Thursday, April 11, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 62

====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ አድኅኖተ ለምጽ።
ምዕራፍ ፰።
                 ******
           ******  
፯፡ ወይቤሎ እግዚእ ኢየሱስ ነየ አነ እመጽእ ወእፌውሶ።
                  ******  
፯፡ እኔ መጥቼ አድነዋለሁ አለው።
                  ******  
፰፡ ወአውሥአ ውእቱ ሀቤ ምዕት፡፡ ሉቃስ ፯፥፮፡፡
                  ******  
፰፡ የመቶ አዝማች መለሰ።
ወይቤ እግዚኦ ኢይደልወኒ ከመ አንተ ትባዕ ታሕተ ጠፈረ ቤትየ።
ጥፉር ቤትየ ሲል ነው ስጠተ ልብስ ንፍቀ ታቦት እንዲል።
ስጡጠ ልብሰ ንፉቀ ታቦተ ሲል። ከኔ ቤት ልትገባ አይገባኝም አንተን ልቀበል አልበቃሁም አለው።
ወባሕቱ አዝዝ በቃልከ ይሕየው ቊልዔየ።
ልጄ ይድን ዘንድ በቃልህ እዘዝ እንጂ። ነገር ግን በቃልህ እዘዝ ።
ወየሐዩ ቊልዔየ።
ልጄም ይድናል።
                  ******  
፱፡ እስመ አነሂ ብእሲ መኰንን አነ፡፡
                  ******  
፱፡ እኔም እንጂ እኔም እኮን አንዳቅሜ ገዢ ነኝ።
ወብየ ሐራ ዘእኴንን።
የምገዛቸው ጭፍሮች አሉኝ።
ወእብሎ ለዝ ሑር ወየሐውር።
ደጅ ሲጠና የሰነበተውን ሂደህ እረፍ እለዋለሁ ይሄዳል።
ወለካልዑኒ ነዓ ይመጽእ።
አርፎ የሰነበተውን መጥተህ ደጅ ጥናኝ አለዋለሁ ይመጣል፡፡
ወለገብርየኒ ግበር ከመዝ ወይገብር።
ባሪያየንም የቆመውን ቀረጥ የተኛውን ፍለጥ ብለው ያዘዝሁትን ሁሉ ያደርጋል። ደዌያትስ ባንተ ዘንድ ምን ቁም ነገር ናቸው ግቡ ብትላቸው የሚገቡ። ውጡ ብትላቸው የሚወጡ አይደሉምን፡፡
                  ******  
፲፡ ወሰሚዖ እግዚእ ኢየሱስ አንከረ።
                  ******  
፲፡ ጌታ ይህን ሰምቶ አደነቀ። ሦስት ነገር አግኝቶ ያደንቅለታል ሃይማኖት፣ ጥበብ፣ ትሕትና። ሃይማኖት ያድንልኛል ብሎ መምጣት። ጥባብ ምሳሌ መስሎ መናገር ትሕትና ኢይደልወኒ አይገባኝም ማለት ነው
ወይቤሎሙ ለእለ ይተልውዎ አማን እብለክሙ ኢረከብኩ ከመዝ ዘይትአመን በውስተ ኵሉ እስራኤል።
ለተከተሉት በእስራኤል ዘንድ እንዲህ ያለ አማኒ አላገኘሁም ብዬ በእውነት እነግራችኋለሁ አላቸው፡፡
አንድም ወበዊዖ ብለህ መልስ። ከልዕልና ወደ ትሕትና በመጣ ጊዜ የሁሉ መገናኛ አዳም መጣ። ቊልዔየ ድውይ፤ አቤቱ ነፍሴ በፍዳ ተይዛለች አለው። ወሕሙም ጥቀ ፍዳ ጸንቶባታል ወይሰክብ ውስተ ቤተ መጻጒዕ በኃጥአን ቤት በሲኦል በፍዳ ተይዛለች።
ነየ አነ እመጽእ ወእፌውሶ። በሐሙስ ዕለት ወበመንፈቃ ለዕለት እትወለድ እምወለተ ወለትከ ያለውን መናገር ነው።
ኢይደልወኒ አዳም አድነኝ አለ እንጂ ሰው ሁንልኝ አለማለቱን መናገር ነው።
እስመ አነሂ እኔም እንጂ እኔም እኮን እንዳቅሜ ገዢ ነኝ።
ወብየ ሐራ የማወጣቸው የማገባቸው ሕሊናት አሉኝ።
ወእብሎ ለዝ ሑር ክፉውን ሕሊና ውጣ ብለው ይወጣል
ወለካልዑኒ ነዓ ወይመጽእ።
በጎውን ሕሊና ግባ ብለው ይገባል።
ወለገብርየኒ ሥጋዬን ለነፍሴ ተገዛ ብለው ይገዛል። አጋንንትስ ባንተ ዘንድ ምን ቁም ነገር ናቸው። ግቡ ብትላቸው የሚገቡ ውጡ ብትላቸው የሚወጡ አይደሉምን አለው።
ወሰሚዖ አይለወጥም።
                  ******  
፲፩፡ ወባሕቱ እብለክሙ ብዙኃን ይመጽኡ እምሥራቅ ወእምዕራብ ወይረፍቁ ውስተ ሕፅነ አብርሃም ይስሐቅ ወያዕቆብ በመንግሥተ ሰማያት።
                  ******  
፲፩፡ ይህ ሰው ትውልዱ ከእስራኤል ነው ያሉ እንደሆነ ይህስ የተገኘ ከኛ አይደለም እንዳይሉት ነገር ግን ካራቱ ማዕዘን የሚያምኑብኝ ብዙ አሉ፡፡ ይህ ሰው ትውልዱ ከአሕዛብ ነው ያሉ እንደሆነ አንድ ሰው ቢያምንበት እንዲህ ያደንቃል እንዳይሉት ሌሎችም ካራቱ ማዕዘን መጥተው የሚያምኑብኝ አሉ ወይረፍቁ በሦስቱ ሕፅን ይቀመጣሉ ማለት በአብርሃም በይስሐቅ በያዕቆብ ቃል ኪዳን በምትወረስ በመንግሥተ ሰማይ ይኖራሉ።
                  ******  
፲፪፡ ወለውሉደ መንግሥትሰ ያወፅእዎሙ ውስተ ጸናፌ ጽልመት፡፡ ሚልክ ፩፥፲፩፡፡
፲፪፡ ይገባናል የሚሉ እስራኤልን ግን ከመንግሥተ ሰማይ አፍአ ወደ ገሃነም ያወጧቸዋል።
                  ******    
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
04/08/2011 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment