Friday, April 5, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 55


====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
ምዕራፍ ፮።
             ******
፳፰፡ ወበእንተ ዓራዝኒ ምንተኑ ትሔልዩ።
                  ******      
፳፰፡ የልብስንስ ነገር ለምን ታስባላችሁ።
ርእዩ ጽጌያተ ገዳም ዘከመ ይልሕቁ ኢይፃምዉ ወኢይፈትሉ።
ሳይደክሙ ሳይፈትሉ እንዲያድጉ ማለት ገዳማት ዕፀዋትን፤ ዕፀዋት ጽጌያትን፤ ጽጌያት መወደድን አጊጸው እንዲኖሩ ዕወቁ።
                  ******    
                  ******      
፳፱፡ እብለክሙ ከመ ሰሎሞን ጥቀ ኢለብሰ በኲሉ ክብሩ ከመ ፩ እምእሉ።
                  ******      
፳፱፡ ሰሎሞንስ እንኳ በዚያ ሁሉ ባለጸግነቱ ከጽጌያት እንዳንዱ አለበሰም ብዬ እንዳለበሰ እነግራችኋለሁ።
(ሐተታ) አበባ ያለበት ሐረግ የተሳበበት ወርቀ ዘቦ ግምጃ ይለብስ አልነበረም ቢሉ የሱ የባሕርዩ አይደለም የእሳቸው ግን የባሕርያቸው ነውና እሱ እነዚያን አብነት አድርጎ ነው፤ እነዚያ ግን እሱን አብነት አያደርጉምኖና። በኲሉ ክብሩ ማለቱ ብዕልን ካንተ በፊት እንዳልተነሣ ካንተም በኋላ እንዳይነሣ አድርጌ ሰጥቼሃለሁ ብሎታልና፡፡
አንድም ወበእንተ አራዝኒ ብለህ መልስ የልጅነትን ነገር ለምን ታስባላችሁ ትንቢት ያልተነገረላቸው ሱባዔ ያልተቈጠረላቸው ልጅነትን ያገኙ አሕዛብን አብነት አድርጉ።
እብለክሙ ከመ ሰሎሞን እስራኤልን በመክብባቸው ሰሎሞን አላቸው እስራኤልስ እንኳ በዚያ ሁሉ ትንቢት በዚያ ሁሉ ሱባዔ ከአሕዛብ አንዳንዱ ልጅነትን አላገኙም ብዬ እንዳላገኙ እነግራችኋለሁ።
                  ******      
፴፡ ወናሁ ሣዕረ ገዳም ዘዮም ሀሎ ወጌሠመ ውስተ ዕቶነ እሳት ይትወደይ ወእግዚአብሔር ዘከመዝ ያለብሶ።
                  ******      
፴፡ የሚያስተምርበት ደጋ ነው ቢሉ ነገ በቈላ መንደድ ፀዐተ ክረምት ነው ቢሉ ነገ በበጋ መንደድ የሚነድ ሣዕረ ገዳምን ዛሬ በልምላሜ የሚያኖር እግዚአብሔር።
እፎ እንከ ፈድፋደ ኪያክሙ አሕፁዓነ ሃይማኖት
እናንት ሃይማኖት የሌላችሁ ለናንተማ እንደምን ልብስ ምግብ ይነሣችኋል
ወለእመ ኮነ ሥርወ ጽጌ ይላል፤ በሉቃስ ሥርወ ጽጌ ዛሬ በልምላሜ የሚኖር ከሆነ ኋላ በቈላ መንደድ የሚነድ ከሆነ እግዚአብሔርም እንዲህ በልምላሜ የሚያኖረው ከሆነ።
እፎ ኪያክሙ::
አንድም ወናሁ ሣዕረ ገዳም ብለህ መልስ ዛሬ በተድላ የሚኖር ኋላ በገሃነም ፍዳ የሚያኖር እግዚአብሔር እፎ ኪያክሙ።
አንድም አይሁዳዊ ዛሬ በተድላ የሚኖር ከሆነ ኋላ በገሃነም ፍዳ የሚቀበል ከሆነ እግዚአብሔር ይህንን በተድላ የሚያኖር ከሆነ እፎ ኪያክሙ እናንት ሃይማኖት የሌላችሁ እናንተንማ እንደምን ቸል ይላችኋል፡፡
                  ******      
፴፩፡ ኢትተክዙኬ እንከ እንዘ ትብሉ ምንተ ንበልዕ ወምንተ ንሰቲ ወምንተ ንትከደን።
                  ******      
፴፩፡ ምን እንበላለን ምን እንጠጣለን ምን እንለብሳለን ብላችሁ አታስቡ።
                  ******      
፴፪፡ እስመ ዘንተሰ ኲሎ አሕዛበ ዓለም ዘአፍኣ የኀሥሥዎ።
                  ******      
፴፪፡ ይህንስ ሁሉ ከምግባር ከሃይማኖት በአፍአ ያሉ አሕዛብ ይሹታልና።
ወለክሙሰ የአምር አቡክሙ ሰማያዊ ከመ ትፈቅዱ ዘንተ ኵሎ።
ለናንተስ ሰማያዊ አባታችሁ ይህን ሁሉ እንድትሹት ያውቅላችኋል ማለት አውቆ ይሰጣችኋል።
                  ******      
፴፫፡ አንትሙሰ ኅሡ መቅድመ መንግሥቶ ወጽድቆ።
                  ******      
፴፫፡ እናንተስ አስቀድሞ ሃይማኖትን ምግባርን ሹ።
አንድም ልጅነትን መንግሥተ ሰማይን ሹ።
ወዝንቱ ኵሉ ይትዌሰከክሙ።
ይህስ ሁሉ ማለት የዚህ ዓለምስ ነገር ሁሉ በራት ላይ ዳረጎት እንዲጨመር ይጨመርላችኋል።
                  ******      
፴፬፡ ኢትበሉኬ ለጌሠም።
                  ******      
፴፬፡  ለነገ አታስቡ ማለት ለነገ ይሆናል ብላችሁ አታሳድሩ።
እስመ ጌሠምሰ ትሔሊ ለርእሳ
ነገ ለራት ያስባል ማለት የነገውን ነገ ታስቡታላችሁና።
የአክላ ለዕለት አክያ ወሥራኃ
የዕለት ፃሯ ጋሯ ይበቃታል።
የበጎ ፃር የበጎ ጋር።
አንድም ኢትበሉ እያልክ መልስ። ለነገ ያጸናናል ብላችሁ አብዝታችሁ አትመገቡ። የነገውን ነገ ትመገቡታላችሁና።
አንድም ነገ እንናዘዘዋለን ብላችሁ ኃጢአታችሁን አታሳድሩ የነገውን ነገ ትናገሩታላችሁና የነገውንስ ነገ ትናገሩታላችሁ።
                  ******      
በእንተ ትእዛዛት
ምዕራፍ ፯ቱ።
፩፡ ኢትኰንኑ ከመ ኢትትኰነኑ ሉቃ ሮሜ ፮፥፩።
፩፡ አንቀጸ መምሕራን ነው። እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ ማለት ንጹሐን ሳትሆኑ አትፍረዱ፡፡
                  ******        
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
27/07/2011 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment