====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ መጻጒዕ።
ምዕራፍ ፱።
******
በእንተ ፪ቱ ዕውራን።
፳፯፡ ወኃሊፎ እግዚእ ኢየሱስ እምህየ ተለውዎ ፪ቱ ዕውራን፤
******
፳፯፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዚያ አልፎ ሲሄድ ሁለት ዕውራን ተከተሉት።
እንዘ ይጸርሑ ወይብሉ ተሣሃለነ ወልደ ዳዊት።
ወልደ ዳዊት እዘንልን ይቅር በለን እያሉ
******
፳፰፡ ወበዊኦ ቤተ መጽኡ ኀቤሁ እሙንቱ ዕውራን።
******
፳፰፡ ለዕውራን ርቆ መሄድ አይሆንላቸውምና ከቤት ገብቶ ቆይቷቸዋል ከቤት በገባ ጊዜ ዕውራን ወደሱ መጡ።
ወይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ ተአምኑሁ ከመ እክል ዘንተ ገቢረ።
ጌታም ዕውር ማዳን እንዲቻለኝ ታምናላችሁን አላቸው።
ወይቤልዎ እወ እግዚኦ።
አቤቱ አዎን እናምናለን አሉት። (ሐተታ) እወ እንዲሉት ያውቅ የለም ቢሉ አላዋቂ ሥጋን እንደተዋሃደ ለማጠየቅ።
ኦኮ ኢያእምሮ ኅቡዓተ አላ ከመ የሀብ መካነ ለጥንተ ትስብእቱ ዘኢየአምር ኅቡዓተ እንዲል፡፡
አንድም አወቅሁት ብሎ ሥራውን አይተውምና በዚያው ሥራውን ለመሥራት
አንድም ሃይማኖታቸውን ለማስገለጽ።
******
፳፱፡ ወገሠሦሙ አዕይንቲሆሙ።
******
፳፱፡ ዓይናቸውን ዳሰሳቸው።
ወይቤሎሙ በከመ ሃይማኖት ከመ ይኩንክሙ።
እንደ ሃይማኖታችሁ ይደረግላችሁ አላቸው።
******
፴፡ ወሶቤሃ ተከሥተ አዕይንቲሆሙ
******
፴፡ ያን ጊዜ ዓይናቸው ዳነ።
ወገሠፆሙ እንዘ ይብል ዑቁ ኢትንግሩ ለመኑሂ።
ለማንም ለማን እንዳትነግሩ ዕወቁ ብሎ አስተማራቸው ውዳሴ ከንቱ አይሻምና የሚያምኑበት ጊዜ አልደረሰምና።
አንድም እስከ ትንሣኤ።
******
፴፩፡ ወወፂኦሙ ነገሩ ለኵሉ ብሔር
******
፴፩፡ ወጥተው ለሰው ሁሉ ተናገሩ አትንገር ያሉት ሰው መንገር ልማድ ነውና።
አንድም ጊዜው ቢደርስ።
በእንተ ጽሙም ዘቦቱ ጋኔን
******
፴፪፡ ወእምዝ አምጽኡ ኀቤሁ ዘጋኔን ፅሙመ ወበሀመ። ማቴዎ ፲፪፥፳፪፡፡ ሉቃ ፲፩፥፲፬።
፴፪፡ ከዚህ በኋላ ጋኔን ድዳ ደንቆሮ ያደረገውን ሰው ይዘው መጡ። ድዳ ደንቆሮ ጋኔን ሲያድርበት ሰውም ድዳ ደንቆሮ ይሆናልና።
******
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
11/08/2011 ዓ.ም
Friday, April 19, 2019
ወንጌል ቅዱስ ክፍል 69
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment