====================
የጌታችን
የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ
ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
ምዕራፍ
፮።
******
፲፰፡ ከመ ኢያእምር ሰብእ ከመ ጾምክሙ።
******
፲፰፡ እንደ ጾማችሁ ሰው እንዳያውቅባችሁ።
ዘእንበለ አቡክሙ ማእምረ ኀቡዓት።
ሁሉን መርምሮ ከሚያውቅ ከሰማያዊ አባታችሁ
በቀር ሰማያዊ አባታችሁ ነው እንጂ።
ወአቡክሙ ዘይሬእየክሙ በኅቡዕ የዓሥየክሥ
ክሡተ።
ጉባኤውን ከሻችሁ ተሰውራችሁ ስትጾሙ ተሰውሮ
የሚያያችሁ ሰማያዊ አባታችሁ በጻድቃን በመላእክት በኀጥአን በአጋንንት መካከል ዋጋችሁን ይሰጣችኋል።
******
፲፱፡ ኢትዝግቡ ለክሙ መዝገበ ዘበምድር ኀበ
ይበሊ ወይማስን።
******
፲፱፡ አንቀጸ ምጽዋት ነው። በመካከል አንቀጸ
ጾምን አንቀጸ ጸሎትን አግብቶበት ነበረና አሁን አመጣው፡፡ ስለ ሦስት ነገር ያመጣዋል። እህሉን ነዳያን ከሚበሉት ብለው አኑረውት
ነቀዝ ቢበላው። ልብሱን ነዳያን ከሚለብሱት ብለው አኑረውት ነቀዝ ቢበላው። ልብሱን ነዳያን ለሚለብሱት ብለው አኑረውት ብል ቢበላው
ምቀኝነት ነውና።
ዳግመኛ ለክፉ ጊዜ ይሆነኛል ብሎ ማኖር እግዚአብሔርን
ከዳተኛ ማድረግ ነው። በዝናብ አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ አይመግበኝም ማለት ነውና፡፡
አንድም ምንም እጅ እግር ባያወጡለት ገንዘብ
ማኖር ጣዖት ማኖር ነውና። ኅልፈት ጥፋት ያለበትን ምድራዊ ድልብ አታድልቡ።
ኀበ ፃፄ ወቊንቊኔ ያማስኖ።
ብል የሚበላውን ነቀዝ የሚያበላሸውን
ወኀበ ሠረቅት ይከርዩ ወይሠርቅዎ።
ሌቦች ናሱን አፍርሰው ግድግዳውን ምሰው የሚወስዱትን
ከሚወስዱት ቦታ አታድልቡ።
******
፳፡ ዝግቡ ለክሙ መዝገበ ዘበሰማያት ኀበ
ኢይበሊ ወኢይማስን። ሉቃ ፲፪፥፴፫፡፡ ፩፡ጢሞ ፮፥፲፱፡፡
******
፳፡ አላ ያለበት ነው፡፡ ኅልፈት ጥፋት የሌለበትን
ሰማያዊ ድልብን አድልቡ እንጂ።
ወኀበ ኢያማስኖ ፃፄ ወቊንቊኔ።
ብል የማይበላውን ነቀዝ የማያበላሸውን።
ወኀበ ሰረቅት ኢይከርዩ ወይሰርቅዎ።
ሌቦች ናሱን አፍርሰው ግድግዳውን ምሰው የማይወስዱትን
ከማይወስዱበት አድልቡ እንጂ።
******
፳፩፡ እስመ ኀበ ሀሎ መዝገብክሙ ህየ ይሄሉ
ልብክሙኒ።
******
፳፩፡ ገንዘባችሁ ካለበት ዘንድ ልቡናችሁ
ከዚያ ይኖራልና፡፡
አንድም ኢትዝግቡ ብለህ መልስ፡፡
ውዳሴ ከንቱ ያለበትን ምጽዋት አትመጽውቱ፡፡
ዘይበሊ ውዳሴ ከንቱ የሚያስቀርባችሁን፡፡
ወኀበ ሠረቅት አጋንንት በውዳሴ ከንቱ የሚያስቀሩባችሁን
አላ ያለበት ነው። ውዳሴ ከንቱ የማያስቀርባችሁን ውዳሴ ከንቱ የሌለበትን ምጽዋት መጽውቱ እንጂ። አጋንንት በውዳሴ ከንቱ የማያስቀሩባችሁን
ምጽዋታችሁ ካለበት ልቡናችሁ ከዚያ ይራኖልና። እስመ ዘይገብራ ለሠናይት ይሴፈዋ ለሠናይት እንዲል።
******
፳፪፡ ማኅቶቱ ለሥጋከ ዓይንከ ውእቱ።
******
፳፪፡ የሥጋህ ፋና ዓይንህ ነው ማለት የሥራህ
መከናወኛ ዓይንህ ነው፡፡
ወእምከመ ዓይንከ ብሩህ ውእቱ ኩሉ ሥጋከ
ብሩሃ ይከውን፡፡
ዓይንህ ብሩህ የሆነ እንደሆነ አካልህ ሁሉ
ብሩህ ይሆናል፡፡ ዓይንህ የቀና እንደ ሆነ ሥራህ ሁሉ የቀና ይሆናል፡፡
******
፳፫፡ ወእመሰ ዓይንከ ሐማሚ ውእቱ ኩለንታከ
ጽልመተ ይከውን፡፡
******
፳፫፡ ዓይንህ የሚታመም የሆነ እንደሆነ ሁሉ
አካልህ ሁሉ ጨለማ ይሆናል ማለት ዓይንህ ግን ያልቀና እንደሆነ ሥራህ ሁሉ ያልቀና ይሆናል።
ወሶበ ብርሃን ዘላዕሌከ ጽልመት ውእቱ ጽልመትከ
እፎ ይከውነከ
በአንተ ያለ ብርሃን ጨለማ ከሆነ ጨለማህ
እንደምን ይሆን በተፈጥሮ የተሰጠህ ዓይንህ የታመመ ከሆነ ጨለማ እንደምን ይጸናብህ ይሆን።
አንድም ጽልመትከ እፎ ብርሃነ ይከውነከ የታመመው
ዓይንህ እንደምን ያይልሃል፡፡
አንድም ማኅቶቱ ብለህ መልስ፡፡
የሥራህ መከናወኛ አእምሮ ጣባይዕህ ነው፡፡
ወእምከመ ዓይንከ
አእምሮ ጠባይዕህ የቀና እንደሆነ ሥራህ ሁሉ
የቀና ይሆናል፡፡
ወሶበ ብርሃን
አእምሮ ጠባይዕህ ያልቀና እንደሆነ ሥራህ
ሁሉ ያልቀና ይሆናል፡፡ በተፈጥሮ የተሰጠህ አእምሮ ጠባይዕህ ያልቀና ከሆነ ፍዳ እንደምን ይጸናብህ ይሆን፡፡
አንድም ጽልመትከ ያልቀና አእምሮ ጠባይዕህ
እፎ ብርሃነ ይከውነከ።
እንደምን መክበሪያ መጽደቂያ ይሆንሃል።
አንድም የሥራህ መከናወኛ ምጽዋትህ ነው፡፡
ምጽዋትህ ውዳሴ ከንቱ የሌለበት እንደሆነ ሥራህ ሁሉ የቀና ይሆናል። ምጽዋትህ ግን ውዳሴ ከንቱ ያለበት እንደሆነ ሥራህ ሁሉ ያልቀና
ይሆናል፡፡
ወሶበ ብርሃን
ከአንተ የሚሰጥ ምጽዋትህ ውዳሴ ከንቱ ያለበት
ከሆነ ፍዳ እንደምን ይጸናብህ ይሆን።
አንድም ጽልመትከ ውዳሴ ከንቱ ያለበት ምጽዋትህ
እፎ ብርሃነ ይከውነከ
እንደምን መክበሪያ መጽደቂያ ይሆንሃል።
አንድም የሥራህ መከናወኛ ኤጲስ ቆጶስህ ነው።
ኤጲስ ቆጶስህ የቀና እንደሆነ ሥራህ ሁሉ
የቀና ይሆናል። ኤጲስ ቆጶስህ ግን ያልቀና እንደሆነ ሥራህ ሁሉ ያልቀና ይሆናል
ወሶበ ብርሃን
በአንተ የተሾመ ኤጲስ ቆጶስህ ያልቀና ከሆነ
ፍዳ እንደምን ይጸናብህ ይሆን።
አንድም ጽልመትክ በአንተ የተሾመ ኤጲስ ቆጶስህ
እፎ ብርሃነ ይከውነከ
እንደምን መክበሪያ መጽደቂያ ይሆንሃል።
******
፳፬፡ ኢይክል ፩ዱ ገብር ተቀንዮ ለ፪ኤ አጋዕዝት።
ሉቃ ፲፮፥፲፫፡፡
፳፬፡ ከፍለን መጽውተን ከፍለን ብናኖር ምነዋ
ትሉኝ እንደሆነ። አንድ ባሪያ ለሁለት ጌታ መገዛት አይቻለውም።
******
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ
በየነ
ደብረ
ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
25/07/2011
ዓ.ም
No comments:
Post a Comment