Tuesday, May 14, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 90

====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ ሃለየ ሄሮድስ ላዕለ ኢየሱስ።
ምዕራፍ ፲፬።
                        ******     
፩፡ ወበውእቱ መዋዕል ሰምዓ ሄሮድስ ንጉሥ ነገሮ ለእግዚእ ኢየሱስ፡፡ ማር ፮፥፲፱፡፡ ሉቃ ፱፥፯፡፡
                    ******     
፩፡ በዚያ ወራት ሄሮድስ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ነገር ሰምቶ ማለት ያደረገውን ታምራት የሠራውን ትሩፋት ሰምቶ ድምፀ ነገሩ ይላል አብነት የታምራቱን ዜና ሰምቶ።
                    ******     
፪፡ ወይቤ ዝ ውእቱ ዮሐንስ መጥምቅ ውእቱ ተንሥአ እምውታን።
                    ******     
፪፡ ለብላቴኖቹ ይህ ዮሐንስ መጥምቅ ነው እሱ ከሙታን ተነሥቶ ይሆናል፡፡
ወበእንተዝ ይትገበራ ሎቱ ኃይላት።
በግፍ አስገድዬው ነበርና ስለዚህ ታምራት ይደረግለታል አላቸው።
                    ******     
፫፡ እስመ ውእቱ ሄሮድስ አኃዞ ለዮሐንስ ወሞቅሖ በቤተ ሞቅሕ ማር ፮፥፲፯፡፡ ሉቃ ፫፥፲፱።
                    ******     
፫፡ ሄሮድስ ዮሐንስን ይዞ አኦሥሮ አግዞት ነበርና።
በእንተ ሄሮድያዳ ብእሲተ እኁሁ ፊልጶስ።
በወንድሙ  በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት።
እስመ ኪያሃ አውሰበ።
እሷን ስለአገባ።
                    ******     
፬፡ እስመ ይቤሎ ዮሐንስ ሎቱ ኢይከውከ ታውስብ ብእሲተ እኁከ ፊልጶስ።
                    ******     
፬፡ የወንድምህን የፊልጶስን ሚስት ማግባት አይገባህም ቢለው።
                    ******     
፭፡ ወእንዘ ይፈቅድ ይቅትሎ ይፈርሆሙ ለሕዝብ።
                    ******     
፭፡ ሊገድለው ወዶ ላለ ሕዝቡን ይፈራቸው ነበረ።
እስመ ከመ ነቢይ ይሬእይዎ ለዮሐንስ
ዮሐንስን እንደ አባት ያፍሩታል እንደ መምህር ያከብሩታልና፡፡
                    ******     
፮፡ ወከዊኖ ዕለተ ልደቱ ለሄሮድስ ዘፈነት ሎቱ ወለተ ሄሮድያዳ በማዕከሎሙ።
                    ******     
፮፡ ሄሮድስ የተወለደበትን ቀን በዓል አድርጎ ሳለ ወለተ ሄሮድያዳ መጥታ በመኳንንቱ ፊት ዘፈነችለት።
(ሐተታ) አሕዛብ የተወለዱበትን ቀን ያከብራሉና በዚህ ቀን ተወልደን ከዚህ መዓርግ ደረስን ሲሉ።
አንድም ከጨለማ ወደ ብርሃን ከፀባብ ወደ ሰፊ የወጣንበት ሲሉ።
ወአደመቶ ለሄሮድስ።
ሄሮድስን ደስ አሰኘችው።
                    ******     
፯፡ ወበእንተዝ መሐለ ላቲ ከመ የሀባ ዘሰአለቶ።
                    ******     
፯፡ ስለዚህ የለመነችውን አንዲሰጣት ማለላት።
                    ******     
፰፡ ወይእቲሰ አቅደመት አእምሮ በኀበ እማ።
                    ******     
፰፡ እሷ አስቀድማ ከእናቷ ዘንድ ነገሩን አውቃው መጥታ ነበርና
(ታሪክ) ከዕለታት በአንድ ቀን ከአንች በቀር ሌላ የምወደው እንደ ሌለ አምላከ እስራኤል ያውቀዋል። ነገር ግን ይኸ ነቢይ ይዘልፈናል አላት።. ለዚህማ ምን ቸገረህ በዓል የምታደርግበት ቀን ደርሷል ልጄ መጥታ ትዘፍንልሃለች ቸብቸቦውን አስቆርጠህ ስጣት ከዚህ በኋላ የወደድነውን እናደርጋለን አለችው ከዚህ በኋላ ስትሄድ ምን ላድርግልሽ ያለሽ እንደ ሆነ ሌላ ነገር አትለምኝ ቸብቸቦውን ቈርጠህ ስጠኝ በዪው ብላ መክራ ሰዳታለች። ሂዳ ዘፈነችለት በማርቆስ እስከ መንፈቀ መንግሥቱ ይላል የመንግሥቴንም እኵሌታ ቢሆን እሰጥሻለሁ አላት ሂዳ ነገረቻት ይልቅስ የነገርሁሽን አድርጊ መንግሥቱንማ መላውን ማን ነሥቶናል አለቻት ሂዳ።
ወትቤሎ ሀበኒ ይእዜ ርእሶ ለዮሐንስ መጥምቅ በፃሕል።
የዮሐንስን ራሱን አስቈርጠህ በፃሕል ስጠኝ አለችው።
                    ******     
፱፡ ወተከዘ ንጉሥ በእንተ መሐላሁ።
                    ******     
፱፡ ስለመሐላው ማለት ከድታ አማለችኝ ብሎ አዘነ።
ወበእንተ እለ ይረፍቁ ምስሌሁ
ከሱም ጋራ ስለተቀመጡት መሐላ አፍራሽ ይሉኛል ብሎ።
አንድም ወበእንተ እለ ይረፍቁ ነቢየ እግዚአብሔር አስገደለ ይሉኛል ብሎ።
ወአዘዘ የሀብዋ።
ቈርጣችሁ ስጧት ብሎ አዘዘ
                    ******     
፲፡ ወፈኒዎ መስተራትዓተ ሐራ።
                    ******     
፲፡ ጭፍራውን የሚሠሩ የሚቀጡ ባለወጎችን ላከ ቤተ አንሣ ቤተ አይጽ ሰቃይ ቈራጭ እንዳለ።
ወመተሩ ርእሶ ለዮሐንስ በቤተ ሞቅሕ፡፡
በግዞት ቤት ሳለ የዮሐንስን ራስ ቈረጡ።
                    ******     
፲፩፡ ወአምጽኡ ርእሶ በፃሕል ወወሀብዋ ለይእቲ ወለት።
                    ******     
፲፩፡ በፃሕል አምጥተው ለብላቴናዪቱ ሰጧት።
(ሐተታ) ለጊዜው እስራኤል ደም ይጸየፋሉ ፍጻሜው ግን የከበረ የዮሐንስ ራስ በዚች በርኵስት እጅ እንዳትያዝ ነው።
ወይእቲ ወሀበት ለእማ።
እሷም ወስዳ ለእናቷ ሰጠች ግዳይ ጣለች።
(ሐተታ) ትሰፋም ትፈትልም ነበር ቢሉ ንጉሥ ንግሥት ስትዘልፍ አታፍር የነበረች አንደበት ታተመች ብላ በያዘችው ግልጽልጽ አደረገችው ወተሰፍሐት ይእቲ ርእስ ወሠጠቀት ዓረፍተ ቤት እንዲል። ሁለት ክንፍ አውጥታ ግንቡን ሠንጥቃ ወጥታ ጌታ በደብረ ዘይት ሲያስተምር ሂዳ ሰገደችለት። ባለሽበት ተወስነሽ አስተምሪ አላት አስራ አምስት ዓመት አስተምራ በብሔረ ዓረቢያ አርፋለች፡፡ ነጋድያን ሲያልፉ እንደ ዕንቊ ስታበራ አይተው የመምህራችሁ ራስ ከዚያ ወድቃለች ብለው ለደቀ መዛሙርቱ ነገራቸው ወስደው ቀብረዋታል።
እሷስ እንደምን ሁናለች ቢሉ እናትና ልጁ ዘፈን እናደርሳለን ብለው ሲሄዱ እናቲቱን ምድር ተከፍቶ ዋጣት ልጂቱ እናቴን ብላ እጅዋን ይዛ ቀርታለች። ከዚህ በኋላ ሄሮድስን ኢይደልወከ ታውስብ ብእሲተ እኁክ ፊልጲስ አለችው ቀድሞ ያልሆነ ሥራ ታሠራ በኋላ ምሥጢር ታወጣ ንሳ በሰይፍ በላት ብሎ በሰይፍ አስመትቷታል። ገድሉ አንበሪ ዋጣት ይላልሳ ቢሉ ሁሉም ተደርጎባታል የሚሰይፍበት ቦታ ከባሕር አጠገብ ነው በሰይፍ መታት ደም ተኩሱዋት ወርዳ ከባሕር ወደቀች አንበሪ ተቀብሎ ዋጣት።
አንድም ገና ሳይቀጣት የታዘዘ አንበሪ ያዛት የንጉሥ ትእዛዝ አይቀርምና በሰይፍ መትቷት ሩጧል ተቀብሎ ውጧታል።
አንድም እናትና ልጁ ሂደው ሄሮድስን ኢይደልወከ ታውስብ ብእሲተ እኁከ ፊልጶስ አሉት ቀድሞ ያልሆነ ሥራ ያሠሩ ኋላ ምሥጢር ያወጡ ብሎ እስከ አንገታቸው አስቀብሮ ወገን አስነድቶባቸዋል።
አንድም እናትና ልጁ ዘፈን እናድሳለን ብለው ሲሄዱ እናቲቱን ምድር ተከፍቶ ዋጣት አንድ ሰው እጅዋን ይዞ ቀረ ልጂቱ ሂዳ ሄሮድስን ኢይደልወከ ታውስብ ብእሲተ እኁከ ፊልጶስ አለችው ቀድሞ ያልሆነ ሥራ ታሠራ ኋላ ምሥጢር ታወጣ ንሳ በሰይፍ በላት ብሎ በሰይፍ አስመትቷታል። ያ ሰው እናቷም እንጂ እንዲህ ሁና ሞተች አለ በምን አውቀህ አሉት እጅዋን አሳይቷል።
እሱስ እንደምን ሁኑዋል ቢሉ አርጣ የሚባል አማች አለው ዘማትን እየሰበሰበ ልጄን ያስቀናታል ሆነ ብሎ አገር መታ ቄሣር ይህን ሰምቶ ያስደፈረኝ እሱ እንጂ ነው ብሎ አስጠርቶ ወስዶ አጋዘው ከዚያ አእምሮውን አጥቶ የገዛ አካሉን እየነጨ እየበላ ሸቶ ተልቶ አብጦ ፈንድቶ ኳ ብሎ ደርቆ ተበላሽቶ ሙቷል። ወመዊቶ ጻድቅ ይኴንን ረሢዓነ ያ ለው ሊደርስ ሊፈጸም ።
                    ******     
፲፪፡ ወመጽኡ አርዳኢሁ ወነሥኡ በድኖ ወቀበርዎ።
                    ******     
፲፪፡ ደቀ መዛሙርቱ በድኑን ወስደው ቀበሩት ልቡ ለጸድቅ ውኩል ከመ አንበሳ እንዲል እሱን ያገኘ ያገኘናል ሳይሉ
መጺኦሙ ዜነውዎ ለእግዚእ ኢየሱስ።
መጥተው የዮሐንስን ሞት ለጌታ ነገሩት።
                    ******     
በእንተ ቀዳሚት አብዝኆተ ኅብስት።
፲፫፡ ወሰሚዖ እግዚእ ኢየሱስ ተግኅሠ እምኅየ በሐመር ውስተ ገዳም አንተ ባሕቲቱ። ማር ፮፥፴፩። ሉቃ ፱፥፲፡፡ ዮሐ ፮፥፩።
                    ******     
፲፫፡ ጌታም የዮሐንስን ሞት ሰምቶ በባሕር በመርከብ ተጭኖ ወደ ገዳም ሄደ።
(ሐተታ) አርድዕተ ዮሐንስ ኀዘንተኞች ናቸውና ለማሳረፍ።
አንድም ሰብአ ሁለቱ አርድዕት መጥተው አጋንንት ገረሩ ለነ ብለውታል ነገሩ እንደምን ነው ለማለት።
ወሰሚዖሙ ሕዝብ ተለውዎ በእግር እምበሐውርት
ሕዝቡ መሄዱን ሰምተው ከሃገሩ ተወጣጥተው የብሱን በእግር ተከተሉት።
                    ******     
፲፬፡ ወወፂኦ ርእየ ብዙኃነ አሕዛበ
                    ******     
፲፬፡ በወጣም ጊዜ ብዙ ሰው አየ
ወምህሮሙ።
አዘነላቸው
ወአሕየወ ድውያኒሆሙ።
ድውያኑን አዳነ
                    ******     
፲፭፡ ወምሴተ ከዊኖ ቀርቡ ኀቤሁ አርዳኢሁ ወይቤልዎ ገዳም ውእቱ ብሔር።
፲፭፡ ሲመሽ በመሸ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ቀርበው አገሩ ምድረ በዳ ነው።
                    ******     
   ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
06/09/2011 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment