Tuesday, April 9, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 60

====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
ምዕራፍ ፯።
                  ******
፳፬፡ ኵሉኬ ዘይሰምዕ ዘንተ ቃልየ ወይገብሮ ይመስል ብእሴ ጠቢበ ዘሐነፀ ቤቶ ዲበ ኰኵሕ ሉቃ ፮፥፵፰፡፡ ሮሜ ፪፥፲፫፡፡ ያዕ ፩፥፳፪።
                  ******                 
፳፬፡ ይኽን የኔን ነገር ሰምቶ የሚሠራው ሰው ሁሉ ቤቱን በጭንጫ ላይ የሠራ ብልህ ሰውን ይመስላል።
 ፳፭፡ ዘንሙ ዝናማት።
                  ******                 
፳፭፡ ዝናም ዘነመ።
ወውኅዙ ወሐይዝት።
ጎርፍ ጎረፈ።
ወነፍሑ ነፋሳት።
ነፋስ ነፈሰ።
ወገፍዕዎ ለውእቱ ቤት።
ያን ቤት እናናውጽሕ አሉት
ወኢወድቀ
አልተናወጸም
እስመ ዲበ ኰኵሕ ተሣረረ
ከጭንጫ ላይ ተሰርቷልና፡፡
(ሐተታ) እንደምን አድርገው ይሠሩታል ቢሉ ዘይት ያፈሱበታል ይላላል ያን እየቈፈሩ ይመሠርቱበታል ይጸናል፡፡
አንድም ኵሉ ዘይሰምዕ ብለህ መልስ። ይህን የኔን ቃል ሰምቶ የሚሠራው ሁሉ ሃይማኖቱን በበጎ ልቡና የያዘ ብልህ ሰውን ይመስላል።
ዘንሙ ዝናማት
ከዓላውያን ነገሥታት ከዓላውያን መኳንንት የሚመጣ መከራ ነው።
ውኅዙ ወኃይዝት
መከራ እቀበላለሁ ባለ ጊዜ ሕዋሳቱ ይፈሩበታል።
ነፍሑ ነፋሳት።
ቤተ ሰቦቹ ንጉሥ የወደደውን ዘመን የወለደውን ይዘህ አትኖርም ይሉታል። ያን ሰው ሃይማኖትህን እናስለቅቅህ ይሉታል።
ወኢወድቀ
አልለቀቀም።
እስመ ዲበ ኰኵሕ ተሣረረ
ሃይማኖቱን በበጎ ልቡና ይዟልና፡፡
አንድም የኔን ቃል ሰምቶ የሚሠራ ሰው ሁሉ ሃይማኖቱን ምግባሩን እንደ ኢዮብ ባለ ሰውነት የያዘ ብልህ ሰውን ይመስላል።
ዘንሙ።
ሞተ ውሉድ ጥፍዓተ ንዋይ ነው።
ወውኅዙ።
በራሱ የሚመጣ ደዌ፡፡
ነፍሑ
አጋንንት በሚስቱ አድረው ፥ አስከ ማእዜኑ ትብል ኢዮብ እትዔገሦ ለእግዚአብሔር በየውሃት እምይእዜሰ ባርኮሁ ወሙት ብለውታል።
ወገፍዕዎ
ይህን ሰው ሃይማኖቱን ምግባሩን እናስለቅቅህ አሉት አልለቀቀም።
እስመ ዲበ ኰኵሕ ተሣረረ ሃይማኖቱን ምግባሩን እንደ ኢዮብ ባለ ሰውነት ይዟልና።
አንድም የኔን ቃል ሰምቶ የሚሠራው ሰው ሁሉ በምክረ ካህን በፈቃደ ካህን የሚኖር ብልህ ሰውን ይመላል፡፡
ነፍሑ ባለው ይነሷል ነፍሑ።
አጋንንት በሕሊና ያወጡታል ያወርዱታል። እንደ ዕንጦስ እንደ መቃርስ ንጽሕ ጠብቄ ከሴት ርቄ እኖራለሁ ያሰኙታል ሂዶ ለመምህረ ንስሐው ይነግረዋል ቈይ ይለዋል።
ዘንሙ ዝናማት።
እንደ ዕንጦስ እንደ መቃርስ ንጽሕ ጠብቄ ከሴት ርቄ መኖር አይቻለኝም እንደ ኢዮብ እንደ አብርሃም በሕግ ጸንቼ እኖራለሁ ያሰኙታል ይህን ሂዶ ለመምሕረ ንስሐው ይነግረዋል። እሱም የሰይጣን ፆር እንደሆነ አውቆ ቆይ ይለዋል።
ወውኅዙ
ሁሉም አይሆንልኝም ያሰኙታል።
ወገፍዕዎ
እናስለቅቅሃለን ይሉታል አልለቀቀም።
እስመ ዲበ ኰኵሕ ተሣረረ።
በምክረ ካህን በፈቃደ ካህን ይኖራልና። ይሀ ሰው ወድቆ ተነሥቶ በሕሊናው ድል ነስቷቸዋል፤ ወመዊቶ ተንሢኦ ሰፈኖሙ ለሕያዋን ወለሙታን እንዳለው ጌታን።
                 ******
                 ******  
፳፮፡ ወኵሉ ዘይሰምዕ ዘንተ ቃልየ ወኢይገብሮ ይመስል ብእሴ ዓብደ ዘሐነፀ ቤቶ ዲበ ኆፃ፡፡
                 ******  
፳፮፡ ይህን የኔን ቃል ሰምቶ የማይሠራው ሰው ሁሉ ቤቱን በድቡሽት ላይ የሠራ ሰነፍ ሰውን ይመስላል።
                 ******  
 ፳፯፡ ዘንሙ ዝናማት።
                 ******  
፳፯፡ ዝናም ዘነመ።
ወውኅዙ ወኃይዝት።
ጎርፍ ጐረፈ።
ወነፍሑ ነፋሳት።
ነፋስ ነፈሰ።
ወገፍዕዎ ለውእቱ ቤት።
 ያን ቤት እናናዋውጽሕ አሉት
ወወድቀ።
ወደቀ።
ወኮነ ድቀቱ ዓቢየ።
የነፍስ ነውና ዓቢየ አለ።
                 ******  
፳፰፡ ወሶበ ፈጸመ እግዚእ ኢየሱስ ዘንተ ነገረ ተደሙ አሕዛብ ወኣንክሩ ምህሮቶ።
                 ******  
፳፰፡ ጌታ ይህን አስተምሮ ከፈጸመ በኋላ ሕዝቡ ትምርቱን አደነቁ፡፡
                 ******  
፳፱፡ እስመ ከመ መኰንን ይሜህሮሙ። ማር ፩፥፳፪፡፡ ሉቃ ፪፥፴፪፡፡
                 ******  
፳፱፡ እንደ ንጉሥ አንሰ እብለክሙ እያለ ያስተምራቸዋልና። ወአኮ ከመ ጸሐፍቶሙ ከመዝ ይብሉክሙ ንጉሥ እንሚሉ እንደ ሹማምንት ያይደለ፡፡
አንድም እንደ አብ አንሰ እብለክሙ እያለ ያስተምራቸዋልና ከመዝ ይቤ እግዚአብሔር እንደሚሉ እንደ ዓበይተ ነቢያት ያይደለ፡፡
አንድም ሠራዔ ሕግ እንደመሆኑ ያስተምራቸዋልና ከመዝ ይቤ ሙሴ ከመዝ ይቤ ሳሙኤል እንደሚሉ እንደ ደቂቀ ነቢያት ያይደለ፡፡
አንድም ፈጻሜ ሕግ አንደመሆኑ ያስተምራቸዋልና ወለሊሆሙሰ በአጽባዕቶሙ ጥቀ ኢይለክፍዎ ለውእቱ ፆር እንዳላቸው እንደ ጸሐፍት ፈሪሳውያን ያይደለ።
አንድም ከመ ሥልጣን ቦ ይላል አብነት እንደ ጌትነቱ በርኅራኄ ያስተምራቸዋልና።
እስመ ቅንየትከ ወምልክናከ ይሬስየከ ትሠሃል ላዕለ ኵሉ እንዲል።
ወአኮ ከመ ጸሕፍቶሙ።
ከወርቁ የጸራውን ከግምጃው ያማረውን ከላሙ የሰባውን እንደሚሉ እንደ ጸሐፍት ፈሪሳውያን ያይደለ።
                 ******  
በእንተ አድኅኖተ ለምጽ።
ምዕራፍ ፰።
፩፡ ወእንዘ ይወርድ እምደብር ተለውዎ ሰብእ ብዙኃን
በጌታ ከብፁዓን ጀምሮ እስከዚህ ያንድ ቀን ነው። ጉባዔው ሲፈታ ብዙ ሰዎች ተከተሉት የቀሩትን አይከተሏቸውም እሱን ተከተሉት አለ ቢራቡ ይመግባቸዋል ቢታመሙ ይፈውሳቸዋል ቢሞቱ ያነሣቸዋልና።
                 ******   
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
02/08/2011 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment