====================
የጌታችን
የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ
ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በከመ
ተፈነዉ ሐዋርያት።
ምዕራፍ
፲።
******
፲፮፡
ወናሁ አነ እፌንወክሙ ከመ አባግዕ ማዕከለ ተኲላት። ሉቃ ፲፥፫፡፡
******
፲፮፡
ተኲላ አለና ብለው አባግዕን ከቤት እንዳያውሏቸው ተኲላ ወዳለበት እንዲያሰማሯቸው፡፡
ወደ
ነገሥተ አሕዛብ ወደ መኳንንተ አሕዛብ እሰዳችኋለሁና።
ኩኑ
እንከ ጠቢባነ ከመ አርዌ ምድር ወየውሃነ ከመ ርግብ
እንደ
እባብ ብልህ ሁኑ እንደ ርግብም የዋህ ሁኑ።
አንድም
በሉቃስ እፌንወክሙ ማዕከለ ተኩሉት ይላል። ወደ ነገሥተ አሕዛብ ወደ መኳንንተ አሕዛብ እሰዳችኋለሁና ኩኑ ጠቢባነ።
(ሐተታ)
የእባብ ብልሃቱ ምንድነው ቢሉ ከመንገድ ዳር ሲተኛ ራሱን ቀብሮ ይተኛል እናንተም ራሳችሁን እኔን አትካዱኝ ሲል።
አንድም
ውሀ ሲጠጣ መርዙን ከየብስ አኑሮ ነው ከውሀው የገባ እንደሆነ ተሰራጭቶ ያጠፋኛል ብሎ እናንተም ቂም በቀል ይዛችሁ አትጸልዩ ሲል
ቂም በቀል ይዞ የጸለዩት ጸሎት አይረባም አይጠቅምምና።
እስመ
ዘይነብር ቂመ ውስተ ልቡ ኢውክፍት ጸሎቱ ቅድመ እግዚአብሔር አንዲል አንድም በኖኅ ጊዜ አፉን ከፍቶ ሳለ ርግብ ዋሻ መስሏት ገብታ
እንቊላሏን ጣለች እሷን የበላኋት እንደሆነ ኖኅ አስወጥቶ ይጥለኛል ብሎ እስክትወጣ አፉን እንደከፈተ ቆይቷል ምክንያት አድርጎ እናንተን
የሚያጠፋበትን ሥራ አትሥሩ ሲል ነው።
አንድም
ዕፀ ዘዌ የሚባል ፍሬውን ይወደዋል ጥላው ሲያርፍበት ያደክመዋል ብልህ ነውና ጧት በምሥራቅ ማታ በምዕራብ ሁኖ ይመገበዋል ምክንያት
አድርጎ እናንተን የሚያዳክምበትን ሥራ አትሥሩ ሲል
አንድም
ጥግ ሳይዝ አይጣላም ምክንያት አድርጎ እናንተን የሚጣላበትን ሥራ አትሥሩ ሲል ራቁቱን የሆነ አይነድፍም ምክንያት አድርጎ እናንተን
የሚጣላበትን ሥራ አትሥሩ ሲል፤ ርግብ የዋህ ናት በቀል የላትም እናንተም ኃዳግያነ በቀል ሁኑ ሲል በኖኅ ጊዜ ዋሻ መስሏት ከዘንዶ
አፍ ገብታ በየውሃት ተጠብቃለች እናንተም በየውሃት ሆናችሁ ተጠብቃችሁ ኑሩ ሲል፡፡
አንድም
ከፅፀ ዘዌ ሥር አርፋ በየውሃት ትጠበቃለች። እናንተም በየውሃት ተጠብቃችሁ ኑሩ ሲል። ፀሐይ ልትሞቅ ስትወጣ በምዕራብ ሸምቆ ቈይቶ
እያነቀ ይፈጃታል። እናንተም በየውሃት ሁናችሁ መከራውን ተቀበሉ ሲል።
******
፲፯፡
ወተዓቀቡ እምሰብአ እኵያን
******
፲፯፡
ከክፉ ሰዎች ተጠበቁ
እስመ
ያገብኡክሙ ውስተ አዕዋዳት አዳርሱን ብለው ወደ አደባባይ ይወስዷችኋልና
ወይቀሥፉክሙ
በምኵራባቲሆሙ
በምኵራባቸው
አግብተው ይገርፏችኋልና
******
፲፰፡
ወይወስዱክሙ ኀበ መሳፍንት ወነገሥት በእንቲአየ
******
፲፰፡ በስሜ ስለ አመናችሁ በስሜ ስለ ተጠራችሁ በስሜ ስለ አስተማራችሁ ወደ መኳንንተ
አሕዛብ ወደ ነገሥተ አሕዛብ ይወስዷችኋልና፤
ከመ
ይኩን ስምዓ ላእሌሆሙ
በእስራኤል
መፈራረጃ ይሆንባቸው ዘንድ ምነው ያላመናችሁበት ይሏቸዋል ምን አይተን እንመን ይላሉ ያውሳ በጸባብ ደረት በአጭር ቁመት ተወስኖ
ቢያስተምራችሁ ጸልታችሁ ተመቅኝታችሁ ሰቅላችሁ የገደላችሁት ተብሎ፡፡
አንድም
ምነው ያላመናችሁበት ይሏቸዋል ምን አይተን እንመን ይላሉ ያውሳ ሐዋርያት የሱን ነገር ቢያስተምሯችሁ አንቀበላቸው ብላችሁ ለአሕዛብ
እያሳለፋችሁ ትሰጧቸው የነበረ ተብሎ።
ወላዕለ
አሕዛብ
በአሕዛብም
መፈራረጃ ይሆንባቸው ዘንድ። ምነው ያላመናችሁበት ይሏቸዋል ምን አይተን እንመን ይላሉ። ያውሳ ሐዋርያት የሱን ነገር ወረደ ተወለደ
ብለው ቢያስተምሯቸው አይሁድ አንቀበላቸው ብለው አሳልፈው ሰጥተዋችሁ የቊልቊሊት ትሰቅሏቸው አቅማዳ ታወጧቸው የነበረ ተብሎ።
******
፲፱፡
ወሶበ ያገብኡክሙ ኢተሐልዩ ዘትብሉ ወዘትነቡ። ሉቃ ፲፪፥፲፩፡፡
******
፲፱፡ አዳርሱን ብለው በወሰዷችሁ ጊዜ የምትናገሩትን አታስቡ ማለት አንዲህ ቢሉን
እንዲህ ብለን እንመልሳለን ብላችሁ አታስቡ፡፡
እስመ
ይትወሀበክሙ በይእቲ ሰዓት ዘትትናገሩ።
የምትናገሩት
ፈጥኖ ይሰጣችኋል ማለት በጠየቋችሁ ጊዜ የምትመልሱት ይገለጽላችኋልና፡፡
******
፳፡
እስመ ኢኮንክሙ አንትሙ ዘትትናገሩ አላ መንፈሱ ለአቡክሙ ውእቱ ይትናገር በላእሌክሙ።
******
፳፡
የምትናገሩት እናንተ አይደላችሁምና የሰማይ አባታችሁ የእግዚአብሔር ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስ በእናንተ አድሮ ይናገራል እንጂ።
******
፳፩፡
ወያገብእ እኁ አኅዋሁ ለሞት
******
፳፩፡
በሃይማኖት ወንድም ወንድሙን ለሕማም ለሞት አሳልፎ ይሰጣል።
ወአብኒ
ወልዶ
አባት
ልጁን ኅርማኖስ ፊቅጦርን አሳልፎ እንደ ሰጠው
ወይትነሥኡ
ውሉድ ላእለ አዝማዲሆሙ።
ልጆችም
በአባት በእናታቸው በጠላትነት ይነሡባቸዋል
ወይቀትልዎሙ።
ይጣሏቸዋል
ወትከውኑ
ጽሉዓነ በኅበ ኵሉ ሰብእ በእንተ ስምየ።
በኔ
ስም ስላመናችሁ በኔ ስም ስለ ተጠራችሁ በኔ ስም ስለ አስተማራችሁ በሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤
ወዘአዝለፈ
ትዕግሥቶ ውእቱ ይድኅን፡፡
ታግሦ
መከራውን የተቀበለ እሱ ይድናል እስከ ፍጻሜ ይላል በሉቃስ እስከ ዕለተ ሞት መከራውን የታገሠ ከፍዳ የሚድን እሱ ነው፡፡
******
፳፫፡
ወሶበ ይሰድዱክሙ እምዛቲ ሀገር ጕዩ ውስተ ካልዕታ።
፳፫፡
ካንዱ አገር አስወጥተው ቢሰዷችሁ ወደ አንዱ አገር ሽሹ፡፡
******
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ
በየነ
ደብረ
ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
16/08/2011
ዓ.ም
No comments:
Post a Comment