====================
ወኢትረከቡ ላዕሌሁ ጌጋየ
ዓቢየ ዘእንበለ ዘተንግሩ ለጲላጦስ መኮንን።
ለጲላጦስ ከመንገር በቀር
ለሞት የሚያበቃው ነገር አታገኙበትም አላቸው።
እስመ ዝንቱ ገብረ ዲቤሁ
ፅርፈተ ላዕለ እግዚአብሔር ወላዕለ ነጋሢ ሰንበትን በመሻሩ ላይ እግዚአብሔር ነኝ ንጉሥ ነኝ አለ ብላችሁ ለጲላጦስ ከመንገር በቀር
ለሞት የሚያበቃ በደል አታገኙበትም።
እስመ ውእቱ ይብል ቦ ጊዜ
ከመ ወልደ እግዚአብሔር ውእቱ ወልደ እግዚአብሔር ነኝ ይላልና ወልደ እግዚአብሔር ነኝ አስብላችሁ
ወቦ ጊዜ ከመ ንጉሠ አይሁድ
ወእቱ።
የአይሁድ ንጉሥ ነኝ ይላልና
የአይሁድ ንጉሥ ነኝ አለ ብላችሁ ፤ አንድም እየራሱ ለማውጣት ወልደ እግዚአብሔር እንደሆነ የሚናገርበት ጊዜ አለና እግዚአብሔር
ነኝ አለ ብላችሁ። ንጉሥ እንደሆነ የሚናገርበት ጊዜ አለና ንጉሥ ነኝ አለ ብላችሁ ለቄሣር ከመንገር በቀር ሌላ በደል አታገኙበትም፡፡
ወንሕነሰ አልብነ ንጉሥ ዘእንበለ
ቄሣር፤
ለኛስ ከቄሣር በቀር ያለቄሣር
ሌላ ንጉሥ የለንም እንዲሉ አደረጋቸው ሐተታ እንዲሁም ባሉ ጊዜ በሥጋቸው ቄሣር በነፍሳቸው ዲያብሎስ ሰልጥኖባቸዋል፡፡
ወናሁ ፈታሕነ ላዕሌሁ በሞተ
ስቅለት።
ስቅሎ ስቅሎ እንዲሉ አደረጋቸው
።
ወተሰመዓ ነገር ከመ ጲላጦስ
ተሰጥዎሙ በዘፈትሑ ቦቱ ላዕሌሁ ወአውሥኦሙ ለሊሁ በሥምረቱ ። ስቅሎ ቢሉት ጲላጦስ ሊያድነው ወዶ ምንተ እኩየ ዘገብረ በዘይመውት
ብሎ እንደመለሰላቸው ታውቋል ተነግሯል ።
ወመጠወ ነፍሶ ለሞት በፈቃዱ
ኅሪት ከመ ይቤዝዎ ለአዳም እሞት ።
አዳምን ከሞት ያድነው ዘንድ
ባማረ በተወደደ ፈቃዱ ነፍሱን ከሥጋው ለየ።
እስመ ሞትሰ እምደለዎ ለአዳም
ስቁለ ዘበኃሣር ጨርቅ ታጥቆ ግንድ ተሸክሞ ተዋርዶ ተሰቅሎ መሞት ለአዳም በተገባው ነበር አንድም ተዋርዶ ተሰቅሎ መሞትስ ለአዳም
በተገባው ነበር ታሪክ ኤልሳዕ መምሩን ኤልያሰን ሸኝቶ ዮርዳኖስን ተሻግሮ ኢያሪኮ ገብቶ ሲያስተምር ሰው በዛ ጉባዔ ሰፋ ደቀ መዛሙርቱ
ጸበበነ ማኅደር ንዑ ንግዝም ዕፀ ወንሕነፅ ካልዓ ማኅደረ ብለው ሄዱ እሱም መምህረ ትሕትና ነውና አብሯቸው ሄደ በዮርዳኖስ ዳር
ሲቆርጡ ወተነጽላ ማኅጼሁ ወቦአ ውስተ ማይ እንዲል ከዛቢያው ወልቆ ብረቱ ከውኃ ገባ፡፡ ወዝኒ ኅቡይ እግዚእየ ጌታዬ ይህም የተውሶ
ጠፋ ተጨርሶ አለው የገባበትን አሳየኝ አለው አሳየው ቅርፍተ ዕፅ
ቀርፎ አመሳቅሎ ከውኃው ላይ ቢጥለው የማይዘግጠው ቅርፍት ዘግጦ የዘገጠውን ብረት ይዞት ወጥቷል ። እንደዚህም ሁሉ ሕማም ሞት የማይገባው
ጌታ ሙቶ ሞት የሚገባው አዳምን የማዳኑ ምሳሌ ጥምቀትም የሞቱ ምሳሌ ነውና።
በእንተ ዘተዓደወ ትእዛዘ
ፈጣሪሁ።
ከፈጣሪው ትእዛዝ ስለወጣ
ወኮነ ቀታሌ ርእሱ።
ራሱን አጥፊ ስለሆነ ።
እስመ በፈቃዱ አስተዳለወ
ሞተ ለርእሱ ወዶ ራሱን አጥፊ ሁኑዋልና ፤ አንድም ራሱን ለመጉዳት ሞትን አስፈርዷልና።
ወዘዕውቅሰ ለእግዚእነ ኢየሱስ
ክርስቶስ ኢኮነ ምጽአቱ ወተሠግዎቱ ዘእንበለ ከመ ይፈጽም ዘረከቦ ለአዳም።
ጌታችን ኢየሱስ ከርስቶስ
ሰው መሆኑ አዳምን ያገኘውን ነገር ለመፈጸም ነው ለሌላ እንዳይደለ የሚያስታውቅ የሚያስረዳ ነገር፤
በጽድቁሰኬ አምጽአ ሞተ ላዕለ
ርእሱ ዘድልው ላዕለ አዳም ።
በአዳም የተፈረደ ሞትን በራሱ
አደረገው ።
ወተወክፎ እንከ ውስተ ሥጋሁ።
በሥጋው ተቀበለው ።
ዘውእቱ ጠቢኦቱ፤
ያውም ጭከናው ነው፤ ዘውእቱ
ጠባይዒሁ ይላል ባሕርዩ በሚሆን በሥጋ ተቀበለው።
እስከ ቤዘዎ እሞት ፤
አዳምን ከሞት እስኪያድነው
ከመ ይከሥት ለነ በውእቱ
ፍኖተ ትሩፋት በዚህ የትሩፋትን ሥራ ይገልጽልን ዘንድ።
እስመ ውእቱ መጠወ ነፍሶ
ለሞት እምድኅረ ተመክሮቱ ውስተ ዓውደ ምኩናን።
እሱ ባደባባይ በመከራ ከተፈተነ
በኋላ ተሰቅሎ ነፍሱን ከሥጋው ለይቷልና ።
ወኢተረክበ ሎቱ ጌጋይ ወኢነውር
በዘይትኴነን ቦቱ።
ነገር ግን ይሙት በቃ በሚፈረድበት
ገንዘብ ይፈረድበት ዘንድ ነውር በደል አልተገኘበትም።
ወበእንተዝ ኮነ ጲላጦስ ሰማዕተ።
ነውር በደል ስላልተገኘበት
ጲላጦስ መሰከረ ።
ወይቤሎሙ ለሕዝብ እሰመ ዝንቱ
ብእሲ ንጹሕ ወጻድቅ ውእቱ ወኢተረክበ ላዕሌሁ ኃጢአት ።
ጻድቅ ንጹሕ ነውና ኃጢአት
አልተገኘበትምና ።
ነሥአ ማየ ወተሐፅበ እዴሁ
ወይቤ ንጹሕ አነ እምደሙ ለዝ ብእሲ ጻድቅ ወኄር። ወይቤሎሙና ይቤ አንድ ወገን በዚህ ሰው ደም ከሚመጣ ፍዳ ንጹሕ ነኝ ብሎ ውኃ
አስመጥቶ ባደባባይ ታፀበ ።
በከመ ሰምዓ ኮነ መጽሐፍ
።
ወንጌል ነሥአ ማየ ወተሐጽበ
እዴሁ ብሎ እንደተናገረ ፤ ታሪከ በአዕሩገ እስራኤል ልማድ ከሀገርና ከሀገር መካከል ሰው ሙቶ የተገኘ እንደሆነ ያ ሰው ለሞተበት ስፍራ አቅራቢያ በሚሆን ሀገር ያሉ
ሰዎች ውኃ በመንቀል ይዘው ጊደር ነድተው ከበረሃው ይወርዳሉ ቋንጃዋን
ይመቷታል ትወድቃለች የዚህን ሰው ደም እኛ አላፈስስንም ያፈሰሰውንም አላየንም ብለው ይታጠባሉ ከገዳዩ ወገን ሲደርስ መወየብ ይጀምራል
ከገዳዩ ሲደርስ ፈጽሞ ደም ይሆናል ። ምእመናንም ጥምቀትን ገንዘብ ማድረጋቸው መናገር ነው ።
ወሶበ ኮነ ከሃሌ ላዕለ ኩሉ
ግብር በእንተ ተሠግዎቱ በፍጥረትነ ፈቀደ ሐሚመ ህየንተ ክሂሎቱ ፤ ባሕርያችንን ስለ ተዋሐደ ሁሉንም ማድረግ የሚቻለው ቢሆን የከሃሊነቱ
ለውጥ የከሃሊነቱ ፈንታ ከሃሊ ሲሆን ወዶ መከራውን ተቀበለ ።
ወተትሕተ ህየንተ ልዕልናሁ
።
የልዕልናው ለውጥ የልዕልናው ፈንታ ልዑል ሲሆን ተዋረደ
ወሞተ ህየንተ ኃይሉ።
የኃያልነቱ ለውጥ የኃያልነቱ ፈንታ ኃያል ሲሆን ሞተ ወእፎኑመ ማንሻ ። አንድም ከሃሊ ባለው
ከሃሌ ይላል ባሕርያትንን ስለ ተዋሐደ ሁሉን ማድረግ የሚቻለው እሱ ወዶ መከራ ስለ ተቀበለ ስለተዋረደ ከሞተ፤
ወእፎኑመ ንሕነ ምኑናን ወጽቡላን
ወምስኪናን ዘኢንትመሰል ቦቱ፤
ምኑናን ጽቡላን ምስኪናን
የምንሆን እኛ በመከራ እሱን የማንመስል እንደምን ይሆን ።
ሶበሰ ኮነ እግዚእነ ሞዖ
ለሰይጣን በኃይሉ መዋኢት እምኢኮነ መንከረ ።
ኮነ ያለውን ሞዖ ብሎ አመጣው
ሰይጣንን ጌታችን በአምላክነቱ ድል ነሥቶት ቢሆን ባልተደነቀም ነበር ።
ወእምኮነት ዘውስቴቱ ትሩፋት
ዘኢስብሕት ወዘኢውድስት፤
ሥራው ያልከበረች ያልተመሠገነች
በሆነች ነበር አንድም እምኢኮነት ዘስብሕት ባልተመሠገነችም ነበር።
ትሩፋትሰ ስብሕት ዛቲ ይእቲ
፤
የምትመሠገንስ ትሩፋት ይህች
ናት ፤
ሙዓት ላዕለ ዝንቱ ገጽ መንክር
እንግዳ ወዕጹብ
ፈጽሞ ድንቅ እንግዳ በሚሆን
በሰውነቱ ሥራ ድል መንሣት ነው ።
ቦቱ ኮነ ፍኖት ሰፉረ ወልብው።
ፍኖት ለኀበ አቡሁ አንቀጽ
ዘመንገለ ወላዲሁ የሚባል ጌታ ሰው ሆኖ ባጭር ቁመት በጸባብ ደረት ተወስኖ በታወቀበት በሰውነት ሥራ ድል መንሣት ነው፡፡
እስከ ኃሠሠ እምኔነ ለበዊዕ
ውስተ ዝንቱ አንቀጽ ጸባብ ።
ከወገን አንዱም አንዱ እያንዳንዱ
ወደ ትሩፋት ለመግባት እስኪሻ ድረስ
ዘውእቶሙ ውሑዳን እለ ይበውኡ
ውስቴታ ፤
ወደ ትሩፋት የሚገቡ ማለት
ትሩፋት የሚሠሩ ጻድቃን ጥቂት ናቸውና ።
ወሶበ ፈቀደ ከመ ይመጡ ነፍሶ
ለሞት በሥምረቱ ኅሩያዊት ፈቀደ እንከ ሰይጣን ሞቅሖታ በፍሥሐ ወበሐሜት ።
ባማረ በተወደደ ፈቃዱ ነፍሱን
ከሥጋው ሊለይ በወደደ ጊዜ ሰይጣን ፈጽሞ ደስ ብሎት እቆራኛለሁ ብሎ ቀረበ።
ወገሠጾ እግዚአብሔር ።
ወግድ ከኔ ፤ ከኔ ምን አለህ
አለው።
ወቀፈጸ ዘእምላዕሌሁ ምክዳነ
።
ከአምላክነቱ ብርሃን ጥቂት
ብልጭ አደረገለት ። ሐተታ በጸባብ መስኮት ብርሃን እንዲገባ ይላሉ ይህስ ይበዛል ብሎ የምጣድ ብልጭልጭታ ያህል ፤
ወርእየ ኃይላት ሰማይ ድንጉጸነ
በአውደ መስቀሉ መላእከትን በመስቀሉ ዙሪያ እንደ ሻሽ ተነጽፈው እንደ ቅጠል ረግፈው እንደ ግንድ ተረብርበው አየ ። አንድም ድኑናነ
ይላል አምላክነ ክርስቶስ እያሉ ሲሰግዱ ሲወድቁ ሲነሡ አየ።
ወተጠብለለ በደዌ ፀዋግ ወፍርሃት
ፍድፉድ ፤
በጽኑ ፍርሃት ተያዘ
ወተጠየቀ ከመ ወልደ እግዚአብሔር
ውእቱ በእላንቱ ራእያት
ወቀፈጸ እምላዕሉ ምክዳነ
ወርእየ ኃይላተ ሰማይ ድንጉጸነ በዓውደ መስቀሉ ባለው ነገር ወልደ እግዚአብሔር እንደሆነ አወቀ ተረዳ ።
ወእምስምዕ እንተ ስምዓ ኮነ
አብ እምሰማይ በክሥት አመ ጊዜ ጥምቀት በፈለገ ዮርዳኖስ በተጠመቀ ጊዜ አብ ከሰማይ መጽቶ ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ብሎ በጉባዔ በዮርዳናስ
ከመሠከረለት ምስክርነት የተነሣ፤
ወዓዲ በላዕለ ደብረ ታቦር፤
ዳግመኛ በደብረ ታቦር ዝንቱ
ውእቱ ወልድየ ብሎ ከመሠከረለት ምስክርነት የተነሣ።
ወእምዝ ልህበ ልህበተ እምኔሁ።
እቆራኛለሁ ብሎ ከመቅረቡ
የተነሣ፤ የባሕርይ ልጅ መሆኑን ከማወቁ የተነሣ መጋልን ጋለ መተኮስን ተኮስ ።
ወተረፈ ቅውመ ግበ ውሣጤ ነፍሳት ዘኢይክል ያንቀለቅል፤
በእሳት ዛንጀር ታሥሮ በነፋስ
አውታር ተይዞ ወዲያና ወዲህ ማለት የማይቻለው ሆኖ ቁሞ ቀረ ወኮነት ምግባራቲሁ ኩላ ወተቃውሞ ዘምስለ እግዚእነ በቅድሜሁ፡፡
የሚሠራው ሥራ ሁሉ ከጌታ
ጋራ የሚቃወመው መቃወም ሁሉ በፊቱ እንደ ሥዕል እንደመስታዋት ተሥላ ተቀርጻ ታየችው። ዘከመ ተቃውሞቱ እንተ ተቃወመ ወትዕግልተ
እንተ ተዓገለ።
እንደ ተቃወመው መቃወም እንደ
ቀማው ቅምያ ያለ ።
እንዘ ያስተነትን ዘይመጽእ
ላዕሌሁ እመቅሠፍት በእንቲአሃ።
ስለ ስድቡ ከመቅሰፍት ወገን
በሱ የሚመጻበትን ሲያወጻ ሲያወርድ እንደ ትቢያ ያበነኝ እንደ ጢስ ያተነኝ ይሆንን እያለ ።
ወእምዝ ተዘከረ ክብራተ እንተ
ኮነት ሎቱ ቀዳሚ ምስለ መላእክት።
ከዚህ በኋላ ከመላእክት ጋራ
ያደርጋት የነበረች ክብሩን አሰበ ሐተታ ተቀብቷል ቢሉ የተመቸ አልተቀባም ቢሉ ቢጸና።
እስመ ውእቱ በሥምረቱ ጸነ
እስከ ወድቀ ወኃደገ ሎቱ እግዚእብሔር ሥልጣኖ እንቲእሁ ይግበር ባቲ ዘፈቀደ።
በሥምረቱ ብሎ ነበርና በምን
ዐውቆ ትሉኝ እንደሆነ የወደደውን እንደ ወደደ ያደርግባት ዘንድ በተፈጥሮ
የተሰጠችውን ግዕዛንኑ አልነሣውም ።
ወውእቱ ከሃሊ በነሢኦታ እምኔሁ።
ግዕዛኑን ነስቶ እንደ ሥዕል
እንደ እንስሳ ሊያደርገው የሚቻለው ሲሆን ።
ወምግባራቲሁ እንተ ቀደመት
ላዕሌሁ ዘምስለ አይሁድ ።
በአይሁድ አድሮ ሲሠራው የነበረውን
ሥራውን አስቦ ወተአግሦተ እግዚአብሔር ላዕሌሁ ዘበእንቲአሃ።
ምንም ቢበድለው እግዚአብሔር
ታግሦት እግዚአብሔር እሱን መታገሡን አስቦ ።
ወአስተዓበየ መጠነ ይፈድዮ
ለወልደ እግዚአብሔር ለወልደ እግዚአዚሔር የሚክሰውን ካሳ አበላለጠ፡፡
ሰማይ ወዘውስቴቱ
ሰማይ የኔ ገንዘብ ሁኖ በሰማይ
ያሉ ፍጥረታትም የኔ ገንዘቦች ሁነው አንድም ከመ ሰማይ ወከመ ዘውስቴቱ እንደዚሀ ሰማይ ያለ ሌላ ሰማይ ኑሮ ያ የኔ ገንዘብ ሁኖ
በዚህ ሰማይ እንዳሉ ፍጥረታት በዚያም ኑረው እኒያ የኔ ገንዘቦች ሁነው።
ምድረ ወዘዲቤሃ
ምድር የኔ ገንዘብ ሁና በምድርም
ያሉ ፍጥረታትም የኔ ገንዘቦች ሁነው ፤ አንድም ከመ ምድር ወከመ ዘውስቴቱ ፤ እንደዚህ ምድር ያለ ሌላ ምድር ኑሮ ያ የኔ ገንዘብ
ሁኖ በዚህ ምድር እንዳሉ ፍጥረታት በዚያም ኑረው እኒያ የኔ ገንዘቦች ሁነው።
ኢይከውኑ አምጣነ ቀዊሞቱ
ቅድመ ጲላጦስ ቅጽበተ ዓይን ኅድግሰ ዘኮነ ቅድመ ዝንቱ ወድኅሬሁኒ ከዚህ አስቀድሞ ከእንግዲህም ወዲህ የሚደረገውን ተወውና ዓይን
ተከድኖ እስኪገለጽ ድረስ በጲላጦስ ፊት ስላቆምሁት ካሣው ሊሆኑት አይበቁም ብሎ አበላለጠ።
ወሶበ አእመረ እግዚአብሔር
ሕሊናሁ አቅለለ ሎቱ ዕፀበ ወላህበ ።
እንዲህ ማለቱን እግዚእብሔር
ባወቀ ጊዜ እስራቱን አላላለት ግለቱን አቀዘቀዘለት ።
ከመ ይኩን ቀዊሞቱ በፍድየት
ህየንተ ፈቃደ ሥምረቱ ።
ወዶ ነፍሳትን እለቃለሁ ማለቱ
በካሣ ይሆን ዘንድ በግድ ቀማኝ እንዳይል ። አንድም ጌታ ስለ ወደደለት አነዋወሩ በዚሀ ዓለም ይሆን ዘንድ።
ወሶበ ፈትሖ እማዕሰሩ ወጠፍአ
ላህቡ ወቆመ ቅድመ እግዚእነ እንዘ ይገርር ወይስግድ ወያስተበቁዕ ።
እስራቱን ባላላለት ግለቱን
ባቀዘቀዘለት ጊዜ እየተገዛ እየሰገደ እየማለደ በጌታ ፊት ቆመ ።
ከመ ይዕትት እምኔሁ ሙስና።
ጥፋቱ ይርቅለት ዘንድ ።
አንድም ያእትት ይላል ጥፋቱን ያርቅለት ዘንድ።
ወያብሖ ለነቢር ውስተ ምድር
።
በዚህ ዓለም ለመኖር ያሰናብተው
ዘንድ።
ወያንሥእ እዴሁ እምነ አዳም
ወዘርዑ
እሱም ቁራኝነት ከአዳም ከልጆቹ
ያርቅ ዘንድ ።
እለ ተጋብኡ ውስተ ሞቅሕ
በፈቃድ ዘእንበለ አእምሮ።
ሳያውቁ ወደው በሠሩት ኃጢአት
። አንድም በነቢብ በገቢር ሳይሆን በሐልዮ በሠሩት ኃጢአት በቁራኝነቱ ካሉ ከአዳም ልጆች ቁራኝነትን ያርቅ ዘንድ ፤
ወተሠጥወ ስእለቶ ። ልመናውን
ተቀበለው።
ወአዕረጎሙ እግዚእብሔር ለአዳም
ወለኩሉ ዘርዑ እምሲአል። አዳምን ልጆቹን ከሲኦል ወደ ገነት አወጣቸው ሐተታ ዲያብሎስም ፈጽመህ ካጠፋኸኝማ ያንተስ ጠላት የኔስ
ወዳጅ በምን ይታወቃል ከፈቃድህ የወጣ ፍርፋሪ ለቅሜ ልኑር ብሎ ለምኖታል።
ወአግብኦ ኀበ ዘቀዳሚ ንብረቱ
ውስተ ገነተ ፍግዓ ተድላ ደስታ ወደሚያደርግበት ወደ ቀደመ ቦታው ወደ ቀደመ ማዕርጉ መለሰው ።
ወአኅለፎሙ ለጻድቃን ምስሌሁ
እምኃጉል፤
ጻድቃንን ከሱ ጋራ እንዳሉ
ከሲኦል አውጥቶ ገነት አገባቸው ።
ኀበ ፍትሐ ጽድቅ ወርትዕ
ቀድሞ ፍትሐ ጽድቅን ፍትሐ ርትዕን ወደሰሙባት ኋላ በፍትሐ ጽድቅ በፍትሐ ርትዕ ወደ ወጡላት አገባቸው ወኃደጎሙ ለእኩያን ህየ ውስተ
ትውከልና ፤ እኩያን ነፍሳትን ግን በሲኦል በቁራኝነት እንዳሉ ተዋቸው ።
ምስለ መላእክቲሆሙ እስከ
ዕለተ ደይን
ከለለቆቻቸው ከአጋንንት ጋራ አንድም ከፈርዖን ከሄሮድስ ጋራ እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ በሲኦል ተዋችው
።
ወእምድኅረዝ ተንሥአ እሙታን
ከመ ይምሐረነ ተንሥኦ ሥጋቲነ እምድኀረ ሞት ።
አጋንንትን ድል ነሥቶ ነፍሳትን
ከሲአል አውጥቶ ገንት ካገባ በኋላ የኛን ትንሣኤ ያስረዳ ዘንድ ተነሣ ። ለሣህል ወለደይን ወለፍትሕ ፤
ሣሕል ለጻድቃን የሚደረገው ደይን በኃጥአን የሚፈረደው። ፍትሕ የወል ነው።
ወዓርገ ውስተ ሰማያት
በተነሣ በዐርባ ቀን ዓረገ
ከመ ያጸቡ ለነ ዕርገተ ጻድቃን
ንጹሐን እምድኀረ ትንሣኤ ኀበ መንግሥት ዘድልው ሎሙ።
ዕርገት እምድኅረ ትንሣኤ ከትንሣኤ በኋላ ጻድቃን በጣዕም በመዓዛ በሥን በብርሃን ወደ ተዘጋጀችላቸው
ወደ መንግሥተ ስማያት መግባታቸውን ያስረዳ ዘንድ ዓረገ ።
ወእምዝ ፈነወ ሎሙ መንፈስ
ቅዱስ ።
ባረገ ባሥረኛው ቀን መንፈስ
ቅዱስን ሰደደላቸው
ከመ ንትመራሕ ቦቱ ኀበ ሐዊረ
ፍኖት ፤
ወድ ትሩፋት ሥራ እንመራበት
ዘንድ ማለት ትሩፋትን እንሠራበት ዘንድ ።
እንዘ ትወስድ ኀበ ሕይወት
ወመድኃኒት ፤
ፍኖት ላለው ወደ ደገኛው
ልጅነት ወደ ትንሣኤ ዘለክብር የምታደርስ አለ ፤ ፈነወ ላለው ዋዌ ፤ የዓረቦኑን ልጅነት ወደ ደገኛው ልጅነት የሚያደርስ አለው
ወናሁ ተጠየቀ ወጸንዓ በቁዔተ ዝንቱ መጽሐፍ ንጹሕ
ከፈቃደ ሥጋ ንጹሕ የሚሆን
የዚህ መጽሐፍ በቁዔት በቁዔትነቱ ታወቀ ተረዳ።
ወብዙኀ ተኃሥሶ መፍቅድ ኀበ
አንብቦቱ ለዘኮነ ልብወ ወማዕምረ ።
ብልህ አስተዋይ የሆነ ደቀ
መዝሙር ከተመለከተው ዘንድ ልቡና የሚሻው ብዙ ምሥጢር አለበት ።
ስድስተኛ ጉባኤ፤
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
06/06/2011 ዓ.ም
No comments:
Post a Comment