Monday, April 8, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 58


====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
ምዕራፍ ፯።
በእንተ ትእዛዛት፡፡
                  ******        
፲፪፡ ኵሎኬ ዘትፈቅዱ ይግበሩ ለክሙ ሰብአ ከማሁ አንትሙኒ ግበሩ ሎሙ፡፡
                  ******
፲፪፡ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተም አድርጉላቸው
እስመ ከማሁ አሪትኒ ወነቢያትኒ
አሪት ነቢያት እንዲሀ ብለዋልና፤ ባኡ ማንሻ።
                  ******         
፲፫፡ ባኡ እንተ ጸባብ አንቀጽ፡፡
                  ******         
፲፫፡ ኦሪትም ነቢያትም ባኡ እንተ ፀባብ አንቀጽ ብለዋልና ወደ ፀባብ በር ግቡ በፀባብ መንገድ ሂዱ
እስመ ርሂብ አንቀጽ ወስፍሕት ፍኖት እንተ ትወስድ ውስተ ኃጕል
ወደ ጥፋት የምታደርስ ሰፊ በር ሰፊ መንገድ አለችና፤
ወብዙኃን እሙንቱ እለ ይበውኡ ውስቴታ
ወደርስዋ የሚገቡ ብዙ ናቸው
                  ******         
፲፬፡ ጥቀ ፀባብ አንቀጽ ወጽዕቅት ፍኖት አንተ ትወስድ ውስተ ሕይወት።
                  ******         
 ፲፬፡ ወደ ሕይወት የምታደርስ እጅግ ጭንቅ በር አጅግ ጭንቅ መንገድ አለችና።
ወውኁዳን እሙንቱ እለ ይበውእዋ።
ወደሷ የሚገቡ ጥቂት ናቸውና ሰፊውን በር ሰፊውን መንገድ ትታችሁ በፀባብ በር በፀባብ መንገድ ሂዱ።
(ሐተታ) ሰፊ በር ሰፊ መንገድ የተባለች ኦሪት ናት ለእመ ዓቀብከ ኦሪተከ ትበልዕ ከራሜ ከራሚከ ወደሰፍሕ ማኅበብተ ወይንከ ወትሬኢ ውሉደ ውሉድከ እስከ ሣልስ ወራብዕ ትውልድ ትላለችና። ጠባብ በር ጭንቅ መንገድ የተባለች ወንጌል ናት ለዘሂ ፀፍዓከ መልታሕቴከ እንተ የማን ሚጥ ሎቱ ካልዕታሂ ወለዘሂ አበጠከ አሐደ ምዕራፈ ሑር ምስሌሁ ወአብጽሕ ሎቱ ፪ተ ምዕራፈ ወለዘሂ ይፈቅድ ይትዓገልከ መልበሰከ ኅድግ ሎቱ ክዳነከሂ ትላለችና።
አንድም ሰፊ በር ሰፊ መን የተባለ ፈቃደ ሥጋ ነው ጠባብ በር ጠባብ መንገድ የተባለች ፈቃደ ነፍስ ናት።
አንድም ሰፊ በር ሰፊ መንገድ የተባለ ባለጸጋን መጽውት ድኃን ጹም ማለት ነው፤ ጠባብ በር ጠባብ መንገድ ባለጸጋን ጹም ድኃን መጽውት ማለት ነው።
አንድም ዕዝራ ያያት መንገድ ናት። የማና እሳት ወፀጋማ ቀላይ ወኢታገምር ዘእንበለ ኪደተ ፩ዱ እግረ ብእሲ እንዲል። ያላንድ ጫማ የማታስቆም መንገድ አይቷል፤ እሷ ቅሉ በሕገ ነፍስ ካልሆኑ አትገገባም ሲል ነው እንጂ በቁሙ አይደለም። ከዚህም ጌታን የጻድቃን ማነስ የኃጥአን መብዛት አያሳዝነውም ጥቂት ዕንቊ ያለው ብዙ ወርቅ ባለው ጥቂት ወርቅ ያለው ብዙ ብር ባለው ጥቂት ብር ያለው ብዙ ብረት ባለው ጥቂት ብረት ያለው ብዙ ሸክላ ባለው ጥቂት ሸክላ ያለው ብዙ ደንጊያ ባለው እንዳይቀና
                  ******         
፲፭፡ ተዓቀቡኬ እምሐሳውያን ነቢያት እለ ይመጽኡ በአልባሰ አባግዕ
                  ******         
፲፭፡ የበግ ለምድ ለብሰው ማለት እውነተኞች መስለው ከሚመጡ ከሐሰተኞች ሃይማኖታውያን መስለው ከሚመጡ ከመናፍቃን መንፈሳውያን መስለለው ከሚመጡ ከሥጋውያን መምራን ተጠበቁ።

ወእንተ ውስጦሙሰ ተኩላት መሰጥ እሙንቱ።
በውስጥ ግን ነጣቂ ተኩላ ናቸው ማለት ቢመረምሯቸው ግን ሰውን እየነጠቁ ወደ ገሃነም የሚያወርዱ ናቸው፡፡ በከመ ይቤ ኢዮብ የሚል አብነት ይገኛል ተናግሮ ሳይጻፍ የቀረ ነው።
                  ******         
፲፮፡ ወእምፍሬሆሙ ተአምርዎሙ።
                  ******         
፲፮፡ እውነተኛ መሰለው የሚመጡ ሐሰተኞችን ሃይማኖታውያን መስለው የሚመጡ መናፍቃንን መንፈሳውያን መስለው የሚመጡ ሥጋውያኑን መምህራን በምን እናውቃቸዋለን ትሉኝ እንደሆነ በሥራቸው ታውቋቸው አላችሁ።
ይቀስሙሁ እምአስዋክ አስካለ ወእምአሜከላ በለሰ።
በዚያውስ ላይ ሥራቸውን አንሠራም እንጂ ትምርታቸውንማ ብንማር ምን ዕዳ ይሆናል ትሉኝ እንደሆነ ከሾህ ፍሬን ከደንደር በለስን ይለቅማሉ ከመናፍቅ መምህር ሃይማኖትን ከሥጋዊ መምህር መንፈሳዊ ትምርትን ከሐሰተኛ መምህር እውነተኛ ትምህርትን ይማራሉን።
ከማሁኬ።
መርዝ መርዝን ኮሶ ኮሶን እንዲያፈራ። መናፍቅ መምህር ክህደት ኑፋቄን ሥጋዊ መምህር ሥጋዊ ትምርትን ሐሰተኛ መምህር ሐሰትን እንዲያስተምር።
                  ******         
፲፯፡ ኵሉ ዕፅ ሠናይ ፍሬ ሠናየ ይፈሪ።
                  ******         
፲፯፡ ወይን ወይንን በለስ በለስን ያፈራል። ሃይማኖታዊ መምር ሃይማኖትን መንፈሳዊ መምር መንፈሳዊ ትምርትን እውነተኛ መምር እውነተኛ ትምርትን ያስተምራል
ወእኩይሰ ዕፅ ፍሬ እኩየ ይፈሪ።
መርዝ መርዝን ኮሶ ኮሶን ያፈራል፤ መናፍቅ መምር ክህደትን ሥጋዊ መምር ሥጋዊ ትምሕርትን ሐሰተኛ መምር ሐሰትን ያስተምራል።
                  ******         
፲፰፡ ኢይክል ዕፅ ሠናይ ፍሬ እኩየ ፈርየ።
፲፰፡ ወይን ኮሶን በለስ መርዝን አያፈራም።
                  ******                 
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
30/07/2011 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment