Tuesday, April 9, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 59

====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
ምዕራፍ ፯።
                  ******
፲፰፡ ኢይክል ዕፅ ሠናይ ፍሬ እኩየ ፈርየ።
                  ******         
፲፰፡ ወይን ኮሶን በለስ መርዝን አያፈራም። ሃይማኖታዊ መምር ክህደትን መንፈሳዊ መምር ሥጋዊ ትምርትን አያስተምርም
ወኢዕፅ እኵይ ፍሬ ሠናየ ፈርየ
ኮሶ ወይንን መርዝ በለስን አያፈራም መናፍቅ መምር ሃይማኖትን ሥጋዊ መምር መንፈሳዊ ትምርትን አያስተምርም።
                  ******                 
፲፱፡ ኵሉ ዕፅ ዘኢይፈሪ ፍሬ ሠናየ ይገዝምዎ። ማቴ ፲፥፫።
                  ******                 
፲፱፡ በጎ ፍሬ የማያፈራውን እንጨት ሁሉ ይቈርጡታል።
ወውስተ እሳት ይወድይዎ
ከእሳትም ይጨምሩታል። አንድም በእኔ አምኖ በጎ ሥራ የማይሠራውን ሁሉ ሥላሴ ነፍሱን ከሥጋው ይለዩታል በገሃነም ፍዳ ያጸኑበታል።
                  ******                 
፳፡ ወእምፍሬሆሙሰ ተአምርዎሙ፡፡
                  ******                 
፳፡ ቢርቀው ቢያምረው ደገመው፡፡
                  ******                 
፳፩፡ አኮ ኵሉ ዘይብለኒ እግዚኦ እግዚኦ ዘይበውእ ውስተ መንግሥተ ሰማያት። ማቴ ፳፭፥፲፩፡፡ ሉቃ ፮፥፵፮።
                  ******                 
፳፩፡ ሁሉ አቤቱ አቤቱ ይልሃል እሚገባውንስ የማይገባውንስ በምን እናውቀዋለን ትሉኝ እንደሆነ፥ አቤቱ አቤቱ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት አይገባም።
አኮ ዘይበውእ።
የሚገባ አይደለም።
ዘእንበለ ዘይገብር ፈቃዶ ለአቡየ ዘበሰማያት።
የሰማያዊ አባቴን ፈቃድ የሠራ ይገባል እንጂ።
                  ******                 
፳፪፡ ወብዙኃን ይብሉኒ በይእቲ ዕለት እግዚኦ እግዚኦ።
                  ******                 
፳፪፡ በእለተ ምጽአት ብዙ ሰዎች አቤቱ አቤቱ ይሉኛል።
አኮኑ በስምከ ተነበይነ። ዘኍ ፳፬፥፲፯፡፡
 በስምህ መጻእያትን ተናግረን የለም ይሉኛልአለ። በለዓም ኮከብ ይሠርቅ እምያዕቆብ ብሎ ተናግሯልና።
ወበስምከ አጋንንተ አውጻእነ። ግብ ፲፱፥፲፬፡፡
በስምህ አጋንንትን ስናወጣ አልነበርንም ይሉኛል ደቂቀ አስዌዋ ጋኔን ያወጡ ነበር።
ወበስምከ ኃይላተ ብዙኃ ገበርነ
በስምህ ፍጹም ታምራት ስናደርግ አልነበርንም ይሉኛል።
ይሁዳ ሙት እስከ ማንሣት ደርሶ ነበርና።
                  ******                 
፳፫፡ ወይእተ ጊዜ እብሎሙ ግሙራ ኢየአምረክሙ ረኃቁ እምኔየ ኵልክሙ እለ ትገብሩ ዓመፃ። መዝ ፮፥፱፡፡ ማቴ ፳፭፥፵፩፡፡ ሉቃ ፲፫፥፳፯።
                  ******                 
፳፫፡ ያን ጊዜ ከቶ አላውቃችሁም ዓመፅን የምትሠሩ ሁላችሁም፡፡
(ሐተታ) ፈጥሮስ አላውቃችሁም አይልም። ወለድኋችሁ ካድኋችሁ እላቸዋለሁ።
                  ******                 
፳፬፡ ኵሉኬ ዘይሰምዕ ዘንተ ቃልየ ወይገብሮ ይመስል ብእሴ ጠቢበ ዘሐነፀ ቤቶ ዲበ ኰኵሕ ሉቃ ፮፥፵፰፡፡ ሮሜ ፪፥፲፫፡፡ ያዕ ፩፥፳፪።
፳፬፡ ይኸን የኔን ነገር ሰምቶ የሚሠራው ሰው ሁሉ ቤቱን በጭንጫ ላይ የሠራ ብልህ ሰውን ይመስላል።
                  ******                 
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
01/08/2011 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment