====================
የጌታችን
የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ
ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ
ሰዊት።
ምዕራፍ
፲፫።
******
፵፭፡
ካዕበ ትመስል መንግሥተ ሰማያት ብእሴ ሠያጤ ዘየኃሥሥ ባሕርየ ሠናየ።
******
፵፭፡
መንግሥተ ሰማያት ሕገ ወንጌል፤ ሕገ ወንጌል ተስፋ፤ ተስፋ ኢየሱስ ክርስቶስ ብሩሃ ሲል ነው ዕንቊን የሚሻ ነጋዴን ትመስላለች።
ወረኪቦ
አኃተ ባሕርየ እንተ ብዙኅ ሤጣ ሖረ ወሤጠ ኵሎ ዘቦ ወተሣየጣ።
ዋጋዋ
ብዙ የሆነ ዕንቊን ባገኘ ጊዜ ያለ ገንዘቡን ሽጦ የገዛትን። ብእሲ ጌታ ዕንቊ አዳም አዳምን ንስሐ ገብቶ ባገኘው ጊዜ ባሕርዩን
ባሕርይ አድርጎ አዳምን ማዳኑን መናገር ነው።
አንድም
ብእሲ ጌታ ዕንቊ አዳም መንግሥተ ሰማይ ሐዋርያት አዳምን የሚሻ ጌታን ይመስላሉ።
አንድም
መንግሥተ ሰማይ ምዕመናን ጌታን የሚሹ ሐዋርያትን ይመስላሉ ሐዋርያ የሚሹት ጌታን ይመስላሉ።
******
፵፮-፵፯፡
ካዕበ ትመስል መንግሥተ ሰማያት ገሪፈ እንተ ተወድየት ውስተ ባሕር ወአስተጋብዓት እምኵሉ ዘመደ ዓሣት።
******
፵፮-፵፯፡
መንግሥተ ሰማይ ሕገ ወንጌል፤ ሕገ ወንጌል ተስፋ፤ ተስፋ ኢየሱስ ክርስቶስ ከባሕር ላይ የጣሏትን ዓሣን ሁሉ ሰብስባ የያዘች ዘረመትራንን
ትመስላለች፡፡
******
፵፰፡
ወሶበ መልዓት አዕረግዋ ውስተ ሐይቅ
******
፵፰፡
በመላች ጊዜ ከወደቡ ያወጧትን
ወነቢሮሙ
ዓረዩ ሠናዮ ወወደዩ ውስተ ሙዳዮሙ።
ከወደቡ
ተቀምጠው ደጋጉን እየመረጡ ከሣጥናቸው አኖሩ። አረዩ ኃረዩ በየኑ ቤጹ ይላል፡፡
ወእኩዮሰ
ገደፍዎ አፍኣ
ክፉውን
ግን መልሰው ከባሕር ጣሉት አጶራግዛ ራስ ከብዶ ይባላል፡፡
******
፵፱፡
ከማሁ ይከውን በኅልቀት ዓለም
******
፵፱፡
በዕለተ ምጽአት እንዲህ ይደረጋል
******
፶፡
ወይመጽኡ መላእክት ወይፈልጡ ኃጥኣነ እማዕከሎሙ ለጻድቃን ወይወድይዎሙ ውስተ ዕቶነ እሳት ኀበ ሀሎ ብካይ ወሐቅየ ሰነን
******
፶፡
መላእክት መጥተው ጻድቃንን ለይተው በመንግሥተ ሰማይ ያኖሯቸዋል። ኃጥኣንን ከጻድቃን ለይተው ልቅሶ ጥርስ ቊርጥማት ባለበት በገሃነም
ያኖሯቸዋል።
አንድም
ትመስል ገሪፈ ብለህ መልስ። ገሪፍ ወንጌል ባሕር ይህ ዓለም። ወአስተጋብአት። ሕዝቡን አሕዛቡን አንድ ያደረገች። ወሶበ መልዓት
ይህ ዓለም የሚያልፍ ጻድቃን በነገደ ዲያብሎስ ልክ ሲሆኑ ነውና።
አንድም
ገሪፍ ሥርዓተ ማኅበር። ባሕር ገዳም። ወአስተጋብዓት ሰውን ሁሉ የሰበሰበች፣ ወሶበ መልዓት ብዙ ዘመን ከረዳ በኋላ ተባሕትዎ ያዝ
ይሉታል። በ፫ በ፯ በ፱ በ፲ ምልክት ይታይለታል በ፬ተኛው በ፰ተኛው በ፲ኛው ተባሕትዎ ይይዛል ምልክት ባይታይለት የረዳበት ዘመን
ተቈጥሮ ይይዛል ምልክት ለሁሉ አይታይምና ወእኩዮሰ፤ ሳይረዳ ተባሕትዎ እይዛለሁ ያለውን ግን ገና ነህ እርዳ ይሉታል ወያወፅእዎ
ዘበአኅሥሮት እንዲል። ከማሁ ይከውን በህልቀተ ዝንቱ ዓለም።
በዕለተ
ምጽአት እንዲህ ይደረጋል።
******
፶፩፡
ወይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ ለበውክሙኑ እንከ ዘንተ ኵሎ።
******
፶፩፡
ጌታ ይህን ሁሉ አወቃችሁት አላቸው፡፡
(ሐተታ)
እንደ ከተማ መምኅር አይደለምና። የከተማ መምህር ቢያዩለትም ባያዩለትም ዝም ብሎ ይሄዳል።
ወይቤልዎ
እወ
አዎን
አሉት። እሳቸውም እንደ ከተማ ደቀ መዝሙር አይደሉምና ያወቁትን አዎን ያላወቁትን ፈክር ለነ ይሉታልና።
******
፶፪፡
ወይቤሎሙ በእንተ ዝንቱ ኵሉ ጸሐፊ ዘይጸመድ ለመንግሥተ ሰማይ ይመስል ብእሴ በዓለ ቤት ዘያወፅእ እመዝገቡ ሐዲሰ ወብሉየ።
******
፶፪፡
ስለዚህ ነገር ወንጌልን የሚያስተምር ሁሉ አሮጌና አዲስ ከሣጥኑ የሚያወጣ ማለት ልልበስ ያለውን የማያጣ ባለ ጸጋን ይመስላል። ልጥቀስ
ቢል አያጣም።
አንድም
አዲሱን ለመልበስ ብሉዩን ለማናፈስ ከሣጥኑ የሚያወጣ ባለጸጋን ይመስላል። ሐዲሱን እያስተማረ ብሉዩን የሚማር ይሆናል፡፡
አንድም
ዘያወፅእ እመዝገቡ ብሉየ ወዘይወዲ ውስቴቱ ሐዲሰ።
ብሉዩን
ከሣጥኑ የሚያወጣ በሣጥኑ ሐዲሱን የሚያኖር ባለጸጋን ይመስላል አእምሮን ገንዘብ የሚያደርግ ውኅደተ አእምሮን የሚያርቅ ይሆናል።
******
ዘከመ
ሖረ እግዚእ ኢየሱስ ውስተ ናዝሬት ።
፶፫፡
ወሶበ ፈጸመ እግዚእ ኢየሱስ እሎንተ ምሳሌያተ ተንሥአ እምህየ ወሖረ ሀገሮ
******
፶፫፡
ጌታችን ኢየሱስ ከርስቶስ ይህን ሁሉ በምሳሌ አስተምሮ ከፈጸመ በኋላ ከዚያ ተነሥቶ ወደ ሀገሩ ወደ ናዝሬት ሄደ።
******
፶፬፡
ወመሀሮሙ በምኵራቦሙ፡፡ ማር ፮፥፩፡፡ ሉቃ ፬፥፲፮፡፡
******
፶፬፡
ከምኵራብ ገብቶ አስተማራቸው
እስከ
ሶበ ይደሙሙ ወይብሉ እምአይቴ እንከ ሎቱ ዝንቱ ኵሉ ጥበብ ወኃይል
ይህ
ሁሉ ጥበብ ኃይል ከወዴት ተገኘለት ብለው እስኪያደንቁ ድረስ። ጥበብ ምሳሌ መስሎ ወኃይል ትርጓሜ ተርጉሞ ማስተማር።
አንድም
ጥበብ ምሳሌ መስሎ ትርጓሜ ተርጉሞ ማስተማር ወኃይል ታምራት ማድረግ ከማን አገኘው
******
፶፭፡
አኮኑ ዝንቱ ውእቱ ወልዱ ለፀራቢ። ዮሐ ፮፥፵፪።
******
፶፭፡
የጠራቢ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን አሉ። በሀገራቸው ልጅ ያባቱን ሥራ ይማራል እንጅ ሌላ አይሰራምና።
ወስማ
ለእሙ ማርያም።
እናቱስ
ማርያም አይደለችምን
ድኃ
ማለት ነው።
ወአኃዊሁኒ
ያዕቆብ ወዮሳ ስምዖን ወይሁዳ።
ወንድሞቹስ
እነዚህ እነዚህ አይደሉምን።
******
፶፮፡
ወአኃቲሁኒ ኵሎን ሀለዋ ኀቤነ
******
፶፮፡
እኅቶቹስ ከኛ ዘንድ ያሉ አይደሉምን።
አንድም
መንፈስ ቅዱስ ፊታቸውን ጸፍቶ አፋቸውን ከፍቶ ምነዋ ቢያደርግ የጸራቤ ሰማያት ወምድር የአብ ልጅ አይደለም። እናቱስ እግዝእተ ብዙኃን
ማርያም አይደለችም ሲያሰኛቸው ነው።
እምአይቴ
እንከ ሎቱ ዝንቱ ኵሉ ጥበብ ወኃይል።
ይህን
ሁሉ ጥበብና ኃይል ከወዴት አገኘው እንዳለፈው ።
******
፶፯፡
ወአኃዙ ያንጐርጕሩ በእንቲአሁ።
******
፶፯፡
በሱ ነገር ይታወኩ ጀመር።
ወይቤሎሙ
እግዚእ ኢየሱስ ኢይትሜነን ነቢይ ዘእንበለ በሀገሩ ወበቤቱ
ነቢይ
ከቤቱና ከሀገሩ በቀር አይነቀፍም ማለት በሀገሩ አይከበርም አላቸው።
******
፶፰፡
ወኢገብረ በህየ ኃይለ ብዙኃ በእንተ ሕፀተ አሚኖቶሙ።
******
፶፰፡
ስለ አለማመናቸው ብዙ ታምራት አላደረገም።
******
በእንተ
ሃለየ ሄሮድስ ላዕለ ኢየሱስ።
ምዕራፍ
፲፬።
፩፡
ወበውእቱ መዋዕል ሰምዓ ሄሮድስ ንጉሥ ነገሮ ለእግዚእ ኢየሱስ፡፡ ማር ፮፥፲፱፡፡ ሉቃ ፱፥፯፡፡
፩፡
በዚያ ወራት ሄሮድስ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ነገር ሰምቶ ማለት ያደረገውን ታምራት የሠራውን ትሩፋት ሰምቶ ድምፀ ነገሩ ይላል
አብነት የታምራቱን ዜና ሰምቶ።
******
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ
በየነ
ደብረ
ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
05/09/2011
ዓ.ም
No comments:
Post a Comment