====================
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል።
ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው።
በከመ ተፈነዉ ሐዋርያት።
ምዕራፍ ፲፩።
******
፰፡ ምንተኑመ ወፃእክሙ ገዳመ ትርአዩ።
******
፰፡ በገዳም ምን ልታዩ ወጥታችኋል።
ብርዓኑ ዘይትሀወስ እምነፋስ።
ነፋስ የሚወዘውዘው መቃ መስዬን ልታዩ ወጥታችኋል።
ወሚመ ብእሴኑ ዘርሡይ በቀጠንተ አልባስ።
ወይም ረፊእ ግምጃ የለበሰን ልታዩ ወጥታችኋል።
እለሰ ቀጠንተ ይለብሱ ውስተ አብያተ ነገሥት ሀለዉ።
ግምጃ የለበሱ በነገሥታት ቤት በገዳም አሉ። ረፊእ ግምጃ የለበሰ በገዳም እንደምን ይገኛል ቢሉ ነገሥታት መኳንንት ተድላ እናድርግ ባሉ ጊዜ ገዳም ወጥተው ጃን ጥላ አስጥለው ድንኳን አስተክለው ይውላሉ በዚህ ጊዜ ብዙ ባለወጎች አጊጠው ይታያሉና።
አንድም ምንተኑመ ብለህ መልስ መቃ መስዬን ነፋስ አንድ ጊዜ ወደ ቀኝ አንድ ጊዜ ወደ ግራ እንደሚወዘውዘው የእናንተም ልቡና አንድ ጊዜ የባሕርይ አምላክ አንድ ጊዜ ዕሩቅ ብእሲ ይላል፡፡ ዮሐንስም አንድ ጊዜ ዕሩቅ ብእሲ አንድ ጊዜ የባሕርይ አምላክ ይልልናል ብላችሁ ወጥታችኋል፡፡
ወሚመ ብእሴኑ ሌት ከቀን ግምጃ እንዲለዋወጥ የእናንተም ልቡና አንድ ጊዜ የባሕርይ አምላክ አንድ ጊዜ ዕሩቅ ብእሲ በማለት ይለዋወጣል፡፡ ዮሐንስም አንድ ጊዜ የባሕርይ አምላክ አንድ ጊዜ ዕሩቅ ብእሲ በማለት ይለዋወጣል ብላችሁ ወጥታችኋል።
አንድም መልስ። መቃ መስዬን ነፋስ አንድ ጊዜ ወደ ቀኝ አንድ ጊዜ ወደ ግራ እንዲለው ዮሐንስም አንድ ጊዜ ዕሩቅ ብእሲ አንድ ጊዜ የባሕርይ አምላክ ይልልናል ብላችሁ ወጥታችኋል።
ወሚመ ብእሴኑ ሌት ከቀን ግምጃ እንዲለዋወጥ ዮሐንስም አንድ ጊዜ የባሕርይ አምላክ አንድ ጊዜ ዕሩቅ ብእሲ በማለት ይለዋወጣል ብላችሁ ወጥታችኋል።
እለሰ የጧቱን ለማታ የማታውን ለጧት የሚለዋውጡ ራት አግቦች በነገሥታት ቤት አሉላችሁ፡፡
አንድም ለምንት ወፃእክሙ ትርአዩ ገዳመ በል፡፡ ወደ ገዳም ታዩ ዘንድ ለምን ወጥታችኋላ፡፡
ብርዓኑ ነፉስ የሚወዘውዘው መቃ መስዬን ልታዩ ወጥታችኋልን ልታዩ ወጥታችኋል ልታዩ ወጥታችኋላ።
ወሚመ ብእሴኑ ረፊዕ ግምጃን የለበሰን ልታዩ ወጥታችኋልን ልታዩ ወጥታችኋል ልታዩ ወጥታችኋላ። ረፊዕ ግምጃ የለበሱስ በነገሥታት ቤት አሉ።
******
፱፡ ወምንተኑመ ወፃእክሙ ትርአዩ።
******
፱፡ ምን ልታዩ ወጥታችኋል፡፡
ነቢየኑ።
ነቢይን ልታዩ ወጥታችኋል።
እወ እብለክሙ ውእቱ ፈድፋደ የዓቢ እምነቢያት።
አዎን ትሉኝ እንደሆነ ዮሐንስ ከነቢያት ይበልጣል ብዬ እንዲበልጥ በእውነት እነግራችኋለሁ
******
፲፡ እስመ ዝንቱ ውእቱ ዘበእንቲአሁ ተጽሕፈ ናሁ አነ እፌኑ መልአኪየ ቅድመ ገጽከ ዘይጸይሕ ፍኖተከ በቅድሜከ። ሚልክ ፫፥፩፡፡ ማር ፩፥፪፡፡ ሉቃስ ፯፥፳፯።
******
፲፡ በፊትሀ መንገድህን የሚጠርግ መልክተኛዬን እነሆ በፊትህ እልካለሁ ተብሎ የተነገረለት ይህ ዮሐንስ ነውና በሌላው አልቦቱ መልአክ ለመልአክ ይላል ከዚህ እንዲህ አለ እንደምነው ቢሉ ለሌላው እውነት ነው እሱ ግን ትንቢት ተነግሮለታልና።
******
፲፩፡ አማን እብለክሙ ኢተንሥአ እምትውልደ አንስት ዘየዓቢ እምዮሐንስ መጥምቅ።
******
፲፩፡ ሴቶች ከወለዷቸው ወገን ከዮሐንስ መጥምቅ የሚበልጥ አልተነሣም ብዬ እንዳልተነሣ በእውነት እነግራችኋለሁ። ስሕተት በሔዋን ተጀምሯልና እምትውልደ አንስት አለ።
ወበመንግሥተ ሰማይሰ ዘይንዕሶ የዐብዮ።
መንግሥተ ሰማይ ሆኖ በመሰጠት ግን መንፈቅ የሚያንሰው ጌታ ይበልጠዋል።
አንድም ወደ መንግሥተ ሰማይ በማገባት ከመንግሥተ ሰማያት በማውጣት ግን ደቀ መዝሙሩ ዮሐንስ ወንጌላዊ ይበልጠዋል፡፡ ለዚያ ሥልጣነ ክህነት አለው ለዚህ ግን ሥልጣነ ክህነት አልነበረውም፡፡
******
፲፪፡ ወእመዋዕለ ዮሐንስ መጥምቅ እስከ ዛቲ ዕለት ትትገፋዕ መንግሥተ ሰማያት።
******
፲፪፡ ዮሐንስ መጥምቅ ማስተማር ከጀመረበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ መንግሥተ ሰማይ ወንጌል የሚቀበላት አጥታ ትበደላለች።
ወግፉዓን ይትማሰጥዋ።
ዓሣ ወጋሪ ልበደ ሠሪ የነበሩ ሐዋርያት ይቀበሏታል፡፡ ገፋዕያን ይላል ሰውን በግብር ምክንያት ይበድሉ የነበሩ እለ ማቴዎስ እለ ዘኬዎስ ይቀበሏታል፡፡ ይትማሰጥዋ ማለቱ ግን የወደዱትን ምግብ እየተሸሙ እንዲመገቡት ወደው ይቀበሏታል ሲል ነው፡፡
አንድም ወእመዋዕለ ዮሐንስ ብለህ መልስ ዮሐንስ ማስተማር ከጀመረበት ቀን ጀምሮ መንግሥተ ሰማያት የሚወርሳት አጥታ ተበድላ ትኖራለች፡፡ ወግፉዓን በንስሐ የሚበደሉ ምእመናን፡፡ ገፋዕያን ይላል ሰውን በንስሐ የሚበድሉ ቀሳውስት ይወርሷታል።
******
፲፫፡ እስመ ኵሎሙ ነቢያትኒ ወኦሪት እስከ ዮሐንስ ተነበዩ
፲፫፡ ኦሪትም ነቢያትም ሁሉ እስከ ዮሐንስ ድረስ አስተምረዋልና
******
ይቆየን፡፡
**************
መልካሙ በየነ
ደብረ ማርቆስ፤ ኢትዮጵያ
23/08/2011 ዓ.ም
Wednesday, May 1, 2019
ወንጌል ቅዱስ ክፍል 78
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment