Saturday, April 13, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 63

====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ አድኅኖተ ለምጽ።
ምዕራፍ ፰።
                ******  
፲፪፡ ወለውሉደ መንግሥትሰ ያወፅእዎሙ ውስተ ጸናፌ ጽልመት፡፡ ሚልክ ፩፥፲፩፡፡
                  ******   
፲፪፡ ይገባናል የሚሉ እስራኤልን ግን ከመንግሥተ ሰማይ አፍአ ወደ ገሃነም ያወጧቸዋል።       
ኃበ ሀሎ ብካይ ወሐቀየ ስነን
ልቅሶ ጥርስ ቁርጥማት ወዳለበት
                  ******  
፲፫፡ ወይቤሎ እግዚእ ኢየሱስ ለውእቱ ሀቤ ምዕት ሑርኬ ይኩንከ በከመ ተአመንከ።
                  ******  
፲፫፡ ጌታም የመቶውን አዝማች ሂድ እንዳመንህ ደደረግልህ አለው።
ወሐይወ ወልዱ በይእቲ ሰአት ልጁም ያንጊዜ ፈጥኖ ዳነ። የአዳም ነፍሱ ከፍዳ ዳነች።
ወገቢኦ መስፍን ውስተ ቤቱ ረከቦ ለወልዱ ሕያዎ።
ወደ ቤቱ በተመለሰ ጊዜ ሐይዎ ድኖ ሕያወ የዳነ ሁኖ በዘሐይወ በዳነ ገንዘብ አገኘው።
                  ******  
በእንተ ሐማተ ጴጥሮስ።
፲፬፡ ወበዊዖ ቤቶ ለጴጥሮስ ረከባ ለሐማተ ጴጥሮስ እንዘ ትሰክብ ወትፈጽን።
                  ******  
፲፬፡ ከጴጥሮስ ቤት በገባ ጊዜ ሐማተ ጴጥሮስን ሆድ ዝማ ታማ ተኝታ አገኛት፡፡
                  ******  
፲፭፡ ወአኃዛ እዴሃ ወገሠሣ።
እጁዋን ይዞ ዳሰሳት።
ወኃደጋ ፈጸንታ።
ሆድ ዝማዋ ተዋት።
ወተንሥአት ወተልእክቶሙ።
ተነሥታ አገለገለችው መፈትፈት ማሳለፍ አይደለም ለጊዜው የሚበሉትን እያዘጋጀች አቀረበችላቸው ፍጻሜው ግን ከ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት ገብታ ተቈጠረች፡፡
አንድም ወበዊዖ ብለህ መልስ እስራኤልን በመክብባቸው ጴጥሮስ አላቸው፡፡ ጌታ ወደ እስራኤል በመምርነት በገባ ጊዜ ረከባ ለሐማተ ጴጥሮስ። ኦሪትን ስብ ስታጤስ ደም ስታፈስ አገኛት፡፡
ወአኃዛ እዴሃ
፲ቱ ቃላትን ባሉት አጽንቶ አሳለፋት።
ወኃደጋ በኦሪት ሥርዓት ደም ማፍሰስ ስብ ማጤስ ቀረ።
                  ******  
፲፭፡ በምሴተ ከዊኖ አምጽኡ ኅቤሁ ብዙኃነ እለ አጋንንት። ማር ፩፥፴፪።
                  ******  
፲፭፡ ወምሴተ ከዊኖ ወሶበ መስየ ይላል። ሲመሽ በመሸ ጊዜ ብዙ አጋንንት ያደሩባቸው ሰዎች ይዘው መጡ። ፈውሱ ከዓቀብተ ሥራይ ልዩ ነውና። እነዚያ በዚህ ዕለት እንጂ በዚህ ዕለት በዚህ ሰዓት እንጂ በዚህ ሰዓት አይቻለንም ይላሉ። እሱ ግን በመጡበት ሰዓት ሁሉ ያድናቸዋልና፡፡
ወአውጽኦሙ በቃሉ፡፡
ጻኡ መናፍስት ርኩሳን ብሎ አወጣቸው፡፡
ወፈወሰ ኵሎ ድውያነ፡፡
ሕሙማኑን አዳነ።
                  ******  
፲፯፡ ይትፈጸም ቃለ ኢሳይያስ ነቢይ ዘይቤ ውእቱ ነሥአ ደዌነ ወፆረ ሕማመነ ። ኢሳ ፶፫፥፬፡፡ ፩፡ጴጥ ፪፥፳፬።
                  ******  
፲፯፡ ደዌያችነን ተሸከመ ማለት ኢሳይያስ ደዌ ሥጋችነን በተአምራት ደዌ ነፍሳችነን በትምህርት አራቀልን ብሎ የተናገረው ትንቢት ይደርስ ይፈጸም ዘንድ ድውያነ ሥጋን በተአምራት ድውያነ ነፍስን በትምህርት አዳነ፡፡
አንድም ድውያነ ነፍስን በትምርት አዳነ ብሎ ኢሳይያስ የተናገረው ይደርስ ይፈጸም ዘንድ ድውያነ ሥጋን በታምራት አዳነ፡፡ ሞተ ሥጋው ለሞተ ነፍስ ምልክት እንደሆነ። ድኅነተ ሥጋው ለድኅነተ ነፍስ ምልክት ነውና።
አንድም እስከ አፅርዓ ወአሰሰለ ይላል አብነት ደዌ ነፍሳችነን በመስቀል ተሰቅሎ እስኪያርቅልን ድረስ ደዌ ሥጋችነን በታምራት አራቀልን ብሎ ኢሳይያስ የተናገረው ይደርስ ይፈጸም ዘንድ፤ ፈወሰ ድውያንን አዳነ።
አንድም ነቢይ ነሥአ ደዌነ ወፆረ ሕማመነ እንዳለ። ወንጌላዊም ነሥአ ደዌነ ወፆረ ሕማመነ ደዌያችነን ነሣ አለ፡፡
(ታሪክ) ከራድዮን የሚባል ፀዓዳ ፆፍ አለ ይዘው ከቤተ መንግሥት ወስደው ያኖሩታል ሰው ሲታመም ወስደው ያቀርቡታል የሚሞት የሆነ እንደ ሆነ አያየውም ፊቱን ይመልስበታል። የሚድን የሆነ እንደ ሆነ ያየዋል ቀርቦ አፉን ካፉ አድርጎ እስትንፋሱን ይቀበለዋል በእስትንፋስ ምክንያት ደዌ ወደሱ ይመለሳል ነጭ የነበረ ይጠቁራል ብርድ ብርድ ይለዋል ዋዕይ ሲሻ ወደ ዓየር ይወጣል ዋዕይ ሲሰማው ከባሕር ይገባል ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በባሕር ኑሮ የቀደመ ጠጕሩን መልጦ ታድሶ ይወጣል። ከራድዮን የጌታ ምሳሌ ፀዐዳ እንደሆነ ፀዓዳ በመለኮቱ ይለዋልና ድውይ የአዳም ምሳሌ እንደ ማየት በዓይነ ምሕረት አይቶታልና ቀርቦ እስትንፋሱን እንደመቀበል ባሕርዩን ባሕርይ አድርጎለታል በእስትንፋስ ምክንያት ደዌ ወደሱ እንደ ተመለሰ በአዳም የተፈረደውን መከራ ጌታ ለመቀበሉ ምሳሌ። ወቦአ እግዚእነ ውስተ ኵሉ ፀዋትወ መከራ እንተ ባቲ አመከረነ ጸላኢ እንዲል። ወደ ዓየር እንደ መውጣት በመስቀል ተሰቅሏል ከባሕር እንደ መግባት ወደ መቃብር ወርዷል። ሦስት ሌሊት ሦስት መዓልት በከርሠ ባሕር ኑሮ የቀደመ ጠጕሩን ትቶ እንደመነሣት ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በከርሠ መቃብር ኑሮ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ አንድ ወገን ሁኖ ለመነሣቱ ምሳሌ። ኀደገ ንዴተ ህላዌ ተመይጠ ወገብአ ኀበ ስብሐቲሁ ወክብሩ እንዲል።
                  ******  
በእንተ ዘከመ ይደሉ ተሊዎተ እግዚእ ኢየሱስ ።
ወሶበ ርእየ ብዙኃነ ሰብአ ዘተለውዎ አዘዘ ይሑሩ ማዕዶተ ባሕር
የተከተሉትን ብዙ ሰዎች ባየ ጊዜ ባሕሩን ተሻግራችሁ ቈዩኝ አላቸው አሁን ብሔረ ጌርጌሴኖን ገባ ብሎ እንዲያመጣው።
(ሐተታ) እስራኤል አሕዛብን ይጸየፏቸዋልና እንዳይጸየፉ ጌታ ኢያሱን አሕዛብን ፈጽመህ አታጥፋቸው ብሎታል።
ከመ ኢትኩን ምድር አፀ።
ምድረ በዳ እንዳትሆን እስራኤል እየቀደም እየበዙ ሊወርሷት ቢታበዩ ሊቀጧቸው ፆር ሊያስተምሯቸው እንደዚህም ሁሉ ጌታ አጋንንትን ፈጽሞ አላጠፋቸውም የምዕመናን ልቡና ከትሩፋት ባዶ እንዳይሁን ቢታበዩ ሊያዋርዱዋቸው ፆር ሊያስተምሯቸው።
                  ******  
፲፰፡ ወመጽአ ኀቤሁ አሐዱ ጸሐፊ
፲፰፡ ጸሐፊ ማለት አዋቂ ነኝ የሚል ሰው ወደሱ መጣ።
                  ******   
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
05/08/2011 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment