድርጐ ሚስቱን ይዞ
ይሄዳል ከመድረኩ ስትደርስ ሊቀ ከህናቱ ክንንብሽን ግለጭ ይላታል ይግለጥብኝ በዪ ሲላት ነው። በኦሪቱ የሚደገም አለ ያነን ደግሞ
ሕራረ ዕጣኑን ጨምሮ በጥብጦ ባልሽ የጠረጠረሽን አድርገሽው እንደሆነ ሥጋሽ ይበጥ ቁርበትሽ ይላጥ አጥንትሽ ይርገፍ፤ አላደረግሽው
እንደሆነ በወንድ ልጅ ተበከሪ ብሎ ይሰጣታል። እርሷም መርገሙ ይደረግብኝ በረከቱ ይሁንልኝ ብላ ትጠጣዋለች። ይህ ደግነቱን ያስቀርበታልን
በኦሪቱ ታዞ የለም ቢሉ ዮሴፍ ጻድቀ ወንጌል ነው እንጂ መቸ ጻድቀ ኦሪት ነዋ።
******
፳፡
ወእንዘ ዘንተ ይሔሊ ናሁ አስተርአዮ መልአከ እግዚአብሔር ለዮሴፍ በሕልም።
ታሪክ
…
******
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ
በየነ
ደብረ
ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
21/06/2011
ዓ.ም
No comments:
Post a Comment