Thursday, April 4, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 54


====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
ምዕራፍ ፮።
             ******
፳፬፡ ኢይክል ፩ዱ ገብር ተቀንዮ ለ፪ኤ አጋዕዝት። ሉቃ ፲፮፥፲፫፡፡
                  ******
፳፬፡ ከፍለን መጽውተን ከፍለን ብናኖር ምነዋ ትሉኝ እንደሆነ። አንድ ባሪያ ለሁለት ጌታ መገዛት አይቻለውም።
                  ******
ወእመአኮሰ ፩ደ ይጸልእ ወካልዖ ያፈቅር
ይህም ባይሆን ማለት እገዛለሁም ቢል አንዱን ይጸላል አንዱን ይወዳል፡፡
ወእመ አኮ ለአሐዱ ይትኤዘዝ
ያፈቅር ያለውን ይትኤዘዝ ይጸልዕ ያለውን ኢይትኤዘዝ አለ ላንዱ ይታዘዛል ለአንዱ አይታዘዝም እንጂ።
(ሐተታ) አንዱ ቆላ ውረድ ሲለው አንዱ ደጋ ውጣ ቢለው ከሁለት ይሆናልን አይሆንም ሲል።
ኢትክሉኬ ተቀንዮ ለእግዚአብሔር ወለንዋይ፡፡ እንደዚህም ሁሉ እናንተም ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አይቻላችሁም። ወለንዋይ ባለው ወለማሞ ይላል ጥሬ፡፡
                  ******
፳፭፡ ወበእንተዝ እብለክሙ ኢትተክዙ ለነፍስክሙ ዘትበልዑ ወዘትሰትዩ ወኢለሥጋክሙ ዘትለብሱ። መዝ ፶፬፥፳፭፡፡ ሉቃ ፲፪፥፳፪፡፡ ፊልጵ ፬፥፮። ፩፡ጢሞ ፮፥፯፡፡ ፩፡ጴጥ ፭፥፮፡፡
                  ******
፳፭፡ ስለዚሀ ነገር ለነፍሳችን ምን እንበላለን ምን እንጠጣለን ለሥጋችን ምን እንለብሳለን ብላችሁ አታስቡ መብል መጠጥን ለነፍስ ሰጥቶ ተናገረ የበሉት የጠጡት ደም ይሆናል በዚህ ምክንያት ነፍስ ከሥጋ ጋራ ተዋህዳ ትኖራለችና። እስመ ነፍስ ተኃድር በደም እንዲል ልብስን ለሥጋ ሰጥቶ ተናገረ ምንም የምታፍር ነፍስ ብትሆን አጊጾ ከብሮ የሚታይ ሥጋ ነውና።
አኮሁ ነፍስ ተዓጽብ እምሲሲት
ምግብ ከመስጠትማ ነፍስን እምኃበ አልቦ አምጥቶ መፍጠር ጭንቅ አይሆንምን።
ወሥጋ የዓጽብ እምልብስ።
ልብስ ከመስጠትማ ሥጋን ከዐራቱ ባሕርያት አዋህዶ መፍጠር ጭንቅ አይሆንምን ነፍስን እምኀበ አልቦ አምጥቼ ሥጋን ከዐራቱ ባሕርያት አዋህጄ የፈጠርኋችሁ ለናንተ ምግብ ልብስ እንደምን እነሣችኋለሁ ለማለት አንዲህ አለ።
አንድም አኮሁ ብለህ መልስ።
ለእናንተ ምግብ ከመስጠትማ ነፍስን ካለችበት ማምጣት ጭንቅ አይሆንምን
ወሥጋ የዓጽብ። ልብስ ከመስጠትማ ሥጋን ካለበት ማንሣት ጭንቅ አይሆንምን። ነፍስን ካለችበት አምጥኛቼ ሥጋን ካለበት አስነሥቼ ኋላ በመንግሥተ ሰማይ መንፈሳዊ ምግብ የምመግባችሁ ዛሬ ለእናንተ ምግብ ልብስ እነሣችኋለሁን ለማለት።
አንድም ወበእንተዝ እብለክሙ ብለህ መልስ
ሥጋውን ደሙን
ወለሥጋክሙ ዘትለብሱ።
ልጅነትን ማን ይሰጠናል ብላችሁ አታስቡ። ሥጋዬን ደሜን ከመስጠትማ ነፍስን ሥጋን መዋሐድ ጭንቅ አይሆንምን ነፍስን ሥጋን የተዋሃድሁላችሁ ሥጋዬን ደሜን እነሣችኋለሁን ለማለት እንዲህ አለ ጭንቅነቱ በሌላ ነው እንጂ በሱ አይደለም።
                  ******
፳፮፡ ነጽሩ አዕዋፈ ሰማይ እለ ኢይዘርዑ ወእለ ኢየዓርሩ ወኢያስተጋብኡ ውስተ አብያት ወአቡክሙ ሰማያዊ ይሴስዮሙ።
                  ******
108 ፳፮፡ ከፍለን መጽውተን ከፍለን ካላኖርን ምን እንመገባለን ትሉኝ እንደሆነ ዘር መከር የሌላቸውን በጎታ በጎተራ በሪቅ የማይሰበስቡን ሰማያዊ አባታችሁ የሚመግባቸው አዕዋፍን እዩ ማለት አዕዋፍን አብነት አድርጉ።
ከመ ኢይዘርዑ ይላል ዘር መከር እንደሌላቸው በጎታ በጎተራ በሪቅ እንዳይሰበስቡ ሰማያዊ አባታችሁ እንዲመግባቸው ዕወቁ።
አኮኑ አንትሙ ፈድፋደ ትኄይስዎሙ።
ለኒያማ እንዴታ ትሉኝ እንደሆነ ከተፈጥሮተ አዕዋፍማ ተፈጥሮተ ሰብእ አይበልጥምን ለኒያ ምግብ የሰጠ ለናንተ ይነሣችኋል ለማለት እንዲህ አለ፡፡
(ታሪክ) እንደ ሁለት መነኮሳት ይኸን ይዘው በተባሕትዎ ሁነው በረኃብ በጽምዕ የሚያልቁ ሁነዋል። ኋላ መልአክ አለ ኢይዘርኡ አለ እንጂ እለ ኢይሰርሩ አለ አላቸው ከዚህ በኋላ ተግባረ እድ ይዘው ራሳቸውን ረድተው የሚኖሩ ሁነዋል። ከአባ ስልዋኖስ ገዳም እንደ ገባ መነኩሴ እንደምን ሁናችሁ ትኖራላችሁ አላቸው ተግባረ እድ ይዘን እንኖራለን አሉት እናንተስ ወንጌላውያንም አይደላችሁ ጌታ በወንጌል ነጽሩ አዕዋፈ ሰማይ ቢል አላቸው። ይህ ነገሩ ሲሳሳብ ከአበምኔቱ ደረሰ እናንተ ሥራችሁን አትተው ለሱም የሚሻውን መጽሐፍ ስጡት ይመልከት አላቸው ቦታ መጣፍ ሰጥተውት ሲመለከት ዋለ ምግብ የሚመገቡ በደወል ነውና ደወል አትምቱ ጊዜያት አቆይታችሁ ተመገቡ አላቸው። ጊዜያት አይተው ተመግበው በየበዓታቸው ሔዱ። ይጠሩኛል ብሎ ቢያይ የማይጠሩት ሆነ ተደሩኑ አኃው እያለ እሱ ካለበት ሄደ እወ ተደሩ አለው በሀገራችሁ እንግዳ አኑሮ መብላት ሥርዓትን ነው አለው አንተማ መንፈሳዊ ነህ አትሻውም ብለን እኛ ሥጋውያኑ ተመገብነው አለው አባቴ አላበጀሁም ብሎ እነሱን መስሎ የሚኖር ሁኑዋል።
አንድም ነጽሩ ብለህ መልስ ዘር መከር የሌላቸውን ሰማያዊ አባታችሁ የሚመግባቸው እስራኤልን አብነት አድርጉ። እንዲመግባቸው ዕወቁ። እስራኤል ልብስህ አላለቀ በትርህ አልወደቀ እንዲሉ፤ ከውቅያኖስ በደመና አይበት ተቋጥሮ በነፋስ ወደል ጋዝ ተጭኖ መጠኑ ድምብላል አህሎ መልኩ በረድ መስሎ ወእንዘ የኃድግ ህቦ ይላል የውርጭ ገበታ ሲነጠፍ እየዘነመላቸው ዐርባ ዘመን መናውን ተመግበዋል።
አኮኑ አንትሙ ትኄይስዎሙ።
ለኒያማ እንዴታ ትሉኝ እንደሆነ። በዘመነ ብሉይ ከነበሩ ከኒያማ በዘመነ ሐዲስ ያላችሁ እናንተ ትበልጡ የለምን ለኒያ የሰጠሁ ለናንተ እነሣችኋለሁ ለማለት እንዲህ አለ።
አንድም ነጽሩ ብለህ መልስ ትንቢት ያልተነገረላቸውን ሱባዔ ያልተቈጠረላቸውን ሰማያዊ አባታችሁ ሥጋውን ደሙን የሚመግባቸው አሕዛብን አብነት አድርጉ እንዲመግባቸው ዕወቁ። ለኒያማ እንዴታ ትሉኝ እንደሆነ ትንቢት ካልተነገረላቸው ሱባዔ ካልተቈጠረላቸው ከአሕዛብማ ትንቢት የተነገረላችሁ ሱባዔ የተቈጠረላችሁ እናንተ የምትበልጡ አይደለምን፡፡
                  ******      
፳፯፡ መኑ እምኔክሙ በተክዞ ዘይክል ወስኮ በዲበ ቆሙ አሐደ እመተ።
                  ******      
፳፯፡ በዚያውስ ላይ ራሳችሁንማ አስባችሁ ታሳድሩ ዘንድ ከናንተ ወገን አጠርሁና ልርዘም ብሎ በቁመቱ ላይ ክንድ ሙሉ ቁመት መጨመር የሚቻለው ማነው። እንደዚህም ሁሉ በቃሁ ነቃሁ ብሎ ሥልጣነ ክህነትን ለራሱ ገንዘብ ማድረግ የሚቻለው ማነው።
                  ******      
፳፰፡ ወበእንተ ዓራዝኒ ምንተኑ ትሔልዩ።

፳፰፡ የልብስንስ ነገር ለምን ታስባላችሁ።
                  ******      
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
26/07/2011 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment