Saturday, April 6, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 56

====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
ምዕራፍ ፯።
በእንተ ትእዛዛት፡፡
             ****** 
፩፡ ኢትኰንኑ ከመ ኢትትኰነኑ ሉቃ ሮሜ ፮፥፩።
                  ******       
፩፡ አንቀጸ መምሕራን ነው። እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ ማለት ንጹሐን ሳትሆኑ አትፍረዱ፡፡
                  ******       
፪፡ እስመ በኵነኔ ዘኰነንክሙ ትትኰነኑ አንትሙ። ማር ፬፥፳፬፡፡
                  ******       
፪፡ ንጹሕ ሳትሆኑ ብትፈርዱ ይፈርድባችኋልና። ይህስ አይደለም ሰማይኒ ኢኮነ ንጹሐ በቅድሜሁ ይላል ብሎ ሳትሾሙ አትፍረዱ ተሾሞ መፍረድ እንዲገባ ሙሴ በሰለጳድ ኢያሱበአካን ቅዱስ ጴጥሮስ በሐናንያ ቅዱስ ጳውሎስ በበርያሱስ ፈርደዋል።
እስመ በኵነኔ ዘኰነንክሙ ትትኰነኑ አንትሙ
ሳትሾሙ ብትፈርዱ ይፈረድባችኋልና።
ወበመስፈርት ዘሰፈርክሙ ይሰፍሩ ለክሙ።
በሰፈራችሁበት ይሰፍሩላችኋልና። በሰፈርህበት ላዳን በመዘንህበት ሚዛን እንዲሉ።
                  ******       
፫፡ ለምንት ትሬኢ ኃሠረ ዘውስተ ዓይነ ቢጽከ ወሠርዌ ዘውስተ ዓይንከክ ኢትኔጽር።
                  ******       
፫፡ በአንተ ዓይን ያለ ሠረገላ ያታይ በወንድምህ ዓይን ያለ ጉድፍ ለምን ታያለህ
ኢታቤይንኑ።
አታስተውልም።
                  ******       
፬፡ ወእፎ ትብሎ ለአኁከ ኅድገኒ አውፅእ ኃሠረ እምውስተ ዓይንከ
ወንድምህን በአንተ ዓይን ያለ ጉድፍ ተወኝ ላውጣልህ ለምን ትለዋለህ።
ወናሁ ኢትሬኢ ሠርዌ ዘውስተ ዓይንከ።
በአንተ ዓይን ያለውን ሠረገላ ያታይ።
                  ******       
፭፡ ኦ መደልው ቅድመ አውፅእ ሠርዌ እምውስተ ዓይንከ።
                  ******       
፭፡ አንተ ግብዝ አስቀድመህ በአንተ ዓይን ያለ ሠረገላን አውጻ
ወእምዝ ትሬኢ ለአውፅኦ ሐሠር ዘውስተ ዓይነ እኁከ።
ከዚህ በኋላ በወንድምህ ዓይን ያለውን ጉድፍ ላውጣልህ ትለዋለህ እንድታወጣለት ትሆናለህ።
ምንተ ትኔጽር ብለህ መልስ በወንድምህ ልፍረድብህ እንደ ምን ትለዋለህ አንተ እንዲፈረድብህ ሁነህ ሳለህ አታስተውልም ወንድምህን ተወኝ ልፍረድብህ እንደምን ትለዋለህ ባንተ እንዲፈረድብህ ሁነህ ሳለህ። አንተ ግብዝ አስቀድመህ አንተ እንዳይፈረድብህ ሁን ከዚህ በኋላ ወንድምህን ልፍረድብህ ትለዋለህ እንድትፈርድበት ትሆናለህ፡፡
(ሐተታ) የወንድሙን ኃጢአት በጕድፍ የሱን በሠረገላ መስሎ ተናገረ የወንድሙን ኃጢአት የሚያውቀው በከፊል ነው የሱን ግን መላውን ነውና ዳግመኛ ልፍረድብህ በማለቱ ይፈረድበታልና።
አንድም ኢትኰንኑ ከጉባዔ ሳትውሉ ምሥጢር ሳታደላድሉ እናስተምራለን አትበሉ። እናስተምራለን ብትሉ ይፈረድባችኋልና፡፡ ወንድምህን ላስተምርህ እንደምን ትለዋለህ፤ አንተ ሳትማር አታስተውልም ወንድምህን ተወኝ ላስተምርህ እንደምን ትለዋለህ። አንት ሳትማር አንት ግብዝ አስቀድሞ አንተ ተማር ዕወቅ። ከዚህ በኋላ ወንድምህን ላስተምርህ ትለዋለህ እንድታስተምረው ትሆናለህ።
አንድም ለራሳችሁ ጦር ሳይጠፋላችሁ ፆር የሚጠፋበትን ግብር ለሌላው እናስተምራለን አትበሉ። ፆር ሳይጠፋላችሁ እናስተምራለን ብትሉ ይፈረድባችኋልና። ወንድምህን ፆር የሚጠፋበትን ግብር ላስተምርህ ለምን ትለዋለህ ላንተ ፆር ሳይጠፋልህ አታስተውልም። አንት ግብዝ አስቀድመህ አንተ ፆር አንዲጠፋልህ ሁን። ከዚሀ በኋላ ወንድምህን ፆር የሚጠፋበትን ግብር ላስተምርህ ትለዋለህ እንድታስተምረው ትሆናለህ።
                  ******       
፮፡ ኢተሀቡ ቅድሳተ ለከለባት። ማቴ ፳፩፥፳፪፡፡ ማር ፲፩፥፳፬፡፡ ሉቃ ፲፩፥፱፡፡ ዮሐ ፲፪፥፲፫፡፡ ያዕቆብ ፩፥፮።
፮፡ የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ ማለት ኢትኰንኑ ካለንስ ብላችሁ ሥጋዬን ደሜን በአይሁዳዊነት ግብር ላለ ሰው አትስጡ።
                  ******       
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
28/07/2011 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment