Monday, May 27, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 103

====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ ዘተግኅሠ ኢየሱስ እምኢየሩሳሌም።
ምዕራፍ ፲፱፡፡
                    ******     
፩፡ ወሶበ ፈጸመ እግዚእ ኢየሱስ ተንሥአ እምገሊላ ወሖረ ወበጽሐ ውስተ ብሔረ ይሁዳ ማዕዶተ ዮርዳኖስ። ማር ፲፥፩፡፡
                    ******     
፩፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ነገር አስተምሮ ከፈጸመ በኋላ ከገሊላ ወጥቶ የዮርዳኖስ ማዶ ወደሚሆን ወደምድረ ይሁዳ ደረሰ።
                        ******     
፪፡ ወተለውዎ አሕዛብ ብዙኃን።
                    ******     
፪፡ ብዙ ሰዎች ተከተሉት።
ወፈወሶሙ በህየ
በዚያም አዳናቸው።
                    ******     
በእንተ ኪዳን ዘኢይትፈታሕ
፫፡ ወመጽኡ ኀቤሁ ፈሪሳውያን ያመክርዎ ወይበልዎ። ማር ፲፥፪
                    ******     
፫፡ ፈሪሳውያን ሊፈትኑት እንዲህ ሊሉት መጡ።
ይከውኖሁ ለብእሲ ኀዲገ ብእሲት በኵሉ ዘአበሰት ሎቱ
ሳትሰስንበት ደረቀች ሰነፈች ብሎ ለሰው ሚስቱን መፍታት ይገባዋልን አሉት።
                    ******     
፬፡ ወአውሥአ
                    ******     
፬፡ መለሰ
ወይቤሎሙ ኢያንበብክሙኑ ዘውስተ ኦሪት ዘከመ ፈጠሮሙ እምትካት ተባዕተ ወአንስተ። ዘፍ ፩፥፳፮።
ጥንቱን አዳምን ወንድ ሔዋንን ሴት አድርጎ እንደፈጠራቸው በኦሪት እንደተጻፈ አልተመለከታችሁም አላቸው፡፡
ብእሴ ወብእሲተ ገብሮሙ
ተባዕተ ያለውን ብእሴ አንስተ ያለውን ብእሲተ አለ።
                    ******     
፭፡ ወይቤ ወበእንተዝ የኃድግ ወእሞ ወይተልዋ ለብእሲቱ፡፡ ዘፍ ፪፥፳፬። ፩፡ቆሮ ፮፥፲፮። ኤፌ ፭፥፴፩፡፡
                    ******     
፭፡ ስለዚህ ነገር ሰው አባት እናቱን ትቶ ሚስቱን ተከትሎ ይሄዳ።
(ሐተታ) ቆላ ብትሆን ቆላ ይወርዳል ደጋ ብትሆን ደጋ ይወጣል።
አንድም እሱ ፈቃድ ቢነሣበት በናቴ ላድርገው አይልም እሷም ፈቃድ ቢነሣባት በአባቴ ላድርገው አትልምና፡፡
አንድም በግብር አንድ ይሆናሉና። ወይታለዋ አባግዓ ቀርሜሎስ እንዲል ይትላጸቃ ሲል።
ወይከውኑ ፪ ሆሙ አሐደ ሥጋ
አንድ አካል ይሆናሉ በግብር፡፡
አንድም ወንዶች ቢወልዱ ያንተ ናቸው ሴቶች ቢወልዱ ያንቺ ናቸው አይባባሉምና።
አንድም እሱን ቢመስሉ ያንተ ይሁኑ አትለውም እሷን ቢመስሉ ያንቸ ይሁኑ አይላትምና።
አንድም በዚህ ዓለም ሳሉ በሕጋቸው ጸንተው አሥራት በኵራት ቀዳምያት አውጥተው እንግዳ ተቀብለው ሥጋውን ደሙን በሚገባ ተቀብለው ቢኖሩ በወዲያውም አንድ ዓለም ወርሰው አንድ ፀሐይ ሞቀው ይኖራሉና።
                    ******     
፮፡ ናሁኬ ኢኮኑ ፪ተ።
                    ******     
፮፡ እነሆ ሁለት አይባሉም።
አላ አሐዱ ሥጋ እሙንቱ።
አንድ አካል ናቸው እንጂ።
ዘእግዚአብሔር አስተጻመረ ሰብእ ኢይፈልጥ።
እግዚአብሔር አንድ ያደረገውን ሰው አይለይም፡፡ አትለይ ሲል ነው።
                    ******     
፯፡ ለምንት እንከ አዘዘ ሙሴ የሀብዋ መጽሐፈ ኅዳጋቲሃ ወይድኃርዋ፡፡ ዘዳ ፳፬፥፩።
                    ******     
፯፡ እንዲህ ከሆነ ሙሴ የምትፈታበትን ነውር የሚናገር ደብዳቤ ሰጥቶ ይፍታት ብሎ ለምን አዘዘን አሉት።
                    ******     
፰፡ ወይቤሎሙ ሙሴሰ አዘዘክሙ በከመ እከየ ልብክሙ ትድኃሩ አንስቲያክሙ ።
                    ******     
፰፡ ሙሴስ እንደ ልቡናችሁ ክፋት ሚስቶቻችሁን ትፈቱ ዘንድ አዘዛችሁ።
ወእምፍጥረትሰ አኮ ከማሁ ዘተገብረ፡፡
ጥንቱን ግን የታዘዘው እንዲህ አይደለም አላቸው።
(ሐተታ) አንዲት ሴት ለአንድ ወንድ አንድ ወንድ ለአንዲት ሴት ነው እንጂ የሞተችበት የሞተባት በፈቲው ፆር የሚናደዱ ሆኑ፡፡ ሙሴ ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክት የሞተበት ያግባ ብሎታል፡፡ ሲጠላት ጊዜ ወንዱ ልቧን እያሸ የሚገድላት ሆነ ሴቲቱም መርዝ አጠጥታ ሥራይ አብልታ የምትገድለው ሁናለችና እንዲህ አለ።
                    ******     
፱፡ ወአነሂ እብለክሙ ኵሉ ዘይድኅር ብእሲቶ ዘእንበለ ትዘሙ ለሊሁ ረሰያ ዘማ፡፡ ማቴ ፭፥፴፪። ሉቃ ፲፮፥፲፰።
                    ******     
፱፡ እኔም ሳትሰስንበት ደረቀች ሰነፈች ብሎ ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ ዘማ አሰኛት ብዬ እነግራችኋለሁ፡፡
ወእንተ ደኃርዋ ዘአውሰበ ዘመወ።
በነውር የተፈታችዪቱንም ያገባ በደለ።
                    ******     
፲፡ ወይቤልዎ አርዳኢሁ እመ ከመዝ ውእቱ ሥርዓተ ብእሲ ወብእሲት ኢርቱዕ አውስቦ።
                    ******     
፲፡ የባልና የሚስት ሥርዓት እንዲህ ከሆነ ማለት ሰነፈች ደረቀች ብሎ መፍታት የማይገባ ከሆነ ሊያገቡ አይገባም አሉት፡፡
                    ******     
፲፩፡ ወይቤሎሙ አኮ ለኵሉ ዘይትከሃል ዝንቱ።
                    ******     
፲፩፡  ይህ ንጽሕ ጠብቆ መኖር ለሁሉ አይቻልም።
ዘእንበለ ለዘተውህቦ።
ሀብተ ንጽሕ ለተሰጠው ግዕዛኑ ለጸናለት አራቱ ባሕርያት ለተስማሙለት ነው እንጂ።
                    ******     
፲፪፡ እስመ ቦ ሕፅዋን እለ ከማሁ ተወልዱ እምከርሠ እሞሙ።
                    ******     
፲፪፡ ከእናታቸው ማኅፀን ጀምሮ ሕፅዋን ሁነው የተወለዱ አሉና፡፡ እንደ አባ ባይሉል ልጆች ሙፃዓ ስንት ብቻ ነበራቸው።
ወቦ ሕፅዋን እለ ሐፀውዎሙ ሰብእ።
ጋላ ሻንቅላ ሕፅዋን ያደረጋቸው አሉና ለኒያ ነው እንጂ
ወቦ ሕፅዋን እለ ሐፀዉ ርእሶሙ በእንተ መንግሥተ ሰማያት።
ከቤተ መንግሥት እንበላለን እንጠጣለን ብለው ሕፅዋን የሆኑ አሉ ለኒያ ነው እንጂ።
(ሐተታ) ይህስ አይደነቅም አህያን አልተዋጋም በሬን አልተራገጠም ብሎ።
እስመ ቦ ሕፅዋን
ከእናታቸው ማኅፀን ሕፅዋን ሁነው የተወለዱ አሉና ለኒያ ነው እንጂ። እለ ኤርምያስ ቀደስኩከ እምከርሠ እምከ እንዲል።
ወቦ እለ ሐፀውዎሙ ሰብእ።
መምራን መክረው አስተምረው ንጹሐን ያደረጓቸው አሉና ለኒያ ነው እንጂ፡፡ ሙሴ ኢያሱን ኤልያስ ኤልሳዕን
ወቦ እለ ሐፀዉ ርእሶሙ በእንተ መንግሥተ ሰማያት።
ባሕርያቸው ደካማ ነውና አይችሉትም ብሎ ነው እንጂ ከሕገ ሥጋ ሕገ ነፍስ ከሕገ እንስሳ ሕገ መላእክት እንዲበልጥ ታውቆ የለም መንግሥተ ሰማያትን እንወርሳለን ብለው ንጽሕ ጠብቀው ከሴት ርቀው የሚኖሩ አሉና ለኒያ ነው እንጂ፡፡
ወዘሰ ይክል ተዓግሦ ለይትዓገሥ።
መታገሥ የሚቻለው ማለት ንጽሕ ጠብቄ ከሴት ርቄ እኖራለሁ የሚል ግን ንጽሕ ጠብቆ ከሴት ርቆ ይኑር።
                    ******     
በእንተ ሕፃናት እለ መጽኡ ኀበ ኢየሱስ።
፲፫፡ ወእምዝ አምጽኡ ሎቱ ሕፃናተ ከመ ያንብር እዴሁ ላዕሌሆሙ ወይጸሊ።፡ ማር ፲፥፲፫፡፡ ሉቃ ፲፰፥፲፭።
                    ******     
፲፫፡ ከዚያ በኋላ እጁን ይጭንባቸው ዘንድ ማለት በአንብሮተ እድ ይባርካቸው ዘንድ ሕፃናትን ይዘው መጡ። በኤልሳዕ ልማድ፡፡ ሕፃናት መጥተው ዕርግ በራህ ብለው ዘበቱበት ሁለት ድባት አስነሥቶ ፵፪ ሕፃናት አስፈጀ የነቢየ እግዚአብሔር መርገሙ እንዲህ የጐዳ በረከቱ እንደምን ይጠቅም ብለው እያመጡ የሚያስባርኩ ሁነዋልና በዚያ ልማድ አመጡለት።
ወገሠፅዎሙ አርዳኢሁ ለእለ አምጽእዎሙ።
አባቶቻቸው ያመጧቸው ሕፃናትን ተቆጧቸው ይጠቀጥቁናል ብለው፡፡
አንድም ሕፃናትን ያመጧቸው አባቶቻችውን ተቆጧቸው ትምህርት ያስፈቱናል ብለው።
                    ******     
፲፬፡ ወይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ ኅድግዎሙ ለእሉ ሕፃናት ኢትክልእዎሙ ይምጽኡ ኀቤየ፡፡ ማቴ ፲፰፥፫።
፲፬፡ ወደእኔ ይመጡ ዘንድ ሕፃናትን ተዋቸው አትከልክሏቸው አለ፡፡
                        ******     
  ይቆየን፡፡
**********
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
19/09/2011 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment