====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ ዘተግኅሠ ኢየሱስ እምኢየሩሳሌም።
ምዕራፍ ፲፱፡፡
******
፲፬፡ ወይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ ኅድግዎሙ ለእሉ ሕፃናት ኢትክልእዎሙ ይምጽኡ ኀቤየ፡፡ ማቴ ፲፰፥፫።
******
፲፬፡ ወደእኔ ይመጡ ዘንድ ሕፃናትን ተዋቸው አትከልክሏቸው አለ፡፡
እስመ ለዘከመ እሉ ይእቲ መንግሥተ ሰማያት።
መንግሥተ ሰማያት ወንጌል የምትነገር እንደነዚህ ላሉ ነውና፡፡
አንድም መንግሥተ ሰማያት የምትወርስ እንደነዚህ ላሉ ነውና።
******
፲፭፡ ወአንበረ እዴሁ ላዕሌሆሙ ወኃለፈ እምህየ።
******
፲፭፡ እጁን ጭኖ ባርኳዋቸው ከዚያ ኄደ፡፡ እነዚህም ከ፪፻ የሚበዙ ናቸው ከኒህም ከፍጹምነት ያልደረስ ሊቀ ጳጳስነት ጳጳስነት ኤጲስ ቆጶስነት ያልተሾመ የለም፡፡ ከእነዚህም አንዱ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ ነው፡፡
******
በእንተ ወሬዛ ባዕል።
፲፮፡ ወናሁ መጽአ ፩ ብእሲ ወይቤሎ ሊቅ ኄር ምንተ እግበር እምሠናያት ከመ እረስ ሕይወተ ዘለዓለም። ማር ፲፥፲፮፡፡ ሉቃ ፲፰፥፲፰፡፡
******
፲፮፡ አንድ ሰው መጥቶ መምህር የማታልፍ መንግሥተ ሰማያትን እወርስ ዘንድ ከበጎ ነገር ወገን ምን ላድርግ አለው፡፡
******
፲፯፡ ወይቤሎ ምንተ ትብለኒ ኄር
******
፲፯፡ አላመነም ብሎ ሳታምንብኝ ለምን ኄር ትለኛለህ አለው።
አንድም ኄር ብለው ይለኛል ብሎ በተንኮል መጥቷልና የሕሊናውን አውቆበት፡፡ብለው ኄር ይለኛል ብለህ ለምን ኄር ትለኛለህ።
አልቦ ኄር ዘእንበለ ፩ እግዚአብሔር።
ከአንድ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር የለም አለው።
ወእመሰ ትፈቅድ ትባእ ውስተ ሕይወት ዕቀብ ትእዛዛተ።
ወደ ሕይወት ማለት መንግሥተ ሰማያት ትገባ ዘንድ ከወደድህስ ሕግጋትን ጠብቅ። ዘፀ ፳፥፲፫፡ ፲፬፡ ፲፭፡ ፲፮።
******
፲፰፡ ወይቤሎ አይቴኑ ዕቀብ።
******
፲፰፡ ማን ማን ልጠብቅ።
ዘአዓቅቦን
የምጠብቃቸው ማን ማን ናቸው አለው።
ወይቤሎ እግዚእ ኢየሱስ ኢትቅትል ነፍሰ
ጌታም ነፍስ አትግደል።
ኢትዘሙ።
አትሰስን።
ኢትሥርቅ።
አትሥረቅ።
ኢትኩን ስምዓ በሐሰት።
በሐሰት አትመስክር።
******
፲፱፡ አክብር አባከ ወእመከ።
******
፲፱፡ አክብር ማለት አባትህን እናትህን እርዳ።
ወአፍቅር ቢጸከ ከመ ነፍስከ
ባልንጄራህን እንደ ራስህ ውደድ አለው።
******
ወይቤሎ ወሬዛ ዘንተሰ ኵሎ ዓቀብኩ እምንዕስየ
******
፳፡ ይህንስ ሁሉ ከሕፃንነቴ ጀምሬ ጠብቄያለሁ።
ምንት እንከ ተርፈኒ።
ምን ቀረኝ
ዘተርፈኒ
የቀረኝ ምንድነው አለው።
ወነጸሮ እግዚእ ኢየሱስ ወአፍቀሮ።
ጌታ አይቶ ወደደው።
******
፳፩፡ ወይቤሎ አሐቲ ተርፈተከ።
******
፳፩፡ አንዲት ቀርታሃለች አለው።
እመሰ ፈቀድከ ፍጹመ ከመ ትኩን ሑር ወሢጥ ኵሎ ጥሪተከ ወሀብ ለነዳያን።
ፍጹምነትስ ከወደድህ ሂደህ ገንዘብህን ሁሉ ሽጠህ ለነዳያን ስጥ አለው።
ወታጠሪ መዝገበ ዘበሰማያት
በሰማይ መዝገብ ታገኛለህ ማለት መንግሥተ ሰማያትን ትወርሳለህ።
(ሐተታ) እርድና ከምጽዋት ነገረው ሑር ሢጥ ብሎ እርድና፡፡ ሀብ ብሎ ምጽ ዋትን።
አንድም ነዳያን ላም በሬ ፈረስ በቅሎ ቢሰጧቸው ወጥቶ ወርዶ መሸጥ አይሆንላቸውምና። ዳግመኛ የከብቱን ዋጋ የሚያውቅ ባለቤቱ ነውና። እንዳገኙ እንዳይጥሉት።
ወነዓ ትልወኒ።
ለጊዜው በእግር ተከተለኝ ፍጻሜው በግብር ምሰለኝ አለው፡፡
******
፳፪፡ ወሰሚዖ ወሬዛ ዘንተ ነገረ ወሖረ እንዘ ይቴክዝ፡፡
******
፳፪፡ እሱም ይኸን ነገር ሰምቶ እያዘነ ሄደ።
እስመ ብዙኅ ጥሪቱ።
ገንዘቡ ብዙ ነውና። ሢጥ ቢለው ስንቱን ይሸጧል ብሎ፡፡
አንድም እሱን መከተል ሽቶ ነበርና ሑር ቢለው።
አንድም ፍጹምነት ሽቶ ነበርና አሐቲ ተርፈተከ ቢለው።
******
፳፫፡ ወይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ ለአርዳኢሁ አማን እብለክሙ ከመ ባዕል እም ዕፁብ ይበውእ ውስተ መንግሥተ ሰማያት፡፡
******
፳፫፡ ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ ባለጸጋ ጨርሶ መጽውቶ በጭንቅ መንግሥተ ሰማያት ይገባል ብዬ አንዲገባ በእውነት እነግራችኋለሁ አላቸው።
******
፳፬፡ ወካዕበ ዕብለክሙ ይቀልል ይኅልፍ ገመል እንተ ሰቊረተ መርፍዕ እምባዕል ይባዕ ውስተ መንግሥተ እግዚአብሔር፡፡
******
፳፬፡ ዳግመኛ ባለጸጋ መንግሥተ ሰማይ ከሚገባ ገመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል ብዬ እነግራችኋለሁ።
(ሐተታ) ባይጻፍ ነው እንጂ በእሱ ጊዜ ተደርጓል። በእሱ ጊዜስ አልተደረገም ደቀ መዝሙሩ ታዴዎስ ያደረገውን መናገር ነው፡፡ ይህን ሲያስተምር ነጋድያን ገመል ጭነው መጡ በቃል ያስተማርኸንን አድርገህ አሳየን አሉት አንጥረኛ ወዳጅ ነበረውና መርፌ ስደድልኝ አለው፡፡ ነገሩን አስቀድሞ ሰምቷልና ቀዳዳውን አስፍቶ ሰደደለት፡፡ ምን ቢሰፋ ገመል ያሳልፋል ያንተንም ዋጋ እግዚአብሔር አያስቀርብህ እንደጥንቱ አድርገህ ስደድልኝ አለው፡፡ እንደጥንቱ አድርጎ ሰደደለት ሦስት ጊዜ እያመላለሰ አሳይቷቸዋል፡፡
አንድም አይሁዳዊ አምኖ ተጠምቆ መንግሥተ ሰማያት ከሚገባ አረማዊ አምኖ ተጠምቆ መንግሥተ ሰማያት ቢገባ ይቀላል ብዬ በእውነት እነግራችኋለሁ፡፡ አይሁዳዊ አያደርገውም አረማዊ ያደርገዋል ማለት ነው።
******
፳፭፡ ወሰሚዖሙ አርዳኢሁ አንከሩ ጥቀ እንዘ ይብሉ መኑ እንጋ ይክል ድኂነ።
******
፳፭፡ ደቀ መዛሙርቱ ይኸን ሰምተው ገንዘቡን ሁሉ ጨርሶ መጽውቶ መንግሥተ ሰማያት መግባት ለማን ይቻለዋል ብለው ፈጽመው አደነቁ።
አንድም ተአምራት ማድረግ ለማን ይቻለዋል ብለው አደነቁ።
******
ወነጸሮሙ እግዚእ ኢየሱስ ወይቤሎሙ በኀበ ሰብእ ኢይትከሀል ዝ።
******
፳፮፡ ጌታ አይቷቸው ተአምራት ማድረግ በሰው ዘንድ አይቻልም
ወበኀበ እግዚአብሔርሰ ኵሉ ይትከሃል።
በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ይህ ሁሉ ይቻላል።
አንድም እግዚአብሔር ባላደረበት ሰው ዘንድ አይቻልም። እግዚአብሔር ባደረበት ሰው ዘንድ ግን ይቻላል።
አንድም ገንዘቡን ጨርሶ መመጽወት እግዚአብሔር ላላደረበት ሰው አይቻልም እግዚአብሔር ላደረበት ሰው ግን ይቻላል።
******
በእንተ ዘከመ ይደልዎሙ ዕሤት ለእለ ይተልውዎ ለእግዚእ ኢየሱስ።
፳፯፡ ወእምዝ አውሥአ ጴጥሮስ ወይቤሎ ናሁ ንሕነ ኀደግነ ኵሎ ወተሎናከ ምንተ እንከ ንረክብ።
፳፯፡ ጴጥሮስ መለሰ እኛ ሁሉን ትተን ተከትለንሃል ምን እናገኝ ይሆን አለው፡፡
******
ይቆየን፡፡
**********
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
20/09/2011 ዓ.ም
Tuesday, May 28, 2019
ወንጌል ቅዱስ ክፍል 104
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment