Saturday, February 16, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 11


===================
ተፈጸመ ።  
አራቱ ወንጌላውያን በዘር የተባበሩበትን ጽፎ መስጠት አለቀ ። 
ወደ ኋላ ተመልሰህ አውሴብስ በል፤
አውሴብስ ለቆጵርያኖስ ። 
ታሪክ አሞንዮስ አውሳብዮስ ይህን ያህል ዓቢይ ምዕራፍ ይህን ያህል ንኡስ ምዕራፍ ይህን ያህል ዘር ብለው ጽፈው ከተለያዩ በኋላ ብልህ ደቀ መዝሙር የተለያዩበትን የተባበሩበትን ዘር ልወቅ ባለ ጊዜ እንደምን ይሆናል ባሕር ለባሕር ሲዋኝ ይኖራል ብሎ ይህን ሲሻ ቀኖና ገባ ባሥሩ ሰንጠረዥ አምሳል አሥር መሪ አኃዝ ተገልጾለት ይጽፋል ። አውሴብስ ስቆጵርያኖስ የላክው ከታብ ይህ ነው ። ዘአውሴብስ የአውሴብስ ክታብ ለቆጵሮያኖስ ትድረስለት እምአውሴብስ ይላል ። ከአውሴብስ የተላከች ክታብ ለቆጽርያኖስ ትድረስለት ፤ ቆጵርያኖስ ካህን ጨዋም ነው ይሉታል ።
ለዘአፈቅር ለእኁየ፤
ለምወደው ለወንድሜ ለ እና ለ አንድ ወገን። 
ፍሥሐ ወሰላም ወዳኅና ለከ እምኀበ እግዚአብሔር
ከእግዚአብሔር ዘንድ መንፈሳዊ ደስታ ይደረግልህ አሞንዮስ እስክንድራዊ በብዙኅ አስተሐምሞ ወጽሒቅ ገብረ ወኀደገ ለነ ዘቃለ ዘከመ ኃብሩ ፬ቱ ወንጌላውያን ወእምዝ አርእስተ ምንባባት ። 
የእስክንድርያው ሰው አሞንዮስ በብዙ ትጋት በብዙ ጻሕቅ አራቱ ወንጌላውያን የተባበሩበትን የተለያዩበትን ፤ አንድም ሰንጠረዡን ቁራኛውን አንድም ዓቢይ ምዕራፉን ንኡስ ምዕራሩን ይህን አንድ ወገን ወእምዝ አርእስተ ምንባባት ዘሩን ጽፎ ተወልን፤ ሐተታ እሱ የሚጽፍ መሪ አኃዙን ነውና አንድ ሁነው የጻፉትን ለሱ ብቻ ስጥቶ ተናገረ። ወበእንተዝ እንከ መፍትው ጥንቶ ይትልው።
ስለዚህ ማቴዎስን ሊመለከቱ ይገባል ።
ከመ ኢይኩን ሙሱነ ምንተኒ በተሊወ ንበቱ ።
በተመለከቱት ጊዜ አንድ በሚሆኑበት ዘር ልዩ እንዳይሆን ።  
ወ፫ቱኒ ኢይትኀደጉ፡፡
ሦስቱም እንዳይለያዩ፡፡
ከመ እሙንቱኒ ይድኃኑ እምተጸርዖ በንበቱ፡፡
እሳቸውን በተመለከቷቸው ጊዜ ከመለየት ይድኑ ዘንድ
ፍጹመ ሥጋ ወመለያልየ ይኩኑ።
እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ይሆኑ ዘንድ እንጂ ፤ አንድም ፍጹም ሥጋ ወመለያልይ ፤ አካል ሕዋስ የተፈጸመለት ሰው ይሆኑ ዘንድ ነው እንጂ።
ወተኣምር ለለ፩ዱ ወንጌል መካነ ትእምርቱ ፤
አእምር ሲል ነው። የያንዳንዱ ወንጌል የሰንጠረዡን ቦታ ዕወቅ።      
ወባሕቱ አሣን በዘህልው እምጻማሁ ለቀዳማዊ ብእሲ ዘነገርነ ስሞ ረከብኩ አነሂ ምክንያተ እንተ ከማሃ ትመሰል ሥርዓተ ወሐፈጥኩ ፲ተ ትእምርታተ ኊልቍ ወአንበርኩ ለከ ፤ 
አሞንዮስ እስከንድራዊ በብዙኀ አስተሐምሞ ወጽሒቀ ገብረ ወኀደገ ለነ ዘቃለ ዘከመ ኃብሩ ፬ቱ ወንጌላውያን ወእምዝ አርእስተ ምንባባት ብለን ስሙን ያነሣነው አሞንዮስ በጻፈበት በኩል እኔም በጽፈት እሷን የምትመስል እንደሷ ያለች አግኝቼ በዐሥር ሰንጠረዥ አምሳል ዐሥሩን መሪ አኃዝ ጽፌ ተውኩልህ፡፡
ወሰመይከዎ ለቀዳማዊ አሐደ።   
ወሰመይኩ አሐደ ቀዳማዊ ይላል መጀመሪያውን ሰንጠረዥ አንድ አልሁት ።
ወአኃዘ ለቀዳማዊ፡፡
የመጀመሪያውን ሰንጠረዥ መሪ አኀዝንም አንድ አልሁት ፤ ወአኀዘ ቀዳማዊ ወአኃዞ ለቀዳማዊ ይላል ወውአደ ኃብሩ አርባዕቲሆሙ ቃላተ ማቴዎስ ወማርቆስ ሉቃሰ ወዮሐንስ ፤    
ወእደ ኃብሩ ይላል ፤ አራቱ በዘር ከተባበሩባት ዘንድ የተባበሩበትን ሰንጠረዥ አንድ አልሁት መሪ አኀዙንም አንድ አልሁት።
ወውስተ ዳግም ፫ቱ ማቴዎስ ወማርቆስ ወሉቃስ ፤ በሁለተኛው ሰንጠረዥ ሦስቱ የተባበሩብትን ሁለተኛውን ሰንጠረዥ ሁለት አልሁት መሪውንም አኀዝ ሁለት አልሁት ወውስተ ሣልስ ሠለስቱ ማቴዎስ ወሉቃስ ወዮሐንስ ሦስቱ የተባበሩበትን ሦስተኛው ሰንጠረዥ ሦስት አልሁት መሪውንም አኀዝ ሦስት አልሁት። ወውስተ ራብዕ ፫ቱ ማቴዎስ ወማርቆስ ወዮሐንስ ሦስቱ የተባበሩበትን አራተኛውን ሰንጠረዥ አራት አልሁት መሪውንም አኀዝ አራት አልሁት፡፡ ወውስተ ኃምስ ፪ቱ ማቴዎስ ወሉቃስ ።  ሁለቱ የተባበሩበትን አምስተኛውን ሰንጠረዥ አምስት አልሁት መሪውንም አኀዝ አምስት አልሁት፡፡ ወውስተ ሳድስ ፪ቱ ማቴዎስ ወማርቆስ ። ሁለቱ የተባበሩበትን ስድስተኛውን ሰንጠረዥ ስድስት አልሁት መሪውንም አኀዝ ስድስት አልሁት፡፡ ወውስተ ሳብዕ ፪ቱ ማቴዎስ ወዮሐንስ ። ሁለቱ የተባበሩበትን ሰባተኛውን ሰንጠረዥ ሰባት አልሁት መሪውንም አኃዝ ሰባት አልሁት ። ወውስተ ሳምን ፪ቱ ማርቆስ ወሉቃስ ። ሁለቱ የተባበሩትን ስምንተኛውን ሰንጠረዥ ስምንት አልሁት መሪውንም አኃዝ ስምንት አልሁት፡፡ ወውስተ ታሥዕ ፪ቱ ሉቃስ ወዮሐንስ ፤ ሁለቱ የተባበሩበትን ዘጠነኛውን ሰንጠረዥ ዘጠኝ አልሁት መሪውንም አኃዝ ዘጠኝ አልሁት ፤  ወውስተ ዐሥር ዘዘዚአሆሙ በዐሥረኛው ሰንጠረዥ አንዱም አንዱ እያንዳንዱ የተለያዩበትን ሰንጠረዥ ዐሥር አልሁት መሪውንም አኃዝ ዐሥር አልሁት ወከመዝ ውእቱ ሥርዓቱ ዘተሠርዓ ።
አራቱ እንደ ተናገሩ እንደ ጻፉ የተጻፈው ጽፈት ይህ ነው።
ወነገሩ ለለአሐዱ ወንጌል በኊልቈ አኃዙ ፤
የያንዳንዱ የወንጌል ዘሩ በንኡስ ምዕራፉ አኃዝ ቍጥሩ ነው ፤ ወይዌጥን እም ቀዳማዊ መጸሐፈ ልደቱ ሲል አንድ ይላል  ወዳግም ወኩሎንኬ ሲል ሁለት ይላል ። ወሣልስ ለእግዚእነ ሲል ሦስት ይላል እስከ ይትፈጸም መጽሐፉ እንዲህ እያለ ማቴዎስ እስኪፈጸም ፤ አንድም መላው እስኪፈጸም እንዲህ እያለ ይሄዳል ።
ወበ ኊልቈ አኃዙ ቦቱ አኃዝ ዘበሲራኩ ዘያኤምር ውስተ አይ ሥርዓተ ቀመር ሀሎ ።
የተባበሩበት የተለያዩበት ዘር በማናቸውም ሰንጠረዥ ጽፈት እንዳለ የሚያስረዳ በየንኡስ ምዕራፍ አኃዛቸው ቍጥር በሲራኩ የተጻፈ መሪ አኃዝ አለ፡፡
ወእምከመ አሐዱ ከመ ውእቱ ውስተ ቀዳማዊ ፤
መሪ አኃዙን አንድ ያለ እንደሆነ በመጀመሪያው ሰንጠረዥ እንዶሆነ ይታወቃል ።
ወአእምከመ ክልኤቱ  ከመ ውእቱ ውስተ ዳግማዊ መሪ አኃዙን ሁለት ያለ እንደሆነ በሁለተኛው ሰንጠረዥ እንደሆነ ይታወቃል ።
ወእምዝ እስከ ይትፌጸም ዐሠርቱ ሥርዓት፡፡ ከዚህም በኋላ ዐሥሩ ሰንጠረዥ አስኪያልቅ መሪ አኃዝ እንዲህ እያለ ይሄዳል ።
ወእምከመ ቦ ፤አመ ከሠትከ እምአርባዕቱ ወንጌል ካራቱ ወንጌል የሻኸው ኑሮህ ብትገልጽ።
ወፈቀድክ ታእምር እለ መኑ እሙንቱ እለ ኃብሩ ቃለ ተኃሥሥ ውስተ አቅማሪሁ ወትረከብ ።
በዘር የተባበሩ እነማንም እንደሆኑ ልታውቅ ብትወድ ከሰንጠረዡ ገብተህ ፈልግ ታገኛለህ ፤
እእሚረከ አኀዘ ኊልቈ ዘበሲራኩ ።
በሲራኩ የተጻፈ መሪ አኃዙን ዐውቀህ ፤

ወእሉሂ ውስቴቱ ።   
እሳቸውም በሰንጠረዡ ተጽፈዋል።  
ከመ ውስተ ግልየቱ ኊልቈ አኃዙ ለለአሐዱ ወንጌል ዘዘዚአሆሙ።  እየራስ እየራሳቸው እያንዳንዱ ወንጌል የመሪ አኃዛቸው ቍጥር በግልየቱ እንደ ተጸፈ እሳቸውም በሰንጠረዡ ተጽፈዋል ።
ወዘከመሂ ኃብሩ ቃለ ዘከመ ኃብሩ አርባዕቱ ወሠለስቱ ወክልኤቱ ፤
አራቱ ሦስቱ ሁለቱ የተባበሩበበትን እንደ ተባበሩ ።
ወአሐዱሂ ዘከመ ይቤሉ ፤
የተለያዩበትን እንደ ተለያዩ እንደ ተናገሩ ።
ወጸሐፍኩ ውስተ ቀዳማዊ ቀመር ዘከመ ኃብሩ አርባዕቲሆሙ ።
አራቱ አንደ ተባበሩ በመጀመሪያው ሰንጠረዥ ጽፌልሃለሁ ።
ውስተ ግልየቱ ለቀመር ኊልቈ አኃዞሙ ለለአሐዱ ወንጌል ።
በሰንጠረዥም የያንዳንዱ ወንጌል የመሪ አኃዛቸው ቍጥር ተጽፏል ።
ወከማሁ ውስተ ወንጌልሂ ጽሑፍ ኊልቈ አኃዙ ከማሁ ለማለት ነው የመሪ አኃዛቸውም ቍጥር በወንጌል ተጽፏል ።
በዘየአምርዎ ኀበ ኃብሩ ፬ቱ በሲራከ አኃዙ ወውእደሂ ፫ቱ ወውእደሂ ፪ቱ ወ፩ዱሂ ። በአኀዘ ሲራኩ ሲል ነው በሲራኩ የተጻፈውን መሪ አኃዙን ዐውቀው አራቱ ሦስቱ ሁለቱ የተባበሩበትን እንደ ተባበሩ ፤ ወ፩ሂ የተለያዩበትን እንደ ተለያዩ ፤ በሚያውቁት ገንዘብ ያውቁት ዘንድ ይህን የሚያውቁበት መሪ አኃዝ ጽፈልሃለሁ ።
ወእምከመ ረከቡ እንዘ ያነብቡ አኃዘ ዘበሲራኩ ። ሲመለከቱ በሲራኩ የተጻፈውን መሪ አኃዙን ያገኙ እንደሆነ ፤ ወፈቀዱ ያእምሩ አስማቲሆሙ ለእለ ኃብሩ ።
በዘር የተባበሩትን ስማቸውን ሊያውቁ ቢወዱ ይኅሥሥ ውስተ አቅማሪሁ ወይረከቡ ፤ ከሰንጠረዥ ገብተው ይፈልጉ ያገኛሉ ።
እስመ ውስቴቱ ጽሑፍ አስማቲሆሙ ። ሰማቸው ከውስጡ ተጽፏልና ።
ወጸሐፍኩ ዓዲ ትእምርት ውስተ ወንጌል ትእምርተ አኃዝ ዘበሲራኩ ።
ዳግመኛም በወንጌል የአንቀጽ ምልክት ጽፌያለሁ ኀበ ገብረ ተአምራተ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተአምራት ካደረገበት የጌትነቱን ሥራ ከሠራበት ዘንድ ፤ ሐተታ ሰንደቅ አላማ ዙፋን መከዳ ድባብ ማሰሪ ይቀርጻል ።
ኀበሂ አዘዘ ወኀበሂ ገሠጸ ባሕረ ወኀበሂ መሐረ ወኀበሂ ነበረ ። 
ፃአ መንፈሰ ርኩስ ብሎ ካዘዘበት ባሕርን ነፋሳትን ከገሠጸበት ከተራራ ተቀምጦ ካስተማረበት ላይ፤ ሐተታ ወምበር መቋሚያ መነሳንስ ድባብ ማሰሪ እንደ ጃንጁላቴ ዖፍ አድርጎ ይቀርጻል ።
ወትእምርት ኀበ አኃዙ ማዕተበ መስቀል ። ነገረ መስቀልን ከሚያነሣሣበት ቦታ የመሰቀል ምልክት አለ፡፡ ሐተታ እንዴት አድርጎ ይቀርጻል ። ነገረ በቀልን ከሚያነሣበት እንደ እግረ ገመል አድርጎ ይቀርጻል ግመል በቀለኛ ናት አጥብቆ የመታትን እስከ ስድስት እስከ ሰባት ዓመት አትረሳውም ስፍራ ሲመቻት ገደል ገፍታ ትጥለዋለች ባጥ ብሳ ትረግጠዋለች ። ነቢያትን ከሚያነሣበት ጋ ጋ ጋ እያለ ይጽፋል ። ጋጋና ማለት ነው። ጋ ጋ ኖ እስኪነጋ እየጮኸ እንዲያድር ነቢያትም ጌታ እስኪወለድ ትንቢት ተናግረዋልና ፤ አንድም ጋጋና ቀን ደጋ ወጥቶ ሲጮህ ይውላል ሌሊት ቆላ ወርዶ ያድራል። ነቢያትም ሲዖል መውረድ አልቀረላቸውም በእደ እግዚአብሔር ተጠብቀዋል እንጂ  ሐዋርያተን ከሚያነሣበት ጌ ጌ ጌ እያለ ይጽፋል ። ባለ ጌ ማለት ነው ። ባለ ጌ ባለርስት ነው ፤ ሐዋርያትም የመንግሥተ ሰማይ ባለቤቶች ናቸውና፤ ይህንንም በነጭ በጥቁር በቀይ ይቀርጸዋል፤ ቀይ ደማቸውን ያፈሳሉና ጥቁር መከራቸው ጽኑዕ ነውና፤ ነጭ ዋጋ አላቸውና ፍሥሐ ወሰላም ለነ በክርስቶሰ ፤
በክርሰቶሰ የሚገኝ ፍቅር አንድነት ይደረግልን ፤ በስመ እግዚአብሔር መሐሪ ወመሰተሣህል ስብሐት ለእግዚአብሔር ማዕርገ ወንጌል ወዝማሬ ዘበአማን ።
ስብሐት ወዝማሬ ብለህ ግጠም ፤ወንጌልን ላከበረ ለእግዚአብሔር የባሕርይ ክብር ይገባዋልና ፤ መሐሪ መስተሣህል በሚሆን በእግዚአብሔር ስም አምነው ጸሐፍዋ ፬ቱ ወንጌላውያን አራቱ ወንጌላውያን ጸፏት በተአምራት ግሁዳት እምኀበ ኩሎሙ ሐዋርያት፤ በሐዋርያት ዘንድ በተገለጸ ተአምራት ።
ወመንክራት መዋኤ ኩሉ ሕሊናት ወተከሥተ ቦቱ ጽድቅ ሃይማኖት ።
ሕሊናትን ድል የሚነሳ የሚያሳምን አንድነቱ ሦስትነቱ በተገለጸበት በተአምራት ወንጌልን ባከበረ ወአስተኃፈረ ቦቱ ስሕተተ ሰይጣናት ።
ኢትጥዓምን ኢትልክፍን ኢትግሥሥን ያሳለፈበት ወንጌልን ላከበረ ።
ወአፍለሰ ፍጥረተ እግዚአብሔር ኀበ አምልኮቱ እምድኅረ አምልኮ ጣዖት ።
ሰውን ሁሉ ከአምልኮተ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር ከገቢረ ኃጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ በመለሰበት በተአምራት ወንጌልን ላከበረ ። አንድም የመለሰባት ወንጌልን ላከበረ ።
ወፄወወ ቦቱ ፄዋዌ ዘይወስድ ኀበ ሕይወት ዘለዓለም ። ወደማያልፍ ሕይወት የሚያደርስ ምርኮኝነትን የማረከባት ወንጌልን በተአምራተ ላከበረ  አንድም ወደማያልፍ ሕይወት የሚያደርስ ምርኮኝነት የተማረኩባት ወንጌልን ላከበረ  ሐተታ ለሞት የሚሆን የነብልጣሶር ምርኮ አለና እንዲህ አለ።
ወአድኃነ ሰብአ እምክህደት ወእምተታልዎተ ፀር ወሞተ ኃጢአት ።
ሰውን ከክህደት ከሰይጣን ምርኮኝነት ቁራኝነት በኃጢአት ከሚመጣ ፍዳ ያዳነባት ወንጌልን በተአምራት ላከበረ ።
ወፈጸመ ሕገ ርትዕ በሕገ ትሩፋት ፤
ኢትቅትልን በኢታምጽእ ኢትዘሙን በዘርእይ ያሳለፈባት ወንጌልን ፤
ወሠርዓ ተፋቅ 
ተፋቀሩ በበይናቲክሙ የምትል ወንጌልን ወምሕረተ ፤ ብፁዓን መሐርያን የምትል ወንጌልን ወአሠንዮ ፤ ሠናየ ግበሩ ለኩሉ ያለባት ወንጌልን ወገዲፈ ጥረት ።
እስመ ትፈቅድ ትኩን ፍጹመ ሑር ወሚጥ ንዋየከ ያለባት ወንጌልን ፤
ወትሕትና ብፁዓን ትሑታን ያለባት ወንጌልን ፤
ወንጽሐ ።
ብፁዓን ንጹሐነ ልብ ያለባት ወንጌልን በተአምራት ላከበረ ።  
ወለዝንቱ መጽሐፍ ቅዱስ ዘያበርሃ ቦቱ ነፍሳት ከመ ከዋከብት ወጽጌያት ።
ነፍሳት እንደ ከዋክብት የሚያበሩባትን እንደ ጽጌያት የሚያሸበርቁባትን ወንጌልን
ወለሊሁ ሕገ መድኃኒት ለኩሉ ነፍሳት 
የድኅነት ሥራ የሚሆን ወንጌልን፤
ወነቅዓ ሕይወት ለዘይትጌበሮ እምነ ኩሉ አንጋድ ከነገደ ካም ከነገደ ሴም ከነገደ ያፌት ተወልደው ለሚሠሩት የድኅነት መገኛ የሚሆን ወንጌልን ፤
ጸሐፍዋ ፬ቱ ወንጌላውያን ። አራቱ ወንጌላውያን ጻፏት ።
በአህጉር ሊሉያን ፤
በቦታ ተለያይተው የጻፏት ፤ ሐተታ ማቴዎስ በፍልስጥኤም ፤ ማርቆስ በግብጽ በሮምም ይላል ሉቃስ በመቄዶንያ ዮሐንስ በኤፌሶን ሁነው ጽፈዋል ።
ወበአዝማን ውሉጣን ።
በዘመንም ተለያይተው ጻፏት ፤ ሐተታ ማቴዎስ ጌታ ባረገ ስምንት ተፈጽሞ ዘጠነኛው ሲጀመር ቀላውዴዎሰ ቄሣር በነገሠ በመጀመሪያው ዘመን ማርቆስ ፤ ጌታ ባረገ ዐሥራ አንድ ተፈጽሞ ዐሥራ ሁለተኛው ሲጀመር፤ ቀላውዴዎስ ቄሣር በነገሠ በአራተኛው  ዘመን ፤ ሉቃስ ሀያ አንደኛው ተፈጽሞ ሀያ ሁለተኛው ሲጀመር ቀላውዴዎስ ቄሣር በነገሠ ባሥራ አራተኛው ዘመን ፤ ዮሐንስ ጌታ ባረገ በሠላሳ በሠላሳ አምስትም ይላል ። ኔሮን ቄሣር በነገሠ በሰባት ዓመት በስምንትም ይላል ሰባት ቢሉ ሲፈጸም ስምንት ቢሉ ሲጀመር ።
ወውእቶሙ ማቴዎስ ወማርቆስ ሉቃስ ወዮሐንስ፤
አራት የተባሉም ማቴዎስ ማርቆስ ሉቃስ ዮሐንስ ናቸው። 
ወለማቴዎስ ስሙ ሌዊ ፤
የማቴዎስ ስሙ ሌዊ ነው ሌዊ ይባላል ።
ወትርጓሜሁ ኅሩይ ፤ ትርጓሜውም ኅሩይ ይባላል፡፡
ወውእቱ ዘእምነገደ ይሳኮር ዘእምህገረ ናዝሬት ፤
ትውልዱ ነገዱ ከነገደ ይሳኮር ናዝሬት በሚባል አገር ነው ።
ስመ አቡሁ ዲቁ   አባቱ ዲቁ ይባላል
ወስመ እሙ ካሩትያስ ፤ እናቱ ካሩትያስ ትባላለች፡፡
ወሶበ ተጋብኡ ኀቤሁ ጉባኤ ብዙኅ እምአይሁድ ዘጸውኦሙ ወእለሂ አምኑ ወተጠምቁ ወኃሠሡ እምኔሁ ከመ ያስተጻንዕ አልባቢሆሙ ዘአእመኖሙ ቦቱ በቃል ወበመጽሐፍ ዘዜነዎሙ በልሳነ ዕብራይስጥ ወተሠጥወ ስእለቶሙ።
ያስተማራቸው ያሳመናቸው ያጠመቃቸው ከአይሁድ ወገን የሚሆኑ ብዙ ምእመናን ተሰብስበው በቃል ያለ ይረሳል በመጽሐፍ ያለ ይወረሳልና ብለው በቃል በዕብራይስጥ ያስተማራቸውን በመጽሐፍ ጽፎ ያስረዳቸው ዘንድ ጻፍልን ባሉት ጊዜ ልመናቸውን ተቀበላቸው ፤ በቃል ዘአእመኖሙ ቦቱ በልሳነ ዕብራይስጥ ያስተጻንዕ አልባቢሆሙ በመጽሐፍ ብለህ ግጠም ። 
ወወጠነ ጽሒፈ ዝንቱ መጽሐፍ በፍልስጥዔም ወፈጸማ በህንድ ዕብራይስጣዊ ።
በፍልስጥዔም ጀምሮ በህንድ ፈጸማት።
አመ ተሰዱ አርድእት እምድረ ይሁዳ በቀዳሚት ዓመት እመንግሥተ አቅሎንድዮስ ቄሣር ።
ምእመናን ከይሁዳ ወጥተው በሄዱ ጊዜ ቀላውዴዎስ ቄሣር በነገሠ በመጀመሪያው ዘመን አቅሎንድዮስ ቀላውዴዎስ ይለዋል ።
ወይእቲ በራብዕት ዓመት እምዓመተ ዕርገት ቅድስት ይችውም ጌታ ባረገ ስምንተኛው ተፈጽሞ ዘጠነኛው ሲጀመር ነው ።
ወኮነ ስምዓ በሀገረ ብስባራ ውጉረ በእብን አመ ፲ቱ ወ፪ቱ ለጥቅምት ፤
በጥቅምት ባሥራ ሁለት ቀን ብስባራ በምትባል አገር በደንጊያ ተመትቶ በሰማዕትነት ሞተ ።
ወተቀብረ በቅርጣግና ዘቄሣርያ ።
የቄሣርያ ክፍል ዕፃ በምትሆን በቅርጣግና ተቀበረ፡፡
ወለዛቲ ብሥራት ተርጐማ ዮሐንስ ወልደ ዘብዴዎስ በሀገረ እልአንሳን ።   
የማቴዎስ ወንጌልን ዮሐንስ ወንጌላዊ በእልአንሳን አስተምሯታል ።
ወሰበከ ባቲ በህንድ ወበኢየሩሳሌም ኪያሃ ሲል ነው እሷን በህንድ በኢየሩሳሌም
አስተማረ ። 
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለዓለመ ዓለም አሜን ፤
አስጀምሮ ላስጨረሰን ለእግዚአብሔር ለዘላለሙ ክብር ይግባው ።
ብሥራተ ማቴዎስ ሐዋርያ ፩ዱ እም ፲ ወ፪ቱ ሐዋርያት ጸሎቱ ወበረከቱ የሀሉ ምስለ ፍቁሩ ለዓለመ ዓለም አሜን።
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
10/06/2011 ዓም

No comments:

Post a Comment