Friday, May 17, 2019

ወንጌል ቅዱስ ክፍል 93

====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ ፈሪሳውያን ወሥርዓቶሙ።
ምዕራፍ ፲፭።
                        ******     
፩፡ ወእምዝ መጽኡ እምኢየሩሳሌም ጸሐፍት ወፈሪሳውያን ኀበ እግዚአ ኢየሱስ፡፡ ማር ፯፥፩፡፡
                    ******     
፩፡ ዝ ሲናገረው የመጣ ነው። ከዚህ በኋላ ጸሐፍት ፈሪሳውያን ከኢየሩሳሌም ወደ ጌታ መጡ።
                    ******     
፪፡ እንዘ ይብሉ ለምንት ይትዓደዉ አርዳኢከ ሥርዓተ ረበናት ወትእዛዞሙ ለሊቃነ ካህናት
                    ******     
፪፡ ደቀ መዛሙርትህ የረበናትን ሥርዓት የሊቃነ ካህናትን ትእዛዝ ለምን ይተላለፋሉ አሉት።
እስመ ኢይትሐፀቡ እደዊሆሙ ሶበ ኅብስተ ይበልዑ።
እንጀራ በሚበሉበት ጊዜ እጃቸውን አይታጠቡም ነበርና ይላል ጸሐፊው። ለእመ በሕቁ ኢተሐጽቡ ይላል በማርቆስ፡፡ እነሱ መላልሰው ደም እስኪሰርበው እስኪመለጥ ካልታጠቡ አይበሉም ነበር።
                    ******     
፫፡ ወአውሥአ ወይቤሎሙ ለምንት አንትሙኒ ትትዓደዉ ትእዛዘ እግዚአብሐር በእንተ ሥርዓትክሙ።
                    ******     
፫፡ እናንተስ የእናንተን ሥርዓት ለማጽናት የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ለምን ታፈርሳላችሁ አላቸው።
                    ******     
፬፡ ወእግዚአብሔር ይቤ አክብር አባከ ወእመከ። ዘፀ ፳፥፲፪፡፡ ዘዳ ፭፥፣፲፮። ኤፌ ፮፥፪። ዘፀ ፳፩፥፲፯፡፡ ዘሌ ፳፥፱። ምሳ ፳፥፳።
                    ******     
፬፡ እግዚአብሔርስ እናት አባትህን አክብር ማለት እርዳ ብሏል።
ወዘአሕሠመ ቃለ ላዕለ አቡሁ ወእሙ ሞተ ለይሙት።
በአባቱና በእናቱ ክፉ ነገር የሚናገር ማለት አባት እናቱን አልረዳም ያለ ሰው ፈጽሞ ይሙት ብሏል።
                    ******     
፭፡ ወአንትሙሰ ትብልዎ ዘይቤሎ ለአቡሁ ወለእሙ ሀብተ ርባን ዘረባኅከ እምኔየ።
                    ******     
፭፡ እናንተ ግን ከእኔ ይልቅ ይረባኛል ይጠቅመኛል ያልከው ይርዳህ ያጽባሕ።
አንድም ዘረበሐከ ዘበቊዓከ ይላል። እኔን ከመውለድህ የተነሣ የበላኸው መሥዋዕት የረባህ የጠቀመህ ነው በለው ትሉታላችሁ።
(ሐተታ) አዕሩገ እስራኤል የወለዱት የሚበሉት ያልወለዱት የሚበሉት መሥዋዕት አለና፡፡
አንድም ዘረባሕኩከ ዘበቋዕኩከ ይላል። እኔን ለቤተ እግዚአብሔር ከመስጠትህ የተነሣ እሰጥሃለሁ ያልኩህ ገንዘብ የቤተ እግዚአብሔር ነው በለው ብላችሁ ለአባትና ለእናቱ የሚመልሰውን ምላሽ ትነግሩታላችሁ። ጌታ ሙሴን የግብፃውያንን በኵር አጥፍቼ አውጥቻችኋለሁና በኵር ለኔ ይገባል በኵሩን ለይልኝ አለው ቢያስቈጥር ሁለት እልፍ ከሁለት ሽህ ሁለት መቶ ሰባ ሶስት ሆኑ። ሌዋውያንን ቊጠራቸው አለው፣ ሁለት እልፍ ከሁለት ሽህ ሆኑ፤ በሁለት እልፍ ከሁለት ሽህ በኵር እኒህን ተቀብያለሁ የሁለት መቶ ሰባ ሦስቱን ዋጋ አምስት አምስት ቀመት እየተቀበልህ ከቤተ እግዚአብሔር አግባ ገንዘብ ያለው ገንዘብ እየሰጠ ልጁን ይውሰድ ገንዘብ የሌለው ልጁን ይስጥ ብሎታል ገንዘብ ያለው እየሰጠ ልጁን አስቀርቷል ገንዘብ የሌለው ልጁን ሰጥቷል፤ የመቶው አምስት መቶ። የመቶው አምስት መቶ። የስሳው ሦስት መቶ። የዐሥሩ አምሳ። የሦስቱ አስራ አምስት። ሽህ ከሦስት መቶ ስሳ አምስት ይሆናል። ከዚህ በኋላ አባት እየደከመ ገንዘብ እያለቀበት ልጅ ገንዘብ እያገኘ ይሄዳል ምንስ ለቤተ እግዚአብሔር ብሰጠው ልጄ አይደለምን እርዳኝ ልበለው ብሎ ይሄዳል እንዲህ ብለህ መልስለት ብለው ተንኮል ያስተምሩታልና።
                    ******     
፮፡ ዝ ብሂል ኢያክብር አባሁ ወእሞ
                    ******     
፮፡ እንዲሀ ማለት እናት አባቱን አይርዳ ማለት ነው።
ወሠዓርክሙ ቃሎ ለእግዚአብሔር በእንተ ሥርዓትክሙ።
የእናንተን ሥርዓት ለማጽናት
የእግዚአብሔርን ትእዛዝ አፈረሳችሁ።
                    ******     
፯፡ ኦ መደልዋን ሠናየ ተነበየ ኢሳይያስ ላዕሌክሙ።
                    ******     
፯፡ እናንት ግብዞች እሙነ ሲል ነው ኢሳይያስ በእናንተ እውነት ነገርን ተናግሮባችኋል።
                    ******     
፰፡ እንዘ ይብል ዝ ሕዝብ በከናፍሪሆሙ ያከብሩኒ። ኢሳ ፳፱፥፲፫፡፡ ማር ፯፥፮።
                    ******     
፰፡  እኒህ ሕዝብ በአፋቸው እናከብርሃለን ይሉኛል ማለት እናምንብሃለን ይሉኛል።
ወበልቦሙሰ ነዋኃ ይርኅቁ እምኔየ።
በልቡናቸው ግን አስረዝመው ይርቃሉ ማለት ዕሩቅ ብእሲ ይሉኛል።
                    ******     
፱፡ ወከንቶ ያመልኩኒ።
                    ******     
፱፡ በሐሰት ያመልኩኛል።
እንዘ ይሜህሩ ትምህርተ ሥርዓታተ ሰብእ።
የሰውን ሥርዓት እያስተማሩ ማለት ሰው ሠራሽ ትምህርት እያስተማሩ።
                    ******     
፲፡ ወፀውዖሙ ለሕዝብ ወይቤሎሙ ስምዑ ወለብዉ ከመ አኮ ዘይበውዕ ውስተ አፍ ዘያረኩሶ ለሰብእ። ማር ፯፥፲፬።
                    ******     
፲፡ ሕዝቡን ጠርቶ ሰውን የሚጐዳው በአፍ የሚገባው እንዳይደለ ስሙ ዕወቁ አላቸው።
                    ******     
፲፩፡አላ ዘይወፅእ እምውስተ አፍ ውእቱ ያረኩሶ ለሰብእ።
                    ******     
፲፩፡ ከአፍ የሚወጣው እሱ ይጐዳዋል እንጂ።
                    ******     

፲፪፡ ወእምዝ ቀሪቦሙ አርዳኢሁ ይቤልዎ ኢተአምርሁ ከመ ፈሪሳውያን ሰሚዖሙ ቃለከ አንጐርጐሩ።
                    ******     
፲፪ ከዚህ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ቀርበው ፈሪሳውያን ትምሕርትህን ሰምተው እንዳዘኑ አታውቅምን አሉት እንደዚህማ ከሆነ ጅብም ቀበሮም ቢበሉ አይጐዳማ ብለው ነው ሐዋርያት በነገሩ እያሉበት ፈሪሳውያንን ጥግ አድርገው ይጠይቁታል።
                    ******     
፲፫፡ ወአውሥአ ወይቤሎሙ ኵላ ተክል እንተ ኢተከላ አቡየ ሰማያዊ ትሴረው፡፡ ዮሐ ፲፭፥፪።
                    ******     
፲፫፡ ሰማያዊ አባቱ ያልሠራት ሥራ ሁሉ ታልፋለች ትሰሮ ትለፍ እላቸው።
                    ******     
፲፬፡ ኅድግዎሙ እስመ እውራን እሙንቱ አምርህተ ዕውራን።
                    ******     
፲፬፡ አምርህት አምህርት ይላል። የዕውራነ አእምሮ መሮች መምህሮች ናቸውና ተዋቸው አለ፡፡ ዕውር ዕውረ ለእመ መርሀ ፪ሆሙ ይወድቁ ውስተ ግብ፡፡ ዕውር ዕውሩን ቢመራው ሁለቱም ከጐድጓድ ይወድቃሉ ዕውር ዕውርን ቢከተል ተያይዘው ገደል እንዲሉ።
                    ******     
፲፭፡ ወአውሥአ ጴጥሮስ ወይቤሎ ንግረነ ዘንተ ምሳሌ ማር ፯፥፲፯።
                    ******     
፲፭፡ ጴጥሮስ መለሰ ይህን ነገር ተርጉመህ ገልጸህ ንገረን አለው፡፡ ሄኖክ ወመጽኡ ዲቤየ ሠለስቱ ምሳሌያት ካለው አንዱን ነገር እንዳለው።
                    ******     
፲፮፡ ወይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ ዓዲሁ አንትሙኒ ኢለበውክሙኑ ዘንተ።
                    ******     
፲፮፡ ጌታም እናንተም ገና ይህን አላወቃችሁትም አላቸው።
                    ******     
፲፯፡ ኢተአምሩኑ ከመ ኵሉ ዘይበውዕ ውስተ አፍ ውስተ ከርሥ ይትገመር፡፡
፲፯፡ በአፍ የሚገባው ሁሉ በሆድ እንዲወሰን አታውቁምን።
                    ******     
   ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
09/09/2011 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment