====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ ምሳሌ ዘዓቀብተ ወይን፡፡
ምዕራፍ ፳።
******
፩፡ እስመ ትመስል መንግሥተ ሰማያት ብእሴ በዓለ ቤት ዘወፅአ ነግሃ ይትዓሰብ ገባዕተ ለዓደፀ ወይኑ።
******
፩፡ መንግሥተ ሰማይ ሕገ ወንጌል ሕገ ወንጌል ተስፋ ተስፋ ኢየሱስ ክርስቶስ ለወይኑ ቦታ ምንደኞችን ሊስማማ ማለዳ የወጣ ባለቤትን ትመስላለችና ቀደምት ወይከውኑ ደኃርተ፤ ደኃርት ይከውኑ ቀደምተ ላለው።
አንድም ትመስላለች እኮን።
******
፪፡ ወተከሃሎሙ በበዲናር ለለዕለት።
******
፪፡ በቀን ድሪም ድረም እሰጣችኋለሁ ብሎ የተስማማቸውን
ወፈነዎሙ ውስተ ዓፀደ ወይኑ ይትቀነዩ።
ወይን ጠብቁ ብሎ ወደ ወይኑ ቦታ የላካቸውን ባለቤት ትመስላለች፡፡
(ሐተታ) ነግህ የተባለ ከተወለዱ ጀምሮ እስከ ሰባት ዓመት ያለው ዘመን ነው፡፡ እስከዚያ ሥርዓት አይሠራባቸውም መምህረ ንስሐ የሚይዙ ጾም የሚጀምሩ ከዚያ በኋላ ነውና።
******
፫፡ ወወፂኦ ጊዜ ፫ ሰዓት ርእየ ካልዓነ እንዘ ይቀውሙ ውስተ ምሥያጥ ፅሩዓነ፡፡
******
፫፡ በሦስት ሰዓት ቢወጣ ሌሎችን ሥራ ፈተው አደባባይ ቁመው አገኘ።
******
፬፡ ወሎሙኒ ይቤሎሙ ሑሩ አንትሙኒ ውስተ ዓፀደ ወይንየ ወተቀነዩ ወዘረትዓኒ እሁበክሙ፡፡
******
፬፡ እሳቸውንም ከወይኔ ቦታ ሂዳችሁ ወይኔን ጠብቁ የቀናኝን እሰጣችኋለሁ አላቸው። በኋላ የመጣን የቀናኝን እሰጥሃለሁ ማለት ልማድ ነው።
ወእሙንቱ ሖሩ።
እሳቸውም ሔዱ።
******
፭፡ ወወፂኦ ጊዜ ስሱ ወተሱዓት ሰዓት ገብረ ከማሁ።
******
፭፡ ዳግመኛም በቀትር በተሠዓት ወጥቶ ሥራ ፈትተው ከአደባባይ ቁመው አገኘ፤ እናንተም ሂዳችሁ ወይኔን ጠብቁ የቀናኝን እሰጣችኋለሁ አላቸው።
******
፮፡ ወጊዜ አሡሩ ወ፩ ሰዓት ወጺኦ ረከበ ከልዓነ እንዘ ይቀውሙ።
******
፮፡ በሠርክ ወጥቶ ሌሎችን ሥራ ፈተው ከአደባባይ ቁመው አገኘ።
ወይቤሎሙ ለምንት ቆምክሙ ዝየ ኵሎ ዕለተ ፅሩዓኒክሙ።
ቀኑን ሁሉ ሥራ ፈታችሁ ለምን ቁማችኋል አላቸው። ከዚያው ገብቶ ከተቆጠረ ብሎ ኵሎ ዕለተ አለ።
አንድም ኵሎ ሰዓተ ሲል ነው። አሥራ ሁለቱን ሰዓተ መዓልት ሥራ ፈታችሁ ለምን ቆማችኋል አላቸው።
******
፯፡ ወይቤልዎ እስመ አልቦ ዘተዓሰበነ።
******
፯፡ የተስማማን የለምና የተስማማን ባይኖር ነው አሉ።
ወይቤሎ ሑሩ አንትሙኒ ውስተ ዓፀደ ወይንየ ተቀነዩ ወዘረትዓኒ እሁበክሙ።
