Sunday, May 19, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 96

  ====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
ዘከመ ኀሠሠ ትእምርተ እምሰማይ።
ምዕራፍ ፲፮።
                    ******     
፩፡ ወመጽኡ ኀቤሁ ፈሪሳውያን ወሰዱቃውያን እንዘ ያሜክርዎ ወይሴእልዎ ትእምርተ እምሰማይ ያርእዮሙ፡፡ ማር ፰፥፲፮።
                    ******     
፩፡ ከዚህ በኋላ ሰዱቃውያንና ፈሪሳውያን ሲፈትኑት ከሰማይ ምልክት አሳየን ሊሉት መጡ፡፡
(ሐተታ) አንዳለፈ፡፡ ምዕ ፲፪ ቊ ፴፰፡፡
                    ******     
፪፡ ወአውሥአ ወይቤሎሙ እምከመ መስየ ወኮነ ሕዋየ ትብሉ ጽሕወ ብሔር።  ሉቃ ፲፪፥፶፬፡፡
                    ******     
፪፡ የመሸ ድግዝግዝ ታም የሆነ እንደሆነ ብራ ያድራል ትላላችሁ።
እስመ ያቅየሐይሕ በማይ።
ሰማይ አልፎ አልፎ በቀይ ሰብኳልና።
                    ******     
፫፡ ወእምከመ ጽሕወ ትብሉ ዮምሰኬ ይዘንም፡፡
                    ******     
፫፡ የነጋ እንደሆነ ግን ዛሬ ይዘንማል ትላላችሁ፡፡
እስመ  ያቅየሐይሕ ሰማይ ድሙነ።
ደመና ዳር እስከ ዳር ገጥሞ ይፈልቃልና።
ኦ መደልዋን።
እናንት ግብዞች።
                    ******     
፬፡ ገጸ ሰማይኑ ተአምሩ ፈክሮ። ማቴ ፲፪፥፴፱። ዮሐ ፪፥፩።
                    ******     
፬፡ የሰማዩን ፊት ማለት የሰማይን ግብር እናውቃለን ትላላችሁ
ወተአምረ መዋዕልሰ እፎ ኢተአምሩ። .
በዘመናችሁ የተደረገውን ተአምራት አለማወቃችሁ ስለምን ነው።
አንድም እምከመ መስየ ብለህ መልስ። ሥጋ የለበሰ ተስፋ የደረሰ እንደሆነ። ጽሕወ ብሔር። ሥጋ አለበሰም ተስፋ አልደረሰም ትላላችሁ እስመ ያቅየሐይሕ ሰማይ፡፡ የተነገረው ትንቢት የተቈጠረው ሱባዔ ገና ነውና ብላችሁ። ወእምከመ ጽሕወ። ሐሳዊ መሢሕ ግን የተወለደ እንደሆነ ገና ዛሬ ሥጋ ለበሰ ተስፋ ደረሰ ትላላችሁ። በሐሰት ተጨፍኖ አምላክ ነኝ ብሏልና። ኦ መደልዋን። እናንት ግብዞች። ገጸ ሰማይኑ። ሰማያዊ ልደቴን እናውቃለን ትላላችሁ። ወተአምረ መዋዕልሰ። በዘመናችሁ የተደረገውን ምድራዊ ልደቴን አለማወቃችሁ ስለምን ነው።
ወይቤሎሙ ትውልድ ዕሉት ወዘማ ትእምርተ ተኃሥሥ
ዕምቢተኛ ሴሰኛ ቤተ አይሁድ ምልክትን ትሻለች፡፡ ወትእምርትሰ ኢተውህባ ዘእንበለ ትእምርተ ዮናስ ነቢይ
ምልክት ግን ዮናስ ከአደረገው ምልክት በቀር አይሰጣትም፡፡ ም ፲፪ ቊ፴፱ ተመልከት።
ወእምዝ ኃደጎሙ ወሖረ።
ከዚህ በኋላ ትቷቸው ሄደ።
                    ******     
በእንተ ብኁዐ ፈሪሳውያን ወሰዱቃውያን።
፭፡ ወበጺሖሙ አርዳኢሁ ማዕዶተ ረስዑ ነሢአ ኅብስት።
                    ******     
፭፡ ደቀ መዛሙርቱ ወንዙን ተሻግረው ከሄዱ በኋላ እንጀራ ረሱ ማለት አለመያዛቸውን እወቁ፡፡
                    ******     
፮፡ ወይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ ዑቊ ወተዓቀቡ እምብኁፆሙ ለፈሪሳውያን።
                    ******     
፮፡ ጌታ ከፈሪሳውያን እርሾ ተከልከሉ አላቸው።
                    ******     
፯፡ ወይቤሉ በበይናቲሆሙ እስመሁ እንጋ ኅብስተ ኢነሣእነ።
                    ******     
፯፡ እርስ በእርሳቸው አስበው እንጀራ አልያዝንምና ተዓቀቡ ይለናል አሉ።
                    ******      
፰፡ ወአእመሮሙ እግዚእ ኢየሱስ ወይቤሎሙ ምንተ ትሔልዩ በበይናቲክሙ ኦ ሕፁፃነ ሃይማኖት።
                    ******     
፰፡ ጌታም አውቆባቸው እናንት ሃይማኖት የሌላችሁ እናንት በእናንት ለምን ታስባላችሁ አላቸው።
እስመሁ ኅብስት አልብክሙ።
እንጀራ አልያዛችሁምና ተዓቀቡ አልኋችሁን።
                    ******     
፱፡ ዓዲሁ ኢትሌብውኑ ወኢትዜከሩ ዘአመ ኃምስ ኅብስት እለ ለ፶ ምእት፡፡ ማቴ ፲፬፥፲፱። ዮሐ ፮፥፱፡፡
                    ******     
፱፡ አምስት እንጀራ አበርክቼ ለአምስት ሽህ ሰው ባበላሁ ጊዜ የተደረገውን አታስተውሉም አታስቡትምን
ወሚመጠነ መዛርዓ አግኃሥክሙ
ምን ያህል ቅርጫት አነሣችሁ፡፡
ወይቤልዎ ፲ ወ፪ተ።
አሥራሁለት አነሣን አሉት።
አንድም ዘአግኃሥክሙ ያነሣችሁት ምን ያህል ነው አላቸው አሥራ ሁለት ነው አሉት።
                    ******     
፲፡ ወእመሂ ሰብዑ ኅብስተ እለ ለ፵ ምዕት። ማቴ ፲፭፥፴።
                    ******     
፲፡ ሰባቱን እንጀራ አበርክቼ ለአራት ሽህ ሰው ባበላሁ ጊዜ የተደረገውን አታስተውሉም።
ሚመጠነ አስፈሬዳተ አግኃሥክሙ
ምን ያህል እንቅብ አነሣችሁ አላቸው ፯ አነሣን አሉት ዘአግኃሥክሙ ያነሣችሁት ምን ያህል ነው ሰባት ነው አሉት።
                    ******     
፲፩፡ እፎ ዘኢትሌብዉ ከመ አኮ በእንተ ኅብስት ዘእቤለክሙ ተዓቀቡ አምብኁኦሙ ለፈሪሳውያን ወሰዱቃውን።
                    ******     
፲፩፡ እንዲህ ከሆነ ተዓቀቡ ያልኋችሁ በቁሙ ከፈሪሳውያን ከሰዱቃውያን እርሾ እንዳይደለ እንደምን አታውቁ አላቸው።
                    ******     
፲፪፡ ወእምዘ ለበው ከመ አኮ ዘይቤሎሙ ይትዓቀቡ እምነ ብኅዓተ ኅብስት።
                    ******     
፲፪፡ ከዚህ በኋላ ተጠበቁ ያላቸው ስለ እርሾ
አላ እምነ ትምህርተ ፈሪሳውያን ወሰዱቃውያን ።
ከፈሪሳውያን ከሰዱቃውያን ትምርት ነው እንጂ።
                    ******     
በከመ ተአመነ ጴጥሮስ።
፲፫፡ ወበጺሖ እግዚእ ኢየሱስ ብሔረ ቂሳርያ ዘፊልጶስ፡፡ ማር ፰፥፳፮፡፡ ሉቃ ፱፥፲፰።
                    ******     
፲፫፡ ጌታ የፊልጶስ ግዛት ከምትሆን ከቂሳርያ አውራጃ በደረሰ ጊዜ በቄሳር ቂሳርያ ተብላለች በጢባርዮስ ጥብርያዶስ በፊልጶስ ፊልጵስዩስ እንደተባለች። ይህ ፊልጾስ የእስክንድር አባት የሄሮድስ ወንድም ሐዋርያው ፊልጶስ ከሰባቱ ዲያቆናት አንዱ ነው።
ተስእሎሙ ለአርዳኢሁ እንዘ ይብል መነ ይብለኒ ሰብእ ለወልደ እጓለ እመሕያው።
ወልደ እጓለ እመሕያው እኔን ሰው ማን ይለኛል ብሎ ደቀ መዛሙርቱን ጠየቃቸው።
                    ******     
፲፬፡ ወይቤሉ ቦ እለ ይብሉከ ዮሐንስሃ መጥምቀ።
                    ******     
፲፬፡ ዮሐንስ መጥምቅ ነው የሚሉህ ዮሐንስ መጥምቅ እንደሆንክ የሚናገሩልህ አሉ። ንጽሕናውን አይተው።
ወካልዓን ይብሉከ ኤልያስሃ።
ኤልያስ ነው የሚሉህ አሉ ኤልያስ እንደሆንክ የሚናገሩልህ አሉ ድንግልናውን አይተው፡፡
ወመንፈቆሙ ይብሉከ ኤርምያስ።
ኤርምያስ ነህ የሚሉህ አሉ። ኤርምያስ እንደሆንክ የሚናገሩልህ አሉ። ቅድስናውን አይተው፡፡
ወእመ አኮ ፩ዱ እምነቢያት ቀደምት።
ይህም ባይሆን ከቀደሙ ነቢያት ማለት ሙሴን ኢያሱን ነው የሚሉህ አሉ አሉት ተአምራቱን አይተው።
                    ******     
፲፭፡ ወይቤሎሙ አንትሙኬ መነ ትብሉኒ።
፲፭፡ እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ።
                    ******     
   ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
12/09/2011 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment