Sunday, April 7, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 57

====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
ምዕራፍ ፯።
በእንተ ትእዛዛት፡፡
                  ******       
፮፡ ኢተሀቡ ቅድሳተ ለከለባት። ማቴ ፳፩፥፳፪፡፡ ማር ፲፩፥፳፬፡፡ ሉቃ ፲፩፥፱፡፡ ዮሐ ፲፪፥፲፫፡፡ ያዕቆብ ፩፥፮።
                  ******       
፮፡ የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ ማለት ኢትኰንኑ ካለንስ ብላችሁ ሥጋዬን ደሜን በአይሁዳዊነት ግብር ላለ ሰው አትስጡ።
ወኢትደዩ ባሕርየክሙ ቅድመ አኅርው።
ዕንቋችሁንም በእሪያ ፊት አታኑሩ።
ከመ ኢይኪድዎ በእገሪሆሙ።
በእግራቸው እንዳይረግጡት።
ወተመይጦሙ ይነጽሑክሙ።
ተመልሰው ይጻሏችኋል።
(ሐተታ) በሀገራቸው ቀን ዋዕየ ፀሐይ ይጸናል። ሌሊት ዕንቊ ከተራራ ላይ አኑረው የሚጽፍ ሲጽፍ የሚያድን ሲያድን ያድራሉ እሪያ መልከ ጥፉ ነው ባጠገቡ ሲሔድ የገዛ መልኩን አይቶ ደንግጦ ሲሔድ ሰብሮት ይሄዳል ዕንቊ የጌታ እሪያ የአይሁድ ምሳሌ። አሌ ለክሙ ጸሐፍት ወፈሪሳውያን እያለ በገዛ ኃጢአታቸው ቢዘልፋቸው ጠልተው ተመቅኝተው ሰቅለው ገድለውታልና። ከመ ኢይኪድዎ። እንዳይነቅፉት ወተመይጦሙ አማርኛችን ከአማርኛችሁ ኃይለ ቃላችን ከኃይለ ቃላችሁ እያሉ ተመልሰው ፍትሑ ርትዑ ሥላሴን ያስፈርዱባችኋልና።
አንድም ኢተሀቡ እያልህ መልስ። ሃይማኖታችሁን ለመናፍቅ አትንገሩ
ከመ ኢይኪድዎ።
እንዳይነቅፉት።
ወተመይጦሙ።
አማርኛችን ከአማርኛችሁ ኃይለ ቃላችን ከኃይለ ቃላችሁ አንድ ነው እያሉ ይከራከራችኋልና።
አንድም መልስ። በተዓቅቦ ያገኛችሁትን ምሥጢር ላልበቃ ሰው አትንገሩ፤ ሰው ሲሆኑ ለዚህን ይበቃሉ እንዳይሏችሁ።
ወተመይጦሙ
ተመልሰው ፍትሑ ርትዑ ሥላሴን ያስፈርዱባችኋል።
                  ******       
፯፡ ሰአሉ ወይትወሀበክሙ።
                  ******       
፯፡ የበቃውን ያልበቃውን በምን እናውቀዋለን ትሉኝ እንደሆነ ለምኑ ይሰጣችኋል።
(ሐተታ) እንደ ዮሐንስ ዘደማስቆ። እንደ ድሜጥሮስ የበቃና ያልበቃ ለይተው ይሰጡ ነበር።
ኀሡ ወትረክቡ።
ሹ ታገኛላችሁ።
ጐድጕዱ ወይትረኃወክም ።
እጅ ጽፉ ይከፈትላችኋል።
                  ******       
፰፡ እስመ ኵሉ ዘሰአለ ይነሥእ።
                  ******       
፰፡ የለመነ ሁሉ ያገኛልና። ሰአሉ ለምነው ያገኙ ብዙ ናቸው ከዚያው ግን አዳም።
ወዘሂ ኃሠሠ ይረክብ
የሻም ያገኛልና
ኅሡ። ሽተው ያገኙ ብዙ ናቸው ከዚያው ግን ከቀደሙ ሰዎች አብርሃም ከኋላ ሰዎች ሙሴ ጸሊም በፀሐይ በስነ ፍጥረት ተመራምረው አምነዋል።
ወለዘሂ ጐድጐደ ይትረኃዎ።
እጁን ለጸፋም ይከፈትለታልና
ጐድጐደ ላለው እንደ ፈያታይ ዘየማን።
                  ******       
፱፡ መኑ ውእቱ እምኔክሙ ዘይስእሎ ወልዱ ወዕብነ ይሁቦ።
                  ******       
፱፡ እኛ ለሌላው በጎ ነገር ስንለምን በኛ ክፉ ነገር ቢደረግብንሳ ትሉኝ እንደሆነ ከናንተ ወገን ልጁ ዳቦ የሚለምነው አባቱ ደንጊያ የሚሰጠው ማን አለ።
አንድም ዕብነኑ ይሁቦ ልጁ ዳቦ ቢለምነው ጥርሱን ይስበረው ብሎ ደንጊያ ይሰጠዋልን ከዚያው ቅሉ ላይ ላዩን ትቶ ልብ ልቡን ይሰጠው የለምን።
                  ******       
፲፡ ወእመሂ ዓሣ ሰአሎ ወዓርዌ ምድር ይሁቦ።
                  ******       
፲፡ ከናንተ ወገን ልጁ ዓሣ የሚለምነው አባቱ እባብ የሚሰጠው ማን አለ። ዓርዌ ምድርኑ ይሁቦ መርዙ ይግደለው ብሎ እባብ ይሰጠዋልን። ከዚያው ቅሉ አጥንት አጥንቱን ትቶ ሥጋ ሥጋውን ይሰጠው የለም
በሉቃስ ወአመኒ አንቆቅሆ ሰአሎ አቅረበኑ ይሁቦ ይላል።
ልጁ እንቁላል የሚለምነው አባቱ እምቧይ የሚሰጠው ማን አለ።
አንድም ልጁ እንቁላል ቢለምነው አባቱ እንቧይ ይሰጠዋልን ከዚያ ቅሉ ቅርፍት ቅርፍቱን ትቶ አስኳል አስኳሉን ይሰጠው የለምን።
                  ******       
፲፩፡ ወሶበ እንዘ እኩያን አንትሙ ተአምሩ ሠናየ ሀብተ ውሂበ ለውሉድከ እፎ እንከ ፈድፋደ አቡክሙ ይሁቦሙ ይስእልዎ።
                  ******       
፲፩፡ ከእኛ ወገን እንዲህ የሚያደርግስ የለም ትሉኝ እንደሆነ፤ ዘአንትሙ እንዘ አንትሙ ይላል። ለባሕርያችሁ ክፋት ጥመት የሚስማማችሁ ስትሆኑ እናንተ ለልጆቻችሁ በጎ ነገርን የምታደርጉላቸው ከሆነ ቸርነት የባሕርዩ የሚሆን ሰማያዊ አባታችሁማ በጎ ነገርን ለሚለምኑት እንደምን በጎ ነገርን ያደርግላቸው ይሆን፡፡
                  ******       
፲፪፡ ኵሎኬ ዘትፈቅዱ ይግበሩ ለክሙ ሰብአ ከማሁ አንትሙኒ ግበሩ ሎሙ፡፡
፲፪፡ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተም አድርጉላቸው
                  ******       
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
29/07/2011 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment