====================
የጌታችን
የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ
ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ
መጻጒዕ።
ምዕራፍ
፱።
******
፩፡
ወዓሪጎ ውስተ ሐመር ዓደወ ወበጽሐ ሀገሮ።
******
፩፡
በመርከብ ተጭኖ ባሕሩን ተሻግሮ ወደ አገሩ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ።
******
፪፡
ወአምጽኡ ኀቤሁ ድውየ መፃጕዓ እንዘ ይጸውርዎ በዓራት፡፡ ማር ፪፥፫፡፡ ሉቃ ፭፥፲፰።
******
፪፡
ደዌ የጸናበት አንድ ሰው ባልጋ ተሸክመው ወደሱ መጡ።
ወርእዮ
እግዚእ ኢየሱስ ሃይማኖቶሙ ይቤሎ ለውእቱ መፃጕዕ ተአመን ወልድየ።
ያድንልናል
ብለው መምጣታቸውን።
አንድም
ሃይማኖቶ ይላል ያድነናል ብሎ መምጣቱን አይቶ ልጄ ሃይማኖትህ አድኖሃልና በሃይማኖትህ ጽና
ወተኀድገ
ለከ ኃጢአትከ።
ኃጢአትህም
ተሰርዮልሃል አለው።
******
፫፡
ወናሁ እለ እምውስተ ጸሐፍት ወፈሪሳውያን ይቤሉ ዝሰ ይጸርፍ።
******
፫፡
ከጸሐፍት ከፈሪሳውያን ወገን የሚሆኑ ይህስ ይሳደባል አሉ
******
፬፡
ወአአሚሮ እግዚእ ኢየሱስ ሕሊናሆሙ ወይቤሉሙ ለምንት ትሔልዩ እኩየ በአልባቢክሙ።
******
፬፡
ጌታ እንዲህ ማለታቸውን አውቆ በልቡናችሁ ክፉ ነገርን ለምን ታስባላችሁ አላቸው።
******
፭፡
ምንት ይቀልል እምብሂለ ተኃድገ ለከ ወእምብሂለ ተንሥእ ወንሣእ ዓራተከ ወሑር።
******
፭፡
ተነሥተህ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ ከማለትና ኃጢአትህ ተሰርዮልሃል ከማለት ማናቸው ይቀላል አላቸው።
******
፮፡
ከመ ታአምሩ ከመ ብውሕ ሎቱ ለወልደ እጓለ እመሕያው ይኅድግ ኃጢአተ በዲበ ምድር።
******
፮፡
ለሰው ልጅ ለክርስቶስ በዚህ ዓለም ኃጢአት ማስተስረይ እንዲቻለው ታውቁ ዘንድ።
(ሐተታ)
ኃጢአት ከማስተስረይ ድውይ መፈወሱን ማብለጡ ነው ሁሉስ የጌትነት ሥራ አይደለም ቢሉ ኃጢአት ሲሰረይ አይታይም ድውይ ሲፈውስ ይታያልና።
ሰውም ካላየው ያየውን ማድነቅ ልማድ ነውና። ሰው በሚያደንቀው ተናገረ።
አንድም
ኃጢአት ተሰረየልህ ከማለትና ተነሥተህ አልጋህን ተሸከመህ ሂድ ከማለት ማን ይቀላል፡፡ ድውይ ሲፈውስ አይታችሁ ኃጢአት ያስተሰርያል
አትሉም አላቸው ሞተ ሥጋ ለሞተ ነፍስ ምልክት እንደሆነ ድኅነተ ሥጋው ለድኅነተ ነፍስ ምልክት ነውና።
ወእምዝ
ይቤሎ ለውእቱ መፃጕዕ ተንሥአ ወንሣእ ዓራተከ ወሑር ቤተከ።
ተነሥተህ
አልጋህን ተሸክመህ ወደ ቤትህ ሂድ አለው፤
(ሐተታ)
ተረፈ ደዌ የለበትምና ፈውሱ ከዓቀብተ ሥራይ ልዩ ነውና እነዚያ አዳንን ከአሉ በኋላ እህል ይቅመስ ይዋል ይደር ይጽናና ይላሉ።
እሱ ግን ተረፈ ደዌ የለበትምና።
አንድም
እነዚያ አዳን ብለው የሚጠጣበት ጽዋው የሚተኛበት አልጋው ምንጣፉ ይገባናል ይላሉ እሱ ግን ይህ ሁሉ የለበትምና ተነሥተህ አልጋህን
ተሸክመህ ሂድ አለው።
******
፯፡
ወተንሢኦ ነሥአ ዓራቶ ወሖረ ቤቶ።
******
፯፡
ተነሥቶ አልጋውን ተሸክሞ ወደ ቤቱ ሄደ።
******
፰፡
ወርእዮሙ ሕዝብ አንከሩ፡፡
******
፰፡
ሕዝቡም አይተው አደነቁ።
ወአእኩትዎ
ለእግዚአብሔር ዘወሀበ ዘከመዝ ሥልጣነ ለሰብእ
ለሰው
እንዲህ ያለ ሥልጣን የሰጠ ማለት አላመኑም ቢሉ እንዲህ ያለ ነቢይ ያስነሣልን ብለው። አምነዋል ቢሉ ለራሱ ድኅነት ይሻ የነበረ
ሥጋን ከባሕርይ ልጅህ ጋራ አዋህደህ ለሌላው ድኅነትን እንዲያድል ያደረግኸው ብለው እግዚኣብሔርን አመሰገኑት።
******
ዘከመ
ተጸውአ ማቴዎስ
፱፡
ወኃሊፎ እግዚእ ኢየሱስ እምህየ ረከበ ብእሴ እንዘ ይነብር ውስተ ምጽባሕ ዘስሙ ማቴዎስ።ማር ፪፥፲፬፡፡ ሉቃ ፭፥፳፯፡፡
፱፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዚያ አልፎ ሲሄድ ማቴዎስ የሚባል ሰው ከሚያስገብርበት ቦታ ተቀምጦ አገኘ።
******
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ
በየነ
ደብረ
ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
08/08/2011
ዓ.ም
No comments:
Post a Comment