እናንተም ሂዳችሁ ወይኔን ጠብቁ የቀናኝን እሰጣችኋለሁ አላቸው፡፡ ሠለስት የተባለ ከሰባት ዓመት እስከ ሀያ ዓመት ያለው ዘመን ነው። ቀትር ከሃያ እስከ አርባ ያለው ነው። ተሠዓት ከአርባ እስከ ስሳ ያለው ዘመን ነው። ሠርክ ከስሳ እስከ ሰማንያ ያለው ዘመን ነው፡፡ እስከዚያ ድረስ ሃይማኖት ሳይማሩ ምግባር ሳይሠሩ ኑረው ከዚህ በኋላ በመምራን አድሮ አስተምሮ በቃለ መጻሕናት ገሥፆ ምግባር እንዲሠሩ ሃይማኖት እንዲይዙ ማድረግ ነው።
******
፰፡ ወሶበ መስየ ይቤሎ በዓለ ዓፀደ ወይን ለመጋቢሁ ጸውዖሙ ለገባዕት ወሀቦሙ ዓስቦሙ
******
፰፡ ሲመሽ የወይን ባለቤት ሹሙን ጠርቶ ለምንደኞች ዋጋቸውን ስጣቸው አለው።
ወአኃዝ ቅድመ እምቀደምት እስከ ደኃርት።
ከገባዕተ ሠርክ ጀምረህ እስከ ገባዕተ ነግህ ስጥ አለው፤
******
፱፡ ወመጽኡ እለ አሠርቱ ወ፩ ሰዓት።
******
፱፡ ገባዕተ ሠርክ መጡ።
ወነሥኡ በበዲናር።
ድሪም ድሪም ሰጣቸው።
******
፲፡ ወመጽኡ ቀደምት
******
፲፡ ገባዕተ ነግህ መጡ።
ወመሰሎሙ ዘያበዝኅ ሎሙ ውሂበ።
አብዝቶ የሚሰጣቸው መስሏቸው ነበር።
ወወሀቦሙ ሎሙኒ በበዲናር
ለእሳቸውም ድሪም ድሪም ሰጣቸው።
******
፲፩፡ ወነሢኦሙ አንጐርጐሩ ላዕሌሁ ለበዓለ ቤት።
******
፲፩፡ ተቀብለው በባለቤቱ አዘኑበት።
******
፲፪፡ እንዘ ይብሉ እሉ ደኃርት አሐተ ሰዓተ ተቀንዩ ወአስተዓረይኮሙ ምስሌነ ለእለ ፆርነ ክበዳ ወላህባ ለዕለት ።
******
፲፪፡ የዕለት ፃሯን ጋሯን ትኩሳቷን ማለት ጧት ጀምረን እስከ
ማታ ስንደክም ከዋልነ ከኛ ጋራ ገባዕተ ሠርክን አስተካከልሃቸው ብለው አዘኑ።
******
፲፫፡ ወይቤሎ ለ፩ እምኔሆሙ ዓርክየ ኢዓመፅኩከ።
******
፲፫፡ ከገባዕተ ነግህ አንዱን ወዳጀ አልበደልሁህም አለው፡፡
አኮኑ በበዲናር ተከሃልኩከ
በድሪም ተስማምቼህ አልነበረም።
******
፲፬፡ ወንሣእ ዘይረክበከ ወሑር።
******
፲፬፡ የሚገባህን ይዘህ ሂድ አለው።
ወፈቀድኩ ለዝ ደኃራዊ አሀቦ ከማከ።
በኋላ ለመጣው ለዚህ እንዳንተ ልሰጠው ወድጃለሁና።
******
፲፭፡ ወሚመ ኢይደልወኒኑ ዘፈቀድኩ እግበር በንዋይየ።
******
፲፭፡ ወይም በገንዘቤ የወደድሁትን ማድረግ አይገባኝምን።
አው ዓንይንከኑ ሐማሚ ውእቱ
ዓይንህ ምቀኛ ናት ማለት አንተስ ምቀኛ ነህን።
ወአንሰ ኄር።
እኔ ግን ቸር ነኝ ማለት ምቀኛ አይደለሁም።
******
፲፮፡ ከማሁኬ ይከውኑ ደኃርት ቀደምተ ወቀደምት ደኃርተ።
******
፲፮፡ እንደዚህም ሁሉ ገባዕተ ሠርክ ገባዕተ ነግህን ገባዕተ ነግህ ገባዕተ ሠርክን ይሆናሉ።
እስመ ብዙኃን ጽውዓን ወኅዳጣን ኅሩያን።
ጥቂትም ሁነው ብዙም ሁነው የተጠሩ የተመረጡ ናቸውና ከጠገቡ ላለው ቀደምት ይከውኑ ደኃርተ ወደኃርት ይከውኑ ቀደምተ ላለው አርእስት ስጥ።
አንድም ወሶበ መስየ ብለህ መልስ። ምጽአት በደረሰ ጊዜ አምጻኤ ዓለማት ፈጣሬ ዓለማት አብ መጋቢሁ ወልድን አምጻኤ ዓለማት ፈጣሬ ዓለማት ወልድ መጋቢሁ መልአኩን ምዕመናንን ጠርተህ ከኋለኞች ጀምረህ እስከ ፊተኞች ስጥ አለው።
ወመጽኡ እለ አሠርቱ ወ፩ዱሰዓት።
ኋለኞች መጡ
ወነሥኡ በበዲናር።
እንደ ሥራቸው ሰጣቸው
ወመጽኡ ቀደምት
ፊተኞች መጡ
ወመሰሎሙ በቀዲመ አዝማናት በአብዝኆ ገድላት
የሚያበልጥላቸው መስሏቸው ነበር።
ወወሀቦሙ ሎሙኒ
ለሳቸውም እንደ ሥራቸው ሰጣቸው።
ወነሢኦሙ አንጐርጐሩ
ማዘን የለም ነገሩ የሚያሰኝ ስለሆነ ነው እንጂ፡፡ ዋጋቸውን ተቀብለው ፍርዱን አደነቁ።
እሉ ደኃርት አሐተ ሰዓተ ተቀንዩ
ጥቂት ሰዓት መከራ የተቀበሉ እሊህን ብዙ ዘመን መከራ ከተቀበልን ከኛ ጋራ አስተከከላቸው ብለው አደነቁ።
ወይቤሎ ለ፩ እምኔሆሙ አርክየ።
ከደኃርት ጻድቃን አንዱን ወዳጄ አልበደልሁህም አለው። መፍቀሬ ሰብእ ነውና ዓርክየ ይለዋል፡፡
ወፈቀድኩ ለዝ ደኃራዊ አሀቦ ከማከ ወሚመ ኢይደልወኒኑ እግበር ዘፈቀድኩ በንዋይየ።
እንዲህ ማለት ይህን ተናግሮ ዕንጦንስን ከአስካፍ መቃሪን ከክልዔቲ አንስት አዮጳን ከኖላዊ ትሩፍ በብኑዳን ከፈያታይ መዓንዝር መስደዱን መናገር ነው።
አው ዓይንከኑ ሐማሚ እስመ አነ ኄር
እንዲህ ማለት ገባዕተ ሠርክን ከገባዕተ ነግህ ገባዕተ ነግህን ከገባዕተ ሠርክ ማለት ኋለኞችን ከፊተኞች ፊተኞችን ከኋለኞች ያስተካከለበትን ፍርዱን ከሱ በቀር የሚያውቀው አለ መኖሩን መናገር ነው።
ከማሁኬ
አሁን እንደ ተናገርሁ ገባዕተ ሠርክ ገባዕተ ነግህን ገባዕተ ነግህ ገባዕተ ሠርክን ይሆናሉ።
እስመ ብዙኃን
ብዙም ሁነው ጥቂትም ሁነው የተጠሩ የተመረጡ ናቸውና ቀደምት ይከውኑ ደኃርተ ደኃርት ይከውኑ ቀደምተ ላለው ለላይኛው ስጥ። ም ፲፱ ቊ ፴፡፡
(ሐተታ) ነግህ የተባለ ዘመነ አበው ነው ሠለስት ዘመነ መሳፍንት ቀትር ዘመነ ነገሥት ተሠዓት ዘመነ ካህናት ሠርክ ዘመነ ሥጋዌ ነው።
አንድም ነግህ የተባለ ዘመነ አዳም ሠለስት የተባለ ዘመነ አብርሃም ቀትር ዘመነ ሙሴ ተሠዓት ዘመነ ዳዊት ሠርክ ዘመነ ክርስቶስ፤ቀደምት ይከውኑ ደኃርተ፤ ደኃርት ይከውኑ ቀደምተ አለ። በአቤል ጊዜ የነበሩ በዕለተ ዓርብ ያሉትን በዕለተ ዓርብ ያሉት በአቤል ጊዜ የነበሩትን ይሆናሉ።
አንድም በዓፀደ ነፍስ ያሉት በዓፀደ ሥጋ ያሉትን በዓፀደ ሥጋ ያሉት በዓፀደ ነፍስ ያሉትን ይሆናሉ።
አንድም ነግህ ዘመነ ክርስቶስ ሠለስት ዘመነ ሐዋርያት ቀትር ዘመነ ሰማዕታት ተሠዓት ዘመነ ሊቃውንት ሠርክ ዘመነ መነኮሳት ዘመነ ሐዋርያትና ዘመነ ክርስቶስ አንድ ወገን ነው ብሎ። ወሠለስት ዘመነ ሰማዕታት ቀትር ዘመነ ሊቃውንት ተሰዓት ዘመነ መነኮሳት ሠርክ ዘመነ ደኃርት ጸድቃን በዕለተ ዓርብ ያሉት በዕለተ ምጽአት ያሉትን በዕለተ ምጽአት ያሉት በዕለተ ዓርብ ያሉትን ይሆናሉ።
አንድም ንሕነ ሕያዋን የተባሉት ኢንበጽሖሙ ለምውታን የተባሉትን ኢንበጽሖሙ ለምውታን የተባሉት ንሕነ ሕያዋን የተባሉትን ይሆናሉ።
******
ትንቢት ሣልሲት ዘሕማማት።
፲፯፡ ወእንዘ የዓርግ ኢየሩሳሌም ነሥኦሙ ለ፲ ወ፪ቱ አርዳኢሁ እንተ ባሕቲቶሙ። ማር ፲፥፴፪፡፡ ሉቃ ፲፰፥፴፩።
******
፲፯፡ ወደ ኢየሩሳሌም ሲወጣ አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን አስከትሏቸው ሄደ።
ወአግኃሶሙ እምፍኖት።
ከመንገድ ፈቀቅ አደረጋቸው
(ሐተታ) ወቀደሞሙ በፍኖት ይላል በማርቆስ፤ በፊት ያሉት በኋላ ነው በኋላ ያሉት በፊት ነው ሲሉ ቀድሟቸው ተገኝቷል እንዲህ ሲሆን እሞታለሁ ይላል ብለውታል።
******
፲፰፡ ወይቤሎሙ ናሁ ነዓርግ ኢየሩሳሌም።
******
፲፰፡ ኢየሩሳሌም እወጣለሁ።
ወይእኅዝዎ ለወልደ እጓለ እመ ሕያው።
ወልደ እጓለ እመሕያውን ይይዙታል ማለት እያዛለሁ።
ወያገብዕዎ ኀበ ሊቃናት ወጸሐፍት።
ለሊቃናት ለጸሐፍት አሳልፈው ይሰጡኛል።
ወይኴንንዎ በሞት።
ይሙት በቃ ይፈርዱብኛል።
******
፲፱፡ ወይሜጥውዎ ለሕዝብ።
******
፲፱፡ ለሕዝብ አሳልፈው ይሰጡኛል
ወይሳለቁ ላዕሌሁ።
ይዘብቱብኛል፣
ወይቀስፍዎ፣
እገረፋለሁ።
ወይሰቅልዎ ።
እገረፋለሁ።
ወይቀትልዎ።
እሞታለሁ።
ወይትነሣእ በሣልስት ዕለት።
በሦስተኛው ቀን እነሣለሁ አላቸው።
******
በእንተ ደቂቀ ዘብዴዎስ።
፳፡ ወእምዝ መጽአት ኀቤሁ እሞሙ ለደቂቀ ዘብዴዎስ ምስለ ደቂቃ፡፡ ማር ፲፥፴፭።
፳፡ ከዚህ በኋላ የዘብዴዎስ ልጆች እናት ማርያም ባውፍልያ ልጆችዋን አስከትላ መጣች።
******
ይቆየን፡፡
**********
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
22/09/2011 ዓ.ም
Thursday, May 30, 2019
ወንጌል ቅዱስ ክፍል 106
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment