Monday, April 22, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 73

====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በከመ ተፈነዉ ሐዋርያት።
ምዕራፍ ፲።
                   ******    
፯፡ ወሐዊረክሙ ስብኩ እንዘ ትብሉ ቀርበት መንግሥተ ሰማያት
                   ******    
፯፡ ሂዳችሁ ደጊቱ በልጅነት ልጅነት በሃይማኖት የምትሰጥበት ጊዜ ደርሷል እያላችሁ አስተምሩ።
                   ******
  ፰፡ ድውያነ ፈውሱ።
                   ******    
፰፡ ድውያንን ፈውሱ።
ሙታነ አንሥኡ።
ሙት አንሡ።
እለ ለምጽ አንጽሑ።
ለምጽ አድኑ
አጋንንተ አውጽኡ።
አጋንንትን አውጡ፥
በጸጋ ዘነሣእአክሙ በጸጋ ሀቡ
በለጋስነት የተማራችሁትን በለጋስነት አስተምሩ።
በከንቱ ዘነሣዕክሙ በከንቱ ሀቡ
ዋጋ ሳትሰጡ የተማራችሁትን ዋጋ ሳትቀበሉ አስተምሩ፡፡
አንድም በጸጋ ዘነሣእክሙ በታምራት የተማራችሁትን በታምራት አስተምሩ በከንቱ ዘነሣእክሙ ሳትጥሩ የተማራችሁትን ሳይጥሩ አስተምሩ
                   ******    
፱፡ ኢታጥርዩ ለክሙ ወርቀ ወኢብሩረ ማር ፮፥፰፡፡ ሉቃ ፱፥፫፡፡ ፲፥፬፡፡
                   ******    
፱፡ ወርቅ ብር አትያዙ
ወኢጸሪቀ ውስተ ቅናውቲክሙ፡፡
 በዝናራችሁ ቊናማቲክሙ ይላል። በተረንተራችሁ ሻሜ መሐልቅ አትያዙ።
                   ******    
፲፡ ወኢጽፍነተ ለፍኖት።
                   ******    
፲፡ የስንቅ አቅማዳም አትያዙ።
ወኢ፪ኤ ክዳናተ።
ሁለት ልብስም አትያዙ። ይህን የሚሹ ሥጋውያን ናቸው እሳቸው ግን መንፈሳውያን ናቸውና ይህን አይሹም።
አንድም ሁለት ልብስ ባይኖረን አንዱን ለብሰን አንዱን ሽጠን ባንመገብ እንደምን በሆነ ነበር ብሎ ያዳክማልና እንዳያዳክማቸው ነው፡፡
ወኢዓሣዕነ።
ጫማ አታድርጉ ይህ ለሥጋውያን ነው እሳቸው ግን መንፈሳውያን ናቸውና ደህን አይሹትም።
አንድም ጫማ ባይኖረን እሾሁን እንቅፋቱን ዋዕዩን እንደምን ባለፍነው ነበር ብሎ ያዳክማልና አንዳያዳክማቸው ነው።
አንድም ጌጸኛውን ሲል ነው።
ወኢበትረ።
በትርም አትያዙ። ይህ ለሥጋውያን ነው እሳቸው ግን መንፈሳውያን ናቸውና ይህን አይሹትም።
አንድም በትር ባንይዝ ውሻው እባቡ እንደምን ባደረገን ነበር ብሎ ሃይማኖት ያዳክማልና እንዳያዳክም ነው
አንድም ጌጸኛውን ሲል ነው
እስመ ይደልዎ አስቡ ለዘይትቀነይ።
ለሚሠራ ዋጋ ይገባዋልና ለሚያስተምር መምህር የለት ራት አንድ እንጀራ ጽዋ ውሀ ይገባዋልና።
ኢታጥርዩ።
አንድም ስናስተምር ውለን ምን እንመገባለን ትሉኝ እንደሆነ ለሚያስተምር ለመምህር እንጂ የዕለት ራት አንድ እንጀራ ጽዋ ውሀ ይገባዋል እነዚያው ይመግቧችሁ።
                   ******    
፲፩፡ ወውስተ ሀገር እንተ ቦእክሙ ወእመኒ አብያት ተስአሉ ወበሉ ለመኑ ይደልዎ ሰላም በውስቴታ።
                   ******    
፲፩፡ ከገባችሁበት አገር ከገባችሁበት ቤት ደግ ሰው የበቃ ማን አለ ብላችሁ ጠይቁ።
ወህየ ኅድሩ እስከ አመ ትወጽኡ።
ለማስተማር ወጥታችሁ እስክትሄዱ ድረስ ከዚያ ኑሩ።
(ሐተታ) ምዕመናን ለመማር በመጡ ጊዜ እንዳያጧቸው ነው።
አንድም ከአንዱ ወደ አንዱ ሲሉ ያይዋቸው እንደሆነ እኒህማ ምግብ ለማሻሻል መጥተዋል እንጂ መቼ ለማስተማር መጥተዋል እንዳይሏቸው።
                   ******    
፲፪፡ ወበዊአክሙ ውስተ ቤት ተአምኅዎሙ።
                   ******    
፲፪፡ ከቤት በገባችሁም ጊዜ እጅ ንሷቸው ማለት አክብሯቸው እንጂ አክብሩን አትበሉ።
ወለእመ ይደልዎ ለውእቱ ቤት ይኅድር ሰላምክሙ ላዕሌሁ
የበቃ ደግ ሰው የተገኘ እንደሆነ ሰላማችሁ እኔ አድርበታለሁ
                   ******    
፲፫፡ ወእመሰ ኢይደልዎ ይግባእ ሰላምክሙ ላዕሌክሙ
                   ******    
፲፫፡  የበቃ ደግ ሰው ያልተገኘ እንደሆነ ግን ሰላማችሁ በናንተ ይደር ማለት ሰላማችሁ እኔ በናንተ እንዳደደርኩ እቀራለሁ።
                   ******    
፲፬፡ ወለዘሰ ኢተወክፈክሙ ወኢሰምዓ ነገረክሙ ወፂአክሙ አፍአ እምውእቱ ቤት ወእም ውእቱ ሀገር ንግፉ ፀበለ እገሪክሙ።
                   ******    
፲፬፡ እናንተን አልቀበልም ትምህርታችሁንም አልሰማም ያለ ሰው ካለበት ቤት ካለበት አገር ወጥታችሁ የእግራችሁን ትቢያ አራግፉ።
(ሐተታ) ስንኳን ገንዘባችሁ ትቢያችሁ አልተከተለንም ለማለት። እኛ ደክመንላችሁ በእምቢታችሁ ቢቀርባችሁ ፍዳችሁ በራሳችሁ ነው ለማለት።
አንድም ይህ ትቢያ ከኛ እንደተለየ እናንተም ከኛ ልዩ ናችሁ ለማለት፡፡
አንድም ትቢያ እንደ ረገፈ እናንተም በሥጋችሁ በመቅሰፍት በነፍሳችሁ በገሃነም ትጠፋላችሁ ለማለት፡፡
አንድም በቄሣር ልማድ የተበደለ ሰው ቢኖር እንጨት ተክሎ ሣር ቋጥሮ መጥቶ ይንገረኝ ብሎ ነበርና።
                   ******    
፲፭፡ አማን እብለክሙ ከመ ይረክባ ሳሕተ ምድረ ሰዶም ወገሞራ አመ ዕለተ ደይን ፈድፋደ እምይእቲ ሀገር።
                   ******    
፲፭፡ እናንተን አልቀበልም ትምህርታችሁን አልሰማም ያለ ሰው ሁሉ ካለበት አገር ይልቅ ሰዶም ገሞራ በፍርድ ቀን ዕረፍትን ያገኛሉ ብዬ እንዲያገኙ በእውነት እነግራችኋለሁ። በሀገሩ ሰዎቹን መናገር ነው ፍዳ ይቀልላቸዋል ማለት ነው።
                   ******    
፲፮፡ ወናሁ አነ እፌንወክሙ ከመ አባግዕ ማዕከለ ተኲላት። ሉቃ ፲፥፫፡፡
፲፮፡ ተኲላ አለና ብለው አባግዕን ከቤት እንዳያውሏቸው ተኲላ ወዳለበት እንዲያሰማሯቸው፡፡
                   ******      
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
15/08/2011 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment