Wednesday, April 17, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 68

====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ መጻጒዕ።
ምዕራፍ ፱።
                   ******
በእንተ ወለተ ኢያኢሮስ
ወበእንተ ደም ዘይውኅዛ ።
                   ******     
፲፰፡ ወእንዘ ዘንተ ይነግሮሙ ናሁ መጽአ አሐዱ መኰንን ወሰገደ ሎቱ። ማር ፭፥፳፪። ሉቃ ፰፥፵፩፡፡
                   ******     
፲፰፡ ይህን ሲነግራቸው ኢያኢሮስ መጥቶ ሰገደለት።
እንዘ ይብል ወለትየ ይእዜ ሞተት።
ልጄ ዛሬ ሞተች አለው።
ወባሕቱ አንብር እዴከ ላዕሌሃ ወተሐዩ።
ነገር ግን መጥተህ እጅህን ጫንባት ትነሳለች አለው።
                   ******    
፲፱፡ ወተንሢኦ ሖረ።
                   ******    
፲፱፡ ተነሥቶ ሄደ።
ወተለውዎ ብዙኃን ሰብእ።
ብዙ ሰዎች ተከተሉት።
ወአርዳኢሁኒ ምስሌሁ።
ደቀ መዛሙርቱን አስከትሎ ሄደ፡፡
                   ******    
፳፡ ወናሁ መጽአት ብእሲት እንተ ደም ይውኅዛ አም ፲ወ፪ቱ ክረምት ወቀርበት እንተ ድኅሬሁ። ማር ፭፥፳፭። ሉቃ ፰፥፵፫፡፡
ካስራሁለት ዓመት ጀምሮ ደም የሚፈሳት ሴት መጣች።
ዘ፲ቱ ወ፪ቱ ዓመት ይላል ደም መፍሰስ ከጀመራት ፲፪ት ዓመት የሆናት ሴት ከወደ ኋላው መጣች።
                   ******    
፳፩፡ ወገሠሠት ጽንፈ ልብሱ እንዘ ትብል በልባ እምከመ ገሠሥኩ ጽንፈ ልብሱ አሐዩ።
                   ******    
፳፩፡ የልብሱን ዘርፍ የዳሰስሁ እንደሆነ እድናለሁ ብላ የልብሱን ዘርፍ ዳሰሰች።
                   ******    
፳፪፡ ወተመይጦ እግዚእ ኢየሱስ ርእያ።
                   ******    
፳፪፡ ጌታም ተመልሶ አያት
ወይቤላ ተአመኒ ወለትየ ሃይማኖትኪ አሕየወተኪ ።
ልጄ ሃይማኖትሽ አዳነችሽ በሃይማኖትሽ ጽኚ አላት። እንዲያው አይደለም ወደ ኋላ ተመልሶ ደቀ መዛሙርቱን መኑ ገሠሠኒ ጽንፈ ልብስየ አላቸው ከዚህ በኋላ ናሁ ብዙኅ ሰብአ ይጸዓቅ ወይጣወቅ አንተሰ ትብል መኑ ገሠሠኒ ጽንፈ ልብስየ አሉት። ታምራት ያደርጋል ነገር ግን ይሠረቀዋል እንጅ እንዳይሉ አአምር ከመ ወፅአ ኃይል እምኔየ ብሏቸዋል ነገሩ ካልቀረስ ብላ ወደ ፊቱ አልፋ ሰገደችለት። ከዚህ በኋላ ተአመኒ ወለትየ ብሏታል እንተ ደም ይውኅዛ የቤተ አይሁድ ልብስ የሐዋርያት አልባሲሁሰ ለክርስቶስ መሃይምናን እሙንቱ እንዲል። ጽንፈ ልብስ ከሐዋርያት ቀጥለው የተነሡ መምሕራን። እንተ ደም ይውኅዛ የልብሱን ዘርፍ ይዛ እንደተፈወሰች ቤተ አይሁድም ከሐዋርያት ቀጥለው ከተነሱ መምህራን ተምረው ስብ ማጤሳቸውን ደም ማፍሰሳቸውን መተዋቸውን መናገር ነው፡፡
ወሐይወት ሶቤሃ ይአቲ ብእሲት።
ፈጥና ያን ጊዜ ዳነች።
                   ******    
፳፫፡ ወመጺኦ አግዚእ ኢየሱስ ቤቶ ለውእቱ መኰንን ረከበ ሰብአ ብዙኀነ መብክያነ እንዘ ይትሀወኩ።
                   ******    
፳፫፡ ጌታችን ከኢያኢሮስ ቤት በደረሰ ጊዜ ብዙ ሰዎች ሲያለቅሱ ሲወጡ ሲገቡ አገኘ። ሹም ቢሞት ፶ የሹም ልጅ ቢሞት መቶ ታምሳ እንዲሉ።
                   ******    
፳፬፡ ወይቤሎሙ ተገኃሡ።
                   ******    
፳፬፡ ተመለሱ አላቸው።
እስመ ኢሞተት ሕፃን።
ብላቴናይቱ አልሞተችምና
አላ ትነውም ።
ተኝታለች አንጂ። እንዲያስነሣት ያውቃልና በነፍስ ሕያዊት ናትና ትቀድሰዋለችና።
ወሰሐቅዎ
በኢያኢሮስ ሳቁበት የሞተና ያልሞተ የማያውቅ ያስነሣልኛል ብሎ ይዞ መጣ ብለው።
አንድም የጌታን ነገሩን እንደ ዋዛ አዩበት ያጠብነ የገነዝነ እኛ እያለን አልሞተችም ይለናል ብለው።
                   ******    
፳፭፡ ወእምዘ ወፅኡ ሰብእ ቦአ ወአኃዛ እዴሃ።
                   ******    
፳፭፡ ሰዎቹ ከወጡ በኋላ ገብቶ እጁዋን ይዞ አስነሣት።
ወተንሥአት ሕፃን።
ብላቴናይቱ ተነሣች። (ሐተታ) እንተ ደም ይውኅዛ የታመመችበት ይህች ብላቴና የተወለደችበት እንተ ደም ይውኅዛ የተፈወሰችበት ይህች ብላቴና የተነሣችበት ቀኑ አንድ ነው።
                    ******    
፳፮፡ ወወፅአ ስሙዓተ ነገሩ ውስተ ኵሉ በሐውርት።
                   ******    
፳፮፡ የተአምራቱ ዜና ስሙዓተ ነገራ ይላል ቀድሞ መሞቷ ኋላ መነሣቷ ባራቱ ማዕዘን ተነገረ፡፡
                   ******    
በእንተ ፪ቱ ዕውራን።
፳፯፡ ወኃሊፎ እግዚእ ኢየሱስ እምህየ ተለውዎ ፪ቱ ዕውራን፤
፳፯፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዚያ አልፎ ሲሄድ ሁለት ዕውራን ተከተሉት።
                   ******    
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
10/08/2011 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment