====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ መጻጒዕ።
ምዕራፍ ፱።
******
በእንተ ጽሙም ዘቦቱ ጋኔን
፴፪፡ ወእምዝ አምጽኡ ኀቤሁ ዘጋኔን ፅሙመ ወበሀመ። ማቴዎ ፲፪፥፳፪፡፡ ሉቃ ፲፩፥፲፬።
******
፴፪፡ ከዚህ በኋላ ጋኔን ድዳ ደንቆሮ ያደረገውን ሰው ይዘው መጡ። ድዳ ደንቆሮ ጋኔን ሲያድርበት ሰውም ድዳ ደንቆሮ ይሆናልና።
አንድም ጽሙም ወበሐም ይላል ድዳ ደንቆሮ ጋኔን ያደረበትን ሰው ይዘው መጡ። ቀድስ ቢሉት አልቀድስም ብሏልና ድዳ አለው። ትእዛዘ እግዚአብሔርን ስማ ቢሉት አልሰማም ብሏልና ደንቆሮ አለው።
******
፴፫፡ ወወፂኦ ጋኔኑ ነበበ ውእቱ በሐም ወሰምን ውእቱ ጽሙም
******
፴፫፡ ጋኔኑ በተለየው ጊዜ ድዳ የነበረው ተናገረ ደንቆሮ የነበረው ሰማ።
******
፴፬፡ ወፈሪሳውያንሰ ይቤሉ በመልአኮሙ ለአጋንንት ያወፅኦሙ ለአጋንንት።
******
፴፬፡ ፈሪሳውያን ግን ታምራት ያደርጋል ሰው ይሳባል ኦሪት ትጠፋለች ወንጌል ትሰፋለች ብለው የንጉሥን ጭፍራ በንጉሥ ቀላጤ እንዲያስወጡት ከአለቃቸው ከብዔል ዜቡል ተጨዋውቶ ያስወጣቸዋል እንጂ አለዚያ ግን አያስወጣቸውም አሉ። አሁን ለነዚህ ዛሬ አይመልስላቸውም በሚመጣው ጉባዔ ይመልስላቸዋል
******
በከመ አንሶሰወ ኢየሱስ ውስተ ገሊላ።
፴፭፡ ወአንሶሰወ እግዚእ ኢየሱስ ውስተ ኵሉ አህጉር ወበሐውርት እንዘ ይሜህር በምኵራባቲሆሙ። ማር ፮፥፮።
******
፴፭፡ በምኵራባቸው እየገባ ሲያስተምር ኖረ
ወይሰብክ ወንጌለ መንግሥት
ጌትነቱን የምትናገር ወንጌልን ሲያስተምር ኖረ። (ሐተታ) እንዳለፈው። ምዕ ፬ ቊ ፳፫፡፡
ወይፈውስ ኵሎ ድውያነ ወኵሎ ሕማመ ዘውስተ ሕዝብ ለዚያው ምልክት በሕዝቡ ዘንድ ያሉ ድውያንን ሁሉ ይፈውስ ነበረ።
******
፴፮፡ ወርእዮ ብዙኃነ ሰብአ አምህርዎ ወተሣሃሎሙ።
******
፴፮፡ ብዙ ሰዎችን ባየ ጊዜ አሳዘኑት አዘነላቸው።
እስመ ስሩሃን እሙንቱ።
በፃማ ኦሪት በፃማ ኃጢአት ደክመዋልና።
ወግዱፋን ከመ አባግዕ ዘአልቦ ኖላዊ፡፡
ጠባቂ እንደሌላቸው አባግዕ ሁነዋልና።
******
፴፯፡ ወእምዝ ይቤሎሙ ለአርዳኢሁ። ሉቃስ ፪፥፪።
******
፴፯፡ ከዚህ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ አንዲህ አላቸው፤
ማዕረሩሰ ብዙኅ
መከሩ ብዙ ነው
ወገባሩ ኅዳጥ።
ሠራተኛው ግን ጥቂት ነው።
******
፴፰፡ ሰአልዎ ለበዓለ ማዕረር።
******
፴፰፡ የመከሩን ባለቤት ለምኑት።
ከመ ይወስክ ገባረ ለማዕረሩ።
ለመከሩ አጫጅ ሠራተኛ ይጨምር ዘንድ።
አንድም ማዕረሩሰ ብዙኀ ሰማዕያኑ ብዙ ናቸሙ። ወገባሩ ኅዳጥ መምሩ አንድ ዮሐንስ ነው ወኅዳጥ ዓሣ እንዲል። ሰአልዎ የመምህርነት ባለቤት እኔን ለምኑኝ።
ከመ ይዌስክ እናንቱን መምራን አድርጌ አስነሣችሁ ዘንድ ወደፊት በሚያመጣው ሹመት አትለምኑ ይል የለም ከዚህ ምነው እንዲህ አለ ቢሉ። ያ ሥጋዊ ነው ይህ ግን መንፈሳዊ ነውና የሚጠቀሙበትም ነውና።
አንድም አስፈቅዶ ለመሾም መከራ በመጣባቸው ጊዜ ተሾሙ ተሾሙ ያለን ለዚህ ነው እንዳይሉ። ምነዋ መከራ ብንቀበል ወደን እንጂ ተሹመነዋል እንዲሉ።
አንድም ማዕረሩ ብዙኅ መጻሕፍተ ነቢያት ንባባቸው ብዙ ነው። ወገባሩ ሕዳጥ ትርጓሜያቸው ጥቂት ነው። ድኅነት አያሰጡም። ሰአልዎ የብሉይ የሐዲስ ባለቤት እኔን ለምኑኝ። ከመ ይወስክ ገባረ። መተርጉማን አድርጌ አስነሣችሁ ዘንድ ድነት እንድታሰጡ አደርጋችሁ ዘንድ፡፡
******
በከመ ተፈነዉ ሐዋርያት።
ምዕራፍ ፲።
፩፡ ወጸውዖሙ ለ፲ቱ ወ፪ቱ አርዳኢሁ፡፡ ማር ፫፥፲፫፡፡ ሉቃ ፮፥፲፫፡፡ ፱፥፩፡፡
፩፡ አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን ጸራቸው፡፡ ማለት ሾማቸው፡፡
******
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
12/08/2011 ዓ.ም
Saturday, April 20, 2019
ወንጌል ቅዱስ ክፍል 70
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment