====================
የጌታችን
የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ
ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
ምዕራፍ
፮።
******
፲፬፡ እስመ ለእመ ኃደግሙ ለሰብእ አበሳሆሙ
የኃድግ ለክሙኒ አበሳክሙ አቡክሙ ሰማያዊ። ሲራክ ፳፰፥፫። ማቴ ፲፰፥፴፭፡፡ ማር ፲፩፥፳፭፡፡
******
፲፬፡ እናንተ ይቅር ብትሉ ሰማያዊ አባታችሁ
የናንተንም ኃጢአት ይቅር ይላችኋልና ይቅር ይላችሁ ዘንድ ይቅር በሉ።
******
፲፭፡ ወእመሰ ኢኃደግሙ ለሰብእ አበሳሆሙ
ለክሙኒ ኢየኃድግ አበሳክሙ አቡክሙ ሰማያዊ።
******
፲፭፡ የሰውን ኃጢአት ይቅር ባትሉ ግን ሰማያዊ
አባታችሁ ይቅር አይላችሁምና ይቅር ይላችሁ ዘንድ ይቅር በሉ፡፡
አንድም ይቅር ብትሉ ይቅር ይላችኋል ይቅር
ባትሉ ይቅር አይላችሁም።
አብዝታትሁ አትጸልዩ ብሎ ነበረና አጭር ጸሎት
ጩኸችሁ አትጸልዩ ብሎ ነበርና
የሕሊና ጸሎት ቋሚ ለጓሚ ገረድ ደንገጽር
ሲቆሙ ሲቀመጡ ሲተኙ ሲነሱ በ፯ቱ ጊዜያት የሚጸልዩት አጭር ጸሎት ሠራልን። እንዲህ ግን ስለሆነ ከሰማንያ አሐዱ መጻሕፍት ያለ አምስት
ነገር አለበት፡፡ ሃይማኖት ተስፋ ፍቅር ትሕትና ጸሎት።
ሃይማኖት፡- ያላዩትን እግዚአብሔርን አቡነ
ማለት።
ተስፋ፡- ትምጻእ መንግሥትከ ማለት።
ፍቅር፡- ለነ ብሎ አንዱ ለአንዱ መጸለይ።
ትሕትና፡- ቅዱሳን ከበቁ በኋላ ኅድግ ለነ
አበሳነ ማለት፡፡
ጸሎት፡- መላው ጸሎት ነው።
******
፲፮፡ ወሶበ ትጸውሙ ኢትኩኑ ከመ መደልዋን።
******
፲፮፡ በምትጾሙበት ጊዜ እንደ ግብዞች አትሁኑ።
እስመ እሙንቱ ይትመጸለዉ ወይቈጽሩ ገጾሙ
ወያማስኑ።
እነዚያ ፊታቸውን አጠውልገው ግንባራቸውን
ቋጥረው ሰውነታቸውን ለውጠው ይታያሉና።
ከመ ያእምር ሰብእ ከመ ጾሙ።
እንደ ጾሙ ሰው ያውቅላቸው ዘንድ።
አማነ እብለክሙ ነሥኡ ዕሤቶሙ፡፡
ነሥኡ ቢል የወዲህኛውን ውዳሴ ከንቱ አገኙ።
ኃጕሉ ቢል የወዲያኛውን ዋጋቸውን አጡት ብዬ በእውነት እነግራችኋለሁ፡፡
******
፲፯፡ ወአንትሙሰ ሶበ ትጸውሙ ቅብዑ ርእሰክሙ።
******
፲፯፡ እናንተስ በምትጾሙበት ጊዜ ራሳችሁን
ተቀቡ።
ወሕጽቡ ገጸክሙ።
ፊታችሁን ታጸቡ የተቀባ የታጠበ አንዳይታወቅበት
አይታወቅባችሁ ሲል ነው። ይህስ በጌታ ጾም ነው በጾመ ፈቂድ? ቢሉ። በጾመ ፈቃድ ነው እንጂ በጌታ ጾምማ ምን ውዳሴ ከንቱ አለበት?
ይኸውስ በከተማ ነው በገዳም ቢሉ በከተማ ነው እንጂ በገዳምማ ምን
ውዳሴ ከንቱ አለ፡፡ ይህም ሊታወቅ ዳንኤል እምእመ ቦእኩ ገዳመ ሱሳ ኢዓርገ ቅብዕ ዲበ ርእስየ ወኢቦአ ሥጋ ወወይን ውስተ አፉየ
ብሏል።
አንድም ቅበዑ፡፡ ፍቅርን ያዙ። ቅብዕ ኢይርኃቀ
ቅብዕሰ ፍቅረ ደቂቀ እጓለ እመ ሕያው እንዲል። ወሕጽቡ ንጽሕናን ገንዘብ አድርጉ፡፡
አንድም ቅብዑ ትሕትናን ያዙ።
ወሕጽቡ ገጸክሙ።
በአንብዓ ንስሐ ታጸቡ፡፡
******
፲፰፡ ከመ ኢያእምር ሰብእ ከመ ጾምክሙ።
፲፰፡ እንደ ጾማችሁ ሰው እንዳያውቅባችሁ።
******
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ
በየነ
ደብረ
ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
24/07/2011
ዓ.ም
No comments:
Post a Comment