====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በእንተ ሰዊት።
ምዕራፍ ፲፪።
******
፵፪፡ ንግሥተ ዓዜብ ትትነሣእ አመ ዕለተ ደይን ምስለ ዛ ትውልድ፡፡ ፩፡ነገ ፲፩፥፪፡፡ ሕፁ ፱፥፩፡፡
******
፵፪፡ በቤተ አይሁድ ትነሣባታለች
ወትትፋታሕ።
ትከራከራታለች።
ወታስተሐፍራ።
ምላሽ ታሳጣታለች ።
እስመ መጽአት እምአጽናፈ ምድር ትስማዕ ጥበቢሁ ለሰሎሞን።
የሰሎሞንን ጥበብ ልትሰማ ከጽንፈ ምድር መጥታለችና፡፡
ወንጌላዊ በወዲያ ሁኖ ይጽፋልና የኛን አገር ጽንፈ ምድር አለው።
ወናሁ ዘየዓቢ እምሰሎሞን ሀሎ ዝየ።
ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ ማለት ቤተ አይሁድ ግን እግዚአ ሰሎሞን ክርስቶስ ቢያስተምራቸው አናምንም ብለዋልና፡፡
(ታሪክ) የሰሎሞንን ጥበብ እያመጣ የሚነግራት ታምሪን የሚባል ነጋዴ ወዳጅ ነበራት ሄጄ ልረዳው ብላ መቶ ሀያ መክሊት ወርቅ ተንከራ ዘኢትዮጵያ ይለዋል ሉል በወዲያ የማይገኝ በኛ አገር የሚገኝ ዝባድ ገጸ በረከት ይዛ ሄደች ስትሄድም እያዘራች ሄዳለች ስትመለስ ስንቅ ሊሆናት አገር እንዳትዘርፍ ከእግሯ እንደ ምዳቋ ቀንድም እንደ አህያ ሰኰናም ቢሉ ነበረባት ከአደባባይ ስትደርስ ብላቴና አይቶ ገብቶ ንጉሥ በዘመንህ የማይመጣ የለም እንዲህ ያለች ሴት መጥታለች አለው ግቢ በላት አለው ስትገባ ከደጁ ወድቆ የሚኖር ግንድ ነበር ብትራመደው ወልቆ ወደቀላት እሱዋን አይቶ በዓይነ መዓት አየው። ንጉሥ ሳላይ አልነገርሁህም ጠይቀህ ቅጣኝ አለው ቢጠይቃት እውነቱ ነው ነበረብኝ ነገር ግን ከደጅህ የወደቀ ገባሬ ታምራት ዕፅ አለ እሱ ፈወሰኝ እንጂ አለችው እሷ አንድ ብር እሱ አንድ ብር ሽበውበታል ከሱ በኋላ ሐያ ስምንት ነገሥታት ነግሠዋል ሐያ ስምንት ብር ይሽቡበታል ወርቁን ለይሁዳ ሰጥተው በእንጨቱ ጌታን ሰቅለውታል። ሐረገ ወይን ዘእምኃሢሦን ይትገዘም ወበጎልጎታ ይተከል ኮነ መድኃኒትየ እንዲል። ብዙ እንቆቅልሽ ጠይቀዋለች ወአልቦ ዘኢፈክረ ላቲ ወዘተሰወረ እምኔሁ ተሰውሮት የቀረ ያልተረጐመላት የለም። እሱም ከዚያ ድረስ መጥታ ሥርዓተ መንግሥት እናሳያት እንጂ ብሎ እሱዋ ሁሉን ከምታይበት እሱዋ ከማትታይበት ቦታ አኑሮ ሥርዓተ መንግሥት አሳያት። ከዚህ በኋላ በጄ በዪኝ አላት የሀገራችን መንግሥት በድንግልና ነው አይሆንም አለችው እንኪያስ አንችም የኔን ገንዘብ አልነካም ብለሽ ማዪ አላት ማለች። የሚያስጠማ ምግብ ሰጥቶ የምትጠጣውን ነሣት፤ ሰሎሞን ሲተኛ እንደ አንበሳ ዓይኑን ያፈጣል ሲነቃ ይጨፍናል ተኝቶ ሳለ ያየኛል ብላ ዝም ብላለች ነቅቶ ሳለ አሁንስ አያየኝም ተኝቷል ብላ በጥበብ ያገባው ውሃ አለ ቀድታ ልትጠጣ መንቀል ይዛ ቀረበች እጇን ያዛት አንች ከኔ ገንዘብ ላትነኪ እኔም ያንቺን ገንዘብ ላልነካ መሐላ አልነበረንም አላት ይህማ ውሀ አይደለም አለችው ከውሀ የበለጠ አለ አላት ያሁኑን ተወኝ ፈቃድህን ትፈጽማለህ አለችው ተገናኙ ምኒልክ ተፀነሰ ወጥታ ስትሄድ ዓምደ ብርሃን ተከትሏት ሲሄድ አይቶ መንግሥት ወደ ኢትዮጵያ ሄደች ብሎ ትንቢት ተናግሯል። ይህ ሁሉ ምሳሌ ነው ንግሥተ ዓዜብ የዚህ ዓለም ሰሎሞን የጌታ ፻፳ መክሊተ ወርቅ የመቶ ሃያ ቤተ ሰብ መቶ ሃያ መክሊተ ወርቅ የተገኘ ከእሱዋ ነው መቶ ሃያ ቤተ ሰብ የተገኙ ከዚህ ዓለም ነውና። ዕንቊ የሃይማኖት ዝባድ የተዋልጦተ ገድል ምሳሌ፡፡
በእንተ መናፍስት ርኩሳን፡፡
፵፫፡ ወእምከመ ወጽአ መንፈስ ርኩስ እምሰብእ የዓውድ በድወ ግበ አልቦ ማይ። ሉቃ ፲፩፥፳፬።
******
፵፫፡ መንፈስ ርኩስ ሰይጣን በፀበል በጸሎት ከሰው ከተለየ በኋላ ውሃ ወደሌለበት ወደ የብስ ይሄዳል፡፡ እሱስ ውሀ ወዳለበት ይሄዳል ገላቸውን ሲታጠቡ ልብሳቸውን ሲያጥቡ አድርባቸዋለሁ ብሎ መንፈስ ቅዱስ ወደ የብስ የሚወስደው ስለሆነ እንዲህ አለ እንጂ፡፡
አንድም ወደ ኢጥሙቃን ይሄዳል እሱስ የሚሄድ ወደ ጥሙቃን ነው መንፈስ ቅዱስ ግን ወደ ኢጥሙቃን የሚወስደው ስለ ሆነ እንዲህ አለ እንጂ።
እንዘ የኃሥሥ ዕረፍተ።
ዕረፍትን ማለት ማደሪያ ሲሻ
ወየኃጥእ
አያገኝም ሁሉ ገንዘቡ ሁኖ።
******
፵፬፡ ወእምዝ ይብል እገብእ እንከሰ ውስተ ቤትየ እምኀበ ወፃእኩ እምኔሁ
******
፵፬፡ ከዚህ በኋላ እስኪ ቀድሞ ወደነበርሁበት ወደ ቀደመ ቦታዬ ልመለስ ብሎ ያስባል፡፡ እንደ ባለ ርስት በአጠገብ በአጠገብ ሁኖ መጐብኘቱን አይተውምና፡፡
ወመፂኦ ይረክቦ ዕሩቀ ወኵስቱረ ወምሩገ።
በመጣም ጊዜ ባዶውን ያገኘዋል ማለት ጸሎቱን ጸበሉን ትቶ ያገኘዋል።
******
፵፭፡ ወእምዝ የሐውር ወያመጽእ ምስሌሁ ካልዓነ ሰብዓተ መናፍስተ እለ የዓክዩ እምኔሁ። ፪፡ጴጥ ፪፥፳።
******
፵፭፡ ከዚሀ በኋላ እሰይ ብሎ ሂዶ በክፋት ከሱ የሚጸኑ ሰባት አጋንንት ይዞ ይመጣል።
ወበዊኦሙ የኃድሩ ውስቴቱ።
መጥተው ያድሩበታል።
ወይከውን ደኃሪቱ ለውእቱ ብእሲ ዘየዓኪ እምቀዳሚቱ።
የዚያ ሰው ከቀደመ ሥራው የኋላ ሥራው የከፋ ይሆናል።
ሁሉም እየራሳቸው ሥራ ያሠሩታልና ።
ከማሁ ይከውና ለዛቲ ትውልድ
በቤተ አይሁድም አንዲህ ይደረግባታል።
አንድም ወእምከመ ወጽአ።
እስራኤል በግብፅ ሳሉ አምልኮተ እግዚአብሔርን ይዘው ቢገኙ ተለይቷቸው ከሄደ በኋላ።
የዓውድ በድወ
ሃይማኖት ምግባር ወደሌላቸው ወደ አሕዛብ ይሄዳል
እንዘ የኃሥሥ
ማደሪያ ሲሻ።
ወየኃጥእ።
አያገኝም ሁሉ ገንዘቡ ሁኖ ሳለ ያጣል።
ወእምዝ ይብል
ከዚህ በኋላ እስኪ ከቀድሞው ቦታዬ ልመለስ ብሎ ያስባል።
ወመፂኦ።
እስኪ ቀድሞ ወደነበርሁበት ልመለስ ብሎ በተመለሰ ጊዜ።
ብፁዕ ዘይበልዕ እምፍርፋረ ማዕዱ ለፈርዖን ወዘይሰቲ እማየ አይጋቲሃነ ለግብፅ ሲሉ አንደ ተገኙ። ቤተ አይሁድም በመንፈሰ እግዚአብሔር ያወፅኦሙ ለአጋንንት ሲሉ ቢገኙ ተለይቷቸው ሄደ ማደሪያ ሲሻ ሁሉ ገንዘቡ ሁኖ ያጣል። እስኪ ወደ ቀደመ ቦታዬ ልመለስ ብሎ በተመለሰ ጊዜ በብዔል ዜቡል ያወፅዖሙ ለአጋንንት ሲሉ መገኘታቸውን መናገር ነው። ወእምዝ ያመጽእ ፯ተ ካልዓነ እስራኤል ብፁዕ ዘይበልዕ እምፍርፋረ ማዕዱ ሲሉ ቢገኙ እሰይ ብሎ በክፋት ከሱ የጸኑ ሰባት አጋንንት ይዞ መጥቶ ባደረባቸው ጊዜ አሮን አሮን ግበር ለነ አማልክተ ዘየሐውሩ ቅድሜነ ወዘይጸብኡ ጸረነ እስመ ዝኩ ሙሴ ዘአውፅአነ እምድረ ግብፅ ኢነአምር ከመ ምንተ ኮነ ብለው በኮሬብ ስብኮ ላህም እንዳቆሙ። ቤተ አይሁድም በብዔል ዜቡል ያወፅኦሙ ለአጋንንት ሲሉ ቢገኙ በክፋት ከሱ የሚጸኑ ሰባት አጋንንት ይዞ መጥቶ አደረባቸው ባደረባቸውም ጊዜ ስቅሎ ማለታቸውን መናገር ነው።
ከማሁ ይከውና
በቤተ አይሁድ አሁን እንደተናገርሁት ይደረግባታል።
አንድም ወእምከመ ወፅአ መንፈስ ርኩስ። መንፈስ ርኩስ ሰይጣን በአንብዕ በትሕርምት ከሰው ከተለየ በኋላ፤ የዓውድ በድወ ኀበ አልቦ ማይ ዕንቡ አልቆ ደም። ደሙ አልቆ እዥ እዡ አልቆ ይቡስ ከሆነው ባሕታዊ ይደርሳል ለትሕርምቱ ከነቅጠሉ ከተወው ባሕታዊ ይደርሳል።
እንዘ የኃሥሥ ማደሪያ ሲሻ።
ወየኃጥእ አያገኝም አሁን የተመቸ እንደ እሳት ያቃጥላልና። ወእምዝ ይብል ከዚህ በኋላ ወደ ቀደመ ቦታዬ ልመለስ ብሎ ያስባል። ወመጺኦ ይረክቦ ዕሩቀ በተመለሰም ጊዜ ዕሩቀ ከትሩፋት ባዶ ሆኖ ወኩስቱረ ወደ ኃጢአት ተጨልጦ ሂዶ ወምሩገ በኃጠጢአት ተለስኖ ያገኘዋል ወእምዝ ይብል ከዚህ በኋላ ዕሰይ ብሎ ሂዶ በክፋት ከሱ የጸኑ ፯ አጋንንት ይዞ መጥቶ ያድርበታል። ወየዓኪ ደኃሪቱ። የዚያ ሰው ከቅደመ ሥራው የኋላ ስራው የጸና ደሆናል አለ። ከበቃ በኋላ ዓለማዊ ሥራ ያሠሩታልና።
******
፵፮፡ ወእንዘ ይነግሮሙ ዘንተ ለሕዝብ ናሁ እሙ ወአኃዊሁ ይቀውሙ አፍአ እንዘ ይፈቅዱ ይትናገርዎ። ማር ፫፥፴፩። ሉቃ ፰፥፲፱፡፡
******
፵፮፡ ለሕዝቡ ይህን ሲነግራቸው እናቱ እመቤታችን ወንድሞቹ ደቂቀ ዮሴፍ ሊገናኙት ወደው ከደጅ ቁመው ነበር።
(ሐተታ) እንዲያው አይደለም አንሰ እብለክሙ አንሰ እብለክሙ እያለ ሲያስተምር ልቡን ሽ ብሎት ሊሞት ነው የሚመክረው ዘመድ የለውም ሲሉ ሰምተው ነው።
******
፵፯፡ ወመጽአ አሐዱ እምአርዳኢሁ ወይቤሎ ናሁ እምከ ወአኃዊከ አፍአ ይቀውሙ ወየኃሥሡ ይትናገሩከ
******
፵፯፡ ከደቀ መዛሙርቱ አንዷ መጥቶ እነሆ ወንድሞችህና እናትህ ሊገናኙህ መጥተው ከደጅ ቁመዋል አለው።
(ሐተታ) እንዲህ ያለው ማነው ቢሉ ትምህርት ሊፈታ የሚወድ ሌላን አለ ያው ይሁዳ ነው እንጂ፣
******
፵፰፡ ወአውሥእ ወይቤሎ ለዘነገሮ መኑ ይእቲ እምየ።
******
፵፰፡ ለነገረው እናቴ ማናት።
ወእለ መኑ እሙንቱ አኃውየ
ወንድሞቼስ እለ ማናቸው ብሎ መለሰለት።
(ሐተታ) መኑ ይእቲ እምየ ማለቱ እሷን መንቀፉ ነው ቢሉ አዎን በጊዜ ግብሯ ንጉሥ ንግሥት የሚገኙበትን ሰዓት ጠይቆ መምጣት ይገባልና። እሱዋንስ አይነቅፋትም ይህም ሊታወቅ ይእቲ ተዓቢ እምሱራፌል በንጽሕ ይላታል ብሎ ከአክብሮተ አብ ወእም አክብሮተ እግዚአብሔር እንዲበልጥ ለማጠየቅ።
አንድም ከጉባዔ መካከል መነሣት ይገባል ብለው አብነት እንዳያደርጉበት።
******
፵፱፡ ወአመረ እዴሁ ኀበ አርዳኢሁ፡፡
******
፵፱፡ እጁን ወደ ደቀ መዛሙርቱ አመለክተ እጅ ለነገር ያግዛልና።
ወይቤሎሙ ናሁ እምየ ወአኃውየ።
እናቴም ወንድሞቼም እነሆ በጉባዔ ያሉ ሕዝብ ናቸው አላቸው፤
******
፶፡ እስመ ኩሉ ዘይገብር ፈቃዶ ለአቡየ ዘበሰማያት ውእቱ እኁየ ወእኅትየ ወእምየኒ ውእቱ።
******
፶፡ የሰማይ አባቴን ፈቃድ የሚፈጽም ሁሉ ወንድሜም እኅቴም እናቴም እሱ ነውና።
******
ምዕራፍ ፲፫።
፩፡ ወበይእቲ ዕለት ወጺኦ እግዚእ ኢየሱስ እምቤት ነበረ መንገለ ሐይቀ ባሕር።
፩፡ በዚያች ቀን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከቤት ወጥቶ ከወደቡ ተቀመጠ፡፡
******
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
29/08/2011 ዓ.ም
Tuesday, May 7, 2019
ወንጌል ቅዱስ ክፍል 84
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment